No summary available.
ግንቦት 6 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ኂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሳሙኤል ጦኖሮ - ቀረቡ ተጠሪ፡- እነ ወ/ሮ አይሻ አርጌሳ (4 ሰዎች) - አልቀረቡም
ለሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ተጠሪዎች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ነው። ተጠሪዎች በስር ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ከ1957 ዓ.ም ጀምሮ በይዞታቸው ስር ያለው ቤት በእርጅና ምክንያት በመፍረሱ ለማደስ ስራ ሲጀምሩ አመልካች ስራው እንዲይጀመር ሁከት ስለፈጠሩ ሁከቱ እንዱወገድላቸው ጠይቀዋል። አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ ቤቱ የተጠሪዎች ሳይሆን የአመልካች ባለቤት ወላጆች መሆኑን፣የባለቤታቸው ወላጆች ወደ ውጪ አገር ሲሄደ ቤቱን የአመልካች ባለቤት እንዱያስተዲድሩ ውክልና መስጠታቸውን፣የአንደኛ ተጠሪ ባለቤት በቤቱ በመጀመሪያ በኪራይ በኋላም ኪራይ መክፈል ሲያቅታቸው በነፃ እንዱኖሩበት መፍቀዲቸውን፣ አንደኛ ተጠሪ ባለቤት በ1995 ዓ.ም ታመው አዱስ አበባ ለህክምና እንደሄደ በዛው መሞታቸውን፣ቤቱ በተጠሪዎች እጅ አለመኖሩን እና ቤቱ በእርጅና ምክንያት በመፍረሱ ፍራሹን ለጏረቤት በአደራ እንዱጠብቁ ማድረጋቸውን በመግለጽ ሁከት እንዲልፈጠሩ ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱን ጉዲዩን መርምሮ ቤቱ አንደኛ ተጠሪ በይዞታቸው ስር አድርገው እየተጠቀሙበት እንደነበር በምስክሮች ተረጋግጧል በማለት አመልካች የፈጠሩት ሁለት እንዱወገድ ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለከምባታና ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል። በተመሳሳይ የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የቀረበለትን የሰበር አቤቱታ ውድቅ አድርጏታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው አንደኛ ተጠሪ አካባቢውን ለቀው ከሄደ ከ15 ዓመት በላይ ቆይቶ የቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም፣የቤቱ ባለቤቶች የአመልካች ባለቤት ወላጆች ስለመሆናቸው በቂ የሰነድ ማስረጃ ቀርቧል፣እነሱ ወደ ውጪ ሲሄደ ቤቶቹን የአመልካች ባለቤት እንዱያስተዲድሩት ውክልና ሰጥተዋል፣በዚህ መሰረት የአንደኛ ተጠሪ ባለቤት እንዱኖርበት አድርገዋል እንዱሁም በቤት ውስጥ ተጠሪዎች ስላልነበሩ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱሻር በማለት ጠይቀዋል። ችልቱም ክርክር ያስነሳው ጉዲይ የዲኝነት ገንዘብ ተከፍል ሥልጣን ባለው ፍ/ቤት ላታይ የሚገባው መሆን አለመሆኑን ይህ ቢታለፍ እንኳን አመልካች ሁከት ፈጥረዋል የመባለን አግባብነት ማየት እንዱቻል አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል።
በዚህ መሰረት ተጠሪዎች ቀርበው ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
በስር ፍ/ቤት ተጠሪዎች ክስ የመሰረቱት ከባለቤታቸው ጋር ከ1957 ዓ.ም ጀምሮ ይዘው የሚገለገለበት ሁለት ክፍል ቤቶች በእርጅና ምክንያት በመፍረሳቸው ለማደስ ስራ ሲጀምሩ አመልካች ሁከት ፈጥረዋል በማለት ነው። አመልካች በበኩላቸው ቤቱ የአመልካች ባለቤት ወላጆች እንጂ የተጠሪዎች አለመሆኑና ተጠሪዎች የሚኖሩት በልላ ቦታ እንደነበር እንዱሁም ቤቱ በተጠሪዎች ይዞታ ስር አለመሆኑ ተከራክረዋል። አንድ ሰው በይዞታው ላይ ሁከት ሲፈጠር ወይም ይዞታው በሃይል ሲነጠቅ ሁከቱ እንዱወገድ ወይም በሃይል የተወሰደው ነገር እንዱመለስ ክስ ማቅረብ የሚችል መሆኑን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1149 መመልከት ይቻላል። በመሆኑም ተጠሪዎች ክስ የመሰረቱት ሁከት ተፈጥሮብናል በማለት በመሆኑ ሁከት ተፈጠረበት ያለበት ንብረት በይዞታቸው ስር እንደሚገኝና በዚህ ይዞታቸው ላይ የሁከት ተግባር የተፈፀመበት ስለመሆኑ ማረጋገጥ ይገባቸዋል። ይዞታ ማለት ደግሞ አንድ ሰው አንድን ነገር በእጁ አድርጏ በእውነት የሚያዝበት ሆኖ ሲገኝ መሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1140 የተመለከተ በመሆኑ ተጠሪዎች ክርክር ያስነሳውን ቤት በእጃቸው አድረገው ሲያዙበት የነበረ ስለመሆኑ የማስረዲት ሽክም አለባቸው። ከክርክሩ ሂደት እንደተረዲነው የ1ኛ ተጠሪ ባለቤት ቤቱን እስከ 1995 ዓ.ም ድረስ ይኖሩበት እንደነበርና ከዛ በኋላ ታመው ለህክምና አዱስ አበባ ሲሄደ ቤቱን ለላላ ሰው አደራ ሰጥተው በመሄዲቸው ቤቱ በተጠሪዎች እጅ አልነበረም። ተጠሪዎች ለቀረበው የሰበር አቤቱታ በሰጡት መልስ ባለቤታቸው ታመው ወደአዱስ አበባ ሲሄደ ቤቱን በአደራ ለላላ ሰው በአደራ ሰጥተው መሄዲቸውን ግልፀዋል። በይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት ከተደረገው ክርክርም አንደኛ ተጠሪ በአላባ ከተማ እየኖሩ ቤቱን እየተመላለሱ ይከታተለ እንደነበር ምስክሮች ማስረዲታቸው ተመዝግቧል። ይህም የሚያሳየው ተጠሪዎች በቤቱ ውስጥ ይኖሩ ያልነበረ ወይም ቤቱን በእጃቸው አድርገው በእውነት የሚያዙበት አለመሆኑን ነው። በመሆኑም ቀድሞውንም ቢሆን ተጠሪዎች ቤቱን በእጃቸው አድርገው የሚያዙበት ባለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1149 መሰረት ሁከት ይወገድልኝ ክስ የሚያቀርቡበት የሕግ አግባብ የለም። ይልቁንም የክርክሩ ሂደት ክርክሩ ከሁከት ጥያቄ ይልቅ ክርክር ያስነሱት ሁለት ቤቶች ባለቤት ማነው?
በሚል ጭብጥ ላይ የሚያተኩር ሆኖ ነው ያገኘነው። ይህ ጥያቄ ደግሞ ንብረቱ ተገምቶ የባለቤትነት መፊለም ክስ የሚቀርብበት እንጂ የሁከት ይወገድልኝ ክስ የሚቀርብበት ጉዲይ አይደለም። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች ተጠሪዎች በክሳቸው ሁከት ይወገድልኝ በማለት መጠየቃቸው ብቻ የተጠሪዎችን ትክክለኛ ጥያቄ በአግባቡ ሳያገናዝቡና ሳይረደ ሁከት እንዱወገድ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የወረዲ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 00928 የካቲት 28 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ፣የከምባታ ጠምባሮ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 02325 ሐምል 17 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የደ/ብ/ብ/ሕ/ክ/መ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 23840 ኀዲር 23 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሽሯል።
ተጠሪዎች ሁከት እንዱወገድ ያቀረቡት ክስ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
No topics extracted.