No summary available.
ሐምል 21 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ግርማ ትኩ - ከማረሚያ ቤት ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን - አልቀረቡም።
መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት በመዝገብ ጥቅምት 21 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኝነት የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት ጥር 4 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር ማመልከቻ ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ መጀመሪያ የታየው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው።
በከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ አመልካች የወንጀል ሕግ አንቀጽ 408 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 በመተላለፈ ሁለት ወንጀልችን እንደፈፀመ በመግለጽ ክስ አቅርቧል። አመልካች ከአቶ መሐመድ ኑር በአቶ ዮናስ ገብርአብ በኩል ብር 2,300(ሁለት ሺህ ሦስት መቶ) ጉቦ ተቀብሎል ተብል የተከሰሰበትን ወንጀል ተጠሪ እንደ ክሱ አቀራረብ ባለማሥረዲቱ አመልካች በከፍተኛ ፍርድ ቤት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 141 መሰረት በነፃ እንዱያሰናበት ብይን በመስጠቱና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ብይን ለይግባኝ ሰሚ ችልት የፀና በመሆኑ በዚህ መዝገብ የግራ ቀኙ የመከራከሪያ ጭብጥ ሆኖ አልተያዘም።
በዚህ መዝገብ አከራካሪ ሆኖ የተያዘው ጭብጥ ተጠሪ አመልካች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 408 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 የተመለከተውን በመተላለፍ ሐምል ወር 1999 ዓ.ም የአዱስ አበባ ከተማ ነክ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ፕሬዚዲንት ሆኖ ሲሰራ በልደታ ምድብ በመዝገብ እነ ካልዩ ኡመር በሚል በሚጠራው ፊይል ተከሳሽ የሆኑት አቶ አልዬ ኡመር ጉዲዩ እንዱወሰንለት ከፈለገ ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ይክፈል በማለት አብረሐም ገብረክርስቶስ በተባለ አደራዲሪ አማካኝነት ጉቦ እንዱሰጠው በመጠየቅ የሙስና ወንጀል ፈጽሟል በማለት ያቀረበውን ክስ ለማስረዲት ተጠሪ የቀረበውን ማስረጃ የአመልካችን መከላከያ ማስረጃና በፍርድ ቤት ተጣርተው እንዱቀርቡ የተደረጉ ማስረጃዎችን በመመርመር የከፍተኛው ፍርድ አመልካች በነፃ እንዱሰናበት የሰጠውን ውሣኔ ተጠሪ በይግባኝ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ፣ ይግባኝ ሰሚው ችልት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ነው።
በሥር የተደረገው ክርክር መሰረታዊ ይዘት ስንመለከተው ተጠሪ በአመልካች ላይ የቀረበውን አንደኛ ክስ ለማስረዲት ሶስት ምስክሮችን አቅርቦ አሰምቷል። አንደኛውን ለማስረዲት የቀረበው የመጀመሪያው የተጠሪ ምስክር ለተጠሪ የወንጀል ክስ በግል ተበዲይነት ስማቸው የተጠቀሰው አቶ ኡመር አልዬ ናቸው። ምስክሩ 1989 ዓ.ም በሉዝ ቦታ ገዝቶ የነበረ ቢሆንም በፍርድ ቤት ክርክር የነበረበት በመጀመሪያ ጉዲዩን የያዙት ዲኛ ላላ ዲኛ የነበሩ መሆኑንና አመልካች ጉዲዩን የያዙት ዲኛ በእድገት ወደ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ከተዛወሩ በኋላ ማየት እንደጀመሩ ጉዲዩ ስለተጓተተብኝ ጉዲዩን ብርሃኑ ለተባለ ጠበቃ እንዲማከሩትና ጠበቃውም አብርሐም ገብረክርስቶስ የሚባለውን የተጠሪ ምስክር አመልካችን ስለሚያውቀው ይጨርስልሐል ብል ያማከረው መሆኑን አስረድቷል።
ከዚህ በኋላ ምስክሩ ላላውን የተጠሪ ምስክር አብርሃም ገብረክርስቶስ ደውል ለሆነ ጉዲይ እፈልግሐለሁ እንዲለውና ጉዲዩን ለመወሰን ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ) አመልካች እንደሚፈልግ አብርሃም ገብረክርስቶስ የነገረው መሆኑን፣ከአመልካች ቢሮ በመሄድ ገንዘቡ ስለሚበዛ እንዱቀንስለት እንደጠየቀው አመልካችም ስልክህን ስጠኝ እደውልልሃለሁ በማለት እንደጠየቀውና ምስክሩ ስልኩን ሰጥቶት እንደወጣ መስክሯል። ምስክሩ ከዚህ በኋላ ግንቦት 23 ቀን 1999 የፋዳራል ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር እንዲመለከተ ገልፆአል። ከዚህ በኋላ አመልካች ስልክ ደውል ተዘጋጅተሐል ወይ ብል እንደጠየቀውና ደሴ ሆቴል አካባቢ እንዱመጣ እንደነገረው ምስክሩም ለአመልካች መልሶ ስልክ እንደደወለለትና ደሴ ሆቴል ሄድ እየጠበቀው እንዲለ አመልካች ስልክ ደውል ቆዲ ጃኬትና ነጭ ሸሚዝ ለለበሰ ሰው እንዱልክ የነገረው መሆኑን ምስክሩም በተነገረው ምልክት መሰረት የተላከውን ሰው ደሴ ሆቴል አግኝቶ ሰላሣ ሺህ ብር እንደሰጠው መሥክሯል። ከዚህ በተጨማሪ ምስክሩ በዚያው እለት ገንዘቡን ሰጥቶ ተመልሶ ቄራ አካባቢ እንደደረሰ አመልካች ስልክ ደውል ገንዘቡ ለምን ከብር 50,000(ሃምሳ ሺህ)እንደቀነሰ እንደጠየቀውና አስር ሺህ ብር ካልጨመረ እንደማያስወስንለት የሰጠው ገንዘብ እንደማይመለስ የገለፁለት መሆኑን ምስክሩም በሐሳቡ በመስማማት ቀደም ብል 30,000(ሰላሳ ሺህ ብሩን) የተቀበለው ሰው ደውልለት ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) እንደሰጠ መሥክሯል።
No topics extracted.
ከዚህ በኋላ ምስክሩ ገንዘቡን የተቀበለውን ሰው አግኝቶት ዓለም ባንክ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ ወደሚገኘው የተከሳሹ(አመልካች) መኖሪያ ቤት ውሣኔ ከመስጠቱ ከአንድ ቀን በፉት በግምት ከዘጠኝ እስከ አስር ሰዓት ባለው ጊዜ ሄደው አመልካች ከቤቱ ወጥቶ ተቀብሎቸው መኪና ውስጥ እንደገባ ብር 10,000(አስር ሺህ ብር) ምክስሩን ከዚህ በፉት ገንዘብ ለተቀበለው ሰው እንደሰጠና ሰውየውም ተቀብል ለአመልካች እንደሰጠው ሐምል 30 ቀን 1999 ዓ.ም ውሣኔ እንደሰጠው ከዚህ በኋላ ለሥነ- ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ሪፖርት እንዲደረገ መሥክሯል።አመልካች ለተጠሪ ምስክር ኡመር አልዬ ይደውልላቸው የነበረው ቁጥራቸው 0911-18-54-60 እና 0911-64-14-31 በሆኑ የሞባይል ስልኮች እንደነበርና የምስክሩ የሞባይል ስልክ ቁጥር 0911-20-00-79 መሆኑን አስረድተው የተመለሱ መሆኑን ከከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል።
ተጠሪ በአመልካች ላይ የቀረበውን አንደኛ ክስ ለማስረዲት አቅርቦ በምስክርነት የሰማው አቶ አስማረ ገበየሁን ሲሆን አመልካችን ከተጠሪ ምስክር አብርሃም ጋር ያስተዋወቀው መሆኑን ከዚያ በኋላ ለአራት ወራት ለመስክ ሥራ መሄደንና ከመስክ ሲመለስ አብርሃም አመልካች ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ጠይቋል በሚል ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን ሲነግረው በመደናገጥ ለአመልካች ደውል የሰማውን ሲነግረው አመልካች በመቆጣት መረጃው ሐሰተኛ መሆኑን የማያውቀው ነገር ውስጥ እንዲይገባ እንደነገረው መስክሯል። ይኸው ምስክር አብርሃምን በመጠራጠር መረጃው የመነጨው ከእሱ አለመሆኑን ተከሳሹን (አመልካችን) ለማሣመን እንድችል አብርሃም መረጃውን በድጋሚ እንድነግረው በማድረግ የአብርሃምን ንግግር በሞባይል ቀድቶ ለአመልካች እንዲሰማው አመልካች አብርሃም ወስላታ ነው አትመነው እዲለውና ከዚህ በኋላ አብርሃምን ያላየኸውን ያልሰማኸውን የምታወራው ለምንድን ነው ሁለተኛ አትደውል ብል የነገረው መሆኑንና የአመልካችና የአብርሃም ግንኙነት እንደተቋረጠ መሥክሯል። አብርሃምን የቀዲው አብርሃም ሣያውቅ ነው። ከዚህ በኋላ የፀረ ሙስና ኮሚሽን መርማሪዎች ጠይቀው ሞባይል ውስጥ የነበረውን ንግግር ቅጅ ወስደዋል በማለት የመሰከረ ነው።
የተጠሪ የመጨረሻው ምስክር አቶ አብርሃም ገ/ክርስቶስ ሲሆን ይኸው ምስክር አመልካችን ቀደም ብል እንደሚያውቀውና አስማረ ገበየሁ የተጠሪ ምስክር አመልካችን እንዲስተዋወቀው ከገለፀ በኋላ መሐመድ የሚባል የተጠሪ የመጀመሪያ ምስክር የሆኑት የአቶ ዐመር አልዬ ልጅ ጋር ቀደም ሲል ጓደኝነት የነበረው መሆኑንና መሐመድ የሚባለው የዐመር አልዬ ልጅ አሁን አሜሪካን አገር የሚኖር መሆኑን ከገለፀ በኋላ መሐመድ የእኔና የአመልካች ጓደኛሞች መሆናችንን ያውቅ ስለነበር በመጀመሪያ የተጠሪ ምስክር ዐመር አልዬ አመልካች የያዘው ጉዲይ እንዲለው ሲነግረው የእኔና የአመልካች ግንኙነት ንፁህ ጓደኝነት ነው ብል እንደመለሰለትና በዲኝነት በያዘው ጉዲይ ማነጋገር እንደማይፈልግ እንደገለፁለት ይህንን ጉዲይ ሁለተኛ እንዲያነሳበት በመግለጽ እንደመለሱለት መሥክሯል።
ከዚህ በኋላ የተጠሪ ምስክር ዐመር አልዬ ልጅ መሐመድ ከአሜሪካን አገር ደውል የጓደኛህ በችልት ላይ እየሰደበው አባቴን አሞታል በማለት የነገረው መሆኑንና እሱም ለማጣራት ለአቶ ዐመር አልዬ ሲደውል ጓደኛህ ከባለጋራዎቼ ፉት በችልት ስለሰደበኝ በዚህ ምክንያት ታምሜአለሁ ብል የነገረው መሆኑን ገልጿል።
ይኸው ምስክር ይህንኑ ጉዲይ ደውል ለአመልካች እንደነገረውና ለአመልካች ስም ጥሩ እንዲልሆነ እንደገለፁለት አመልካችም አቶ ዐመር አልዬ ጉዲያቸው በተለየ መልኩ የተያዘ አስመስለው ችልት ላይ ኦቨር አክት በማድረጋቸው እንደተቆጣቸው የገለፁለትና ቢሮ ላካቸው አነጋግራቸዋለሁ እንዲለ መስክሯል።
ከዚህ በኋላ የተጠሪ ምስክር ዐመር አልዬ አመልካች ቢሮ በመሄድ እንዲነጋግራቸው ጉዲዩን አመልካች በብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ሉይዝልኝ ነው በማለት አቶ ዐመር እንደነገሩትና ስለዚህ ጉዲይ የማውቀው የለኝም ብል ምስክሩ አቶ ዐመርን እንደመለሰስላቸውና ስለዚህ ጉዲይ አመልካችን እንዲልጠየቀው አቶ ዐመር አልዬ ቤት ሲመጣ የለም ብለው እንዱመልሱት ለቤተሰቦቹ መናገራቸው ስልኩንም ማንሣቱን በማቆም ግንኙነቱ እንዲቋረጥ ከአቶ ዐመር አልዬ ጋር የሚከራከሩት ሙክታርና ሴኮ የሚባለ ወንድማማቾች አመልካች ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ተቀብል ሉወስንብን ስለሆነ አመልካችን አናግርልን ብለው የጠየቁት መሆኑንና አመልካች ጋር የነበረው ግንኙነት ተቋርጦ የነበረ በመሆኑ ለአመልካች እንዲልነገረው መመሥከሩን ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል ተጠሪ አመልካች በመዝገብ በዲኝነት ተሰይሞ የነበረውና ሐምል 30 ቀን 1999 ዓ.ም ውሣኔ የሰጠ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ አስማረ ገበየሁ የተባለው የተጠሪ ምስክርና አብርሃም ገብረክርስቶስ የተባለው የተጠሪ ምስክር የተለዋወጡትን ንግግር ቅጅ የያዘ ሲዱ በማስረጃነት አቅርቧል። አመልካች አምስት የመከላከያ ምስክሮች ቃል ያሰማ ሲሆን ላልች የሰነድ ማስረጃዎች የመዝገብ የሰጠው ውሣኔ እንዱያያዝለት አድርጓል።
የሥር ፍርድ ቤት አንደኛ የተጠሪ ምስክር አቶ ዐመር አልዬ እና በአመልካች መካከል የስልክ ልውውጥ የተደረገ መሆኑን ለማረጋገጥ ከሚያዝያ 1 ቀን 1999 ዓ.ም እስከ ሐምል 30 ቀን 1999 ዓ.ም በተጠሪ ምስክር ዐመር አልዬና በአመልካች መካከል የተደረገ የስልክ ጥሪ መኖሩን አጣርቶ እንዱልክ ለቴላኮሚኒኬሽን ተደጋጋሚ ትእዛዝ ሰጥቶ መጋቢት 17 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ሸኝ ደብዲቤ ጋር ተያይዞ ስድስት ገጽ ማስረጃ ተልኮለታል።
ከቴላኮሚኒኬሽን በተላከው ደብዲቤ መሰረት የአመልካች ስልክ ነው በማለት የተጠሪ ምስክር አቶ ዐመር አልዬ ቁጥራቸውን የገለፃቸው ሞባይልች ቁጥር 0911-18-54-60 የሆነው በአቶ ሰይድ አደም ዐመር ስም ቁጥሩ 0911- 64-14-31 የሆነው በአመልካች ስም ያለ መሆኑን ተረጋግጧል ከዚህ በተጨማሪ።
የተጠሪ ምስክር የሆነው የአቶ ዐመር አልዬ ነው የተባለው ቁጥሩ 0911-20-00-79 እና የአመልካች ስልክ ናቸው በተባለት ቁጥራቸው 0911-18-54-60 እና 0911 40-90-99 መካከል የተደረገ የስልክ ግንኙነት ፍርድ ቤቱ በጠየቀው ጊዜ ውስጥ አለመኖሩንና ከተጠሪ ምስክር አቶ ዐመር አልዬ ስልክ ነው በተባለው ቁጥር 0911-20-00-79 የተከሳሹ ስልክ ነው ወደተባለው ቁጥሩ 0911-64-14-31 ወደሆነው ሞባይል በፈረንጆች አቆጣጠር ጁላይ 8 ቀን 2007 ዓ.ም አንድ ጥሪ ጁላይ 21 ቀን 2007 ዓ.ም ሁለት ጥሪዎች በድምሩ ሶስት ጥሪዎች መደረጋቸው ተረጋግጧል።
ከዚህ በተጨማሪ የተከሳሽ ነው ከተባለው ቁጥሩ 0911 64-14-31 ከሆነው ሞባይል የተጠሪ ምስክር የአቶ ዐመር አልዬ ስልክ ነው ወደተባለው ቁጥሩ 0911-20-00-79 ወደሆነው ሞባይል የተደረገ የስልክ ጥሪ የላለ መሆኑን በቀረበው ማስረጃ ተገልጿል። የከፍተኛው ፍ/ቤት የተጠሪ ምክስርና የግል ተበዲይ ነኝ የሚለት አቶ ዐመር አልዬ አመልካች በስልክ ደውል ገንዘቡን እሱ በምልክት ለላከው ሰው አቀብያለሁ በማለት የሰጡት ምስክርነት ከአመልካች ወደ ተጠሪ ምስክር ስልክ የስልክ ጥሪ ያልተደረገ መሆኑ ከቴላኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽን በቀረበው ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ የምስክሩ ቃል ታዓማኒነት የለውም በማለት አመልካች በነፃ እንዱሰናበት በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 149/2/ መሰረት ወስኗል።
ተጠሪ በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ የይግባኝ ችልቱ መዝገቡ ለአስራ ሁለት ቀጠሮዎች የተቀጠረ መሆኑ በቴላኮሚኬሽን የመጣው መረጃ የአቃቤ ሕግ ማስረጃ የሚያጠናክር ሆኖ እያለ ለጉዲዩ ግንኙነት የለውም መባለ ተገቢ አይደለም የግል ተበዲዩ ቤቱ ድረስ መሄዲቸውን 10,000(አስር ሺ ብር) መስጠታቸው የመሰከሩ በመሆኑንና ምስክሩ እውነቱን ይመሰክራለ ተብለው ስለሚገመቱ የአቃቤ ሕግ ማስረጃ አመልካች ወንጀለን መፈፀሙን አረጋግጦል በማለት አመልካች በክሱ የተጠቀሰበትን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 408 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 የተላለፈ ጥፊተኛ ነው ብል በሰባት ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 1000/አንድ ሺህ ብር/ መቀጮ እንዱቀጣ ፍርድ ሰጥቷል።
አመልካች ጥር 4 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪ በሕግ የተጣለበትን የማስረዲት ሸክም አልተወጣም። የአቃቤ ሕግ ማስረጃ ወንጀለን አለመፈፀሜን የሚያስረደ ናቸው። የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የወንጀል ይግባኝ ችልት ውሣኔ የሰጠው በአቃቤ ሕግ ምስክሮች የተረጋገጠውን ፍሬ ጉዲይ መሰረት በማድረግ ሣይሆን የራሱን የሕሉና ግምት በውሰድ ነው። በአቃቤ ሕግ ማስረጃ የተገለፀው ፍሬ ጉዲይ እና ወንጀለን የፈፀምኩ ስለመሆኔ ለማቋቋም ብቃት የላላቸው ናቸው የተጠሪ ምስክር ከግል የነበራቸውን ጥላቻ መነሻ በማድረግ በሰጡት የሐሰት ምስክርነት መነሻ በማድረግ የተሰጠው የጥፊተኝነት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው የቅጣት ውሣኔም የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶችን ያገናዘበ አይደለም የሚል ይዘት ያለው አስራዘጠኝ ገጽ የሰበር አቤቱታ አቅርቧል። ተጠሪ በበኩለ አመልካች የሰበር ችልቱን የሚጠይቀው የፍሬ ጉዲይና የማስረጃ ስህተት እንዱታረምለት ነው። አመልካች የግል ተበዲዩን ከአስራ ሁለት ቀጠሮ በላይ በማጉላላት የግል ተበዲይ ጉቦ እንዱሰጧቸው ያስገደዶቸው መሆኑን በማስረጃ ተረጋግጧል ይግባኝ ሰሚው ችልት ለህሉና ግምት ሣይሆን በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ጉዲይ መሰረት በማድረግ የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም የሚል ይዘት ያለው ሰፉ የቃል ክርክር አቅርቧል አመልካች በቃል ክርክሩ የመልስ መልስ ሰጥቷል።
የግራ ቀኙ መካከል በሥር ፍርድ ቤት የቀረበው ክርክርና በተጠሪ በኩል የቀረቡትን ማስረጃ ይዘት የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት ማስረጃ ተዓማኒነት በመመርመር ረገድ በመለያየት የሰጡት የተለያየ ፍርድ ይዘትና በሰበር አመልካችና ተጠሪ ያቀረቡት ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው ተጠሪ አመልካች በክሱ የተገለፀውን የወንጀል ድርጊት የፈፀሙ ስለመሆኑ በሕግ የተጣለበትን ሸክም ተወጥቷል ወይስ አልተወጣም? የሚለውን ጭብጥ በወንጀል ጉዲይ ተከራካሪዎች ስላለባቸው የማስረዲት ግዳታ ኃላፉነት (Burden of proof) ፍርድ ቤቶች የተከራካሪዎቹን ማስረጃ ታዓማኒነት በሚመረምሩበት ወቅት ሉከተላቸው የሚገባቸውን መሰረታዊ የማስረጃ ሕግ መርሆችንና ላልች አግባባነት ካላቸው የሕግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በዝርዝር ማየት አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ የከሳሽ(ተጠሪ) የማስረዲት ሽክምና ኃላፉነት የሚወጣው በምን ሁኔታ ነው? የሚለውንና ላልች ተያያዠነት ያላቸውን ነጥቦች መመርመር አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
የወንጀል ክስ የቀረበ ከሳሽ ጉዲዩን የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነቱን ተወጥቷል ወይም አልተወጣም?
የሚለው ጭብጥ ለመወሰን የመጀመሪያው የማነፃፀሪያና የመመዘኛ መስፈርት ራሱ ከሳሽ ያቀረበው የወንጀል ክስ ማመልከቻ ነው። አንድ ድርጊት የተፈፀመ መሆኑን በመግለጽ ክስ ያቀረበ ወገን በክሱ የገለፀውን ፍሬ ጉዲይ የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነት አለበት የሚለው የማስረጃ ሕግ መርህ ይህንኑ የሚያጠናክር ነው። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ተጠሪ ጉዲዩን የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነቱን ተወጥቷል ወይስ አልተወጣም? የሚለው ነጥብ እልባት የሚሰጠው ተጠሪ ባቀረበው የወንጀል ክስ ውስጥ የተገለፁትን ፍሬ ጉዲዮች ትክክለኛነት ተጠሪ የወንጀል ክሱን ለማስረዲት ባቀረባቸው የተለያዩ ማስረጃዎች የሚያረጋግጡና በወንጀል ክሱ ውስጥ የተገለፀው ፍሬ ጉዲይና ክሱን ለማስረዲት ያቀረቡት ማስረጃዎች እርስ በርሳቸው የሚደጋገፈና ተያያዝነት ያላቸው ሆነው ሲገኙ ነው።
በአጠቃላይ ካሳሽ ክሱን ለማስረዲት ያቀረባቸው ማስረጃዎች ለጉዲዩ ያላቸው አግባብነት (Relevancy of Evidence) እና የከሳስ ማስረጃ የአስረጅነት ዋጋ ያላቸውና ታዓማኒነት ያላቸው መሆኑ የሚመረመረው ከሳሽ በወንጀል ክስ ማመልከቻው የገለፃቸውን ፍሬ ጉዲዮች መሰረት በማድረግ ነው። ተጠሪም ክሱን የማስረዲት ሸክሙን(ክሱን የማስረዲት ግዳታውን) የተወጣ መሆኑ ወይም አለመሆኑ መመርመር ያለበት ተጠሪ በክሱ ማመልከቻው የገለፃቸውን ፍሬ ጉዲዮች እውነት መሆናቸውን በተጠሪ ማስረጃ የተረጋገጡ መሆኑንና ተጠሪ ክሱን ለማስረዲት ያቀረባቸው ማስረጃዎች ተደጋጋፉ እና እርስ በርሳቸው የማይቃረኑ መሆናቸውን መሰረት በማድረግ ማስረጃዎቹን በመመርመር ነው።
የከፍተኛ ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ችልት ተመሣሣይ ይዘት ያላቸውን ማስረጃዎች ታዓማኒነት አስመልክቶ የተለያዩበት ዋናው ምክንያት የተጠሪ ማስረጃዎች እውነተኛ መሆናቸው መመርመር ያለበት ከምን አንፃር ነው በሚለው መስፈርት ላይ ከተጠሪ ክስ አንፃር ባለመመርመራቸው ነው። ተጠሪ በክሱ አመልካች በወንጀል ሕግ አንቀጽ 408 ንኡስ አንቀጽ 1 እና 2 የተመለከተውን በመተላለፍ በሐምል ወር 1999 በመዝገብ ተከራካሪ የነበሩትን አቶ ዐመር አልዬ( የተጠሪ ምስክር) ብር 50,000(ሃምሣ ሺህ ብር) ይክፈል በማለት በሶስተኛ የተጠሪ ምስክር አብርሃም ገብረክርስቶስ በተባለ አደራዲሪ በኩል ጉቦ ጠይቋል የሚል ክስ አቅርቧል።
የተጠሪ ክስ አመልካች በአብርሃም ገብረክርስቶስ በኩል ጉቦ ጠይቋል በሚል ሲሆን የግል ተበዲዩና አንደኛ የተጠሪ ምስክር አብርሃም እንዱያነጋግርልኝ አድርጌ ብር 50,000(ሃምሣ ሺህ ብር) አምጣ ተብለሐል ብል ነገረኝ በማለት የመሰከረ ሲሆን በወንጀል ክሱ አደራዲሪና ጉቦ ለአመልካች የተጠሪ ምስክርና የግል ተበዲዩ እንዱሰጥ ጠየቀ የተባለው ሶስተኛው የተጠሪ ምስክር አብርሃም ገብረክርስቶስ አመልካች የግል ተበዲይ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ይሰጠኝ ብል ያልጠየቀው በመሆኑ በተቃራኒው አመልካች ስለያዘው ጉዲይ የአቃቤ ሕግ ምስክር የሆነው የግል ተበዲይ እንዲያነሳበት እንደነገረው የአቶ ዐመር አልዬ አሜሪካን አገር የሚኖር መሐመድ የተባለ ልጅ አባቴን ጓደኛህ በድልት ታሞ ተኝቷል ብል እንደደወለለት እሱም ወደ አቶ ዐመር አልዬ ስልክ ሲደውል ከባለጋራዎቼ ፉት ሰደበኝ አዋረደኝ በዚህ ምክንያት ታምሜአለሁ ብለው እንደነገሩት እሱም አመልካችን ለስሙ ጥሩ እንዲልሆነና የተባለውን ስነግረው ምስክሩ በችልት ከሥርአት ወጥተው ስለነበር እንደተናገራቸውና ቢሮ ላካቸው አነጋግራቸዋለሁ በማለት እንደነገረውና የተጠሪ አንደኛ ምስክር ዐመር አልዬ ከአመልካች ቢሮው ውስጥ እንዲነጋገራቸውና በብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ሉሰራልኝ ተስማምተናል ብለው እንደነገሩት አብርሃም ገብረክርስቶስ ስለዚህ የሚያውቀው የላለ መሆኑን ገልፆ ከግል ተበዲይ ጋር የነበረውን ግንኙነት እንዲቋረጠ መሥክሯል። በልላ ጊዜ ከተጠሪ አንደኛ ምስክር ጋር የሚከራከሩ ሰዎች አመልካች ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ተቀብል ሉፈርድብን ነው ብለው እንደነገሩት መሥክሯል።
ተጠሪ በክሱ የተገለፀውን ፍሬ ጉዲይ “አመልካች በአብርሃም ገብረክርስቶስ በኩል ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ጉቦ እንድሰጠው የግል ተበዲይ ዐመር አልዬን መጠየቁን ያስረዲልኛል” በማለት ያቀረበው የተጠሪ ምስክር አብርሃም ገብረክርስቶስ አመልካች በዚህ አይነት ጥያቄ ያላቀረበለትን የግል ተበዲዩ ሰደበኝ ብል ስሞታ ከተናገረ በኋላ ቢሮው ሄድ እንዱያነጋግረው ከተደረገ በኋላ በብር 50,000(ሃምሳ ሽህ ብር) ሉይዝልኝ ተስማምተናል በማለት የግል ተበዲይ ራሱ ለተጠሪ ምስክር አብርሃም እንደነገረው መስክሯል። ከዚህ አንፃር ስንመለከተው ተጠሪ በአመልካች ላይ ያቀረበውን ክስ ለማስረዲት ያቀረባቸው ምስክሮች ዕርስ በርሱ የሚቃረን ማስረጃ (contradictory evidence) የሰጡ መሆናቸውን ለመገንዘብ ይቻላል። የተጠሪ ማስረጃ ዕርስ በርሱ የሚደጋገፍና በክሱ የተገለፀውን ፍሬ ጉዲይ የማያረጋግጥ በሆነ ጊዜና በተቃራኒው የተጠሪ ማስረጃና በክስ የተገለፀው ፍሬ ጉዲይ በልላ የተጠሪ ማስረጃ እውነትነት የላለው መሆኑ በተገለፀ ጊዜ ተጠሪ ክሱን የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነትቱን በአግባቡ ተወጥቷል ከሚል መደመደሚያ ላይ መድረስ አይቻልም። ከዚህ አንፃር የሥር ፍርድ ቤቶች በተጠሪ ክስ የተገለፀውንና በግል ተበዲይ የተሰጠውን የምስክርነት ቃል ተጠሪ ክሴን ያስረዲልኛል በማለት ባቀረበው አብርሃም ገብረክርስቶስ በሰጠው የምስክርነት ቃል እውነትነት የላለው መሆኑ የተገለፀ ሆኖ እያለ አመልካች የመከላከያ ማስረጃ እንዱያቀርብ ብይን መስጠቱ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ይግባኝ ሰሚው ችልትም ተጠሪ ባቀረበው ክስና በተጠሪ አንደኛ ምስክር ቃልና በተጠሪ ሶስተኛ ምስክር ቃል መካከል ያለውን ሰፉ ልዩነት በማየት ሣይመረምር ማለፈ ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። ተጠሪ ይህ ጉዲይ የፍሬ ጉዲይ ክርክር እንጅ የሕግ ስህተት አይደለም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ተጠሪ ባቀረበው የወንጀል ክስ አመልካች ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) በመዝገብ ተከራካሪ የነበሩት አቶ ዐመር አልዬ ከሶስተኛ የተጠሪ ምስክር(አብርሃም) አደራዲሪነት እንደሰጡት ጠይቋል ከማለት ውጭ አመልካች ከግል ተበዲይ ገንዘብ የተቀበለ መሆኑ መቼ እንደተቀበለና በማን በኩል እንደተቀበለ የገለፀ አለመሆኑን ከከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ እነዚህ ነገሮች ግልጽ በማድረግ ክሱን አሻሽል እንዱያቀርብ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርአት ሕግ ቁጥር 119 መሰረት ትእዛዝ መስጠት ነበረበት።
ተጠሪ በወንጀል ክሱ በዝርዝር ያልገለፃቸው ፍሬ ጉዲዮች የግል ተበዲይና የተጠሪ ምስክር በሆኑት አቶ ዐመር አልዬ ተገልፆዋል። ይኸው ምስክር በአንድ ቀን አመልካች በራሱ ስልክ ሶስት የስልክ ጥሪ ያደረገለት መሆኑን በመጀመሪያ ተዘጋጅተሐል ወይ ብል እንደጠየቀውና ደሴ ሆቴል አካባቢ እንደነገረው ከዚያም ምስክሩ ወደ አመልካች ስልክ በመደወል ደሴ ሆቴል እየጠበቀው መሆኑን ነግሮት እንደዘጋ ከዚያ በኋላ አመልካች ስልክ በመደወል ቆዲ ጃኬትና ነጭ ሸሚዝ ለለበሰ ሰው እንዱልክ እንደነገረው ምስክሩ በተነገረው መሰረት ደሴ ሆቴል ሰውየውን አግኝቶ ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ) እንደሰጠው ከዚያ በኋላ ተመልሶ ወደ ቄራ አካባቢ ሲደርስ አመልካች ለሶስትኛ ጊዜ ስልክ ደውል ገንዘቡ ለምን ከ50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) እንደቀነሰ እንደጠየቀውና አስር ሺህ ብር (10,000) ካልጨመረ እንደማይሰራለት እንደነገረው መሥክሯል። አመልካች ከግል ተበዲይና የተጠሪ ምስክር ጋር ግንኙኝነት ያደርግ የነበረው በስልክ መሆኑን የተጠሪ ምስክር ገልጿል። የተጠሪ ምስክር ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ ብር ) ማንነቱን ለማላውቀው ሰው ላዘር ጃኬትና ነጭ ሸሚዝ የለበሰ የሚል ምልክት አመልካች በስልክ ደውል ነግሮኝ ሰጥቻለሁ ያለበትን ቀን ሰዓት አልገለፀም። ምስክሩ ብር 30,000(ሰላሳ ሺህ) ስሙ ማንነቱ ለማይታወቅ ሰው ሰጠሁ ባለበት ቀን ብቻ አመልካች በእሱ የስልክ ሞባይል ሶስት ጥሪያዎችን እንዲደረገላቸው መስክረዋል።
ይሕ የተጠሪ ምስክር በእምነታቸው መሰረት ቃለ መሐላ ፈጽመው ለፍርድ ቤቱ የመሰከሩት እና የገለፁት ፍሬ ጉዲይ ነው። ሆኖም ይህንን ምስክርነት እውነት ነው ብል ለመቀበል ምስክሩ ቃለ መሐላ መፈፀማቸው ብቻ በቂ አይደለም። የምስክሩ ቃል ታዓማኒነት ያለው መሆኑን ለማረጋገጥ ከሚያዚያ 1 ቀን 1999 ዓ.ም የምስክሩ ጉዲይ ውሳኔ እስካገኘበት ሐምል 30 ቀን 1999 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ ከአመልካች ወደ ምስክሩ የስልክ ጥሪ ስለመደረጉ እንዲያረጋግጥ የቴላኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽን ተጠይቆ እንኳንስ በአንድ ቀን አመልካች ለተጠሪ ምስክር ሶስት ጊዜ ስልክ ሉደውል ይቅርና በሶስት ወራት ውስጥ አመልካች ለተጠሪ ምስክር ያደረገው የስልክ ጥሪ የላለ መሆኑ ተረጋግጧል።፡ ምስክሩ እንደ አውሮፖ አቆጣጠር ጁላይ 8 ቀን 2007 አንድ ጥሪ ጁላይ 21 ቀን 2007 ሁለት ጥሪዎች ወደ አመልካች ማድረጉ ምስክሩ ተጠሪ በቀን ሶስት ጊዜ ያሕል ደውል የት ቦታ እንደምጠብቀው ገንዘቡን ለማን እንደምሰጥና ለምን ገንዘቡ 30,000(ሰላሣ ሺህ) ሆነ አስር ሺህ ብር ጨምር በማለት አናግሮኛል በማለት የሰጠው ምስክርነት እውነት መሆኑን አያረጋግጥም። ስለዚህ የተጠሪ አንደኛ ምስክርና የግል ተበዲይ ነኝ ባዩ ዐመር አልዬ እውነት ነው በማለት ለፍርድ ቤት ስለወንጀለ አፈፃፀም ያስረደት ፍሬ ነገር ጭራሹኑ አመልካች የተደረገላቸው የስልክ ጥሪ የላለ መሆኑ በተረጋገበት ሁኔታ ምስክሩ የሰጡት ቃል ታዓማኒነት ያለው ነው በማለት ይግባኝ ሰሚ ችልት መደምደሙ አንድ ማስረጃ ሉመርመርና ሉመዘን የሚገባው ከነ ሙለ ይዘቱ እንጂ ተከሳሹን የሚጠቅመውን ክፍል ነጥል በማውጣትና ከሳሽ ካቀረበው ክስ ጋር የሚጣጣመውን የማስረጃ ክፍልና ይዘት ለይቶ በመያዝ መሆን እንደማይገባው በበርካታ አገሮች ተቀባይነት ያለውን የማስረጃ ታዓማኒነት ምርመራና ምዘና መርህ የሚጥስ ሆኖ አግኝተነዋል።
በአጠቃላይ አመልካች ጉቦ ጠየቀኝም ጉቦ ሰጠሁትም የሚለው ወሬ ብቸኛ ምንጭ የግል ተበዲዩ ዐመር አልዬ ሲሆን ላልቹ የግል ተበዲይ አወራን ወይም አብርሃም ሲያወራ ሰማሁ በማለት ሁለተኛ ምስክር የመሰከረ መሆኑንና የስሚ ስሚ ማስረጃ መሆናቸው ለመገንዘብ ይችላል።
አንደኛ የተጠሪ ምስክርና የግል ተበዲይ አመልካች ጉቦ የጠየቀው በአብርሃም አደራዲሪነት እንደሆነ በምስክርነቱ የገለጸ ሲሆን አብርሃም የተጠሪ ምስክር ሆኖ በመቅረብ ይህ የግል ተበዲይ ምስክርነት በሚቃረን መንገድ መሥክሯል። ከዚህ በተጨማሪ ምስክሩ አመልካች በችልት ሰደበኝ በሚል ምክንያት ታሞም እስከመተኛት ደርሶ የነበረ መሆኑንና ይህንን ሁኔታ የግል ተበዲይ ውጭ የሚኖር ልጅ ጭምር ሰምቶ ከውጭ አገር አብርሃምን ስልክ ደውል እንዲናገረው የተጠሪ ምስክር አረጋግጧል። ከዚህ በተጨማሪ የግል ተበዲይ ብር 30,000(ሰላሣ ሺህ ብር) ሰጠሁ ባለበት አንድ ቀን ውስጥ ብቻ አመልካች በእሱ ስልክ ሶስት ጊዜ ደውል ነበር በማለት የሰጡት ምስክርነት ከሚያዚያ 1 ቀን 1999 እስከ ሐምል 30 ቀን 1999 ዓ.ም ባለው ጊዜ ውስጥ አመልካች ለተጠሪ ምስክርና የግል ተበዲይ ዐመር አልዬ ያደረገው የስልክ ጥሪ አለመኖሩን በማረጋገጫ የቴላኮሚኒኬሽን ኮርፖሬሽን ከሰጠው ማስረጃ ተረጋግጧል። ይግባኝ ሰሚው ችልት ይህንን ያለፈው ከተጠሪ ምስክር ዐመር አልዬ ቃለ መሐላ ፈጽመው የሰጡት የምስክርነት ቃል እውነት ነው ተብል ይገመታል በማለት ነው። ሆኖም ከላይ የተገለፁት ማስረጃዎች ምስክሩ እውነተኛ አለመሆናቸውን የሚያሣዩ ግምቱን የሚያፈርሱ መሆኑን ሣይመረምር ማለፈ በራሱ ተገቢነት የለውም።
በልላ በኩል አንድ ዲኛ የዲኝነት ሥራውን ከማናቸውም ሰው ጣልቃገብነት ነፃ ሆኖና ገለልተኛ ሆኖ ያከናውናል ተብል የሚገመት መሆኑ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው መርህ ነው። ዲኛው በጉቦ ወስኗል የሚል ወገን ይህንኑ ፍሬ ጉዲይ ተዓማኒነት ያለው በቂ ማስረጃ በማቅረብ የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነት አለበት። ተጠሪ ያቀረበው ማስረጃ አመልካች በዲኝነት በያዘው ጉዲይ በችልት አዋርድኛል፣ጉዲዩን አጓትቷል የሚል ቅሬታ ያላቸው መሆኑ ተጠሪ ምስክሬ ነው በማለት ባቀረበው አብርሃም ገብረክርስቶስ በኩል ተረጋግጧል። አመልካች ብር 50,000(ሃምሳ ሺህ ብር) ሰጥቻለሁ የሚለው አመልካች በዲኝነት ባየው ጉዲይ ተከራካሪ የነበረው አቶ ዐመር አልዬ ከሰጠው የምስክርነት ቃል ውጭ አመልካች ይህንን ገንዘብ መቀበለን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ተጠሪ አላቀበም። የተጠሪ ምስክር አቶ ዐመር አልዬ ገንዘቡን ሰጠሁ የሚለበትና አመልካች ጠየቀኝ የሚለበት ሁኔታ በተለይ አመልካች ስልክ ደውል የት ቦታ እንደሚጠብቁት ከዚያም ሁለተኛ ደውል ገንዘቡን ለማን እንደሚሰጡ ሶስተኛ ደውል ገንዘቡ ለምን አነሰ ብል እንደጠየቃቸው የሰጡት ምስክርነት ከአመልካች ወደ ምስክሩ የተደረገ የሥልክ ጥሪ አለመኖሩ ስለተረጋገጠ እውነትነት የላለው መሆኑ ተረጋግጧል። ይኸም የተጠሪ ምስክር የአቶ ዐመር አልዬ የምስክርነት ቃል ታዓማኒነት የላለው መሆኑን የሚያረጋግጥ ሆኖ እያለ ከላይ በተገለፀው መንገድ ተጠሪ ክሱን የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነቱን አልተወጣም በማለት የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን ፍርድ በመሻር በአመልካች ላይ የሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ውሣኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠውን የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 195/2/ለ1/ መሰረት ሽረናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የሰጠው ውሣኔ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 195/2/ለ-2/ መሰረት አጽንተናል።
አመልካች በነፃ የተሰናበተ ስለሆነ ከእስር እንዱፈታው ለማረሚያ ቤት ይፃፍ ብለናል።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።