No summary available.
ሰኔ 18 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ተስፊዬ አደላ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቃቤ ሕግ (መርማሪ ከሳሽ) - የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በአዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በዚሁ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ ያቀረበው ክስ አመልካች በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 555(ለ) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ቀኑ ባልታወቀ ጊዜ መስከረም ወር 2001 ዓ.ም በግምት ከምሽቱ 2፡00 - 3፡00 ባለው ጊዜ ሕጋዊ ባለቤቱን በቦክስ በመምታት አንድ ጥርስ ሲያወልቅ ላልች ሁለት ጥርሶች ላይም ጉዲት አድርሶ በሐኪም እንዱወልቅ በመደረጉ በሰው አካል ላይ ከባድ ጉዲት አድርሷል የሚል ነው። የአሁኑ አመልካችም ክሱ ደርሷቸው እንዱረደት ከተደረገ በኋላ በክሱ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን ገልጸው ስለድርጊቱ አፈጻጸም ግን የክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል። አቃቤ ህግ በበኩለ አለኝ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል። ከዚያም አመልካች እንዱከላከለ ተደርጎ የባለቤታቸው ጥርስ በልላ ምክንያት የወለቀ መሆኑን የሚያሳይ ጭብጥ በማስያዝ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን አሰምተዋል። የስር ፍርድ ቤትም የአመልካች ምስክሮች በግል ተበዲይ ጥርስ በልላ ምክንያት የወለቀ ስለመሆኑ የማያስረደና የአቃቤ ሕግ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን የማያስተባብለ መሆኑን በመግለጽ ውድቅ አድርጎ አመልካችን በአቃቤ የክስ ማመልከቻ በተጠቀሰው የሕግ ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ አድርጎ በሁለት አመት ጽኑ እስራት ወይም በብር 500.00(አምስት መቶ ብር) እንዱቀጣ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ተጠሪ ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለአዋሳ ከተማ መደበኛ ችልት ይግባኝ አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት አመልካችን በከባድ የአካል ማጉደል ወንጀል ጥፊተኛ ካአለ በኋላ በድንጋጌው ላይ ያልተመለከተውን የገንዘብ መቀጮ በአማራጭነት በመጠቀም ቅጣት መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ምክንያት ይዞ ቅጣቱን በመጨመር አመልካች በአምስት አመት ፅኑ እስራት እንዱቀጡ ሲል ወስኗል።
በዚህ ውሳኔ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታቸውን ደግሞ ለሰበር ሰሚ ችልቱ ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሐምል 09 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተተ ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ድርጊቱ የተፈፀመው በቸልተኝነት እንጂ ሆነ ተብል አይደለም ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቅጣቱን ጨምሮ የወሰነው ባልተጠየቀ ዲኝነት ነው በማለት ምክንያታቸውን ዘርዝረው ውሳኔው እንዱሻርላቸው ወይም በገደብ እንዱለቀቁ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም አመልካች ጥፊተኛ ተብለው በሁለት አመት እስራት ወይም በብር 500.00(አምስት መቶ) እንዱቀጡ በስር ፍርድ ቤት በተሰጠው ውሳኔ ላይ አቃቤ ሕግ አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ሕግ አንቀጸ 555(ለ) አማራጭ ቅጣት የማይደነግግ ሆኖ ሳለ አማራጭ ቅጣቱን መወሰኑ አግባብነት የለውም በማለት ባቀረበው ይግባኝ መነሻ ይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤት አማራጭ ቅጣቱን የመሻር አግባብነት እንደተጠበቀ ሆኖ የስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ የወሰነውን የሁለት አመት እስራት ቅጣት ወደ አምስት አመት እስራት ከፍ አድርጎ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ አቃቤ ሕግ በቁጥር 1230/85/2002 በቀን 26/04/2002 ዓ.ም በተጻፈ ማመልከቻ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ጥፊተኛ የተባለት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 555(ለ) ስር ነው። በዚህ ድንጋጌ ጥፊተኛ የተባለ አጥፉ ሉቀጣ የሚገባው እንደነገሩ ሁኔታና እንደ ጉዲቱ ከባድነት ከአስራ አምስት አመት በማይበልጥ ፅኑ እስራት ወይም ከአንድ አመት በማያንስ ቀላል እስራት ነው። የስር ፍርድ ቤት አመልካች የተቀመጡት በቀላል እስራት ስለመሆኑ በውሳኔው ላይ አልገለፀም ይህንኑ ተጠቅሞ እስራቱን በገንዘብ በአማራጭ ስለመቀየሩም ያስፈለገው ነገር የለም(ቅጣቱ አንቀጽ 179”ን” መሰረት ተደርጎ የተወሰነ መሆኑን አያሳይም)። የሆኖ ሆኖ ግን ተጠሪ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሲያቀርብ ለይግባኙ ምክንያት ያደረገው አመልካች ጥፊተኛ ከተባለት ድንጋጌ አንጻር በገንዘብ መቀጮ በአማራጭ ሉቀጣ አይገባም በሚል ስለመሆኑ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔ ግልባጭ በግልፅ ያሳያል። ተጠሪም በዚህ ችልት ባቀረበው መልስ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ተገቢው ቅጣት እንዱወሰን ይግባኝ ብለናል ከማለት ውጪ የእስራት ቅጣቱም ቢሆን ያነሰ ሰለሆነ ሉጨምር ይገባል በማለት ይግባኝ አቅርበናል የሚል ክርክር የለውም። በመሆኑም ተጠሪ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ ያቀረበው በአማራጭ የገንዘብ ቅጣት መተላለፈ ያላግባብ ነው በሚል ስለመሆኑ ተገንዝበናል። እንግዱህ በወንጀል ጉዲይ ውሳኔ ሲሰጥ ቅሬታ ያለው ወገን ይግባኙን የሚያቀርብበት ሥርዓት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195 ስር በግልፅ ተመልክቷል። ስለቅጣት በተለይ የተደነገገው የዚሁ ድንጋጌ ንዐስ ድንጋጌ በንዐስ ቁጥር ሁለት በፉደል “መ” ስር የተመለከተው ሲሆን ይዘቱም ቅጣት አነሰ በዛ በሚል በግልጽ ይግባኝ ላቀርብበት የሚገባ መሆኑን ያሳያል። ስለሆነም በግልፅ ጥያቄው ካልቀረበ ፍርድ ቤት ቅጣት ጨምሮ ሉወሰን የሚችልበት ሥርዓት የለም።
እንዱህ ሆኖ ከተገኘ ባልተጠየቀ ጉዲይ ዲኝነት እንደመስጠት የሚቆጠር ነው። ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ በአመልካች ላይ የተጣለው የእስራት ቅጣት አንሷል በሚል የይግባኝ ቅሬታ ባላቀረበበት ሁኔታ የበላይ ፍርድ ቤቶች የሁለት ዓመቱን የእስራት ቅጣት ወደ አምስት አመት እስራት ቅጣት ከፍ አድርጎ መወሰናቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መደበኛ ጉዲይ ችልት በመ/ መጋቢት 21 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በደ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ ግንቦት 14 ቀን 2001 ዓ.ም በዚሁ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ደግሞ በመ/ ሰኔ 23 ቀን 2001 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2)(ለ-2) መሰረት ተሻሽሎል።
በአዋሳ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 03 ቀን 2001 ዓ.ም የተሰጠው ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195(2)(ለ-2) መሰረት ተሻሽሎል።
አመልካች ሉቀጡ የሚገባው በሁለት አመት ፅኑ እስራት ነው ብለናል።
አመልካች በጉዲዩ ላይ የታሰሩት ማናቸውም የእስር ጊዜ በቅጣቱ ላይ የሚታሰብላቸው መሆኑን ተገንዝቦ ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈፅም ተገልፆ ለማረሚያ ቤቱ ይፃፍ ብለናል።
No topics extracted.