No summary available.
የካቲት 26 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ዘነበች ሽብሩ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የፋ/ዐ/ህግ - ፈቃደ አብዱሣ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የዐ/ህግ ምስክሮች ተሟልተው ባለመቅረባቸው መዝገቡ ለጊዜው ሲዘጋ ያለውን ውጤት የሚመለከት ነው።
የስር ፍርድ ቤት በአመልካች ላይ ተጠሪ ያቀረበውን የወንጀል ክስ በሚያስተናግድበት ጊዜ በጉዲዩ ላይ የተቆጠሩት ምስክሮች ተሟልተው ባለመቅረባቸው የዐ/ህግ ክስ ምስክሮቹ ተሟልተው ሲቀርቡ ይቀጥል ዘንድ ትዕዛዝ ሰጥቶ መዝገቡን ዘግቶታል። አመልካች በዚህ የስር ፍ/ቤት ትዕዛዝ ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋ/ከ/ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የበታች ፍ/ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡትን ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት በመሆኑ ሉታረም ይገባል በማለት ነው። ይህ ችልትም የግራ ቀኙን የቃል ክርክር ጥር 20 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ሰምቷል። እኛም ጉዲዩን ከስር ፍ/ቤት ትዕዛዝ ይዘትና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል። ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በአመልካች ላይ ተጠሪ የመሰረተው ክስ ለጊዜው የተዘጋው የዐ/ህግ ምስክሮች ሲሟለ ዐ/ህግ ክሱን የማንቀሳቀስ መብት ተጠብቆለት መሆኑን ነው። የአመልካች ጠበቃ አጥብቀው የሚከራከሩት ይህ የስር ፍ/ቤት ትዕዛዝ ገደብ የለሸ ሆኖ አመልካች በስጋት ውስጥ እንደኖሩ የሚያደርግ ነው በሚል ነው። ሆኖም የስር ፍ/ቤት ትዕዛዝ በጉዲዩ በህጉ የተመለከተውን የይርጋ ጊዜ ተግባራዊ አይሆንም የሚል አንድምታ የላለው በመሆኑ የአመልካች ጠበቃ ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም። በመሆኑም በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ትዕዛዝ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት ስላልተቻለ አፅንተነዋል።
No topics extracted.