No summary available.
ግንቦት 03 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ኂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሰመንጉስ አሰፊ - ቀረቡ ተጠሪ፡- መ/ርት ምህረት ክበበው - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በጋብቻ ወቅት በግል ለመጣ እዲ ለአፈፃፀም የሚውለውን ንብረት የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች በአሁኑ ተጠሪ ላይ በይርጋለም ከተማ የመ/ደረጃ ፍ/ቤት በመሰረቱት የአፈፃፀም ማመልከቻ ነው። የአፈፃፀም ማመልከቻ ይዘቱም ባጭሩ፡- አመልካች የአሁኑ ተጠሪ ባለቤት በነበሩት በአቶ ፀጋዬ ከበደ ላይ የብድር ገንዘብ ይከፈለኝ ጥያቄ አቅርበው በዋናው ጉዲይ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ አቶ ፀጋዬ ከበደ የብድር ገንዘቡን ለአሁኑ አመልካች እንዱከፈላቸው የተወሰነ መሆኑን ገልፀው አፈፃፀሙ በተጠሪ ደሞዝ እንዱቀጥልላቸው ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። በዚህ መሰረት አፈፃፀሙ ቀጥል ተጠሪ በላለበት እንዱታይ ተደርጏ ከተጠሪ ደመወዝ 1/3ኛ እየተቆጠረ ለአፈፃፀሙ እንዱውል የሚል የፍርድ ትእዛዝ ተሰጥቷል።
ከዚህ በኋላም ተጠሪ እዲውን የማያውቁት መሆኑን ገልፀው በላለበት የተሰጠው የአፈፃፀም ትእዛዝ እንዱነሳላቸው አመልክተው የስር ፍርድ ቤት ሳይቀበለው ቀርቷል። የአሁኗ ተጠሪ በዚህ ውሳኔ ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ፍርድ ቤቱ እዲው የመጣው በተጠሪ ባለቤት በነበሩት ግለሰብ የግል ጉዲይ በመሆኑ በተጠሪ ደመወዝ አፈፃፀሙ ሉቀጥል የሚችልበት የሕግ ምክንያት የለውም የሚለውን ምክንያት በመያዝ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮታል። ይህ ውሳኔ በደቡብ ብሓር ብሓረሰቦች እና ሕዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚውም ሆነ ሰበር ሰሚው ችልት ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ ውሳኔ ባለመስማማት ለማስቀየር ነው።
አመልካች ነሐሴ 07 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮም በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል ተብል በመወሰኑ ተጠሪ ቀርበው መጋቢት 30 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ አንድ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም አመልካች ያስፈረደት ፍርድ በተጠሪ ደመወዝ ላይ እየተቆጠረ ሉፈፀም አይገባም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑ በጭብጥነት ላታይ የሚገባው ሆኖ አግኝቶታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካች ዋናውን ፍርድ ያስፈረደት በተጠሪ ባለቤት በነበሩት አቶ ፀጋዬ ከበደ ሲሆን እዲውም በግል የመጣ መሆኑ በፍርድ መረጋገጡን ነው። እንዱሁም አቶ ፀጋዬ ከበደ የግል ንብረት የላላቸው ስለመሆኑ አልተረጋገጠም።
በመሰረቱ አንድ ተጋቢ በግለ ያመጣው እዲ ከላላኛው ተጋቢ የጋራ ንብረት እንዱከፈል የሚደረገው እዲውን ያመጣው ተጋቢ በግለ መክፈል ያልቻለ መሆኑ ሲረጋገጥ እና እዲው የመጣው በጋብቻ ወቅት ሆኖ ተጋቢዎቹ እዲው በሚከፈልበት ወቅት የፀና ጋብቻ ውስጥ ያለ ከሆነ ስለመሆኑ ለውሳኔው መሰረት ከሆነው የደቡብ ብሓር ብሓረሰቦች እና ሕዝቦች ብሓራዊ ክልላዊ መንግስት የተሻሻለው የቤተሰብ ሕግም ሆነ ከተሻሻለው የፋዳራለ የቤተሰብ ሕግ (አዋጅ ቁጥር 213/92) ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው።
በተያዘው ጉዲይ እዲው በአቶ ፀጋዬ ከበደ በግል የመጣ እና ለቤተሰቡ የጋራ ጥቅም ያልዋለ መሆኑ የዞኑ ከፍተኛ ፍ/ቤትም ሆነ የክልለ በላይ ፍ/ቤቶች ያረጋገጡት ነጥብ ነው። እንዱህ ከሆነ ተጠሪ ከአቶ ፀጋዬ ጋር እዲው ሲወሰድ ጋብቻ መስርተው ነበር ተብል ለጋራ ጥቅም ላልዋለውና በግልጽ አቶ ፀጋዬ ለግል ጉዲይ ብለው ለተበደሩት ገንዘብ የተጠሪ ደመወዝ የሚቆረጥበት የሕግ አግባብ የለም። ስለሆነም አመልካች በአቶ ፀጋዬ የግል ንብረት ላይ አፈፃፀሙን ከሚቀጥለ በስተቀር በተጠሪ ደመወዝ ላይ አፈፃፀሙን እንዱቀጥለ የሚደረግበት የሕግ አግባብ የለም። በመሆኑም በጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ በሥነ-ሥርአትም ሆነ በመሰረታዊ ሕግ ረገድ የተፈፀመ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት አልተገኘም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
በሲዲማ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 08543 ታህሣሥ 14 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በደ/ብ/ብ/ሕ/ብ/ክልላዊ መንግስት ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት በመ/ቁ. 21205 ግንቦት 14 ቀን 2000 ዓ.ም፣በሰበር ችልቱ በመ/ ሐምል 11 ቀን 2000 ዓ.ም የጸናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።