No summary available.
ሚያዝያ 25 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ኂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡- 1ኛ. አቶ ፍሰሐ ዓባይ 2ኛ. ወ/ሪት ህይወት የሰራው ጠበቃ አቶ ሰለሞን ደምሴ ተጠሪ፡- የገቢዎችና ጉምሩክ ዓ/ሕግ አቶ ገ/እግዛብሓር ሙናቸው ቀረቡ መዝገቡ የተቀጠረው ለምርመራ ሲሆን፣ መርምረን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ የሰበር መዝገብ ላቀርብ የቻለው በአመልካቾች ላይ በቀረበው የወንጀል ክስ ጉዲይ በየደረጃው ባለት ፍ/ቤቶች ጉዲዩ ሲታይ ቆይቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በይግባኝ ተመልክቶ በሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ አመልካቾች ቅር ተሰኝተው የሰበር አቤቱታ በማቅረባቸው ነው።
የጉዲዩም አመጣጥ ባጭሩ እንደሚከተለው ነው። የገቢዎችና ጉምሩክ አቃቤ ሕግ በአልካቾች ላይ ያቀረበው ክስ አመልካቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 56/1/ እና እንደተሻሻለው አንቀጽ 22/1/ እና መ/ለ/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብይት ፈጽመዋል። የሚል ሲሆን፣ አመልካቾች ይህንኑ የወንጀል ድርጊት አልፈፀምንም በማለት ክደው በመከራከራቸው ክርክር ቀጥል ሁለቱም ወገኖች በየፉናቸው ማስረጃ አቅርበው አሰምተዋል።
የስር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም በኮ/መ/ቁ. 144285 ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም በዋለው ችልት ጉዲዩን መርምሮ ሁለተኛ አመልካች ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብይት ስለመፈጸሟ የተረጋገጠ ሲሆን፤አንደኛ አመልካች የንግድ ድርጅቱ ላለቤት እንደመሆናቸው ግብይት ያለደረሰኝ እንዲይከናወን አስፈላጊውን ጥንቃቄ ባለማድረጋቸው በሰራተኛ ለተፈፀመው ድርጊት ኃላፉነት አለባቸው በማለት በሁለቱም ላይ የጥፊተኝነት ውሳኔ ሰጥቷል።
በቅጣት ረገድም የግራ ቀኙ የቅጣት አስተያየት ካገናዘበ በኋላ 1ኛ ተከሳሽ በብር 20,000.00(ሃያ ሺ ብር) እና በ1(አንድ) ዓመት እስራት ሁለተኛ አመልካች በብር 10,000.00 (መቶ ሺ ) ብር እና በ1(አንድ) ዓመት እስራት እንዱቀጡ ወስኗል።
በዚህ የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ አመልካቾች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የይግባኝ አቤቱታ በማቅረባቸው ፍ/ቤቱም ጉዲዩን ተመልክቶ የአሁን አንደኛ አመልካች በተፈፀመው ድርጊት ቀጥተኛ ተሳትፍ የነበረው ስለመሆኑ በማስረጃ ስላልተረጋገጠ በነፃ ይሰናበታል በማለት ሲወስን፤ከጠቅላይ ፍ/ቤት የውሳኔ ግልባጭ ላይ መረዲት፣ እንደሚቻለው የሥር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካቾች ላይ የተሰጠው የእስራት ቅጣት አንሷል በማለት አቅርቦት የነበረው የይግባኝ አቤቱታ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል።
የከፍተኛው ፍ/ቤት በይግባኝ ደረጃ በጥፊተኝነትም ሆነ በቅጣት ረገድ በሰጠው ውሳኔ የገቢዎችና ጉምሩክ ዓቃቤ ሕግ ሁለተኛ የይግባኝ አቤቱታ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በማቅረቡ፤የጠቅላይ የፍ/ቤቱ ሁለቱም ወገኖች ክርክር ካዲመጠ በኋላ በወ/ይ/መ/ቁ. 51336 የካቲት 05 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት በጥፊተኝነት ውሳኔ አሰጣጥ በኩል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በአንደኛ አመልካች ላይ የሰጠውን የጥፊተኝነት ውሳኔ ከፀና በኋላ በቅጣት አጣጣል ረገድ አመልካቾች ጥፊተኛ በተባለበት ድንጋጌ ሥር ከተመለከተው ዝቅተኛ የቅጣት መነሻ በታች ለመውረድ የሚያበቃ ህጋዊ ምክንያት አልተገኘም በማለት የገንዘብ መቀጮውን ሳይነካ ሁለቱም አመልካቾች እያንዲንዲቸው በሁለት ዓመት እስራት እንዱቀጡ በማሻሻል ወስኗል።
የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ከዚህ በላይ በተመለከተው አኳኋን የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት የሰጠው የጥፊተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ዝርዝር ቅሬታ በማቅረባቸው ነው።
ለዚህም የሰበር ቅሬታ ተጠሪ የገቢዎችና ጉምሩክ አቃቤ ሕግ መልስ እንዱሰጥበት ተደርጏ በሰበር ደረጃ ግራ ቀኙ የጽሐፍ ክርክራቸውን አቅርበዋል።
እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
1ኛ. አመልካች ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ግብይት ተፈጽሟል በተባለበት ጊዜ በተፈፀመው አድራጏት ተሳትፍ የነበረው ስለመሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠ ጉዲይ አይደለም። የአንደኛ አመልካች የጥፊተኝነት መሰረት ሆኖ የተያዘው በአድራጏቱ የተነሣ ለፈፀመው ጥፊት ሳይሆን በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 56/1/ እንደተመለከተው ድርጅቱ አዋጁን በመተላለፈ ስለፈፀመው ጥፊት ተተክቶ ተጠያቂ ላሆን በመቻለ ነው በዚህ መሰረት ከተጠያቂነት ለመዲን የሚቻለው በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 56/3/ የተመለከቱትን ሁኔታዎችን ለማስረዲት የተቻለ እንደሆነ ብቻ ነው። በዚህ ረገድ በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤትም ሆነ በጠቅላይ ፍ/ቤት የውሳኔ ሐተታ እንደተመለከተው ይህ ስለመሆኑ አንደኛ አመልካች ሕጉ የጣለበትን ግምት ለማስተባበል የሚያስችል የመከላከያ ማስረጃ አልቀረበም።
በአዋጁ አንቀጽ 56/1/ “…አንድ ድርጅት….“ የሚለውን አባባል ከአንቀጽ 56/4/ ድንጋጌ ሥራ አስኪያጅ የሚለው አባባል ለየትኞቹ ድርጅት የሚለውን ጥያቄ ሉያስነሳ እንደሚችል የተረዲን ቢሆንም በአዋጁ መግቢያ “ትርጓሜ” ለሚለው አንቀጽ 2/5/ እና 2/11/ ጋር አገናዝበን ስንመለከተው ድርጅት ማለት በሽርክና ማህበር በኩባንያ እና በሰዎች ህብረት ላይ ብቻ ተወስኖ የሚቀር ሆኖ አይታይም።
ሁለተኛ አመልካችንም ቢሆን ድርጊቱ በተፈፀመበት ጊዜ ቦታ ተገኝታ ከፈፀመችው ካደረገችው እና ከተናገረችው አድራጏት አንፃር በድርጊቱ አፈፃፀም ቀጥተኛ ተሳትፍ ስለመሆኑ በበቂ ማስረጃ የተረጋገጠ ሆኖ አግኝተነዋል።
በዚህ ሁለ ምክንያት በሥር ጠቅላይ ፍ/ቤት የጥፊተኝነት ውሳኔን አስመልክቶ የተሰጠው ዲኝነት መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩል የጠቅላይ ፍ/ቤት በተጠሪ ይግባኝ መነሻ በአመልካቾች ላይ ተጥል የነበረውን የአንድ ዓመት እስራት ወደ ሁለት ዓመት እስራት ለውጦ በማሻሻል ሉወሰን የቻለው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 82/1//ሀ/ ከተመለከተው ዝርዝር የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች አንደ የሆነው የጥፊተኛው የዘወትር ጠባይ መልካም መሆን ብቻውን እንደ ቅጣት ማቅለያ ሉወሰድ አይችልም። የዘወትር ጠባዩ መልካም መሆን ብቻ ሳይሆን ያጠፊውም በእውቀት ማነስ፣ባለማወቅ፣በየዋህነት ወይም ባልታሰበና ድንገተኛ አጋጣሚ እንደሆነ ጭምር መሆን ይገባዋል።
በዚሁ ድንጋጌ የዘወትር ጠባይኑና የአፈፃፀሙን ሁኔታም “እና” በሚለው ምፃሃረ ቃል መያያዙ ሁለቱም ሁኔታዎች ድርብ የቅጣት ማቅለያ ማሟያ ምክንያቶች መሆናቸውን አመልካች ነው የሚለውን በመያዝ እንደሆነ ከመዝገቡ ግልባጭ ተረድተናል።
ይሁን እንጂ ቅጣትን የማቅለልና ለቅጣት ነፃ የማድረግ ደንብን አስመልክቶ በተመለተው የሕግ ክፍል በወ/ሕ/ቁ. 179 ላይ “ፍርድ ቤቱ በዚህ አንቀጽ መሰረት ቅጣትን ለማቅለል እንደሚችል በሕግ በተደነገገ ጊዜ ሁለ……” ለሚለው አነጋገር “በሕግ በተደነገገ ጊዜ ሁለ….” የሚለው ሐረግ ስለቅጣት ማቅለል በወ/ሕ/ቁ.
82/1/ሀ/ የተመለከተው ድንጋጌ ብቻ ሳይሆን ከቅጣት አወሳሰን ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ስለቅጣት አጣጣል አግባብነትና ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር አጣቅሶ ማየት እንደሚያስፈልግ አመላካች ነው።
ከዚህም አኳያ በወ/ሕግ ቁጥር 88/2/ ቅጣት ሉወሰን የሚገባው የወንጀል አድራጊውን ያለፈ የሕይወት ታሪክ ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደሆነ መደንገጉ አንድ አጥፉ ወንጀለን እስካደረገበት ጊዜ ድረስ የዘወትር ጠባዩ መልካም የነበረ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ለቅጣት ማቅለያነት የማይወሰድበት ምክንያት አይኖርም።
ይህም ሁለ ታልፍ በወንጀል ሕግ ቁጥር 82/1/ሀ/ የተመለከተው የቅጣት ማቅለያ ወጥነት ያለው የተጣመረ ምክንያት ነው እንኳ ቢባል በሥር ፍ/ቤቶች የቅጣትን አስተያየት አስመልክቶ በግራ ቀኙ በየደረጃው ከተደረጉት ክርክሮች፣ ከድርጊቱ አፈፃፀም ወንጀለን ላቋቋመው ድንጋጌ ወይም ሕግ ጋር ሁለ ተገናዝቦ ሲታይ በዚህ አከሪካሪ በሆነው ድንጋጌ “እና” ከሚለው ቀጥል ካለት ወይም በሚል ምሕጻረ ቃል ከተያያዙት አንደን ምክንያት ቢሆን እንኳ አመልካቾች አላሟለም ማለት የሚቻል ሆኖ አልተገኘም። በዚህም የተነሣ ቅጣቱ በመደበኛ የቅጣት ማቅለያ ደንብ መሰረት ማውረድ አይገባም የሚለውን ታሳቢ በማድረግ አመልካቾች ጥፊተኛ በተባለት ድንጋጌ ሥር የተመለከተውን መነሻ የሁለት ዓመት እስራት የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት መጣለ/መወሰኑ የቅጣት አጣጣል ሥርአትን የተከተለ ሆኖ አላገኘነውም።
በቅጣት አወሳሰን ረገድ ላይ ብቻ የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በወ/ይ/መ/ቁ. 51336 የካቲት 05 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሎል። በዚህ ረገድ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኮ/መ/ቁ. 144285 ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም የጣለው ቅጣት ፀንቷል።
አመልካቾች በመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ እንደተገለፀው አንደኛ አመልካች በብር 20,000.00(ሃያ ሺህ ብር) እና በአንድ ዓመት፣ሁለተኛ አመልካች በብር 10,000 (አስር ሺህ ብር) እና በአንድ ዓመት እስራት ይቀጣለ በማለት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 195/2/ለ/2/ መሰረት አሻሽለን ወስነናል። ለፋዳራል ማ/ቤቶች ይፃፍ።
No topics extracted.