No summary available.
ሰኔ 23 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ቡርቄሶ ዋቆ - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- ዓቃቤ ሕግ - የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ በጋሞ አካባቢ ፍርድ ቤት በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። ክሱ አመልካች በ1996 ዓ.ም በወጣው የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 27/1/ እና 540 ስር የተመለከተውን በመተላለፍ መጋቢት 09 ቀን 1997 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 12፡00 ሰዓት ሲሆን የግል ተበዲይ ሳራ ሳንቃ የተባለ ሰው ለመግደል ሞክሯል የሚል ነው። የአሁኑ አመልካችም ክሱ ተነቦለት እንዱረዲው ከተደረገ በኋላ በክሱ ላይ ተቃውሞ የላለ መሆኑን ገልጾ የወንጀል ድርጊቱን አፈፃፀም በተመለከተ ግን የክህደት ቃል ሰጥቷል። አቃቤ ሕግ በበኩለ እንደክሱ የሚያስረደለት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ያለት መሆኑን ገልፆ የግል ማስረጃዎቹን አቅርቦ አሰምቷል። ከዚህም በኋላ አመልካች እንዱከላከል ተደርጏ የመከላከያ ማስረጃ የላለው መሆኑን በማረጋገጡ ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት አመልካች በመከላከያ ምስክሮች የአቃቤ ሕግ ማስረጃዎችን ለማስተባበል ያልቻለ መሆኑን ገልፆ አመልካችን በአቃቤ ሕጉ በኩል ተጠቅሶ በቀረበው ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ አድርጏ ቅጣቱን በተመለከተም የግራ ቀኝን አስተያየት በመቀበል እና ከህጉ ጋር በማገናዘብ አመልካች ቀድሞ የወንጀል ሪኯርድ ያለበት መሆኑን አረጋግጦ በአስራ ስምንት አመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለደቡብ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት በጉዲዩ ላይ የሰጠው የጥፊተኛነትና እና የቅጣት ውሳኔ ሙለ በሙለ ጸንቷል። አመልካች የሰበር አቤቱታውን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
አመልካች መስከረም 13 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጸሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡የወንጀል ድርጊቱን ስለመፈጸሙ አቃቤ ሕግ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ ውጪ ባላስረዲበት ሁኔታ በሐሰተኛ ማስረጃዎች ጥፊተኛ መባላ ያላግባብ ነው። ቅጣቱን በተመለከተም ከብድ የተወሰነው ከወ/መ/ሕ/አንቀጽ 230 ድንጋጌ ውጪ ነው በማለት ዘርዝሮ ውሳኔው እንዱሻር ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች ፈጸመ የተባለው የወንጀል ተግባር አንዲችም ውጤት ያላመጣ ከመሆኑ እንፃር እና አመልካች በምህረት የተለቀቀበትን ምክንያት የስር ፍርድ ቤት እንደ ቅጣት ማክበጃ ምክንያት አድርጏ በመውሰድ የአስራ ስምንት ዓመት ጽኑ እስራት መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጏ ተጠሪ ሰኔ 03 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ መልሱን ሰጥቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለጸው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
አመልካች የወንጀል ድርጊቱን አለመፈጸሙን ገልጾ በመከራከሩ አቃቤ ሕግ ማስረጃ አቅርቦ አመልካች የወንጀል ድርጊቱን መፈጸሙን በሚገባ አኳኋን ማረጋገጡን የበታች ፍርድ ቤቶች ያረጋገጡት ፍሬ ጉዲይ ነው።
አመልካች በዚህ ችልት ባቀረበው የሰበር አቤቱታም ከግል ተበዲይ ጋር በእለቱ ከመገፈታተር ወጪ ላላ ድርጊት የፈጸመ ስለመሆኑ አልተመሰከረም በማለት የሚከራከር ሲሆን ይህንኑ መከራከሪያ ነጥብ የሚያስረዲ መከላከያ ማስረጃ ግን በስር ፍርድ ቤት አላቀረበም። በመሆኑንም አመልካች ስለድርጊቱ አፈፃፀም በማስረጃ አልተረጋገጠም በማለት የሚያቀርበው ቅሬታ ይህ ችልት በኢ.ፋ.ዱ.ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 80/3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/1988 አንቀጽ 10 ድንጋጌ መሰረት ያለው ሥልጣን መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ማረም እንጂ የማስረጃ ምዘናን የሚመለከት ጉዲይ የማጣራት ስልጣን ካለመሆኑ አንፃር ሲታይ ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ላላው አመልካች በቅሬታ ነጥብነት ያነሳው ክርክር በልላ የመግደል ሙከራ ተከሶ ጥፊተኛ ተብል በስምንት አመት ጽኑ እስራት የተቀጣበት ጉዲይ የእስራት ቅጣቱን ከመጨረሱ በፉት በይቅርታ የተፈታበትን እንደሪኯርድ ተወስድ ቅጣቱ መወሰኑ ያላግባብ ነው የሚል ነው። ይህ ችልት ለአመልካች የተሰጠው ይቅርታ መሆኑን ተገንዝቧል። ለአመልካች የተሰጠው ይቅርታ ነው ከተባለ ይቅርታ ጽንሰ ሐሳቡና ውጤቱ ምን እንደሆነ የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ በአንቀጽ 230 ስር አስቀምጧል። በዚህ አንቀጽ ንኡስ ቁጥር ሁለት ፓራግራፍ ሁለት መሰረት ይቅርታ ሲሰጥ በተቀጪው ላይ የተወሰነው ፍርድ ከሚያስከትለው ውጤት ጋር በወንጀለኞች መዝገብ ላይ ተመዝግቦ እንደሚኖር ተመልክቷል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ይቅርታ የጥፊተኛነት ውሳኔ እንዲልነበረ የሚያስቆጥር አይደለም። በመሆኑም የወንጀለኞች መዝገብ ላይ ተመዝግቦ የሚኖር በመሆኑ በሪኯርድነት የማይያዝበት ምክንያት የለም። ስለሆነም አመልካች በዚህ ረገድ የስር ፍርድ ቤት በምህረት የወጡበትን ጉዲይ በቅጣት ማክበጃነት ተጠቅመዋል በማለት ያቀረቡት ቅሬታ የስር ፍርድ ቤቱ ሉጽፈው ከፈለገው እና በትክክልም ለአመልካች የተሰጠው ይቅርታ እንጂ መህረት ያለመሆኑ ያላገናዘበ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም ብለናል።
አመልካች ተደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን የስር ፍርድ ቤቶች መሰረት አድርገው በአስራ ስምንት አመት ጽኑ እስራት እንዱቀጣ መወሰናቸው ስለቅጣት የተመለከቱትን አጠቃላይ መርሆዎችን ያላገናዘበ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አላገኘነውም። በአጠቃላይ አመልካችን የበታች ፍርድ ቤቶች ጥፊተኛ በማለት በአስራ ስምንት ዓመት ጽኑ እስራት መቅጣታቸው ባግባቡ በመሆኑ ተከታዩን ወስነናል።
195/2/ለ/2/ መሰረት ፀንቷል።
No topics extracted.