No summary available.
ሚያዝያ 21 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አብደራሑም አህመድ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አምሣለ ጀመሪ - አልቀረቡም ተጠሪ፡- አቶ ፍርደ ገበያሁ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት በመዝገብ ሰኔ 15 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ነሐሴ 28 ቀን 2001 ዓ.ም ተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው።
ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመጀመሪያ ጉዲዩን አይቶ ጥር 23 ቀን 1998 ዓ.ም ተጠሪንና አመልካችን በማከራከር ውሣኔ ሰጥቷል። ሆኖም በውሣኔው ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ቀርቦ የከፍተኛው ፍርድ ቤት በዚህ ክርክር ተካፊይ ያልሆነችው የወ/ሮ አስካለ ወ/አማኑኤል ወራሾችን በክርክሩ ተካፊይ በማድረግ ውሣኔ እንዱሰጥ ትዕዛዝ በመስጠት ጉዲዩን መልሶ ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የላከለት መሆኑን ከሥር ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ለመረዲት ችለናል። የሥር ፍርድ ቤት በከፍተኛው ፍርድ ቤት በተሰጠው ትዕዛዝ መሰረት የወ/ሮ አስካለ ወ/አማኑኤል ወራሾች እንዱቀርቡ በጋዜጣ ጥሪ አድርጎ ባለመቅረባቸው ጉዲዩን በላለበት አይቷል። የሥር ፍርድ ቤት ከዚህ በፉት ጥር 23 ቀን 1998 ዓ.ም የተሰጠው ውሣኔ በወ/ሮ አስካለ ወ/አማኑኤል ወራሾች እንደተሰጠ ይቆጠራል ውሣኔውን የሚያስቀይር ጉዲይ የለም በማለት መጋቢት 23 ቀን 2000 ዓ.ም ሰጥቷል።
በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች በወረዲ 20 ቀበላ 40 በቁጥር 320 የተመዘገበው ቤት የአመልካች መሆኑን የሚያረጋግጥ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት (ካርታ) ያቀረቡ መሆኑንና ካርታውም ማህተም ያለውና የአመልካች ስም የተፃፈበት መሆኑን በመግለፅ ቤቱ አመልካች ከአገር ከወጣ በኋላ አልተመለሰም በሚል የህዝብ ደህንነትና ጥበቃ አስተዲደር 1970 የተያዘ መሆኑን ገልፆና ጉዲዩ የሁለት ግለሰቦች ክርክር በመሆኑ የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ጉዲዩን የማየት ሥልጣን የለኝም ያለ በመሆኑ ቤቱ የአመልካች ነው። ተጠሪ ክርክር ያስነሣውን ቤት ከነቦታው ለይግባኝ ባይ ያስረክቡ በማለት ውሣኔ ሰጥቷል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ይግባኝ ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚ ችልቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ “ይግባኝ ባይ (የአሁን ተጠሪ) ቤቱን እንዳት አገኙ የሚለው ጥያቄ እንዲለ ሆኖ መልስ ሰጭ (የአሁን አመልካች) መልስ ሰጭ ቤቱን ያስረክቡኝ በማለት ክስ ሲመሰርቱ በቅድሚያ ከሚመለከተው አካል ቤቱ የተሰጣቸው መሆኑን አረጋግጠው የቤት ባለቤትነት መታወቂያ ደብተር ማቅረብ ይገባቸዋል።” የሚል ትችት ከሰጠ በኋላ አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ ለማቅረብ በንብረቱ ላይ ጥቅም ወይም መብት ያላቸው መሆኑን አላስረደም በማለት በትሐብሓር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 33(2) በመጥቀስ የከፍተኛውን ፍርድ ቤት ውሣኔ ሽሮታል።
አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ይግባኝ ችልት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት። በመጀመሪያ ይግባኝ ሰሚ ችልቱ በጭብጥነት ያልቀረበለትንና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ከዚህ በፉት በመዝገብ ግንቦት 15 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ ሽሯል። ተጠሪ ከዚህ በፉት የከፍተኛ ፍርድ ቤት በመዝገብ በሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ አላቀረበም።
አሁን ባቀረበው ይግባኝ መነሻ በፉት ተሰጥቶ የነበረ ውሣኔ መሻር መሰረታዊ የሆነ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ስህተት ነው። የከፍተኛው ፍርድ ቤት በመዝገብ በክርክሩ ተካፊይ መሆን የሚገባቸውን ወ/ሮ አስካለ ወልደአማኑኤል በማስገባት ከተከራካሪዎች መካከል የቤቱ ባለሀብት ለመሆን የሚያስችለው ማስረጃ ያለው ማን ነው የሚለውን መዝኖ እንዱወስን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343(1) ጭብጥ መሥርቶ የመለሰለት ሲሆን ይህንን ውሣኔ ይግባኝ ሣይቀርብበት መሻሩ የሥነ-ሥርዓት ግድፈት ነው። በሁለተኛ ደረጃ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት ለአዋጅ ቁጥር 47/67 አንቀፅ 12 ንዐስ አንቀፅ 2 የሰጠው ትርጉም የአዋጁንና የህጉን ድንጋጌ መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። አመልካች ካርታው ሣይለወጥ የቀረው በኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ በብድር መያዣነት ተይዞ መሆኑን ከግንዛቤ ውስጥ ሣያስገባ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክተዋል። ተጠሪ በበኩለ ቤቱን መንግስት ወርሶት ሲያስተዲድረው የነበረና ለወ/ሮ አስካለ ወ/አማኑኤል በምትክ ትቶ የተሰጠ ነው። ጉዲዩ በፍርድ ቤት መታየት የለበትም። አመልካች ያቀረቡት የባለቤትነት ካርታ በ1953 ዓ.ም የተሰጠና በሚኒስትሩ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ያልፀደቀ በመሆኑ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት ወይም ጥቅም የለውም ማስረጃውም በማህተም ያልተረጋገጠ ነው። ቤቱ 1983 ዓ.ም በቅል ቤት አካባቢ ተፈጥሮ በነበረው ከፍተኛ ፍንዲታ ምክንያት የወደመ ሲሆን እኔ ከወ/ሮ አስካለ ወ/አማኑኤል ወራሾች ተከራይቼ ለጋራዥ እየተጠቀምኩበት እገኛለሁ የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ ሰጥቷል።
አመልካች የመልስ መልስ አቅርቧል። ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች ክርክር ባስነሳው ቤት ተጠሪ እንዱለቅለት ክስ ለማቅረብ የሚያስችል የክስ ምክንያትና መብትና ጥቅም አለው ወይስ የለውም በሚለው ጭብጥ እልባት ሉሰጠው የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል። ይህንን ጭብጥ እልባት ለመስጠት አመልካች ያቀረበው ክርክር ከአዋጅ ቁጥር 47/67 አጠቃላይ ግብና አግባብነት ያላቸውን ድንጋጌዎች ማገናዘብና ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸው ላልች የህግ ማዕቀፍች መተርጎም አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች በቀድሞው ወረዲ 20 ቀበላ 40 ቁጥር 320 የሆነው ቤትና የቦታው ሥፊት 855 ካሬ ሜትር የሆነው ንብረት ባለቤት መሆኑንና ይህንንም ንብረቱን ለኮንስትራክሽንና ልማት ባንክ በመያዣነት የተያዘ መሆኑን በመግለፅ የተከራከረና ይህንንም የሚያሣዩ ማስረጃዎችን ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና ጉዲዩን በይግባኝ ላየው የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ከሰጠው ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። ይግባኝ ሰሚው ችልት አመልካች በንብረቱ ላይ ጥቅም ወይም መብት ያለህ መሆኑን አላስረዲህም በማለት የፍትሐብሕር ሥነሥርዓት ሕግ ቁጥር 33(2) በመጥቀስ ውሣኔ የሰጠው የቤቱና የቦታው ካርታና ፕላን አዋጅ ቁጥር 47/67 ከመውጣቱ በፉት የተሰጠና በዚሁ አዋጅ አንቀፅ 12 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረት በሚኒስትሩ አልፀደቀለትም በሚል ምክንያት ነው።
አዋጅ ቁጥር 47/67 አንቀፅ 12 ንዐስ አንቀፅ 2 ተፈፃሚነትና ውጤት አዋጁ አጠቃላይ ግብና ዓላማና አግባብነት ካላቸው የአዋጁ ድንጋጌዎች ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጎም አለበት። የአዋጁ ዓላማ አንድ ሰው ወይም ቤተሰብ ለመኖሪያ የሚሆነው አንድ ቤትና ለድርጅት የሚሆነው አንድ ቤት ካለው ይህንን አንድ ቤት መውረስና የመንግስት ማድረግ እንዲልሆነ በመግቢያው በሰፉው ተዘርዝሯል። የአዋጁ መሰረታዊ አላማ በአንቀጽ 3 ንዐስ አንቀፅ 3 “ትርፍ ቤት” በሚለው ትርጉም የሚሸፈንና ከአንድ በላይ የመኖሪያ ቤት ወይም የድርጅት ቤት ያለውን ሰው ቤትና ቦታ በመውረስ የመንግስትና የሕዝብ ንብረት ማድረግና በከተሞች የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ማቃለል ነው። ከዚህ በተጨማሪ አዋጁ ከመውጣቱ በፉት ቦታ ያለው ቤተሰብ ወይም ግለሰብ ላላ መኖሪያ ቤት የላለው ከሆነ በቦታው ላይ የባለይዞታነት መብት እንደሚኖረው በአዋጁ አንቀፅ 7 ንዐስ አንቀፅ 1 በግልፅ ተደንግጓል። የአዋጁ አንቀፅ 12 ንዐስ አንቀፅ 2 ከላይ የተጠቀሰውን መሰረታዊ ዓላማና አዋጁ ከመታወጁ በፉት አንድ የመኖሪያ ቤትና የይዞታ ቦታ ያላቸው ሰዎች በአዋጁ የተሰጣቸውን መብት ሙለ በሙለ በሚያሣጣ መንገድ መተርጎም የለበትም።
ሚኒስትሩ በአዋጅ ቁጥር 47/67 አንቀፅ 12 ንዐስ አንቀፅ 2 መሰረትና በአዋጁ አንቀፅ 35 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት በአገሪቱ ከተሞች የሚገኙ ሁለንም ቤቶች በመመዝገብ አዱስ የባለቤትነት ማስረጃ ለሁለም በአዋጁ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ለሚፈቀድላቸው ሰዎች ሰጥቶ አጠናቅቋል ብል መደምደም የማይቻል መሆኑ በዚህ መዝገብና በላልች መዝገቦች በቀረቡ ክርክሮች ለመገንዘብ ይቻላል። ሚኒስትሩ በነበረበት የማስፈፀም ችግር ወይም ቤቱ በባንክ በመያዣነት በመያዙ ወይም በላልች በፍርድ ቤት ሉጣሩና በማስረጃ ሉረጋገጡ በሚችለ አጥጋቢ ምክንያቶች የቤቱን ባለሀብትነት በማፅደቅ አዱስ የባለቤትነት ማስረጃ ያልሰጠው ሰው በንብረቱ ውስጥ ገብቶ ያገኘውን ማናቸውንም ሰውና በአዋጅ መሰረት ሣይወረስ ቤቱን የያዘውን አካል በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 37 መሰረት ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን ላለው ፍርድ ሰጭ አካል ክስ አቅርቦ ከመጠየቅ የሚገድበው አይደለም።
በያዝነው ጉዲይ ቤቱ በግለሰቦች እጅ በመሆኑ ጉዲዩን አከራክሮ ውሣኔ የመስጠት ሥልጣን የላለው መሆኑን የኢትዮጵያ ፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ በፅሐፍ ላመልካች ያሣወቀው መሆኑን ከከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል።
ስለዚህ አመልካች ከእሱ ፈቃድና ስምምነት ውጭ በቤቱ ውስጥ ገብተውና ቤቱን ይዘው የሚገኙ ሰዎች ከቤቱ ለማስለቀቅና የቤቱ ባለሀብት መሆኑን በፍርድ ለማረጋገጥ በቤቱና መብትና ጥቅም ያለው መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ አቅርቧል። የአዋጅ ቁጥር 47/67 አንቀፅ 12 ንዐስ አንቀፅ 2 ተፈፃሚነትና ውጤት አጠቃላይ አዋጅ ሉያሣካው ከሚፈልገው መሰረታዊ ግብ ከአዋጁ አንቀፅ 2 ንዐስ አንቀፅ 3 እና ከአዋጁ አንቀፅ 7 ንዐስ አንቀፅ 1 ጋር በተጣጣመ መንገድ መተርጎም ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። ከዚህ አንፃር አመልካች ጉዲዩ በፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ እንደማይታይ ከተገለፀለት በኋላ የቤቱ ባለሀብት የነበረ መሆኑን የሚያሣይ ካርታና ፕላን በማስረጃነት በማቅረብ ቤቱ ያልተወረሰ መሆኑንና ከቤቱ ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ቤቱን ለመጠቀም የሚያስችላቸው መብትና ጥቅም የላላቸው በመሆኑ ቤቱን እንዱለቁለት የመጠየቅ መብት አለው። የቤቱ ባለቤትነት ካርታና ፕላን በሚኒስትሩ አለመፅደቁ በቤቱ ላይ መብትና ጥቅም የለውም ከሚለው መደምደሚያ ላይ አያደርስም። ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት በአዋጅ ቁጥር 47/67 አንቀፅ 12 ንዐሰ አንቀፅ 2 የሰጠው ትርጉም መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍትሐብሕር ይግባኝ ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
አመልካች ያቀረበው የሰነድ ማስረጃ አመልካች በቤቱ ላይ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው ብለናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፍትሐብሕር ይግባኝ ችልት አመልካች ቤቱ ላይ መብትና ጥቅም ያለው መሆኑንና ክስ ማቅረብ እንደሚችል በመገንዘብ በይግባኝ በቀረቡለት ላልች ነጥቦችንና ክርክሮችን በመመርመርና በመመዘን ውሣኔ እንዱሰጥባቸው ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.