No summary available.
ጥር 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- የኦሮሚያ ክልል ዓቃቤ ሕግ - ዮሴፍ ሐጎስ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- መሰረት መኮንን - የቀረበ የለም።
**
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የወንጀል ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ ሕዲር 13 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበበት ክስ በ1996 ዓ.ም. የወጣውን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ሟች ሲያኔ ታሬሳን ተከሣሽን ባለማግባትዋ ምክንያት ቂም ይዞ ሲሳይ በተባለው ሆቴል ጥቅምት 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. አብሯት አድሮ በንጋታው ጥቅምት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በጩቤ ሆዶንና ግራ እግሯን ወግቶ በግፍ ስለገደለ በፈፀመው ከባድ የሰው ግድያ ወንጀል ሉጠየቅ ይገባል የሚል ነው። የአሁኑ ተጠሪም በሥር ፍርድ ቤት ቀርቦ በሰጠው የእምነት ክህደት ቃል በክሱ ተቃውሞ የላለው መሆኑን በመግለጽ የወንጀል ድርጊቱን አፈፃፀም በተመለከተ ግን ስለመፈፀሙ አምኖ ጥፊተኛ አይደለሁም በማለት ተከራክሯል።
ዓቃቤ ሕግ በበኩለ አለኝ ያላቸውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል። የሥር ፍ/ቤትም ተጠሪ እንዱከላከል አድርጎ የመከላከያ ማስረጃዎችን ሰምቷል። ከዚህም በኋላ የተጠሪ መከላከያ ማስረጃዎችን የዓቃቤ ሕጉን ማስረጃዎችን ማስተባበል ያልቻለ መሆኑን በመግለጽ የመከላከያ ምስክሮችን ቃል ውድቅ ከአደረገ በኋላ ተጠሪን ለሰው ግድያ ወንጀለ ተጠያቂ ሉሆኑ ይገባል ካለ በኋላ ድርጊቱ ሉሸፈን የሚችለው በዓቃቤ ሕግ በኩል ተጠቅሶ በቀረበው አንቀጽ ሥር ሳይሆን በወ/መ/ሕ/ቁጥር 54ዐ ሥር ነው በማለት በዚሁ አንቀጽ ሥር ጥፊተኛ አድርጎ የቅጣት አስተያየት ተቀበል እና ከሕጉ ጋር በማገናዘብ የቅጣቱን መጠን 14 /አስራ አራት ዓመት/ በማድረግ ወስኗል። በዚህ ውሣኔ ላይ የአሁኑ አመልካች ቅር በመሰኘት ይግባኙን ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰበር አቤቱታውን ደግሞ ለሰበር ችልቱ ቢያቀርብም ተቀባይነት አላገኘም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካቾች ግንቦት ዐ7 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡ድርጊቱ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎበት በቂም በቀል የተፈፀመ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ፤ ተራ ሰው ግድያ ወንጀል በሚያስጠይቅበት ድንጋጌ ሥር ይወድቃል መባለ ያላግባብ ስለሆነ የጥፊተኝነት ውሣኔው በወ/መ/ሕ/ቁጥር 539/1/ሀ/ ሥር ተሰጥቶ ተመጣጣኝ ቅጣት ሉጣል ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታቸው ተመርምሮም በማስረጃ የተረጋገጠው ፍሬ ነገር በወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ ሥር የተመለተውን ከባድ የግድያ ወንጀል ያቋቁማል አያቋቁምም? የሚለውንና የዚሁ ተከታይ የሆነውን ቅጣት መጠን ለማየት ሲባል በሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ መስከረም 15 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም. በተፃፈ 2 ገጽ የሰበር አቤቱታ መልሱን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለ መልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ሟችን በቂም ተነሳስቶ በጩቤ የተለያዩ የሰውነት ክፍልቿን በመውጋት ለሕልፈት ዲርጓል በሚል አመልካች ክስ መስርቶ የድርጊቱን መፈፀም ተጠሪ ሳይክድ ጥፊተኛ አይደለሁም በማለቱ ዓቃቤ ሕግ አለኝ ያላቸውን የሰነድና የሰው ምስክሮችን አቅርቦ ማሰማቱን ነው። በዓቃቤ ሕግ የሰው ምስክሮች ቃል የተነገረው ፍሬ ነገር ሲታይም በነቀምቴ ቴላኮሙኒኬሽን አካባቢ፣ ሲሳይ ማሞ ሆቴል ፉት ለፉት ቁመው መኪና ሲጠበቁ ከቆዩ በኋላ በመኪናው ሥር ቁመው ባለበት ሁኔታ ተጠሪ ሟችን ይዟት ጩሃ እያዩአቸው ጉድኗን በጩቤ ወግቶ ከጣላት በኋላ ጨምሮ ሁለት ጊዜ ደግሞ ጭኗን /እግሯን/ ወግቶ ወጣለን ከዚህም በኋላ የተጠሪን እጅ ምስክሮች በመምታት ጩቤውን በማስጣል ተጠሪን ፖሉስ መያዙን እንዱሁም ሟችን ሆስፒታል ወስደዋት በእለቱ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ላይ መሞቷን መመስከራቸውን የሚያስገነዝብ ነው። በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ተጠሪ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 35 መሰረት ለወረዲው ፍርድ ቤት በሰጠው ቃል ሲሆን ይዘቱም ሲታይ ሟች ጓደኛዬ /ፍቅረኛዬ/ ሆና ለሦስት ዓመት በየወሩ ብር ሦስት መቶ እየረዲት በነቀምቴ መምራን ኮላጅ ሲያስተምራት ቆይቶ በሽምግልና ሲያስጠይቃት እምቢ ስላለችው ገንዘቡን እመልስለታለሁ፣ አልፈልገውም ብላ ስለተናገረች ጥቅምት 26 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ሲሳይ ማሞ ሆቴል አብረው አድረው ጥቅምት 27 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ጠዋት ላይ በጩቤ ሟችን ወግቶ የገደላት መሆኑን ቃለን በነፃ ፈቃደ መስጠቱን የሚያስረዲ ነው። ላላው በዓቃቤ ሕግ በኩል የቀረበው የሰነድ ማስረጃ ከነቀምቴ ሆስፒታል የተሰጠ የሕክምና ማስረጃ ሲሆን ይዘቱም በሟች አካል ላይ በሦስት በተለያዩ ክፍልች የተለያየ መጠን ያላቸው ቁስልች የነበሩ ስለመሆኑና በዚሁ ምክንያትም መሞቷን የሚያሳይ ነው። እንግዱህ በአቃቤ ሕግ በኩል የቀረቡት ማስረጃዎች ያረጋገጡት ፍሬ ጉዲይ ከላይ የተመለከተው ስለመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶችም ያረጋገጡት ጉዲይ ሲሆን በተጠሪ መከላከያ ማስረጃም ይኸው ፍሬ ጉዲይ የተስተባበለ ወይም ላልች ሁኔታዎች ባለበት የተፈፀመ ስለመሆኑ የተነገረ ነገር የላለ መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪን ጥፊተኛ ሲያደርግ በዓቃቤ ሕግ በኩል የተጠቀሰውን አንቀጽ ዝቅ ወደአለ አንቀጽ መቀየሩ ባግባቡ ነውን? የሚለው ጥያቄ ምላሽ የሚያስፈልገው ነው።
በመሰረቱ የሰው ግድያ ወንጀል በወንጀል ሕግ አንቀጽ 539/1/ሀ/ መሰረት ድርጊት ፈፃሚውን ሉያስጠይቅ የሚችለው ድርጊቱ ሆነ ተብል አስቀድሞ በማሰብና በመዘጋጀት ሲፈፀም ወይም በአንቀጽ 84 ወይም 86 ሥር የተመለከቱት አክባጅ ሁኔታዎች በተገኙበት ሁኔታ የወንጀል አድራጊው በተለይ ጨካኝ፣ ነውረኛ ወይም አደገኛ መሆኑን ሲያመለክቱ ስለመሆኑ ተጠቃሹ ድንጋጌ በግልጽ ያሳያል። ከዚህም መገንዘብ የሚቻለው በድንጋጌው ሥር የተመለከቱት የወንጀለ ማቋቋሚያ ነጥቦች በየራሳቸው መቆም የሚችለ ነጥቦች ስለመሆናቸው ነው።
በተያዘው ጉዲይ ተጠሪ ሟችን የገደለው ፍቅረኛው ሆና ትምህርት በራሱ ወጪ ሲያስተምራት ቆይቶ አላገባህም፣ ገንዘብህን እመልስልሃለሁ ስላለችው በዚህ መልሷ ቂም ይዞ ቆይቶ እንዱሁም ወንጀለ ከመፈፀሙ በፉትም አንድ ቀን ቀደም ብለው አብረው በሆቴል ውስጥ አድረው ከወጡ በኋላ በጩቤ ደጋግሞ በመውጋት ለሕልፈት የዲረጋት ስለመሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ጉዲይ ነው። እነዚህ ፍሬ ነገሮች ተጠሪ የግድያ ወንጀለን አስቦበትና ቀድሞ ተዘጋጅቶበት በጭካኔ ወይም በአደገኛነት የፈፀመው ስለመሆኑ ያሳያለ ከሚባለ በስተቀር በእለታዊ ፀብ እና አለመግባባት ምክንያት የፈፀመው ድርጊት ነው ለማለት የሚያስችለ አይደለም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች በዓቃቤ ሕጉ ማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ከሕጉ ጋር ማገናዘብ ሲገባቸው ያለ ምክንያት በተጠሪ ላይ ተጠቅሶ የቀረበውን ድንጋጌ መቀየራቸው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተጠሪ ለፈፀመው የሰው ግድያ ወንጀል ሉጠየቅ የሚገባው በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 539/1/ሀ/ ሥር እንጂ በአንቀጽ 54ዐ ሥር ባለመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች በተጠሪ ላይ የሰጡትን የጥፊተኛነት ውሣኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195/2/ለ/2/ መሰረት ለውጠን ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 539/1ሀ/ ሥር ጥፊተኛ ተብል ሉቀጣ የሚገባ ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ ሉቀጣ የሚገባው በዚህ ፍርድ ቤት ጥፊተኛ በተባለበት ድንጋጌ ሥር በተመለከተው ቅጣት አንፃር ነው። ቅጣት የሚወሰነው ደግሞ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 82፣ ሥር የተመለከቱትን ሁኔታዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ነው። ይህ ችልትም እነዚህ ሁኔታዎችን ተመልክቷል፤ አመዛዝኗልም። ተጠሪ የወንጀል ድርጊቱን ሰለመፈፀሙ በዝርዝር ማመኑ፣ ሪኮርድ ያልቀረበበት መሆኑም መልካም የነበረ መሆኑን እንደሚያሳይ የሚያስገነዝብ ነው። እነዚህ ነጥቦች ደግሞ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 82/1/ሀ/ እና /ሰ/ መሰረት የቅጣት ማቅለያ ምክንያቶች ሲሆኑ መጠኑም በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 179/ለ/ መወሰኑ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል። ሲጠቃለልም የበታች ፍርድ ቤቶች ተጠሪን ተጠያቂ ያደረጉበት ድንጋጌ በማስረጃ የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር መሰረት ያላደረገና በምክንያትም ያልተደገፈ በመሆኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሲሆን የተጠሪን አድራጎት በከባድ የሰው መግደል ወንጀል የሚሸፈንና የቅጣት መጠኑንም ከፍ ብል መወሰን ያለበት ሆኖ ስለተገኘ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በአመልካቾች ላይ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት የጥፊተኛነትም ሆነ የቅጣት ውሣኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁጥር 195/2/ለ/2/ መሰረት ተሻሽሎል።
ተጠሪ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 539/ሀ/ ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ የተላለፈ ጥፊተኛ ነው ብለናል።
ተጠሪ በጉዲዩ የታሰረው የሚታሰብለት ሆኖ ሉቀጣ የሚገባው በ2ዐ /ሃያ/ ዓመት ጽኑ እስራት ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶችን ውሣኔ በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 195/2/ለ2/ መሰረት አሻሽለን ወስነናል።
ውሣኔው የተሻሻለ መሆኑን አውቆ ቅጣቱን ተከታትል እንዱያስፈጽም ለማ/ቤት ይፃፍ።
No topics extracted.