No summary available.
የሰ/መ/ ጥቅምት 3 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሀይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - አልቀረበም ተጠሪ፡- እማሆይ ፀሐይቱ አምበለ - ወኪል ቀረቡ መዝገቡ ተመርምሮ ቀጥል የተመለከተው ፍርድ ተሰጥቷል።
የሰበር አቤቱታው የቀረበው የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ ሰኔ 29 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመጽናቱ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት አመልካች ቅሬታ በማቀረቡ ነው።
ጉዲዩ የተጀመረው በምዕራብ ጏጃም ዞን አስተዲደር ከፍተኛ ፍ/ቤት ሲሆን ተጠሪ በአመልካች ላይ ባቀረቡት ክስ በጅጋ ከተማ በ500 ካ/ሜትር ቦታ ላይ ያረፈውን ቤት ከሳሽና ሟች ባለቤቴ ቄስ አለሙ ከበደ ወ/ሮ አስካለ አድማሱ ከተባለት ግለሰብ ገዝተን ባለሀብትነቱን በባለቤቴ ስም አዙረን ከዚያም ባለቤቴ ሲሞቱ በከሳሽ ስም ዞሮ ከነሐሴ 1975 እስከ ሰኔ 1998 ዓ.ም ድረስ ከሳሽ ግብር እየከፈልኩ ለ23 ዓመት በባለሀብትነት ይዤው የምገኝ ሲሆን ቤቱን መያዣ ለማድረግ የሚያበቃ ውክልና ሳይኖር ተከሳሽ መያዣ አድርጌዋለሁ በማለት በጨረታ ለመሸጥ የጋዜጣ ማስታወቂያ ያወጣ ስለሆነ ባንኩ ቤቱን ለመሸጥ ከሕግ ወይንም ከውል የመነጨ መብት ሳይኖረው ሉሸጥ ስለማይችል መብት የለውም ተብል ይወሰንልኝ በማለት ጠይቀዋል።
የከሳሽ ክስና ማስረጃም ለተከሳሽ ደርሶ በሰጠው መልስ ክስ የቀረበበትን ቤት ተከሳሽ በሐራጅ ለመሸጥ የተነሳው ከአቶ ምንውየለት ዓለሙ ጋር ባደረገው የብድር ውል ተበዲሪው መጋቢት 4 ቀን 1987 ዓ.ም ለንግድ ሥራ ማስፊፉያ የሚያውለት ብር 30 ሺህ በብድር ሲወስደ መያዣ ስለሰጡ ነው። ይህም የሆነው ቤቱ በተበዲሪው ስም የተመዘገበ ስለመሆኑና ዕዲና ዕገዲ የላለበት ስለመሆኑም የጅጋ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በሰጠው ማረጋገጫ መሰረትና መያዣውም በማዘጋጃ ቤቱ በመመዝገቡ ነው። ስለሆነም ክሱ ውድቅ ላደረግ ይገባል በማለት ተከራክሯል።
የግራ ቀኙ ክርክር በዚህ መልኩ የቀረበለትም የምዕራብ ጏጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክር የተነሳበትን ቤት ከሳሽና ባለቤታቸው የገዙት ነው ወይንስ የተበዲሪው የአቶ ምንውየለት ዓለሙ ነው? የሚል ጭብጥ መስርቶ ጉዲዩን በመመርመር ከሳሽ ከባለቤታቸው ቄስ ዓለሙ በላይ ጋር በትዲር አብረው በነበሩ ጊዜ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውን ቤት ከወ/ሮ አስካለ አድማሱ ላይ ገዝተናል ቢለም ይህንን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ካለማቅረባቸውም በላይ ስመ ንብረቱም ከወ/ሮ አስካለ አድማሱ ወደ ቄስ ዓለሙ በላይ ስለመዞሩ የቀረበ ማስረጃ የለም። አንድ የማይንቀሳቀስ ንብረት ሽያጭ ውል ንብረቱ ባለበት አገር በሚገኘው በማይንቀሳቀስ ንብረት መዝገብ ካልተጻፈ በስተቀር በ3ኛ ወገኖች ዘንድ ውጤት እንደላለው በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2878 ላይ የተመለከተ ስለሆነ ከሳሽም በስማቸው ከ1975-1998 ዓ.ም ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ቢረጋገጥም የሽያጭ ውለ ሥልጣን ባለው አካል ካልተመዘገበ ውጤት የላለው ነው ካለ በኋላ አቶ ምንውየለት ዓለሙ ከተከሳሽ ገንዘብ ሲበደሩ ይህንኑ ቤት አስይዘው መሆኑን እንደዚሁም የጀጋ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ክርክር የተነሳበት ቤት የአቶ ምንውየለት ዓለሙ መሆኑን ያረጋገጠ ስለሆነ ከሳሽ የቤቱ ባለቤት ስለሆንኩ ተከሳሽ መብት የለውም ተብል ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡት ክስ የማስረጃ ድጋፍ የለውም በማለት ሳይቀበለው ቀርቷል።
ከሳሽ በዚህ ውሳኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ጠቅላይ ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ ለክርክሩ መነሻ ምክንያት የሆነውን ቤት፤የይግባኝ ባይ ባለቤት የነበሩት ቄስ ዓለሙ በላይ ከወ/ሮ አስካለ አድማሱ ገዝተው ስም ንብረቱ መዞሩንና በስማቸው መመዝገቡን በደረሰኝ በሆነ ለውል ማስመዝገቢያ መክፈል የሚገባውን በማስከፈል የመዘገበ መሆኑን የጅጋ ከተማ ማዘጋጃ ቤት የሰጠው ማስረጃ ያስረዲል። ከዚያ በኋላም ይግባኝ ባይና ባለቤታቸው የከተማ ቦታ ኪራይ ለመንግስት እየከፈለ እስከ 1977 ዓ.ም ይዘውት እደቆዩና ከዚያም ቄስ ዓለሙ በላይ ሲሞቱ ይግባኝ ባይ በስማቸው በማዛወር የከተማ ቦታ ኪራይ ለመንግስት ሲከፍለ እንደነበር የቀረቡት ማስረጃዎች ያረጋግጣለ ካለ በኋላ በልላ በኩልም መ/ሰጭ ቤቱ የተበዲሪው የአቶ ምንውየለት ዓለሙ መሆኑን ያቀረበው ማስረጃ የጅጋ ከተማ ልዩ ቀበላ ፍርድ ሸንጏ በማስረጃ አረጋግጦ በመስጠቱና የከተማው ማዘጋጃ ቤትም የተበዲሪው ቤት መሆኑን በማረጋገጥ የጻፈውን ደብዲቤ መነሻ በማድረግ ነው። ሆኖም ግን ቤቱ የተበዲሪው ቢሆን ኖሮ ጅጋ ከተማ ማዘጋጃ ቤት እያለ የከተማ ቤትና ቦታን የማስተዲደርና የመመዝገብ ሥራ እንደሚሰራ እየታወቀ ከዚሁ አካል ቤቱ የተበዲሪው መሆኑን ማረጋገጥ እየተገባ በቀበላ ፍርድ ሸንጏ በኩል ይህንን ማረጋገጥ ሥልጣን አለው ለማለት አይቻልም። የጅጋ ከተማ ማዘጋጃ ቤትም ክርክር የተነሳበት ቤት የተበዲሪው መሆኑን ቢገልጽም የመያዣ ውለን ተቀብል ስለመመዝገቡ ያላረጋገጠ ስለሆነ የመያዣ ውለ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3052 አግባብ መሰረት ተመዘግቧል ለማለት ስለማይቻል በዚህ ሁኔታ መ/ሰጪ ቤቱን መያዣ አድርጎታል ተብል የይግባኝ ባይ መብት ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱ በአግባቡ አይደለም በማለት የከፍተኛውን ፍ/ቤት ውሳኔ በመሻር ቤትና ይዞታው የይግባኝ ባይ ነው ሲል ውሳኔ ሰጥቷል።
No topics extracted.
መ/ሰጭም (የአሁን አመልካች) በዚህ ውሳኔ ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው ውሳኔ ጉድለት የላለው ነው በማለት አጽንቶታል።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን ይህ ችልትም አቤቱታውን መርምሮ አመልካች ክርክር ባስነሳው ቤት ላይ የመያዣ መብት የለውም ተብል በአማራ ክልል ጠቅላይና በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት መወሰኑ ለሰበር ቀርቦ ላታይ እንደሚገባው በማመኑ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የጉዲዩ አመጣጥና ይዘት ከፍ ብል የተመለከተው ሲሆን የዚህን ሰበር ችልት ምላሽ የሚሻው የጉዲዩ ጭብጥ ለክርክሩ ምክንያት በሆነው ቤት ላይ አመልካች የመያዣ መብት አለው? ወይንስ የለውም?
የሚለው ነው።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3041 ላይ እንደተመለከተው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ በቀጥታ ከሕግ፣ ከፍርድ ወይንም ከውል ሉመነጭ ይችላል። አንድ የመያዣ ንብረት በመያዣ ከተሰጠ በመብቱ ለመገልገል እንዱቻል መያዣው አግባብ ባለው አካል መመዝገብ እንዲለበትም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 3052 ላይ ተመልክቷል።
በዚህ ጉዲይ አቶ ምንውየለት ዓለሙ የተባለት ተበዲሪ ከአመልካች ላይ ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ) ሲበደሩ በጅጋ ከተማ ቀበላ 01 ክልል የሚገኘውንና ቁጥር 835 የሆነውን ቤት በመያዣነት ሲያቀርቡ የከተማው ማዘጋጃ ቤት ይሄው ቤት በተበዲሪው በአቶ ምንውየለት ዓለሙ ስም እንደተመዘገበና ዕዲና ዕገዲም እንደላለበት ለአበዲሪው ባንክ (ለአመልካች) በማረጋገጥ መያዣውንም የመዘገበ ስለመሆኑ በምዕራብ ጏጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ክርክር ሲደረግ አመልካች ባቀረበው ማስረጃ መረጋገጡን ከመዝገቡ ተረድተናል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች ክርክር ባስነሳው ቤት ላይ የመያዣ መብት የለውም ወደሚል መደምደሚያ ለመድረስ የቻለው ከፍ ብል እንደተመለከተው ብድሩ በሚሰጥበት ወቅት ቤቱ የተበዲሪው መሆኑን ያረጋገጠው የከተማው ማዘጋጃ ቤት ሳይሆን የቀበላው ፍርድ ሸንጏ ስለሆነ ይህ አካል ይህንን የማረጋገጥ በሕግ ሥልጣን የለውም እንደዚሁም መያዣው ስለመመዘገቡ አልተረጋገጠም የሚለ ምክንያቶችን መሰረት በማድረግ ነው።
ሆኖም ግን የቀበላው ፍርድ ሸንጏ የቤት ባለቤትነትን በማረጋገጥ ማስረጃ የመስጠት ሥልጣን የለውም ቢባል እንኳን ቤቱ በተበዲሪው ስም ተመዝግቦ እንደሚገኝና ዕዲና ዕገዲም እንደላለበት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ከማረጋገጡም በላይ፤ ተበዲሪው አቶ ምንውየለት ዓለሙ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍኖተሰላም ቅርንጫፍ ለክርክሩ ምክንያት የሆነውንና ቤት በዋስትና አስይዘው ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ) ሲበደሩ መያዣውንም ተቀብል መመዝገቡንም የከተማው ማዘጋጃ ቤት ያረጋገጠ እንደመሆኑ መጠን ተበዲሪው የቤቱ ባለቤት ስለመሆኑ ሥልጣን ባለው አካል በተሰጠ ማስረጃ አልተረጋገጠም መያዣውም አልተመዘገበም መባለ ተገቢነት ያለው ሆኖ አልተገኘም።
በልላ በኩልም ተጠሪ የዚሁ ቤት ባለሀብት ስለመሆናቸው አጥብቀው የተከራከሩ ቢሆንም የንብረት ባለሀብትነት ከሕግ ወይንም ከውል የሚመነጭ ሲሆን ይህንኑ መሰረት አድርጎ በዚሁ ክርክር ባስነሳ ቤት ላይ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1195(1) መሰረት ከመንግስት አስተዲደር አካል ባለሀብትነታቸውን በማወቅ የተሰጠ የባለቤትነት የምስክር ወረቀት ወይም ባለሀብትነትን የሚያሳይ ማስረጃ በማቅረብ ባለሀብትነታቸውን ያላረጋገጡ ስለሆነ በዚህ ሁኔታ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ተጠሪ የቤቱ ባለሀብት ናቸው በማለት የሰጠው ውሳኔ የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤትም ይህንኑ ውሳኔ ማጽናቱ የአመልካችን የመያዣ መብት የሚጻረርና መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ. ሰኔ 29 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እንደዚሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ. ሰኔ 29 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 348(1) መሰረት ሽረናል።
የምዕራብ ጏጃም ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ.