No summary available.
ጥር 05 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- ዲዊት መስፍን ተጠሪ፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ ለቀረበው የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የባለሀብትነት መብትን መሰረት በማድረግ የቀረበው የቤት ይለቀቅልኝ ክርክርን የሚመለከት ነው። ክርክሩ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲጀመር ከሳሽ የነበረው አመልካች በተጠሪ ላይ ክስ የመሰረተው በአዱስ አበባ ከተማ በቀድሞ ወረዲ 118 ቀበላ ዐ5 ክልል የሚገኘውን፣ ቁጥር B-8/8008/30 በሚል የሚታወቀውን ቤት እንዱያስረክበው ይወሰንለት ዘንድ ጠይቀዋል።
ለማስረጃነትም ጥቅምት 23 ቀን 1985 ዓ.ም በከተማ ልማትና ቤት ሚኒስቴር ተሰጠኝ ያለትን ቁጥር 18/31246 የሆነ የከተማ ቤት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር አቅርበዋል። የአሁኑ ተጠሪም በተከሳሽነት ቀርቦ ለክሱ በሰጠው መልስ፤ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርቧል። ጉዲዮን በመጀመሪየ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1677/1/ እና 1845 ስር የተመለከቱትን ድንጋጌዎች መሰረት በማድረግ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት በብይን የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ አድርጓል። በዚህ ብይን አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
እኛም አመልካች ጥር 22 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም በፃፈት የሰበር ማመልከቻ ያቀረቡትን ቅሬታ መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው አመልካች በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የመባለን አግባብነት ለመመርመር ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኙ ወገኖች ያሰሙት ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ብይን እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
አመልካች በሰበር አቤቱታው ያነሷቸው የመከራከሪያ ነጥቦች ለክሱ መነሻ የሆነው ንብረት /ቤት/ የማይንቀሳቀስ ሀብት በመሆኑ ክርክተ መታየት ያለበት በንብረት ሕግ መሰረት ነው። ከንብረት ሕጉ አንፃር ሲታይም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1195 መሰረት የተሰጠኝ የንብረት ባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተር አልመነከም። በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1196 በተመለከተው ድንጋጌ መሰረት ደብተሩ ይሰረዘልኝ የሚል ጥያቄ ለሚመለከተው አካልም አልቀረበም።
የሚመለከተውን የአስተዲደር ክፍልም ደብተሩ ሕገወጥ ነው አላለውም። በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1168 መሰረት ንብረቱ የኔ ነው የሚል ጠያቂ ወገን አልቀረቡም የሚለ ናቸው። ተጠሪ በበኩለ ይርጋን በሚመለከት የተያዘው ጭብጥ ላይ ተመስርቶ ክርክሩን አቅርቧል። በዚህም መሰረት በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 ድንጋጌ ስር የተመለከተው የይርጋ ድንጋጌ ለጉዲዩ አግባብነት አለው። ድንጋጌው ውልን መሰረተ አድርጏ ለሚነሳ ክርክር ብቻ ነው አግባብነት ያለው የሚለው የአመልካች ክርክር ተቀባይነት የለውም። ግዳታዎች ከውል ባይመነጩም የውል ደንቦች ተፈፃሚ እንደሚሆንባቸው በሕጉ ተደንግጓል የሚለትን የመከራከሪየ ነጥቦችን አቅርቧል።
ግራ ቀኙ ወገኖች ከስር ጀምረው ያደረጉት ክርክር ተጠቃል ሲታይ የሚያስነሳው ጭብጥ የማይንቀሳቀስ ንብረትን በተመለከተ የሚቀርበው የመፊለም ክስ በይርጋ ቀሪ የሚሆንበት አግባብ አለ ወይ? የሚለው ነው።
ጭብጡ የሕግ ጭብጥ በመሆኑ መልስ ሉያገኝ የሚችለው በዚህ ረገድ አግባብነት ያላቸውን የፍትሐብሕር ሕጉን ድንጋጌዎችን በመፈተሽ ነው።
አመልካች ክሱን የመሰረቱት የቤቱ ባለቤት መሆናቸውን ገልፀውና በዚህ ረገድ የባለቤትነተ ማረጋገጫ ደብተር እንዲላቸው በማመልከት ነው። ጥያቄው የቤቱ ባለሐብት በመሆኔ ከሕግ ውጪ ይዞብኝ የሚገኘውን ተጠሪ በፍርድ ኃይል እንዱለቅ ይደረግልኝ በሚል በግልጽ የቀረበ ነው። በመሆኑም ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1206 ድንጋጌ ስር የተመለከተውን የመፊለም ክስ (petitory action) የሚመለከት መሆኑ ግልጽ ነው። ክሱ በዚሀ መልክ ቢቀርብም ተጠሪ የክሱ መቅረብ አግባብ አለመሆኑን የሚመለከቱና ይጠቅሙኛል የሚላቸውን የመከራከሪያ ነጥቦች በማንሳት መከላከያውን ያቀርባል ተብል ይገመታል። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ለመከላከያ ይጠቅሙኛል ያላቸውን የመከራከሪያ ነጥቦችን ያቀረበ ሲሆን የመጀመሪያው ይርጋን መሰረት ያደረገ መቃወሚያ ነው። ለዚህ ክርክሩ በዋቢነት የጠቀሰው በፍትሐብሕር ሕጉ በአራተኛ መፀሐፍ “ስለግዳታዎች” በተደነገገው በአንቀጽ 12 ስር ካለት ድንጋጌዎች ስር የሚገኘውን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 ስር የተመለከተውን የአስር ዓመት የይርጋ ጊዜ ገደብ ነው። እንግዱህ ይህ ድንጋጌ የሚገኘው በፍትሐብሕር ሕጉ ሦስተኛ መፀሐፍ “ስለንብረት” ከሚለው አንቀጽ ስድስት እና “ስለግል ሐብት” ከሚለው ከአንቀጽ ሰባት ውጪ በመሆኑ ከተያዘው የይርጋ መቃወሚያ አግባብነት ያለው ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ከማየታችን በፉት አግባብነት ያላቸው የንብረት ሕጉ ድንጋጌዎችን ሁኔታ መመርመሩ ተገቢ ሆኖ አግኝተናል።
በመሰረቱ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ በሕግ የተከበረ መሆኑ፣ ይህ መብት የሕዝብን ጥቅም ለመጠበቅ በልላ ሁኔታ በሕግ እስካልተወሰነ ድረስ ንብረት የመያዝና በንብረት የመጠቀም ወይም የላልችን ዜጏች መብቶች እስካልተቃረነ ድረስ ንብረትን የመሸጥ፣ የማውረስ ወይም በልላ መንገድ የማስተላለፍ መብቶችን የሚያካትት ስለመሆኑ በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት በአንቀጽ 40/1/ ስር በግልጽ አስቀምጧል።
የንብረት ሕጉ በጥቅለ ሲታይ ደግሞ ንብረት ምንድን ነው?፣ ንብረት ወይም ሀብት የሚገኘው እንዳት ነው?፣ ሀብት ከአንድ ወደ ላላ የሚተላለፈው በምን አግባብ ነው? የሚለትን ጥያቄዎች ይመልስልናል።
ባለሀብትነት ስለሚቀርበት ሁኔታ እና ስለባለሀብትነት ማስረጃም ዝርዝር ድንጋጌዎችን ያስቀምጣል።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ.1126 ስር እንደተመለከተው ንብረቶች ግዙፍነት ያላቸው ሆነው ተንቀሳቃሽ የሆኑና የማይንቀሳቀሱ ተብለው ይከፈላለ። ይህን ክፍፍል በመከተልም ሐብቶች የሚገኙበትን፣ የሚተላለፈበት፣ ባለሐብትነት ቀሪ የሚሆንበት አግባብ እንደዓይነታቸው የተለያዩ እንደሆኑ በሕጉ ተመልክቷል። የያዝነው የማይንቀሳቀስ ንብረትን /ሀብት/ የሚመለከት በመሆኑ በአብዛኛው ትኩረታችን በዚህ ላይ ይሆናል።
የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብት ከሚሆንባቸው ወይም የማይንቀሳቀስ ሀብት የሚገኝባቸው ሁኔታዎች በበፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1168/1/ ስር የተመለከቱትን ሁኔታዎችን የሚያሟላ ይዞታ ስለመሆኑ ሕጉ ያሳያል። ላላው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1184 እና 1186 ድንጋጌዎች ስር የተመለከተው ሲሆን በዚሀ አግባብ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብት መሆን የሚቻለው በሕግ ወይም በውል የወይም በኑዛዜ መሰረት ነው። በውል ወይም በኑዛዜ መሰረት ባለሐብት ለመሆንም የማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ማስመዝገብ የግድ እንደሚል ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1553 እስከ 1646 ድረስ ያለት ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። ባለሐብትነት በእነዚህ መንገድች ይገኛል ካልን ቀጥለን ደግሞ ባለሐብትንት ቀሪ የሚሆንበት አግባብ ማየቱ ተገቢ ይሆናል። በዚህ ረገድ አግባብት ያላቸው ድንጋጌዎች ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1188 እስከ 1192 ድረስ ያለ ናቸው። እነዚህ ድንጋጌዎች ሁለቱንም የንብረት አይነቶች የሚመለከቱ ሲሆን ባለሀብትነት ቀሪ ስለሚሆንበት ይርጋም ይጨምራለ። ከእነዚሀ ውስጥ በሕግ መሰረት “ ባለሀብትነቱ ለላላ ሰው የሆነ ወይም የተላለፈ እንደሆነ” በሚል የተደነገጉት ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1189 አና 1190 እና ባለሐብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን በሚለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1192 ስር የተመለከተውን መጥቀስ በቂ ይሆናል።
እንደምንመለከተው እስካሁን ድረስ ካየነው ሂደት ንብረቱ የኔ ነው በሚል የመፊለም ክስ የሚመሰረተው ከሳሽ ሉያቀርባቸው የሚችላቸው ሕጉን መሰረት ያደረጉ የመከራከሪያ ነጥቦች ምን ሉመስለ እንደሚችለ ግንዛቤ እናገኛለን። ክርክር የንብረት ባለሃብትነትን መሰረት ያደረገ የመፊለም ክርክርን የሚመለከት በመሆኑ ወደላላው መጽሐፍ ከመሻገራችን በፉት የንብረት ሕጏን መሰረት በማድረግ ሉነሳ የሚችለ /የሚገባቸው/ የመከራከሪያ ነጥቦችን በቅድሚያ ማየትም ነው አግባብ የሆነው። ተጠሪ በተከሳሽነቱ ያቀረበው የመጀመሪያው የመከራከሪያ ነጥብ ይርጋን የሚመለከት በመሆኑ በንብረት ሕጉ የተቀመጠውን የይርጋ ድንጋጌ አስቀድሞ ማየቱ ተገቢ ይሆናል። ከላይ እንደገለጽነው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1192 ስር የተመቀጠው ድንጋጌ ይርጋን የሚመለከት ነው።
ባለሀብትነትን የሚያስቀር የይርጋ ዘመን” በሚል ርእስ ያለው ሆኖ ይዘቱም በሚንቀሳቀስ ንብረት ላይ ያለውን መብት በአስር ዓመት የጊዜ ወሰን /ይርጋ/ ቀሪ የሚሆንበትን አግባብ ያመላክታል። የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን ግን አያሳይም። ድንጋጌው ይህን ያህል ግልጽ ከሆነ ለያዝነው ክርክር እልባት ለመስጠት ሁለት አማራጮችን አነፃጽረን ማየት አስፈላጊ ነው። በዚህ ረገድ የተደነገጉትን የንብረት ሕግ ድንጋጌዎች ስንመለከት ባለቤትነት ከሁለ የሰፊ መብት መሆኑን ያስገነዝባለ። በሕግ የተቀመጡትን ገደቦችንና ወሰኖችን (Restriction and Limitations) ሳያልፍ የአንድ ንብረት ባለቤት በንብረት እንደፈለገው የመጠቀምና የመገልገል መብቱን ነፃነቱ በሕግ የተከበረለት ስለመሆኑም ድንጋጌዎቹ ያሳያለ። ለባለሀብቱ የባለቤትነት መብት ከሚሰጣቸው መብቶች መካከልም ንብረቱ ያለእርሱ ፈቃድ ከሕግ ውጪ በልላ ሰው ወይም ኃይል ከተወሰደ ንብረቱን ካለበት ድረስ በመከታተል የማስመለስ ወይም የመፊለም መብት አንደ ስለመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1206 ድንጋጌ ያስረዲል። ከዚህ ድንጋጌ ይዘት፣ መንፈስና አቀራረጽ መረዲት የሚቻለው ሁለት መሰረታዊ የሆኑ ነጥቦችን ነው። ይኸውም የመፊለም መብት ባለሐብቱ ንብረቱን ማንም ያልተፈቀደለት ሰው ሕገ ወጥ በመሆነ መንገድ እንዲይነካ፣ በማንኛውም መልኩ ወደ ራሱ ወይም ወደ ላላ እንዲይዛወር ወይም የንብረቱን ህልውና እና ደህንነት እንዲያውክ በኃይል ተጠቅሞ የማስወገድ (the right to apply force against any act of intervention or usurpation) መብት አንደ ሲሆን ላላው ደግመ ያለባለቤቱ ፈቃድ ወይም ከሕግ ውጪ ደንብረቱ ተወስድ ከሆነ ባለቤቱ ይህን ንብረት የመከተልና እንዱመለስለት በዲኝነት የመጠየቅ መብት (Right to bring petitory action) ነው። የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1206 ባለሀብት የሆነ ሰው መብት ሳይኖረው እጁ ካደረገው ሰው ወይም ከያዘው ሰው ላይ ሐብቱ ይገባኛል ሲል ለመፊለምና ማናቸውንም የኃይል ተግባር ለመቃወም ይችላል ሲል የማደነግገው እንዝህን ነጥቦች የሚያረጋግጥ ሲሆን የባለቤትነት መብት ከሁለ የሰፊ መብት መገለጫ ከሆኑትም ዋናው ንብረቱን ተከታትል በዲኝነት የመጠየቅና የማስመለስ መብትን ለባለሃብቱ ማጏናፀፈ መሆኑ ይታመናል።
ምንም እንኳ አንድ ሰው በሕግ ያገኘው ወይም በመተላለፍ የተጏናፀፈው የንብረት ባለቤትነት ቋሚነት /ዘላለማዊነት/ (prrpetutiy) እንደለው ቢታወንም በራሲ በባለመብቱ ፈቃድ ወይም ያለፈቃደ ይኸው በአንድ ወይም በተወሰኑ ንብረቶቹ ላይ የባለቤትነት መብት የሚጠፊበት፣ ቀሪ የሚሆንበት ሁኔታ አለ። የባለቤትነት መብት ቀሪ (extinction of ownership) የሚሆንባቸው ሁኔታዎች በፍትሐብሕር ህጋችን ከቁጥር 1188 እስከ 1192 ድረስ መመለከታቸውን ከላይ ጠቅሰናል። የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1190 በተለይ ሲታዩ በማይንሰሳቀስ ንብረት ላይ የተቋቋመ የባለቤትነት መብት ቀሪ የሚሆነው የዚህ ሰው የባለቤትነት መብቱ ከማይንቀሳቀሰው ንብረት መዝገብ ሲሰረዝ /ሲፊቅ/ ስለመሆኑ ያስገነዝባል።
እንግዱህ ይህን ያክል በሕጉ ጥበቃ የተደረገው መበት ቀሪ የሚሆነው መቻ ነው? የሚለው ጥያቄ ከመብቱ ጠቅላላ ባህርይና ከሕግ አውጪው ሐሳብ አንፃር ቀጥተኛ፣ ተፈፃሚነትና አግባብነት ካለው የሕጉ ክፍል ጋር ተዛምድ ታይቶ ተገቢ ምላሽ ላሰጥበት የሚችለው ነው።
የማይንቀሳቀስ ንብረት በሚመለከት የሚቀርበው የመፊለም ክስ (petitory action) ለመቃወም የሚቀርበው የይርጋ ክርክር መታየት ያለበት በንብረት ሕጉ መሰረት ነው የሚለውን አማራጭ ከያዝን የምንደርስበት መደምደሚያ ግልጽ ነው። ሕጉ የይርጋ ወሰን ያስቀመጠው ለሚንቀሳቀስ ንብረት ብቻ በመሆኑ የይርጋው መቃወሚያ ለማይንቀሳቀስ ንብረት የመፊለም ክስ አግባብነት የለውም ወደሚለው ነው የምንደርሰው።
የተጠሪን ክርክር በመቀበል ሁለተኛውን አማራጭ ብንይዝ ደግሞ የማይንቀሳቀሰውን ንብረት በሚመለከት የሚነባው የይርጋ መቃወሚያ ከንብረት ሕጉ ወጥቶ በልላው የሕጉ ክፍል /አራተኛው መጽሐፍ/ ነው የሚታየው የሚለውን አካሄድ መከተል ሉኖርብን ነው። ይህ ግን በእርግጥም ሕጉ ሉደርስበት የፈለገው ምክንያታዊ የሆነ አካሄድ ነው ለማለት የሚያስቸግር ነው የሚሆነው። ምክንያቱም የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1192 የሚንቀሳቀስ ንብረት ባለሀብትነት የሚቀረው በአስር አመት የጊዜ ገደብ ነው ለማለት ካስቀመጠ በኋላ ስለማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሐብትነት ቀሪ መሆን በዝምታ ያለፈው ለጉዲዩ ቀጥተኛ ፈተፃሚነት በላለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 ስር የተመለከተውንና ተመሳሳይ የሆነ የአስር ዓመት የይርጋ ጊዜ ተፈፃሚ ለማድረግ ነው ብል ማሰብ ምክንያታዊ ላሆን አይችልምና።
ቀደም ሲል ለማመልከት እንደሞከርነው ንብረቶች የሚንቀሳቀሱና የማይንቀሳቀስ በሚል በሁለት የሚከፈለ ቢሆንም፣ የሚገኙበት፣ የሚተላለፈትበት እንዱሁም ባለሀብትነታቸው ቀሪ የሚሆኑበት አግባብ በንብረት ሕጉ ነው የሚገዛው። በዚህ ረገድ ሕጉ ያልታሰበበት ክፍተት ትቶአል ለማለት የሚያስችል ምክንያት የለም።
ይልቁንም የማይንቀሳቀስ ንብረት ከሚንቀሳቀን ንብረት በተለየ ሁኔታ የዘላቂነት /ነዋሪነት/ ባህሪይ ያለው እና ከትውልድ ወደ ትውልት በቋሚነት የሚተላለፍ በመሆኑ ቀሪ የሚሆንበት አግባብ ከሚንቀሳቀስ ንብረት የጠበበ እንደሆነ ሕጉ ፍልጓል የሚለው አስተሳሰብ ነው ከሕጉ መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1168 በተደነገገው መሰረት የማይንቀሳቀስ ንብረት በእጁ አድርጏ እና በተከታታይም ለአስራ አምስት አመታት ያክል በስሙ ግብር የገበረ ሰው የንብረቱ ባለቤት ይሆናል ሲባል የቀድሞው ባለቤት ነኝ የሚል ቢመጣ እንኳን ባለሃብትነቱ ቀሪ ስለሚሆን ንብረቱን ሉያስመልስ አይችልም ማለት ነው። በዚህ ረገድ የተቀመጠው የጊዜ ወሰን በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1845 ከተቀመጠው የረዘመ ነው። የንብረቱ ባለሀብት ነው በሚል አሳቤ ለረዥም አመታት በስሙ ግብር እየገበረ ንብረቱን ሲቆጣጠር የቆየው ሰው የሚያቀርበው መከራከሪያ ይህን ያክል ጥብቅ እይታ የሚፈልግ ከሆነ እንዱሁ ማለትም ግብር ሳይገብር የያዘው ሰው የሚያቀርበው መከራከሪያ በቀላል የሚታይ ነው ለማለት የሚያስቸግር ነው የሚሆነው። እነዚህን ሁኔታዎች በአጠቃላይ ደምረን ስንመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለሃብትነት ቀሪ የሚሆነው በይርጋ ሳይሆን በላልች ሁኔታዎች ይሆን ዘንድ የሕጉ ፍላጏት እንደሆነ ነው መገንዘብ የምንችለው። በመሆኑም ጉዲዩ የቀረበላቸው ፍርድ ቤቶች ሉያደርጏ የሚገባው ጉዲይ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ክሱን ማቋረጥ ሳይሆን ክሱ እንዱቀጥል በማድረግ ከሳሹ በእርግጥም የባለቤትነት መብት ያለው መሆኑን ወይም አለመሆኑን ማጣራት፣ ባለቤትነት ከነበረም ሕጋዊ በሆነ ስርአት የባለቤትነት መብቱ መቋረጥ አለመቋረጡን በማስረጃ በማጣራት እና ተገቢ የሆነውን ውሣኔም መወሰን ነው።
ከላይ እንደተገለፀው የባለቤትነት ባሕርይ ቀጣይነት (perpetuity) በመሆኑ ፍርድ ቤቶች በዚህ የህግ ትርጉም መሰረት አንዳ ክሱ በይርጋ አይታገድም ከማለታቸው በፉት የክሱ መሰረታዊ ይዘት የባለቤትነት መፊለም (petitory action) መሆኑን ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል። ከባለቤትነት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ነገር ግን ከመፊለም መብት ውጪ ያለ ላልተ ክሶች እነደሚጠይቁ መፍትሓ (remendy) እና ለክሱ ምክንያት እንደሆነው ጉዲይ አይነት /ጋብቻ፣ ውርስ፣ ሽያጭ ወ.ዘ.ተ../ በላልች ል ሕጎች የይርጋ ደንቦች የሚተዲደሩ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ የይርጋ ጉዲይ ክስ ይቀጥል አይቀጥል የሚለውን ነጥብ የሚመለከት ብቻ በመሆኑ ሙግቱ ከጠተናቀቀ በኋላ በፍሬ ነገሩ የሚሰጠው ውሣኔ በሕጉ ይዘትና ተከራካሪ ወገኖች በሚያቀርቡት ማስረጃ ጥንካሬ የሚወሰን መሆኑን የሰር ፍርድ ቤቶች የዚህን ውሣኔ የሕግ ትርጉም በዚሀ መንፈስ ሉረደት ይገባል። ከላይ ከተሰጠው ትንታኔ አንፃር አቤቱታ የቀረበበት ብይን የንብረት ሕጉን መሰረተ ሐሳብ ያልተከተለ፣ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለአገኘነው ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
አመልካች ያቀረቡት የማይንቀሳቀስ ንብረት የመፊለም መብት ክስ (petitory action) በይርጋ ቀሪ አይሆንም ብለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ወደ ክሱ ስረ-ነገር በመግባት ግራ ቀኙን ወገኖች ከአከራከረ በኋላ ተገቢ ነው የሚለውን ውሣኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341/1/ መሰረት መልሰንለታል።
ይፃፍ።
No topics extracted.