No summary available.
መጋቢት 15 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካቾች በተከሰሱበት የወንጀል ድርጊት የከፍተኛው ፍ/ቤት የሰጠውን የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ የክልለ ይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤት እና ሰበር ሰሚ ችልት በማጽናታቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በሚል ነው።
አመልካቾች የተከሰሱት የኢ.ፋ.ዱ.ሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ/ለ/ እና 540 የተመለተውን በመተላለፍ በቀን 09/05/99 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ በሻክሶ ወረዲ ቀንጢቻ ቀበላ በታንታለም ፊብሪካ አጠገብ ሰው በመሞቱ ምክንያት ተሰብስቦ ካለው ሕዝብ ውስጥ አንደኛው ተጠሪ ሟች ጴጥሮስ ቦሩን ጏኑ ላይ መትቶ በመግደለ፣ሁለተኛው ተጠሪ ሟች በዳሳ ሚጣ ከለቻን መትቶ በመግደለ ሦስተኛው ተጠሪ ሟች በቀለ ጂልና ደከላ ደረስ ላይ ተኩሶ በመግደለ እንዱሁም ሁለተኛ ክስ በሦስተኛው ተጠሪ ላይ የወንጀል ሕግ ቁጥር 27/1/ እና 540 በመተላለፍ በአንደኛው ክስ በተገለፀው ቦታና እና ቀን በብዛት ቆመው ባለት ህዝብ ላይ ደግኖ ተኩሶ ተበዲይ ጂል ጡኔን እግሩን፣ዱጏ ገናላን፣እያሱ ደደቻን ግራ እጅ እና ዋጩል ሙደን በጥይት መትቷቸው የግድያ ሙከራ ወንጀል ፈጽሟል በሚል የጏጂ ዞን ዓ/ሕግ ክስ መስርቶባቸዋል።
አመልካቾች ጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ቀርበው ወንጀል አለመፈፀማቸውን ክደው ተከራክረዋል።
የከፍተኛው ፍ/ቤት የግራ ቀኙን ማስረጃ ከሰማና ከመረመረ በኋላ በተከሰሱበት የወንጀል አንቀጽ ጥፊተኛ ናቸው ካለ በኋላ አንደኛ እና ሁለተኛ አመልካቾች በ15 (አስራ አምስት ዓመት) ጽኑ እስራት እንዱቀጡ ሦስተኛው አመልካች በአንቀጽ 540 በሁለት ድርጊት ጥፊተኛ ነው በሚል በሃያ ዓመት (20) ጽኑ እስራት እንዱቀጣ ፈርዶል። ይግባኝ የቀረበለት የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት እና የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ ስሕተት የለውም በሚል አጽንተዋል።
አመልካቾች በፋ/ፖ/ኮ/ሕግ አገልግልት ነ/ፈጅ በኩል ሚያዝያ 5 ቀን 2001 ዓ.ም የተሻሻለ የሰበር አቤቱታ ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አቅርቧል። የሰበር አቤቱታ ይዘት ባጭሩ ችግሩ በተፈጠረበት ቦታ ቁጥራቸው ከ300 በላይ የሚሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ክላሽ ጠመንጃ፣ጦርና ገጀራ በመያዝ ቃንጥቻ የሚገኘውን የታንታለም ማምረቻ ፊብሪካን ለመዝረፍ ሲንቀሳቀሱ በተፈጠረ ግጭት ከሕዝቡ በተተኮሰ ጥይት የፖሉስ አባላትም የቆሰለ ስለመሆኑ በማስረጃ ተረጋግጦ እያለ አመልካቾችን ጥፊተኛ ማድረጉ የግራ ቀኙን ማስረጃ በአግባቡ ሳያገናዝብ ነው በሚል የሥር ፍ/ቤት ፍርድ ተሽሮ አመልካቾች በነፃ እንዱሰናበቱ አመልክቷል።
የሰበር ችልትም አመልካቾች ድርጊቱን ፈጽሟል ቢባል እንኳ ጥፊተኛ የመባላቸውን አግባብነት ከወንጀል ሕጉ መርህ እና ድንጋጌዎች አንፃር ለመመርመር ሲል ዓ/ሕግ መልስ እንዱሰጥ አዟል።
የኦሮሚያ ክልል ዓ/ሕግ በ28/12/2001 ዓ.ም ጽፍ ባቀረበው መልስ አመልካቾች የተከሰሱበት የወንጀል ድርጊት ስለመፈጸማቸው ከጥርጣሬ ውጪ የተመሰከረባቸው ስለሆነ በሥር ፍ/ቤት የተወሰነው የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ እንዱፀና በማለት አመልክቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ እና የግራ ቀኙ ክርክር ከፍ ሲል ባጭሩ የተመለከተው ሲሆን እኛም ከሕጉ ጋር በማገናዘብ መርምረናል። ይህ ሰበር ሰሚ ችልት የግራ ቀኙን ክርክር እና የሥር መዝገብ ውሳኔ ይዘት ከመረመረ በኋላ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ምላሽ የሚያሻው የሕግ ጥያቄ ሆኖ ያገኛው አመልካቾች ጥፊተኛ ሉባለ የሚገባው በወ/ሕ/ድንጋጌ አንቀጽ 540 ወይንስ 541 የሚለውን ነው። ይህንኑ ለመፍታት የጉዲዩን አፈፃፀም እና መነሻ ሁኔታዎች በአጭሩ መመለከት ተገቢ ነው።
ከሥር ፍ/ቤት መዝገብ መረዲት የተቻለው ፍሬ ነገር ወንጀለ ተፈፀመ ከተባለበት ቀን አስቀድሞ ላሉቱን በታንታለም ፊብሪካ አጠገብ አንድ ሰው ተገድል የነበረ ስለመሆኑ፣ይህንንም መነሻ በማድረግ የአካባቢው ሕዝብ እዚያው ፊብሪካ አጠገብ የተሰበሰበ ስለመሆኑ፣የተሰበሰበው ሕዝብ ክላሽ፣ገጀራና ጦር ይዞ የነበረ ስለመሆኑ እና የታንታለም ፊብሪካ ሰራተኞችም ወደ ሥራ እንዲይገቡ እንዲይወጡ በዚሁ በተሰበሰበው ሕዝብ ሁከት የተፈጠረ ስለመሆኑ ነው። የአሁን አመልካቾች እና ላልች ባልደረቦቻቸው ወደ ቦታው የተንቀሳቀሱት ይህንኑ የፊብሪካው ሥራ መስተጓጏልና ላላ ጉዲት እንዲይደርስ ለመከላከል እንዱቻል ስለመሆኑም በምስክሮች ተነግሯል።
አመልካቾች እና ባልደረቦቻቸው በቦታው ሲደርሱ እነሱን በያዘው መኪና እና አባልቻቸው ላይም ጉዲት የደረሰ ስለመሆኑም ተመስክሯል። በልላ በኩል አመልካቾች የተከሰሱበትን ወንጀል ስለመፈጸማቸውም በሥር ፍ/ቤት በቀረቡት ማስረጃዎች የተመሰከረ ስለመሆኑ መዝገቡ ያስረዲል። እንግዱህ አጠቃላይ የወንጀለ አፈፃፀም ሁኔታ ይህንን የሚመስል ሲሆን አመልካቾች ወንጀለን አልፈጸምንም በማለት እዚህም ፍ/ቤት ዘንድ አጥብቀው የተከራከሩ ቢሆንም ስለወንጀለ አፈፃፀም እና የማስረጃ ምዘና ጉዲይ በዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ሥልጣን የሚታይ ባለመሆኑ በሥር ፍ/ቤት የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር እንዲለ በመቀበል በሕግ ረገድ የሚኖረውን ውጤት ብቻ እንደሚከተለው መርምረናል።
አመልካቾች የተከሰሱበትን የወንጀል ድርጊት የፈፀሙት በታንታለም ፊብሪካ ላይ የተቃጣን አደጋ ለመከላከል እንደሆነ ከፍ ሲል የተመለከተው ፍሬ ነገር እና ከወንጀለ አፈፃፀም ከባቢያዊ ሁኔታ መረዲት ይቻላል።
ድርጊቱ ወንጀል ነው ቢባልም በሕግ በተመለከተ ልዩ ሁኔታ በሕግ በተፈቀደ ድርጊቶች የማያስቀጡት እና ይቅርታ የሚያሰጡ ሁኔታዎች በወንጀል ሕጉ ጠቅላላ ክፍል የተመለከተውን ድንጋጌ ከተያዘው ጉዲይ ጋር ማየት ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል። ለተያዘው ጉዲይ ቀጥታና አግባብነት ያለው የወንጀል ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 78”ን” እንመለከታለን።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት የራሱን ወይም የላላውን ሰው መብት ሕገወጥ ከሆነ ጥቃት ወይም በቅርብ ከሚደርስ ሕገ-ወጥ ጥቃት ለማዲን ጥቃቱ እንዲይደርስ ለማድረግ ላላ መንገድ ሳይኖር ከሁኔታው መጠን ባለማለፍ የተፈፀመ ድርጊት አያስቀጣም ተብል ተደንግጓል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ተከሳሹ ከቅጣት ነፃ የሚሆነው ሕገ-ወጥ ጥቃት በራሱ ወይም በልላው ሰው መብት ላይ የተሰነዘረ ወይም በእርግጠኛነት ሉደርስ የሚችል ጥቃት ስለመኖሩ፣ይህንንም ለማስወገድ ወይም ለመከላከል ላላ አማራጭ የላለው ስለመሆኑ እና የወሰደው የመከላከል ወይም ጥቃቱን የማስወገድ እርምጃ ከተሰነዘረው ጥቃት ጋር ተመጣጣኝ ኃይል የተጠቀመ መሆኑን ማስረዲት ሲችል ብቻ ነው። ይህንኑ የሕጉን መንፈስ እና ይዘት መሰረት አድረገን የተያዘውን ጉዲይ ስንመለከት በአመልካቾች በኩል የቀረበው ፍሬ ነገር በታንታለም ፊብሪካ አካባቢ የተሰበሰበው ሕዝብ የፊብሪካውን ሥራ ስለማወኩ፣ ሕዝቡም የተለያዩ መሣሪያዎችን ያየዘ ስለመሆኑ፣ አመልካቾች ፀጥታ ለማስከበር ያደረጉትን ጥረት በፀጥታው ሃይል አባላት እና ንብረት ላይ ጥቃት የተሰነዘረ ስለመሆኑ እና በፊብሪካውም ላይ አደጋ ሉሰነዘር የተቃጣ መሆኑ ተመልክቷል። ይህ ፍሬ ነገር የሚያስገነዝበን በፊብሪካውም ሆነ በፀጥታ አስከባሪዎች ላይ የተቃጣ ሕገ-ወጥ ጥቃት ስለመኖሩ ነው ይህንን ጥቃት ለማስወገድ አመልካቾች ተኩሰው ሰው መግደላቸው እና ማቁሰላቸው ተረጋግጧል። ነገር ግን ተከትል የሚነሳው ጥያቄ አመልካቾች የተሰነዘረውን ጥቃት ለማስወገድ ላላ አማራጭ ያልነበራቸው ስለመሆኑ እና የወሰደት አማራጭም ተመጣጣኝ ስለመሆኑ አስረድተዋል ወይ? የሚለው ነው። በዚህ ረገድ አመልካቾች በሥር ፍ/ቤት ያቀረቧቸው ማስረጃዎች ያስረደት ፍሬ ነገር የለም። አመልካቾች ሕገ-ወጥ ጥቃትን ለማስወገድ እርምጃ ስለመውሰዲቸው የተመለከተ ቢሆንም እርምጃው ላላውን አማራጭ ያሟጠጠ ስለመሆኑ እና ተመጣጣኝ ስለመሆኑ ለማስረዲት ያልቻለ ስለሆነ በወ/ሕ አንቀጽ 78 የተመለከተውን ድንጋጌ ይዘት አሟልተዋል ለማለት የሚቻል ሆኖ አላገኘነውም። ስለዚህም ድርጊታቸው ሕገወጥ ጥቃትን ለማስወገድ ነው የሚያስብል መነሻ ቢኖረውም የፈፀሙት የነፍስ ግድያ ወንጀል በሕጉ ከተመለከተው መጠን በማሳለፍ መሆኑን መገንዘብ ችለናል።
ሕጋዊ መከላከልን ከመጠን በማሳለፍ የተፈፀመ የወንጀል ድርጊት ደግሞ ከቅጣት ነፃ የማያደርግ ስለመሆኑ የወ/ሕ ድንጋጌ ቁጥር 79/1/ ያመለክታል። ይልቁንም ይህ አድራጏት የቅጣት ማቅለያ ምክንያት ስለመሆኑ ይህ ድንጋጌ ቁጥር 79/1/ ይገልፃል። ይህንን መሰረታዊ ጉዲይ ከተረዲን የአመልካቾች ድርጊት ጥፊተኛ ሉያሰኝ የሚገባው በየትኛው የወ/ሕጉ ድንጋጌ ነው? የሚለውን መሰረታዊ ጭብጥ ወደ ማየት ስንመለስ የአመልካቾች ድርጊት ሕጋዊ መከላከልን ከመጠን ማሳለፍ መሆኑ መሰረት በማድረግ የወ/ሕጉ ልዩ ክፍል በዚህ ጊዜ ተፈፃሚ የሚሆን ድንጋጌ እንዲለው እንረዲለን። ይኸውም በወ/ሕጉ አንቀጽ 541/ሀ/ ሥር ከተመለከቱት የድንጋጌው ማቋቋም ምክንያቶች አንደ ሕጋዊ መከላከልን ከመጠን በማሳለፍ የተፈፀመ የነፍስ ግድያ ወንጀል እንደሆነ ተመልክቷል። ከፍ ሲል እንደተመለከትነው የወ/ሕጉ አንቀጽ 79/1/ የቅጣት ማቅለያ ምክንያት አድርጏ በገለፀው አኳኋን አንቀጽ 541/ሀ/ ሁለተኛው ሐረግ ደግሞ ወንጀለን ለማቋቋም እንደሚችል ደንግጓል።
እንዱህ ያለ ሁኔታ በተፈጠረ ጊዜ ደግሞ በወ/ሕጉ አንቀጽ 82/2/ እንደተደነገገው ድርጊቱን ለማቋቋም የተደነገገው ልዩ ክፍል ተፈፃሚነት ይኖርዋል። ይህንን ለማለት የወ/ሕጉን ድንጋጌ ቁጥር 82/2/ እና 84/2/ ይዘት እና አቀራረጽ አገናዝቦ መመልከት ተገቢ ነው።
ስለሆነም አመልካቾች የፈፀሙት የወንጀል ድርጊት የወ/ሕጉን አንቀጽ 540 የሚያቋቁም ነው በማለት የሥር ፍ/ቤቶች የሰጡት የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ የድርጊቱን አፈፃፀም ከባቢያዊ ሁኔታ እና ምክንያት በአግባቡ ባለማገናዘብ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት መሆኑን መረዲት ችለናል።
ስለሆነም አመልካቾች የፈፀመት የወንጀል ድርጊት ሉደርስ ይችል የነበረን ሕገ-ወጥ ጥቃት ለማስወገድ እና ለመከላከል መሆኑን ነገር ግን አፈፃፀማቸው ሲታይ ሕጋዊ መከላከልን ከመጠን በማሳለፍ በመሆኑ የወ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 541/ሀ/ ያቋቁማል ብለናል።
ስለዚህም በአንደኛው ክስ አንደኛ፣ሁለተኛ እና ሦስተኛ አመልካቾችን በወ/ሕ ቁጥር 32/1/ (ሀ)ና(ለ) እና 540 ሥር እንዱሁም በሁለተኛው ክስ ሦስተኛ አመልካችን በወ/ሕግ ቁጥር 27/1/ እና 540 ሥር ጥፊተኛ መባላቸው አግባብ ሆኖ ስላላገኘው ሕጉን በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 113/2/ መሰረት ለውጠን በአንደኛው ክስ ሦስቱም አመልካቾች በወ/ሕግ ቁጥር 32/1/ (ሀ)ና(ለ) እና 541/ሀ/ ሥር እንዱሁም በሁለተኛው ክስ ሦስተኛ አመልካች በወ/ሕግ ቁጥር 27/1/ እና 541/ሀ/ ሥር ጥፊተኞች ናቸው ብለናል።
ቅጣትን በተመለከተ አመልካቾች በዚህ ፍ/ቤት ጥፊተኛ የተባለበት አንቀጽ እስከ አምስት ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት እንደሚያስቀጣ ድንጋጌው ያመለክታል። በመሰረቱ ቀላል እስራት በመደቡ የሚጣለው ከአሥር ቀን እስከ ሦስት ዓመት የሚደርስ ስለመሆኑ የወንጀል ሕጉ አንቀጽ 106/1/ ድንጋጌ ያመለክታል። ቀላል እስራት ቅጣት ከዚህ መደብ ጣሪያ ከፍ ብል አምስት ዓመት ሉደርስ የሚችለው በዚሁ አንቀጽ ሥር የተመለከቱት ምክንያቶች ወይም ሁኔታዎች ውስጥ ቢያንስ አንደ ተሟልቶ ሲገኝ ስለመሆኑም ተደንግጓል። ይህንኑ በማገናዘብ አመልካቾች ላይ ሉፈፀም የሚገባውን ቅጣት እንደሚከተለው ወስነናል።
የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 02204 ታህሣሥ 30 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው የጥፊተኛነት እና የቅጣት ውሳኔ፣የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 60135 መጋቢት 19/2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ እና የኦሮሚያ ጠ/ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ቁ. 64351 ነሐሴ 20/2000 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 195/2/ለ/2/ መሰረት አሻሽለናል።
በዚሁ መሰረት በአንደኛው ክስ አንደኛ፣ሁለተኛ፣እና ሦስተኛ አመልካቾች በወ/ሕግ አንቀጽ 32/1/ (ሀ)ና(ለ) እና 541/ሀ/ ድንጋጌ በሁለተኛው ክስ ሦስተኛ አመልካች በወ/ሕግ አንቀጽ 27/1/ እና 541/ሀ/ ድንጋጌ በመተላለፍ ጥፊተኞች ናቸው ብለን ወስነናል።
አንደኛ እና ሁለተኛ አመልካቾች በዚህ ጉዲይ እጃቸው ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በሦስት(3)ዓመት ቀላል እስራት እንዱቀጡ ብለናል። ሦስተኛው አመልካች በሁለት ቀላል ወንጀል ጥፊተኛ የተባለ በመሆኑ በዚህ ጉዲይ እጁ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በሚታሰብ በአምስት (5) ዓመት ቀላል እስራት እንዱቀጣ ብለናል።
የጥፊተኛነት አንቀጽ እና ቅጣቱ የተሻሻለ መሆኑን እንዱያውቅ የዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ውሳኔ ግልባጭ ለጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ይተላለፍ። ይፃፍ።
ማረሚያ ቤቱ በዚህ ችልት በተሻሻለው ቅጣት መሰረት እንዱያስፈጽም ብለናል። ይፃፍ።
የጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መዝገብ በመጣበት ሁኔታ ይመለስ።
No topics extracted.