No summary available.
ሀምላ 19 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሀኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት መስከረም 2ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስላቀረቡ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ከሳሽ አመልካቾች ተከሳሾች በመሆን ተከራክረዋል።
የክርክሩን መነሻ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት በከሣሽነት ቀርበው ያለ ፍላጏቴ በተንኮልና በማስገደድ ለአንደኛ አመልካች/አንደኛ ተከሳሽ/ ሚያዝያ 18 ቀን 1999 ዓ.ም የስጦታ ውል እንድፈፅም ያደረገችኝ በመሆኑ የስጦታ ውለ እንዱፈርስና አንደኛ ተከሳሽ/ አመልካች/ ምንም አይነት ግንባታ እንዲታከናውን ይወሰንልኝ በማለት ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካችና በሥር በተከሳሽነት ቀርበው አመልካች ወደውና ፈቅደው በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት ቀርበው ባደረጉት የሥጦታ ውል መሰረት አንደኛ አመልካች ቤት ገንብተው እየኖሩበት የሚገኙ መሆኑን ገልፀው የተጠሪ ጥያቄ ውድቅ እንዱደረግላቸው ተከራክረዋል። የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪ በኩል ያቀረቡት ምስክሮች ሁለተኛው አመልካች ተጠሪ ለአንደኛ አመልካች የስጦታ ውል እንዱፈርሙላት ብቻና ማስፈራራት ይፈፅሙ ነበር ስጦታው ከመደረጉ በፉት ሁለተኛ አመልካችና ተጠሪ ስጦታው መደረግ አለበት የለበትም በሚል ምክንያት ይጨቃጨቁ ነበር በማለት የመሰከሩ መሆኑን መዝግቦ በተጠሪ ሚያዝያ 18 ቀን 1999 ዓ.ም የተደረገው የስጦታ ውል በማሣሣትና በተንኮል የተደረገና ስህተት ያለበት ስለሆነ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2442/3/ መሰረት የስጦታ ውለ ፈርሷል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኙን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
መስከረም 2ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ አመልካቾች አንደኛ አመልካች ብር 6ዐዐ.ዐዐዐ /ስድስት መቶ ሺ ብር/ ያላነሰ ወጭ በማውጣት ተጠሪ ከሁለተኛው አመልካች ጋር በመሆን ከነበራቸው ሰፉ ግቢ ከፊፍለው 261 ካ.ሜ ቦታ ላይ የነበረ ጅምር ቤት በውልና ማስረጃ ጽ/ቤት ቀርበው በሰጧቸው ላይ ትልቅ ቤት ገንብተዋል። ተጠሪ የስጦታ ውለን በፈረሙበት ጊዜ መገደድም ሆነ ማታለል ያልተደረገባቸው መሆኑን የተጠሪ ምስክሮች ለፍርድ ቤት አስረድተው እያለ፣ ከህጉ ጋር ምንም ግንኙነት የላለው ሁኔታ የስጦታ ውለ እንዱፈርስ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩላቸው የስጦታ ውለን ሲፈርሙ ተጠሪ በሁለተኛ አመልካች ስለመገደዲቸው የንስሀ አባታቸው መሥክረዋል። የሁለተኛው አመልካች አድራጎት ባልና ሚስት የጋራ ሀብታቸውን በማስተዲደር በኩል እኩል መብት ያላቸው መሆኑን የሚደነግገውን ድንጋጌ የሚቃረን በመሆኑ፣ የስጦታ ውለ እንዱፈርስ የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት ሰፉ ክርክር አቅርቧል። አመልካቾች በቃል ክርክር የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ ለአንደኛ አመልካች ያደረጉት የጅምር ቤት ስጦታ ውል ይፈርሣል በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጭብጥ በዝርዝር መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ የተያዘውን ጭብጥ ለመወሰን ተጠሪ የህጉን መስፈርት የሚያሟላ የውል ማፍረሻ ምክንያት ያላቸው መሆኑን የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነታቸውን ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም የሚለውን ነጥብ አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
የሥር ፍርድ ቤት ተጠሪ ለአንደኛ አመልካች ያደረጉት የስጦታ ውል እንዱፈርስ የወሰነው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2442 ንዐስ አንቀጽ 3 ድንጋጌ በመጥቀስ ነው። በእርግጥ የፍትሐብሕር ሕግ ድንጋጌዎች የቀጥታ ንባብ የስጦታ ሰጭው ወራሾች ሰጭው በህይወት ሣለ ስጦታው እንዱፈርስ ያቀረበውን ክስ ለመቀጠል ስለሚችለበት ሁኔታ የሚደነግግ ድንጋጌ ነው። ሆኖም የድንጋጌውን መሰረታዊ ግብ እና አላማ መሰረት በማድረግ ስናገናዝበው ስጦታ ሰጭው በስህተት ወይም በተንኯል የተደረገ ስጦታ እንዱፈርስለት ክስ የማቅረብ መብት ያለው መሆኑን ያመለክታል። የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2442 ድንጋጌ በተያዘው ጉዲይ በቀጥታም ባይሆን በትርጉም ግንኙነት ያለው ቢሆንም የስጦታ ውል ለማፍረስ የሚያስችል " ስህተት" ምን አይነት ስህተት ነው; የስጦታ ውል በተንኮል ተደርጓል ተብል የሚፈርሰው ምን ሁኔታዎችን ሲሟላ ነው; የሚለትን መሰረታዊ ሁኔታዎች የሚደነግግ ባለመሆኑ እነዚህን ነጥቦች ለመረዲት ስለ ጠቅላላ ውል የተደነገጉትን ድንጋጌዎች ማገናዘብ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አንድ ውል በመዋዋል የደረሰው ስህተት የውል ማፍረሻ የሚሆነው ተዋዋዬቹ አስፈላጊ አቋም ነው ሲለ በሚቀበለበት አኳኋን ላይ የተደረገ ስህተት ሲሆንና ውለ ሲፈፀም በአኳኋኑ በቅን ልቦና አስፈላጊ አቋም በሚሆነው ላይ መሆኑ ሲገመት እንደሆነ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1698 ተደንግጓል። አንድ ውል በስህተት ምክንያት የሚፈርሰው በተለይ በውለ ዓይነት ላይ ስህተቱ የደረሰ እንደሆነ ወይም አንደኛው ተዋዋይ ወገን በሰጠው ቃል ስለመሣሣቱ የሚያቀርበው መከራከሪያ ከፍ ያለ አስረጅነት የሚያገኝ ሲሆን እንደሆነ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1699 ይደነግጋል። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ ሚያዝያ 18 ቀን 1999 ዓ.ም ለአንደኛ አመልካች በሰነድችና ውል ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርበው ያደረጉት ውል የስጦታ ውል መሆኑን ሣያውቁ በስህተት ያደረጉት ስለመሆኑ ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት በምስክርነት ቀርበው የሰጡት ቃል እንኳን አያረጋግጥም። ተጠሪ ለአንደኛ አመልካች የጅምር የቤት ስጦታ እንዱያደርጉ በተደጋጋሚ በሽማግላዎች ሁለተኛ አመልካች እንዲስጠየቋቸው የምስክርነት ቃል ሰጥተዋል። ስለዚህ ተጠሪ የስጦታ ውል ያደረጉ መሆኑን አውቀውና ተገንዝበው ያደረጉትና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1698 እና በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1699 ድንጋጌዎች በተደነገገው መሰረት ውለን ለማፍረስ የሚያስችል ስህተት የፈፀሙ መሆኑን በማስረጃ የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነታቸውን ያልተወጡ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት መዝገብ በማስቀረብ ተጠሪና ላልች ምስክሮች የሰጡትን የምስክርነት ቃል በመመርመር ለመገንዘብ ችለናል። ስለሆነም ተጠሪ ውል በማዋዋል ሥልጣን ባለው አካል ፉት ቀርበው የሚያደርጉትን የስጦታ ውል መሆኑንና ስጦታ ተቀባይ አንደኛ አመልካች መሆናቸውን ሙለ ግንዛቤ ይዘውና በስጦታ የሚሰጡት ጅምር የመኖሪያ ቤት መሆኑን ተረድተው ያደረጉት የስጦታ ውል ለማፍረስ የሚያስችል መሰረታዊ የሆነ ስህተት የፈፀሙ መሆኑን በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1698 እና በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1699 መሰረት ሣያስረደ የበታች ፍርድ ቤቶች የስጦታ ውለ የተፈፀመው በስህተት ስለሆነ ፈራሽ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ የህግ መሰረት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
አንድ ውል በተንኮል የተደረገ ውል ነው በሚል ምክንያት ፈራሽ የሚሆነው ከተዋዋዬቹ አንደኛው ወገን ውለ እንዱያደርግ ያደረገው በሁለተኛው ተዋዋይ ላይ ተንኮል ባይደርስበት ኖሮ ውል የማያደርግ የነበረ መሆኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 17ዐ4 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ የስጦታ ውል ከአንደኛ አመልካች ጋር እንዱያደርጉ በሽማግላ የተጠየቁ መሆኑን ገልፀዋል። ከዚህ አንፃር ተጠሪን ለማስፈረም እውነታውን የመደበቅ ወይም ተጠሪ ዕውነታውን እንዲይረደ የሚያደርጉ የተንኮል ተግባራት በአንደኛ አመልካች በኩል ስለ መፈፀሙ ተጠሪ ለሥር ፍርድ ቤት አቅርበው ያሰሟቸው ምስክሮችም ሆኑ ተጠሪ የሰጡት የምስክርነት ቃል አላስረደም። ተጠሪ በአንደኛ አመልካች በፈፀሙት የተንኮል ተግባር ምክንያት በሰነድችና ውል ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርበው የስጦታ ውል የፈረሙ ስለመሆኑ የማስረጃነት በማስረዲት የማስረዲት ሸክማቸውን ባልተወጡበት ሁኔታ የበታች ፍርድ ቤት የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2442 ንዐስ አንቀጽ 3”ን” በመጥቀስ ውለ በተንኮል የተደረገ ስለሆነ ፈራሽ ነው በማለት የሰጡት ውሣኔ የስጦታ ውል እንዱፈርስላቸው የጠየቁት ተጠሪ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 17ዐ4 ድንጋጌ መሰረት በተንኮል ውል የተዋዋለ ስለመሆኑ ያቀረቡት ማስረጃ የላለ መሆኑን ያላገናዘበና መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤትና በሰበር የሚከራከሩት የስጦታ ውለን የፈረምኩት ባለቤቴ /ሁለተኛው አመልካች/ በፈፀመብኝ ዛቻና ማስፈራራት ምክንያት ነው በማለት ነው። ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ቀርበው የሰጡት ውለን በሰነድችና ውል ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርበው የፈረሙት ሁለተኛ አመልካች የስጦታ ውለን ካልፈረምሽ ከዚህ ቤት መኖር አትችይም እያለ ስለአስፈራራኝና ስለዛተብኝ ነው በማለት የምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል። ተጠሪ ውለን እንዱፈርም የማስገደድና የማስፈራራትና የዛቻ ተግባራትን ተፈፅሞብኛል የሚለት በስጦታ ተቀባይዋ አንደኛ አመልካች ሳይሆን ከተጠሪ ጋር በስጦታ ሰጪነት ያፈረሙት በሁለተኛ አመልካች ነው።
ሁለተኛ አመልካች የስጦታ ውለ ተጠቃሚና ስጦታ ተቀባይ ባይሆኑም ተጠሪ የስጦታ ውለን እንዱፈፅሙ የማስገደድ ተግባር መፈፀማቸው ከተረጋገጠ የውለ ማፍረሻ ምክንያት ላሆን እንደሚችል በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 17ዐ7 ንዐስ አንቀጽ 1 ተደንግጓል።
ስለሆነም በውለ በስጦታ ሰጪነት ከተጠሪ ጋር ፈራሚ የነበሩት ሁለተኛ አመልካች ተጠሪ ውለን እንዱፈርሙ የማስገደድ ተግባር ፈፅመዋል ወይስ ወይም አልፈፀሙም? የሚለው ነጥብ ከፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 17ዐ6 ድንጋጌዎች አንፃር መመዘን ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል። አንድ ውል በሀይል ሥራ ወይም በመገደድ የተፈፀመ ነው ተብል የሚፈርሰው፤ ተዋዋዩን ራሱን ወይም ወላጆቹን ወይም ተወላጆቹን ወይም ባልን ወይም ሚስትን ከባድና የማይቀር አደጋ በህይወቱ፣ በአካለ፣ በክብሩ ወይም በንብረቱ እንደሚመጣበት ያሳመነው ሲሆንና ተዋዋዩን ሥጋት ላይ የጣለው ሆኖ ሲገኝ እንደሆነ ከፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 17ዐ6 ንዐስ አንቀጽ 1 እና ንዐስ አንቀፅ 2 ድንጋጌዎች ለመገንዘብ ይችላል።
በህጉ መስፈርት በተዋዋዩ ላይ የሚደርሰው አደጋ ከባድ የማይቀር ነው የሚል እምነት የሚያሣድርና ለስጋት የሚዲርግ መሆኑን የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነት ውለ በመገደድ የፈፀምኩት ስለሆነ ሉፈርስልኝ ይገባል በማለት የሚጠይቀው ወገን ነው። በያዝነው ጉዲይ ተጠሪ የስጦታ ውለን የፈረምኩት ሁለተኛ አመልካች ውለን ካልፈረምሽ እዚህ ቤት እትኖሪም በማለት ስላስፈራራንና ስለዛተብኝ ነው የሚል ምስክርነት ቃል የሰጡ ሲሆን ላልችም ምስክሮች ተጠሪ ሁለተኛ አመልካችና ፈፅመውብኛል እያለ የነገሯቸው መሆኑን የሚመሰከሩ ናቸው። ሆኖም ዝቅተኛ አደጋ የሚያስከትል መድረሱን እርግጠኛ ያልሆነ ዛቻና ማስፈራራት ተደርጎብኛል በሚል ውለ እንዱፈርስ መጠየቅ እንደማይቻልና የሀይል ተግባሩ በህይወቱ ወይም በአካለ ወይም በንብረቱ ላይ ከባድና የማይቀር አደጋ እንደሚደርስበት የሚያሣምን መሆን እንዲለበት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 17ዐ6 የተደነገገ በመሆኑ ተጠሪ በሰነድችና ውል ምዝገባ ጽ/ቤት በመቅረብ ለአንደኛ አመልካች የስጦታ ውል ያደረግሁት ሁለተኛው አመልካች ውለን ካልፈረምሽ እዚች ቤት አትኖሪያትም ብል ስለዛተብኝና ስላስፈራራኝ ነው በማለት የስጦታ ውለ እንዱፈርስ ተጠሪ ያቀረቡት ጥያቄ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 17ዐ7 ንዐስ አንቀጽ 1 እና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 17ዐ6 ድንጋጌ መሰረት ያላደረገና ተቀባይነት የላለው ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም ተጠሪ ሚያዝያ 18 ቀን 1999 ዓ.ም በሰነድችና ውል ምዝገባ ጽ/ቤት ቀርበው በውል አዋዋይ ባለሥልጣን ፉት ፈርመው ለአንደኛ አመልካች የጅምር የመኖሪያ ቤት ስጦታ ውል ያደረጉት በፍትሐብሕር ህጉ ድንጋጌዎች መሰረት በመሣሣት፤ በተንኮል ወይም በመገደዲቸው መሆኑን የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነታቸውን አልተወጡም። ተጠሪ በውል አዋዋይ ፉት የተደረገ ውል ጉድለት ያለበትና የሚፈርስበት በቂ ህጋዊ ምክንያት ያለ መሆኑን በማስረጃ ሣያስረደና ሣያረጋግጡ የበታች ፍርድ ቤቶች አንድ ውል በስህተት የተደረገ ነው፤ በተንኮል የተፈፀመ ወይም በመገደድ የተፈፀመ ነው ተብል የሚፈርሰውም ምን ምን ሁኔታዎች ተሟልተው ሲገኙ አንደሆነ ከላይ በዘረዘርናቸው የፍትሐብሕር ህግ ድንጋጌዎች የተቀመጠውን መሥፈርት ሣያገናዝቡ የስጦታ ውል በስህተትና በተንኮል የተፈፀመ ስለሆነ እንዱፈርስ በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ው ሣ ኔ የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤትና የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
ተጠሪ እና ሁለተኛ አመልካች ለአንደኛ አመልካች ሚያዝያ 18 ቀን 1999 ዓ.ም ያደረጉት ጅምር የመኖሪያ ቤት ስጦታ ውል ህጋዊ አስገዲጅነትና ተፈፃሚነት ያለው ውል ነው ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት አመልካቾችና ተጠሪ ያወጡትን ውጭ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.