No summary available.
ሐምል 2 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ድልበጌ ራሕመቶ ተጠሪዎች፡-
ለሰበር አቤቱታው መነሻ የሆነው ጉዲይ በአፈጻጸም ጊዜ የተነሳን ክርክር የሚመለከት ነው። ከመዝገቡ እንደሚታየው አንደኛ አመልካች የፍርድ ባለመብት ሲሆን የሁለተኛ ተጠሪዎች አውራሽ አቶ መሐመድ ዐስማን ደግሞ የፍርድ ባለዕዲ ነው። አመልካች ክርክሩ ውስጥ የገባችው የፍርድ ባለመብቱ የአፈጻጸም ትዕዛዝ (በሐራጅ ይሸጥ) ያሰጠበት ቤት የፍርድ ባለዕዲ ንብረት አይደለም። ቀደም ሲል ኑርሐሴን በርሄ የተባለው ሰው ንብረት የነበረ፤ በኋላም ከዚህ ሰው ወራሾች (እነ ዘይኑ ኑርሐሴን) ላይ የገዛሁት ነው። በንብረቱ ላይ የተሰጠው የሐራጅ ትዕዛዝ እና እግድ ይነሳልኝ በማለት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.418 መሰረት በማለት መቃወሚያ በማቅረብዋ ነው።
መቃወሚያው የቀረበለት ፍ/ቤት የግራ ቀኝ ወገኖችን ክርክር ከሰማ በኋላ፣ የአመልካችን መቃወሚያ በመቀበል የሐራጁ ሽያጭ ቀሪ ሆኖ ቤቱ ለአመልካች ይለቀቅ በማለት ወስኖአል። በልላ በኩል ደግሞ አንደኛ ተጠሪ ውሳኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ በማቅረቡ ክርክሩ በድጋሚ የተሰማ ሲሆን፣ ፍ/ቤቱም አመልካች ቤቱን ገዝቻለሁ በማለት ውል ከማቅረብዋ ውጪ ስመሃብቱን በስምዋ አላዛወረችም። ባለቤት ናት ለማለት የሚያስችል ማስረጃ የላትም የሚለትን ምክንያቶች በመስጠት መቃወሚያው ተቀባይነት የለውም ብልአል። በዚህ መሰረትም በሥር ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ ሽሮአል። ጉዲዩ በይግባኝ የቀረበለት የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤትም ውሳኔው ጉድለት የለበትም በማለት የአመልካችን ይግባኝ ሰርዞአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
እኛም አመልካች ግንቦት 24 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈችው ማመልከቻ ያቀረበችውን አቤቱታ መሰረት በማድረግ ተጠሪዎችን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው ለክርክሩ መነሻ የሆነው ቤት በውል መገዛት እየታወቀ በስምሽ አልተመዘገበም በሚል ምክንያት መቃወሚያዬ ውድቅ መደረጉ አግባብ አይደለም የሚለውን የአመልካች አቤቱታ ሉመረመር ይገባል በመባለ ነው። በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
ክርክሩ በአፈጻጸም ደረጃ ያለን ጉዲይ የሚመለከት ስለመሆኑ ከላይ ተገልጾአል። አንደኛ ተጠሪ ቤቱን በአፈጻጸም እንዱያዝለት የጠየቀው የፍርድ ባለዕዲው የአቶ መሐመድ ዐስማን (የሁለተኛ ተጠሪዎች አውራሽ) ንብረት ነው በማለት ነው። አመልካች ቤቱን ገዛሁት የምትለው ደግሞ ከፍርድ ባለዕዲው ላይ ሳይሆን፣ አቶ ኑርሁሴን በርሄ ከተባለው ሰው ወራሾች ላይ ነው። በመሆኑም አመልካች ያቀረበችው መቃወሚያ አንደኛ ተጠሪ ከአቀረበው ክርክር አንፃር ከመታየቱ በፉት በእርግጥ ቤቱ የፍርድ ባለዕዲው ንብረት ለመሆኑስ ተረጋግጦአል ወይ? የሚለውን ነጥብ መመልከቱ ተገቢ ይሆናል። አንደኛ ተጠሪ በዚህ ረገድ አንድም ያቀረበው ማስረጃ የለም።
ሲከራከር የቆየው አመልካች የሽያጭ ውል ከማቅረብ አልፊ የቤቱን ስመሃብት በስምዋ አላዛወረችም በሚለው ነጥብ ላይ ብቻ በመመስረት ነው። የሥር ፍ/ቤቶችም ይህን የክርክር አቅጣጫ ተከትለው ነው የወሰኑት።
በበኩላችን እንደምናየው ግን ለሽያጭ የቀረበው /አንደኛ ተጠሪ በአፈጻጸም ያስያዘው/ ቤት በእርግጥም የፍርድ ባለዕዲው ንብረት ለመሆኑ በቅድሚያ ሉረጋገጥ ይገባል። ይህ ከተረጋገጠ በኋላም ነው በአመልካች እና በአንደኛ ተጠሪ መካከል ያለውን ክርክር ማየት የሚገባው።
ከላይ እንዲመለከትነው አመልካች ቤቱን የገዛችው ከፍርድ ባለ ዕዲ ላይ እንዲልሆነ አላከራከረም። አንደኛ ተጠሪም ቤቱ የፍርድ ባለዕዲ ንብረት ለመሆኑ ወይም የአቶ ኑርሁሴን በርሄ ንብረት ላለመሆኑ በማስረጃ ሉያስረዲ ቀርቶ በክርክር ደረጃ እንኳን ምንም ያለው ነገር የለም። በዚህ ሰበር ችልት በተደረገው ክርክርም የአንደኛ ተጠሪ ነገረ-ፈጅ ተጠይቆ የሰጠው መልስም ከዚህ የተለየ አይደለም። በሁለተኛ ተጠሪነት የቀረቡት የሥር የፍርድ ባለዕዲ ወራሾችም ቤቱ የእነሱ እንዲልሆነ በመግለጽ መልስ ሰጥተዋል። እነዚህን ሁኔታዎች መሰረት በማድረግ ጉዲዩን ስናየው ቤቱ አንደኛ ተጠሪ በሁለ ተኛ ተጠሪ ባስፈረደው ገንዘብ ምክንያት በአፈጻጸም የሚያዝበት የሕግ ምክንያት አላገኘንም። ስለዚህም ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. የካቲት 5 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋዳራል ጠ/ፍ/ቤት በፍ/ብ/ይ/መ/ ሚያዝያ 19 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁ.348(1) መሰረት ተሽረዋል።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው በአፈጻጸም ሉያዝ አይችልም ብለናል።
ግራ ቀኝ ወገኖች ወጪና ኪሣራቸውን ይቻቻለ።
No topics extracted.