No summary available.
መጋቢት 23 ቀን 2002ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ፀሐይ ወንድም - ቀረቡ ተጠሪ፡- 1/ አቶ አያለው መለስ - አልቀረቡም 2/ ወ/ት ፍሬህይወት - ተመስገን ቀረቡ መዝገቡን መርምረን ተከታዮን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ የውሳኔ አፈፃፀም የሚመለከት ነው። ጉዲዩ የውርስ ንብረት ክፍፍልን መነሻ ያደረገ ሲሆን ግራ ቀኙ በአይነት ለመከፊፈል ከስምምነት ለመድረስ አለመቻላቸውን ጠቅሶ በጨረታ ተሸጦ ውጤቱ እንዱቀርብ ሲል የምስራቅ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአፈፃፀም መዝገብ የሰጠውን ትዕዛዝ የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት እና የክልለ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልቶች በማጽናታቸው አመልካች ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት አቤቱታ አቅርበዋል።
አመልካች የካቲት 26 ቀን 2001ዓ.ም ጽፈው ያቀረቡት አቤቱታ ይዘት ባጭሩ የውርስ ሐብቱን ስመሐብት ወደ ስማቸው ለማዞር ያቀረቡትን አቤቱታ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይሰጥበት ማለፈ እና የቤቱ ዋጋ በባለሙያ ወይም በሽማግላ ሳይገመት ቤቱ በወር በሚያስገኘው የኪራይ ገቢ መነሻ በጨረታ እንዱሸጥ መደረጉ መብታቸውን እንደሚጎዲ ጠቅሰው ንብረቱን በስምምነት ለመሸጥ ወይም ለማከራየት እንዱችለ እንዱወሰን አመልክተዋል።
ይህ ችልትም አቤቱታውን ከመረመረ በኋላ የስር ፍ/ቤት አፈፃፀሙን የሰራው በተከራከሪ ወገኖች ፈቃድ እና በውሳኔው መሰረት መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ተጠሪዎችን አስቀርቧል። አንደኛ ተጠሪ ጥር 25 ቀን 2002ዓ.ም ጽፍ ባቀረቡት መልስ በውሳኔው መሰረት ቤቱን ማስረከቡን ገልጿል። ሁለተኛ ተጠሪ ጥር 3 ቀን 2002ዓ.ም በጽሐፍ በሰጡት መልስ ከአመልካች ጋር ወራሽ መሆናቸውን ጠቅሰው ቤቱን በአይነት ለመከፊፈል አመቺ አለመሆኑን አመልካች እያወቁ ቤቱን ይዞ አፈፃፀሙን ማጓተት ተገቢ አለመሆኑን ጠቅሰው ቤቱ በጨረታ ተሸጦ ገንዘቡን እንዱካፈለ እንዱወሰን አመልክተዋል።
የግራ ቀኙ ክርክር እና የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተመለከተው ሲሆን እኛም ከተያዘው ጭብጥ አንፃር ጉዲዩን መርምረናል።
በዚህ ፍ/ቤት ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በዚህ ፍ/ቤት ምላሽ የሚያሻው ነጥብ ግራ ቀኙ ንብረቱን በስምምነት ለመከፊፈል ያልቻለ እንደሆነ የጨረታው ሽያጭ መነሻ ዋጋ ተብል የተወሰደውን አግባብነት እንደሚከተለው መርምረናል።
ከከፍተኛው ፍ/ቤት ትዕዛዝ መረዲት እንደተቻለው የጨረታ መነሻ ዋጋ ተብል የተጠቀሰው ብር 16,527.29(አስራ ስድስት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ሰባት ከሃያ ዘጠኝ ሣንቲም) ቤቱን የቅደስ ጊዮርጊስ ቢራ ማከፊፈያ የተከራየበት ግምት መሆኑ ነው። ይህ ገንዘብ የቤቱ የአመት የኪራይ ዋጋ ስለመሆኑ አመልካች በአቤቱታቸው ገልፀዋል። ተጠሪዎች ይህ ሐሰት ነው አላለም። ይህ ፍሬ ነገር ሲታይ ቤቱ በሐራጅ እንዱሸጥ ሲወሰን የቤቱ ዋጋ ተብል ሉወሰድ የሚገባው የኪራይ ዋጋ ማለት እንዲልሆነ መረዲት የሚያዲግት አይደለም።
አፈፃፀሙን የያዘው ፍ/ቤት ግን የኪራይን ዋጋ ለቤቱ ሽያጭ የጨረታ መነሻ ዋጋ አድርጎ ወስድታል። በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1083 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች የውርስ ንብረት ግምት አፈፃፀም ተመልክቷል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የንብረቱ ግምት በወራሾች ስምምነት ሉወሰን የሚችል ሲሆን ከስምምነት ካልደረሱ እነሱ በመረጧቸው የሽምግልና ዳኞች አሉያም ፍ/ቤቱ በሚመርጣቸው የሽምግልና ዳኞች ሉገመት እንደሚችል ተጠቅሷል። ይህም ካልተቻለ በፍ/ብ/ሕግ ድንጋጌ ቁጥር 1084 መሰረት በባለሙያ እንዱገመት ማድረግ ይገባል።
ይህ ግምት የሚከናወነው የንብረቱን ይዞታ እና የገቢያ ዋጋ ለማመልከት እንደሆነ መረዲት ይቻላል።
በተያዘው ጉዲይ ፍ/ቤቱ የንብረቱ ግምት ነው ብል የኪራይ ዋጋ ግራ ቀኙ የተስማሙበት ነው በማለት ለሽያጭ መነሻ ዋጋ ግምት አድርጎ መውሰድ አግባብ ሆኖ አላገኘነውም።
ስለሆነም በዚህ ገረድ ፍ/ቤቱ የሰጠው ትዕዛዝ የግራ ቀኙን መብት የሚያጣብብ ከመሆኑ አንፃር እንዱሁም በሕጉ ከተመለከተው አግባብ ውጪ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል።
ስለሆነም ሉታረም ይገባል ብለናል። ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የምሥራቅ ጎጃም ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የሰጠው የአፈፃፀም ትዕዛዝ እና የአማራ ብ/ክ/መ/ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ በመ/ የሰጠው ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
No topics extracted.
ግራ ቀኙ የሚከራከሩበት የውርስ ንብረት ዋጋ በግራ ቀኙ ስምምነት አሉያም በባለሙያ ተገምቶ እንዱቀርብ በማድረግ የሐራጅ ሽያጭ እንዱደረግና በውጤቱም መሰረት እንዱያስፈጽም መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 343/1/ መሰረት ለምሥራቅ ጎጃም ከፍተኛ ፍ/ቤት እንዱመለስ አዝዘናል።
የዚህ ፍ/ቤት ውጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ። መዝገቡ ተዘግቷል ይመለስ። ይፃፍ።