No summary available.
ታህሣሥ 22 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡-
እናኑ ጀንበሬ - ቀረቡ።
ላቀች ጀንበሬ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡-
ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ጉዲይ የተጀመረው በደሴ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት ነው።
አመልካቾች በተጠሪዎች ላይ ባቀረቡት ክስ የከሳሾች እናትና አባት በሕይወት በነበሩ ጊዜ በደሴ ከተማ ቀበላ ዐ1 ክልል በገዙት ቦታ ላይ ቁጥር ዐ45 እና ዐ46 የሆኑ ቤቶችን ሰርተዋል። ከእነዚህ ቤቶች ውስጥ ቁጥር ዐ45 የሆነው ቤት በአዋጅ 47/67 በትርፍነት ያልተወረሰ ሲሆን ከሳሾች በማናውቀው ሁኔታ አንደኛ ተከሣሸ ለሁለተኛ ተከሣሽ አከራይቶት ይገኛል። ከሣሾች ቤቱ እንዱመለስልን ለፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ አመልክተን ጉዲዩ አይመለከተኝም በማለት ይህንኑ በደብዲቤ አረጋግጠናል።
ስለሆነም አንደኛ ተከሣሽ ቤቱን ይዞ ለሁለተኛ ተከሣሽ በማከራየት ላይ የሚገኘው በአዋጅ ባልተወረሰበት ሁኔታ ስለሆነ ተከሣሾች ቤቱን እንዱያስረክቡን ኪራይም እንዱከፍለ ይወሰንልን ብለናዋል።
የደሴ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤትም ግራ ቀኙን አከራክሮ ክስ የቀረበበት ቤት በአዋጅ ተወርሷል ወይንስ አልተወረሰም? የሚለውን ጭብጥ ይዞ ጉዲዩን በመመርመር ቀደም ሲል ለፕራይቬታይዜሽን ኤጀንሲ ይህንኑ ቤት አስመልክቶ አቤቱታውን ሳይቀበለው መቅረቱ ቤቱ አልተወረሰም ተብል ውሣኔ እንደተሰጠ የወረዲው ፍ/ቤት በመቁጠር ለከሣሾች ሉመለስ ይገባል በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢነት የለውም ብል የወረዲውን ፍ/ቤት ውሣኔ ሽሯል።
የሥር ከሣሾችም የሰበር አቤቱታ ለክልለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት አቅርበው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አልተፈጸመም በማለት አቤቱተው ለሰበር አይቀርብም ብል መዝገቡን ዘግቷል።
ለዚህ ችልትም የሰበር አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ በመቃም ሲሆን ይህ ችልትም አቤቱታ የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ችልትም አቤቱታውን መርምሮ የደሴ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት አመልካቾች ከፕራይቤታይዜሽን ኤጀንሲ ውሣኔ አላሰጡም በሚል ምክንያት የወረዲው ፍ/ቤት ውሣኔ መሻሩ አግባብነቱን ለማጣራት አቤቱተው ለሰበር እንዱቀርብ አድርጓል። ግራ ቀኙንም በቃል አከራክሯል።
ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው አመልካቾች ክስ ያቀረቡት በውርስ የተላለፈልንን ቤት ተጠሪዎች ከሕግ ውጭ ይዘው ስለሚኙ ያስረክቡን በማለት ነው።
ከሥር ፍ/ቤት ከተደረገው ክርክርና በዚህ ችልትም በተደረገው ማጣራት ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ሁለተኛ ተጠሪ ይዘው የሚገኙት ከ1973 ዓ.ም. ጀምሮ ከአንደኛ ተጠሪ ጋር ባደረጉት የኪራይ ውል መነሻነት እንደሆነ ተገንዝበናል። ክርክር የተነሳበት ቤት ለረጅም ዓመታት በመንግሥት እጅ የቆየ ከሆነ አመልካቾች ቤቱ በአዋጅ ቁጥር 47/67 መሰረት ተፈቅድላቸው ባለንብረት ስለመሆናቸው ወይንም ደግሞ ከአዋጅ ውጭ ያለአግባብ ተወስድብናል የሚለ ከሆነም ለሚመለከተው አካል አቤቱታ አቅርበው ውሣኔ አግኝተው ባለመብት ስለመሆናቸው ያቀረቡት ማስረጃ የለም። አመልካቾች በዚህ መልኩ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ መብት ያላቸው መሆኑን ካላረጋገጡ ደግሞ ከመነሻውም ቢሆን ክስ ባቀረቡት ነገር መብት ወይም ጥቅም የላላቸው መሆኑን የሚያሳይ ነው። ለረጅም ጊዜ መንግሥት ተረክቦ ሲያስተዲድራቸው የነበሩ ቤቶች ሉመለስልኝ ይገባል በማለት ክስ የሚያቀርብ ወገንም ከላይ እንደተጠቀሰው በአዋጅ 47/67 የተፈቀደለት ስለመሆኑ ወይንም ከአዋጅ ውጪ ተወስድብኛል የሚል ከሆነም ለሚመለከተው አካል አቤቱታ አቅርቦ ውሣኔ አንኝቶ ባለመብት መሆኑ ካልተረጋገጠ ክስ በቀረበበት ነገር ላይ መብት ወይም ጥቅም እንደላለው እንደሚቆጠር ይህ ሰበር ችልት በመ/ቁ. 14ዐ94 የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
ስለሆነም በተያዘውም ጉዲይ አመልካቾች ቤቱ ሉመለስልን ይገባል በማለት ክስ ያቀረቡት በቤቱ ላይ መብት ያላቸው መሆኑን ባላረጋገጡበት ሁኔታ ስለሆነ የደሴ ከተማ ወረዲ ፍ/ቤት ቤቱ ሉመለስላቸው ይገባል በማለት የሰጠውን ውሣኔ የደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በተለየ ምክንያት ቢሽረውም ከውጤት አኳያ ግን የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
ው ሣ ኔ የደሴ ከተማ ነክ ጉዲዮች ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐዐዐ5 በ19/3/2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠው ፍርድ እንደዚሁም የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. ዐዐ751 በ14/5/2ዐዐ1 ዓ.ም. የሰጠውን ትዕዛዝ ምክንያቱን ለውጠን አጽንተነዋል።
አመልካቾች ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ ክስ ለማቅረብ የሚያስችል መብት ያላቸው መሆኑን ስላላረጋገጡ ክሱ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
ወጪና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
No topics extracted.