No summary available.
ታህሣሥ 8 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መሰለ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡-
ይህ ጉዲይ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ ጋር በተያያዘ የቀረበ የወንጀል ክስ ሲሆን ተጠሪ በአመልካቾችና በሥር ሁለተኛ ተከሳሽ ላይ የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ያቀረበው የወንጀል ክስ አንደኛ እና ሁለተኛ ተከሳሾች የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 56/1/ እና እንደተሻሻለው አንቀጽ 22/1/ እና 50/ለ//1/ የተመለከተውን በመተላለፍ ሦስተኛ ተከሳሽ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 34/1/ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ ቁጥር 285/94 እና እንደተሻሻለው አንቀጽ 22/1/ እና አንቀጽ 50/ለ/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ አራተኛ ተከሳሽም የተጨማሪ አዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 55 እና እንደተሻሻለው አንቀጽ 22/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ መጋቢት 26 ቀን 2001 ዓ.ም ከቀኑ 5፡45 ሰዓት ላይ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ በካላብ ጌጣጌጥ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ወንጀል ተከሰዋል የሚል ነው።
ተከሳሾች ቀርበው ክሱን እንዱረደት ከተደረገ በኋላ የእምነት ክህደት ቃል ሲጠየቁ ክሱን እንደማይቃወሙ ገልጸው ድርጊቱን አልፈጸምንም ጥፊተኞችም አይደለንም በማለት ክደው ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የዓ/ሕግ ማስረጃን ሰምቶ ተከሳሾች በክሱ ላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሥፍራ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ በካላብ ጌጣጌጥ ኃ/የተ/የ/ማህበር ድርጅት ውስጥ የአንገት ሐብል ሽያጭ ስለማከናወናቸው የተረጋገጠ ስለሆነ ይከላከለ በማለት ብይን ሰጥቶ ተከሶሾች መከላከያ ማስረጃቸውን አሰምተዋል። ከዚያም ተከሳሾች የወንጀለን ድርጊት ስለመፈጸማቸው በአቃቤ ሕግ ማስረጃ ተረጋግጦባቸው በመከላከያ ማስረጃቸው ማስተባበል እንዲልቻለ ፍ/ቤቱ ዘርዝሮ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ቃል ውድቅ ከአደረገ በኋላ ተጠቅሶ በቀረበባቸው ድንጋጌ ሥር ጥፊተኛ ናቸው ካለ በኋላ አንደኛ እና አራተኛ ተከሳሾች እያንዲንዲቸው በአንድ ዓመት እሥራትና በብር 10ሺህ የገንዘብ መቀጫ እንዱቀጡ ሦስተኛ ተከሳሽም በብር 60 ሺህ የገንዘብ መቀጫ እንዱቀጣ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። ሁለተኛ ተከሳሽ ግን በተከሰሰበት ወንጀል ኃላፉነት የለበትም በማለት በወ/መ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ. 149/2/ መሰረት በነፃ እንዱሰናበት ወስኗል።
ከ1-3 የተጠቀሱት ተከሳሾች የአሁን አመልካቾች በውሳኔው ቅር በመሰኘት የይግባኝ ቅሬታ ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም።
የሰበር አቤቱታውም የቀረበው በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ስለሆነ ሉታረም ይገባል በሚል ሲሆን የሰበር አቤቱታው ተመርምሮ አመልካቾች ጥፊተኛ ተብለው የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር ሲባል አቤቱታው ለሰበር እንዱቀርበ ተደርጏ ግራ ቀኙ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ ባጭሩ የተመለከተው ሲሆን በአመልካቾች ላይ የተሰጠው የጥፊተኛነትና የቅጣት ውሳኔ ከሕጉ አኳያ አግባብነቱ እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት ለመገንዘብ እንደተቻለው አመልካቾች ፈጽመዋል ተብለው የተከሰሱበትን የወንጀል ድርጊት ለማስረዲት አቃቤ ሕግ ሁለት ምስክሮች በፋዳራል የመ/ደ/ፍ/ቤት አቅርቦ ያሰማ ሲሆን እነዚህም ምስክሮች የሰጡት ቃል ተጠቃል ሲታይ መጋቢት 26 ቀን 2001 ዓ.ም ከቀኑ 5፡45 ሰአት ሲሆን ወደ አንደኛ አመልካች የጌጣጌጥና ወርቅ መሻጫ ድርጅት ሄደን ባለ 18 ካራት የወርቅ የአንገት ሐብል ጠይቀን 5.9 ግራም ወርቅ በብር 2100 ተሰማምተን ሐብለን ከገዛን በኋላ የድርጅቱ የሽያጭ ሰራተኛ የነበረውን ሦስተኛ አመልካችን የቫት ደረሰኝ እንዱሰጠን ስንጠይቀው የቢዝነስ ካርድ ሰጠን ከዚያም ማንነታችንና የመጣንበትን ስንገልጽለት ስልክ በመደወል ደረሰኝ እንዱመጣለት ጠይቆ አንደኛ ተከሳሽ የቫት ደረሰኙን ይዘው ወደ ሱቁ መጥተዋል የሚል ነው።
ማንኛውም በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዝገብ ድርጅት የሚያካሂደውን ማንኛውንም ሽያጭ ያለ ተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ካከናወነ ድርጊቱ ሕገወጥ እንደሆነና እንደሚያስቀጣም የተጨማሪ እሴት ታክስን ባሻሻለው አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀጽ 50/ለ/ /1/ ላይ ተደንግጓል። እንደዚሁም ማንኛውም ለተጨማሪ እሴት ታክስ ክፍያ የተመዘገበ ድርጅት ታክስ የሚከፈልበትን ሽያጭ ያከናወነ ሰው ደረሰኝ ለገዢው ወዱያውኑ መስጠት እንዲለበት በዚሁ በተሻሻለው አዋጅ ቁጥር 609/2001 አንቀጽ 22/1/ ላይ ተመልክቷል።
ስለሆነም የሁለተኛ አመልካች የካላብ ጌጣጌጥ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሽያጭ ሰራተኛ የሆኑት ሦስተኛ አመልካች ከፍ ብል በተጠቀሱት የአዋጁ ድንጋጌዎች መሰረት የወርቅ ሽያጩን ካከናወኑ በኋላ ደረሰኝ ለገዢዎች ወዱያውኑ መስጠት ሲገባቸው ደረሰኙን ወደያውኑ ሳይሰጡ መቅረታቸው በአቃቤ ሕግ ማስረጃ ተረጋግጦባቸው በመከላከያ ማስረጃ ያላስተባበለ በመሆኑ ጥፊተኛ መባላቸው የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አላገኘነውም።
በልላ በኩልም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል (Body corporate) በወንጀል ተጠያቂ ለመሆን በወንጀል ሕግ አንቀጽ 23/3/ መሰረት ወንጀል የመፈጸም ሐሳብ(criminal intention) ግዐዝ ከመሆኑ አኳያ እንዱሟላ የሚጠበቅ ሳይሆን ኃላፉነቱ በወንጀል ሕጉ አንቀጽ 34/1/ ላይ እንደተመለከተው ከድርጅቱ ኃላፉዎች ወይንም ከሰራተኞቹ አንደ የድርጅቱን ሕጋዊ ግዳታ ባለመወጣት የድርጅቱን ጥቅም ሕገወጥ በሆነ መንገድ ለማራመድ ተንቀሳቅሰው በሚገኙበት ጊዜ ሉመነጭ ይችላል። በሁለተኛ አመልካች ድርጅትም የድርጅቱን ሕጋዊ ግዳታ በመወጣት ረገድ ከፍ ብል በተጠቀሰው አኳኋን የድርጅቱ ሰራተኛ በሆኑት ሦስተኛ አመልካች ዓማካኝነት የተፈጸመ እንደመሆኑ መጠን በወንጀል ሕግ ቁጥር 34/1/ እና በአዋጅ ቁጥር 285/94 አንቀጽ 56/1/ መሰረት ድርጅቱ ጥፊተኛ መባለ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አልተቻለም።
ከዚሁ ጋር በተያያዘም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ ድርጅት አዋጁን በመተላለፍ ጥፊት ፈጽሞ በሚገኝ ጊዜ የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ በድርጅቱ የተፈጸመውን ጥፊት እንደፈጸመ ተቆጥሮ በአዋጁ የተጣለው ቅጣት ተፈፃሚ እንደሚሆንበት በዚሁ አንቀጽ 56/1/ ሥር የተመለከተ ሲሆን ሥራ አስኪያጁ ከኃላፉነት ነፃ የሚሆነው በንኡስ አንቀጽ /3/ ላይ እንደተመለከተው ጥፊቱ የተፈጸመው ግለሰቡ ሳያውቅ ወይም ሳይስማማበት ሲቀር እንደዚሁም ነገሮችን በጥንቃቄ የሚያሳይ ሰው በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ የጥፊቱን መፈጸም ለመከላከል ይወስዲቸዋል ተብል የሚገመቱ ጥንቃቄዎችን ተገቢውን ትጋትና የአሰራር ጥበብ የተሞላበት እርምጃ ወስድ የተገኘ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው።
ሆኖም ግን ከጉዲዩ መገንዘብ እንደተቻለው አንደኛ አመልካች እንደ ድርጅቱ ሥራ አስኪያጅነታቸው አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ሽያጭ በሚከናወንበት ጊዜ ገዢዎች የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ወዱያውኑ እንዱያገኙ የሚያስችል የአሰራር ሥርአት መዘርጋት ሲገባቸው ይህንን በሕግ የተጣለባቸውን ግዳታ ባለማክበር የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኙ ሽያጩ ከተከናወነበት ሱቅ ወደ ላላ ሱቅ ሁልጊዜ እየተወሰደ የኦዱት ሥራ እንዱሰራ መደረጉ ኦዱት ተደርጏ እስከሚመጣም ሱቁ ያለደረሰኝ እንዱቆይ ግድ ስለሚያደርገው የኦዱት ሥራው በዚያው ሱቅ ደረሰኙ ሳይወሰድ እንዱከናወን ማድረግ ከአንድ ጠንቃቃ ሥራ አስኪያጅ የሚጠበቅ ተግባር እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። የተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኙ ወደ ላላ ሱቅ እንዱሄድ ማድረግ ከውጤት አኳያ ያለደረሰኝ ሽያጭ ለማካሄድ እንደመወሰን የሚቆጠርና የማያመች አሰራርን በመከተል ሕጉ የታለመለትና ዓላማና ግብ እንዲያገኝ የሚያበቃ ነው።
በመሆኑም አንደኛ አመልካች እንደ ሥራ አስኪያጅነታቸው በሕግ የተጣለበባቸውን ግዳታ በመከተል ተገቢውን ጥንቃቄ ያላደረጉና ይልቁንም የዘረጉት የአሰራር ሥርአት ያለደረሰኝ የሚደረገውን ግብይት አውቀውና ፈቅደው እንደሚከናወን ከክርክሩና ከማስረጃው መገንዘብ የተቻለው ስለሆነ በአንደኛ አመልካችም ላይ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው የጥፊተኛነት ውሳኔ የሕግ ስህተት ተፈጽሞበታል ለማለት አልተቻልም።
ሲጠቃለልም አመልካቾች በተከሰሱበት ወንጀል ጥፊተኛ ሆነው መገኘታቸው በሕጉ አግባብ ከመሆኑም በላይ በቅጣቱም ላይ ከአመልካቾች ቅሬታ አኳያ የሕግ ስህተት የተፈጸመ ሆኖ አላገኘውም።
No topics extracted.