No summary available.
ሚያዝያ 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ዓብደራሂም አህመድ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ሐረገወይን ተፈራ - ጠበቃ ጥበቡ ምህረቴ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋዳራል ዓቃቤ ሕግ ወርቁ ገመቹ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ ለሰበር ችልቱ የቀረበው ጉዲይ የወንጀል ሲሆን አመልካች በበታች ፍርድ ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት በጠበቃቸው አማካኝነት ግንቦት 24 ቀን 2001 ዓ.ም የተፃፈ ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ጥቅምት 25 በዋለው ችልት ተሰምቷል።
ይህ ችልትም የአመልካች አቤቱታ፣ ከበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔዎች እንዱሁም አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። በዚህም መሰረት አመልካች የተከሰሱት፡- በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወ/መ/ሕ/ቁ. 32(1(ሀ) እና (ለ)) እና 692/1/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ የማይገባቸውን ብልጽግና ለማግኘት አስቀድሞ በማሰብ ክሱ በስር ፍርድ ቤት ከተቋረጠው ከአቶ ዘላለም ተስፊዬን የሰሉጥ ነጋዳና አቅራቢ በማስመሰል ለግል ተበዲይ ሽቶ በቀለ ካስተዋወቀች በኋላ የግል ተበዲይን በማሳመን ወደ ተሳሳተ እምነት በመምራት ግንቦት 21 ቀን 1998 ዓ.ም ከቀኑ በግምት 5፡30 ሰዓት በሚሆንበት ጊዜ በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 15 ክልል ውስጥ ልዩ ቦታው ከኢምፔሪያል ሆቴል በስተጀርባ ከሚገኘው የግል ተበዲይ ድርጅት በሆነው ፏርፍ ኢንተርናሽናል ትሬዱንግ ግቢ ውስጥ ክስ የተቋረጠበት ግለሰብ ለድርጅቱ ብዛቱ 6000(ስድስት ሺህ) ኩንታል ሰሉጥ በብር 3,618,000(ሶስት ሚሉዮን ስድስት መቶ አስራ ስምንት ሺህ ብር) ለማቅረብ ከተነጋገሩ በኋላ የቅድሚያ ክፍያ ያስፈልገኛል በማለት በእለቱ ብር 500,000(አምስት መቶ ሺህ) የያዘ ቼክ በመቀበል እንዱሁም ግንቦት 24 ቀን 1998 ዓ.ም ብር 50,000(አምሳ ሺህ ብር) ጏንደር ከሚገኘው የአቢሲኒያ ባንክ እንዱቀበል በአቶ ያለው በቀለ ስም ተልኮለት በአጠቃላይ ብር 550,000(አምስት መቶ አምሳ ሺህ ብር) ወጪ አድርጏ ከወሰደ በኋላ ገንዘቡን ይዞ በመሰወሩ ሁለቱም የማታለል ወንጀል ፈጽመዋል የሚል ነው። አመልካች በክሱ ተቃውሞ የላላቸው መሆኑን በመግለጽ የድርጊት አፈፃፀሙን በመካዲቸው አቃቤ ሕጉ አለኝ ያላቸውን የሰውና የሰነድ ማስረጃዎች ለማስረጃነት አቅርቦ አመልካች ክሱን እንዱከላከለ ተደርጏ የወንጀለ ድርጊት በተፈፀመበት ጊዜና ቦታ ተገኝተው በሰሉጥ ውለ ላይ በእማኝነት መፈረማቸውን በጭብጥነት አሲይዘው የሰነድና የሰው ማስረጃዎችን አቅርበዋል፣ አሰምተዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም አመልካችን በመከላከያ ማስረጃ በሰሉጥ ውለ ላይ በእማኝነት ስለመፈረማቸው እና የግል ተበዲይም በአቶ ዘላለም ተስፊዬ የፍትሐብሕር ክስ አቅርበው ገንዘቡ እንዱመለስላቸው ማስፈረዲቸው ቢረጋገጥም የግል ተበዲይን ወደ ስህተት እንዱመሩ አላደረጉም ለማለት የሚያስችል አይደለም በማለት በአቃቤ ሕግ በኩል ተጠቀሶ በቀረበባቸው ድንጋጌ ስር ጥፊተኛ አድርጏ በአንድ ዓመት ቀላል አስራት እንዱቀጡ እና የቅጣቱ አፈፃፀም በሦስት አመት ገደብ እንዱሆን ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቅርበው ተቀባይነት አላገኙም።
የአመልካች በዚህ ችልት ባቀረቡት ክርክር በአመልካች በኩል የተፈፀመው ድርጊት የማታለል ወንጀልን የሚያቋቁም አይደለም በማለት የሚከራከሩ ሲሆን ተጠሪ በአንፃሩ ድርጊቱ የማታለል ወንጀልን የሚያቋቁም ነው በማለት ተከራክሯል። ይህ ችልትም በአመልካች ላይ የቀረበው የወንጀል ክስ የማታለል ወንጀልን ያቋቁማል ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ይዞ ጉዲዩን በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
በመሰረቱ አንድ ሰው በወንጀል ሕግ አንቀጽ 692/1/ መሰረት ተጠያቂ የሚሆነው የማይገባ ብልጽግና ለራሱ ለማግኘት ወይም ለላላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ አሳሳች የሆኑ ነገሮችን በመናገር፣የራሱን ማንነት ወይም ሁኔታ በመሰወር ወይም መግለጽ የሚገባውን ነገር በመደበቅ ወይም የላላውን ሰው የተሳሳተ እምነት ወይም ግምት በመጠቀም፣በማድረግም ሆነ ባለማድረግ ላላውን ሰው አታልል የራሱን ወይም የሦስትኛ ወገንን የንብረት ጥቅም የሚጏዲ አድራጏት እንዱፈፀም ያደረገ የሆነ እንደሆነ ነው። እንግዱህ አንድ ሰው የወንጀል ተጠያቂነት የሚኖርበት በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/2/ ስር እንደተመለከተው ወንጀለን የሚያቋቁሙት ሕጋዊ፣ግዙፊዊ እና ሞራላዊ ፍሬ ነገሮች በአንድነት ተሟልተው ሲገኙ ነው። ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካች ፈፀሙ የተባለው ክሱ የተቋረጠውን አቶ ዘላለም ተስፊዬን የሰሉጥ ነጋዳና አቅራቢ በማስመሰል ለግል ተበዲይ ለአቶ ሽቶ በቀለ አስተዋውቀው የግል ተበዲይ ገንዘብ ላይ ጉዲት አድርሰዋል በሚል ነው። ይሁን እንጂ አቶ ዘላለም ተስፊዬ የሰሉጥ ነጋዳ አለመሆናቸው ካለመረጋገጡም በላይ አመልካች ይህንኑ እያወቁ ለግል ተበዲይ የተሳሳተ ነገር እውነት አስመስለው የተናገሩበት ሁኔታ ስለመኖሩ አልተረጋገጠም። ይልቁንም አቃቤ ሕጉ የሰሉጥ ነጋዳ ሳይሆኑ ነጋዳ ናቸው የተባለትን ግለሰብ በተመለከተ ክሱን ያቋረጠ መሆኑ ተረጋግጧል። የግል ተበዲይም ከአቶ ዘላለም ተስፊዬ ጋር የነበራቸው ግንኙነት ፍትሐብሓራዊ የነበረ ስለመሆኑ ተረጋግጦ በፍትሐብሕር ችልት ውሳኔ ተሰጥቶ ገንዘባቸው እንዱከፈላቸው ተወስኗል። ይህ ሁለ የሚያሳየው አመልካች የማታለል ተግባር አለመፈፀማቸውን ነው። በመሆኑም የአመልካች ተግባር የማታለል ተግባርን የሚያቋቁም ባለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የወንጀል ሕጉን አንቀጽ 23/2/ እና 692/1/”ን” ይዘትና መንፈስ ያላገናዘበና መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ጥቅምት 25 እና ኀዲር 04 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጠቶ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 42198 የካቲት 25 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው የጥፊተኝነትና የቅጣት ውሳኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 195/2/ለ/2/ መሰረት ሙለ በሙለ ተሽሯል።
የአመልካች ተግባር የማታለል ወንጀልን የሚያቋቁም አይደለም ብለናል።
No topics extracted.