No summary available.
መጋቢት 28 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ቄስ ጌታቸው ተሾመ ተጠሪ፡- ዓቃቤ ሕግ
አመልካች በስር ፍርድ ቤት በቀረበባቸው ሁለት የወንጀል ክሶች ጥፊተኛ ተብለው በሁለት አመትና በ300.00 ብር እንዱቀጡ የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት አለበት በሚል ይህን የሰበር አቤቱታ ሉያቀርቡ ችለዋል።
በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቃቤ ሕግ ባቀረበባቸው አንደኛ ክስ የወንጀል ሕግ ቁጥር 543/1/”ን” በመተላለፍ የካቲት 29 ቀን 2000 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰዓት ድርጊቱ ሞትን ሉያስከትል እንደሚችል ማሰብ ሲገባው ባለመጠንቀቅ የቡዲ መድሃኒት ነው ብል ቅጠላቅጠል አጪሶ በማጠንና ማረሻ አግል ከፉቷ ላይ በመተኮስ ሟችን የገደለ በመሆኑ በቸልተኛነት ሰው መግደል ወንጀል ተከሷል፣እንዱሁም በሁለተኛ ክስ ጏጂነቱ ጉዲቱ በተረጋገጠ ልማዲዊ ድርጊት የቡዲ መድሃኒት ነው ብል ቅጠላ ቅጠል አጪሶ በማጠን ማረሻ አግል ፉትዋን በተመተኮስ ለሞት ያበቃት በመሆኑ በልማዲዊ ድርጊት ጉዲት ማድረስ ወንጀል ተከሷል በማለት ክስ መስርቶባቸዋል።
አመልካች ድርጊቱን አልፈፀምኩም ጥፊተኛ አይደለሁም በማለታቸው አቃቤ ሕግ ሶስት የሰው ምስክሮች አቅርቦ አሰምቷል። ፍ/ቤቱም የአቃቤ ሕግ ምስክሮች እንደክስ አቀራረቡ አስረድተዋል በማለት አመልካች ክሱን እንዱከላከለ በማለቱ አመልካች ድርጊቱ ተፈፀመ በተባለበት እለት ሟች ቤት ያልነበሩ ስለመሆናቸው ይመሰክሩልናል ያሎቸውን ሁለት ምስክሮች አቅርበው አሰምተዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ማስረጃ ከመረመረ በኋላ የአመልካች ምስክሮች ቃል እርስ በእርሱ የሚጋጭና የአቃቤ ሕግ ምስክሮች ያሰረደትን ለማስተባበል ያልቻለ ነው በማለት በሁለቱም ክሶች አመልካችን ጥፊተኛ በማለት በአንደኛው ክስ ሁለት አመት ቀላል እስራት በሁለተኛው ክስ 300.00(ሶስት መቶ ብር) እዱቀጡ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም ይግባኙ ተቀባይነት ያላገኘ ሲሆን ለክልለ ሰበር ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታም አቅርበው ችልቱ በአብላጫ ድምጽ ውሳኔው መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለበትም በማለት መዝገቡን ዘግቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ሲሆን አመልካች በቅሬታቸው ጥፊቱን ለመፈፀማቸው ከጥርጣሬ በላይ የተረጋገጠባቸው መሆኑን፣ሟች ቀድሞውኑ ታማ ስለነበር ለሞቷ ምክንያት የሆነው የያዛት ህመም መሆኑን፣ባትታመም ኖሮ ቅጠለ ወይም ማረሻው ጉዲት ያደርስ እንደሆነ እንጂ ለሞት የማያበቃት መሆኑን፣ቅጠለ ሰው ገዲይ ለመሆኑ በህክምና አለመረጋገጡን እንዱሁ በተደራራቢ ክስ መከሰሳቸው አግባብ አለመሆኑን በመዘርዝር የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔው እንዱሻር ይህ የሚታለፍ ከሆነ ደግሞ በወ/ሕ/ቁ. 567 ብቻ ተጠያቂ እንዱሆኑ ጠይቀዋል። ይህ ችልት አመልካች በወ/ሕ/ቁ. 543 እና 567 መሰረት መከሰሳቸው በአግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ተሰምቷል።
ከፍ ሲል እንደተመለከትነው አመልካች የተከሰሱት በቸልተኛነት ሰው ገድለዋል እንዱሁም በልማዲዊ ድርጊት ጉዲት አድርሰዋል በማለት በሁለት የወንጀል ድርጊቶች ነው። አመልካችም በሁለት ተደራራቢ ወንጀልች ልጠየቅ አይገባም በማለት የሚከራከሩ ሲሆን ተጠሪም በቃል ክርክር ወቅት አመልካች በተደራራቢ ወንጀልት መከሰሳቸው አግባብ አልነበረም በማለት ገልጿል። ችልቱም ተፈፀመ ከተባለው ድርጊት አኳያ አመልካች በተደራራቢ ወንጀልች ጥፊተኛ ሉባለ ይገባል ወይ የሚለው ጭብጥ መርምሯል። አመልካች በሁለቱም ክሶች ፈፀሙ የተባለው ሟችን የቡዲ መድሃኒት ነው ብለው ቅጠላ ቅጠል አጭሰው በማጠንና ማረሻ አግለው ፉትዋን በመተኮስ ለሞት ዲርገዋታል በማለት ነው። አመልካች በክሱ የተገለፀውን ድርጊት መፈፀማቸው ተረጋግጧል።
አመልካች ፈጽመዋል የተባለው ይኸው ድርጊትም በግል ተበዲዩዋ ላይ ጉዲት ማድረስ ብቻ ሳይሆን ሞትን በማስከተለ ሁለት ክስ መቅረቡን ተገንዝበናል። ነገር ግን በሕግ በተጠበቀ በአንድ መብት ላይ የሚደረጉ አንድ ወይም ከአንድ በላይ የሆኑ የተቀላቀለ የወንጀል ድርጊቶች የተደረጉት በአንድ የወንጀል ማድረግ ሃሳብ ወይም ቸልተኛነት ሲሆን እና ድርጊቶቹ በሙለ በአንድ ድንጋጌ ሥር የሚሸፈኑ ሲሆኑ አድራጊው በተመሳሳይ ባህሪ ባላቸው በሁለት ወይም ከሁለት በበለጡ ተደራራቢ የቅጣት ድንጋጌዎች እንደማይቀጣ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 61/1/ ያመለክታል። አመልካች መፈፀማቸው የተረጋገጠው የቡዲ መድሃኒት ነው በሚል ቅጠላ ቅጠል አጭሶ በማጠንና ማረሻ አግል በመተኮስ የግል ተበዲይ ድርጊቱ ከተፈፀመ ከአንድ ሰአት በኋላ እንድትሞት ማድረጋቸው ነው። አመልካች በልማዲዊ ድርጊት ጉዲት ያደረሱና ጉዲቱም ሞትን ያስከተለ ቢሆንም ወንጀለን የፈፀሙት በአንድ ቸልተኛነት ድርጊት በመሆኑ በተደራራቢ ቅጣት ሉቀጡ አይገባም። በልላ በኩል በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 567 እንደተመለከተው ማንም ሰው ኢሰብአዊነቱ በታወቀና ጏጂነቱ በህክምና ሙያ በተረጋገጠ በልማዲዊ ድርጊት አማካኝነት በልላ ሰው ላይ አካል ወይም አእምሮ ጉዲት ወይም ሞት እንዱደርስ ያደረገ ከሆነ በወንጀል ይቀጣል።
በመሆኑም ምንም እንኳን አመልካች የፈጸሙት ጏጂ ልማዲዊ ድርጊት ሞትን ያስከተለ ቢሆንም ድርጊቶቹ በሙለ ከፍ ሲል በተጠቀሰው ድንጋጌ ስር የሚሸፈን በመሆኑ አመልካች በቸልተኛነት ሰው በመግደል የወንጀል ድርጊት ሉቀጡ የሚገባበት የሕግ መሰረት የለውም። በመሆኑም አመልካች በወንጀል ሕግ ቁጥር 543 ጥፊተኛ መባላቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት አለበት።
በልላ በኩል ግን የተፈፀመው ልማዲዊ ድርጊት ሞትን ያስከተለ ከሆነ እንደነገሩ ሁኔታ በአንቀጽ 561 ወይም 562 ከተመለከቱት ቅጣቶች አንደ ተፈፃሚ እንደሚሆን የወንጀል ህጉ አንቀጽ 567 ያመለክታል። በዚህም መሰረት ወንጀል ሕጉን 561/2/ ስንመለከት የሞት አደጋ የተከሰተው በቸልተኛነት የሆነ እንደሆነ አንቀጽ 543 ተፈፃሚ ላሆን እንደሚገባ ያመለከታል። በዚህም መሰረት አምልካች ከስድስት ወር እስከ ሶስት አመት ቀላል እስራት ወይም ከሁለት ሺህ ብር እስከ አራት ሺህ ብር በሚደርስ የገንዘብ መቀጫ ሉቀጡ እንደሚችለ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 543/1/ ያስገነዝበናል። አመልካች ጉዲት ሉያደርስ እንደሚችል እያወቁ ወይም ማወቅ ሲገባቸው በሕመም ላይ ያለን ሰው ቅጠል አጭሰው በማጠንና ማረሻ አግለው በመተኮስ ለሞት መዲረጋቸው ሲታይ ድርጊቱ አስከፉ መሆኑንና በልላ በኩል ደግሞ አመልካቹ ያልተማሩና የ9 ቤተሰብ አስተዲዲሪ በመሆናቸው ቅጣቱን ሉያቀል የሚችል መሆኑ ከግምት ውስጥ በማስገባት የስር ፍ/ቤት አመልካችን በሁለት አመት ቀላል አስራት እንዱቀጡ የሰጠው የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም።
የሰሜሽ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ግንቦት 19 ቀን 2000 ቀን ዓ.ም የሰጠው ውሣኔ፣የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 6880 መስከረም 15 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ እንዱሁም የክልለ ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 00683 ታህሣስ 13 ቀን 2001 ዓ.ም በድምጽ ብልጫ የሰጠው ትእዛዝ ተሻሽሎል።
አመልካች በወንጀል ሕግ ቁጥር 543 ጥፊተኛ ናቸው ተብል የተሰጠው የጥፊተኛነት ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካች የወንጀል ሕግ ቁጥር 567”ን” በመተላለፍ በፈፀሙት በልማዲዊ ድርጊት ጉዲት ማድረስ ወንጀል የተሰጠው የጥፊተኛነት ውሳኔ ፀንቷል። አመልካች በዚህ ድንጋጌ ጥፊተኛ ስለተባለ በሁለት አመት ቀላል እስራት እንዱቀጡ የተሰጠውም የቅጣት ውሳኔ ፀንቷል።
አመልካች ጥፊተኛ የተባለበት የወንጀል ድርጊት የሚያስቀጣው በቀላል እስራት ወይም በአማራጭ በገንዘብ መቀጮ በመሆኑ አመልካች ብር 300.00 እንዱቀጡ የተሰጠው የቅጣት ውሳኔ ተሽሯል።
No topics extracted.