No summary available.
ሐምል 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የአቶ ደሳለው ፊንታ ወራሾች - እነ ሙለጌታ ደሳለው ጠበቃ ግሩም አየለ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ አየለ ደበላ - ጠበቃ ኤሉያስ ተ/ብርሃን ቀረቡ መዝገቡን መረምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ በእቁብ ገንዘብ የመክፈያ ጊዜ ጋር በተያያዘ እዲው እንደተከፈለ ሉቆጠር የሚችልበትን የሕግ አግባብና ትርጉም የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ የካቲት 08 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈት አቤቱታ የአሁኑ አመልካቾች አውራሽ በተጠሪ የሚሰበሰበው እቁብ በአባልነት ተመዝግበው ዋስ ቆጥረው ብር 650,000.00(ስድስት መቶ ሃምሳ ሺህ) መውሰዲቸውን፣ተከሳሽ በተመዘገቡበት እጣ እቁብ ከተጀመረበት ከሕዲር 03 ቀን 1992 ዓ.ም ድረስ እስከ ጥቅምት 02 ቀን 1995 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 28 ክፍያዎችን ከከፈለ በኋላ ኀዲር 7 ቀን 1995 ዓ.ም ጀምሮ እስከ እቁቡ ማለቂያ እለት ድረስ መክፈል የሚገባቸውን 29 ክፍያዎችን ሳይከፍለ መቅረታቸው በመግለጽ ተከሳሽ ከእቁቡ የሚደርሳቸውን ገንዘብ ከወሰደ በኋላ መክፈል ሲገባቸው ያልከፈለትንና ባለመክፈላቸው በእቁቡ ስምምነት መሰረት ሉከፈል የሚገደደበትን በቀን የሚታሰብ ተጭማሪ ክፍያ በድምር የሆነውን ብር 342,600.00 (ሦስት መቶ አርባ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ) ከወጪና ኪሳራ ጋር እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። አመልካቾች ቀርበው በሰጡት መከላከያ መልስ የተጠሪ ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024/ረ/ ስር በተመለከተው የክፍያ ግምት መሰረት ውድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከተመለከተ በኋላ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024/ረ/ ድንጋጌን በዋቢነት በመጥቀስ የከሳሽን ክስ ውድቅ አድርጓአል። ከዚህም በኋላ ተጠሪ ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ ለእቁብ ገንዘብ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024/ረ/ አግባብነት የላለው መሆኑን በመግለጽ የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ሽሮ ጉዲዩን ለስር ፍ/ቤት መልሶለታል።
ጉዲዩ ላይ በተሰጠው ውሳኔ ያሁኑ አመልካቾች ቅር በመሰኘት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ጠቅላይ ፍ/ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ግንቦት 14 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝርው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- የይግባኝ ሰሚው ፍርድ ቤቶች የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024/ረ/”ን” ተደርጏ የቀረበውን ክርክር ውድቅ ማድረጋቸው ያላግባብ መሆኑን፣ድንጋጌው ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1677/1/ ድንጋጌ አንፃር ሲታይ ለእቁብ ገንዘብ አግባብነት ያለው መሆኑን በመዘርዘር ውሳኔው እንዱሻር ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጏላቸው ቀርበው ጥር 25 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- የፍ/ብ/ህ/ቁ. 2024/ረ/ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው መሆኑን፣የአመልካቾች አውራሽ የእቁብ ገንዘቡን ያልተከፈለ በመሆኑ ክርክራቸው ተቀባይነት የላለው መሆኑን ገልፀው በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ ሉፀና ይገባል በማለት የተከራከሩ ስለመሆኑ የሚያሣይ ነው። የአመልካቾች ጠበቃ የካቲት 22 ቀን 2002 ዓ.ም በፃፈት ሦስት ገጽ የሰበር ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም በግራ ቀኙ የቀረበውን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ተብል ከተያዘው ጭብጥ አኳያ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በተጠሪ እና በአመልካቾች አውራሽ መካከል ያለው ግንኙነት የእቁብ ገንዘብን የሚመለከት መሆኑን፣የአመልካቾች አውራሽ ተጠሪ በሚሰበስቡት እቁብ ውስጥ አባል ሆነው እጣው ደርሷቸው ገንዘቡን በመውሰድ 28 እጣዎችን ከከፈለ በኋላ 29 እጣዎች ሲቀሩ መክፈላቸውን ማቋረጣቸውን ገልጸው ተጠሪ ክስ መመስረታቸውን፣የእቁቡን ገንዘብ የሚከፈልበት ጊዜም የተቆረጠ መሆኑን ነው። በዚህ ችልት አመልካቾች አጥብቀው የሚከራከሩት የይግባኝ ሰሚ ፍ/ቤቶች የእቁብ እዲው ክፍያ ጥያቄ በሁለት አመት ጊዜ ማለፍ እንደተከፈለ ሉቆጠር ይገባል ማለት ያቀረብነውን ክርክር ያለፈው ያላግባብ ነው በሚል ነው።
ዋናውና የሕግ ትርጉም የሚያስፈልገው ጉዲይ፡- የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024/ረ/ ድንጋጌ ለእቁብ ገንዘብ እግባብነት አለው ወይስ የለውም? የሚለው ነው። ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይቻል ዘንድ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024/ረ/ ድንጋጌን በሚገባ መረዲት ያስፈልጋል።
የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 በጠቅላላው ሲታይ በሕግ የሕሉና ግምት የሚሸፈን የፍሬ ነገር ነጥብን (legal presumptions) የሚመለከት ሲሆን ዓይነቱም ከፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2025 እና 2026 ድንጋጌዎች ጋር ተዛምድ ሲታይ ውስን የሆነ የማስተባበያ ማስረጃ የሚቀርብበት (not freely rebuttable or rebuttable but in limited way) የሕግ የሕሉና ግምት ነው። የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር የተለያዩ የክፍያ አይነቶች የሚዘረዝር ሆኖ 2024 በጠቅላላው ሲታይ ግን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሉከፈለ የሚገቡ ክፍያዎች(እዲዎች) በዚሁ የሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሳይጠየቁ የቀሩ እንደሆኑ ክፍያውን (እዲዎች) የመክፈል ኃላፉነት ያለበት ወገን የተባለውን ክፍያ (እዲ) እንደከፈለ የሕግ ግምት እንደሚወስድበት ያስገነዝባል። ድንጋጌው እቁብን ለይቶ አላስቀመጠም።
ለተያዘው ጉዲይ ቀጥተኛ አግባብነትና ተፈፃሚነት ያለው ድንጋጌ ተብል በአመልካቾች የሚጠቀሰውን በስር ፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ተቀባይነት ያገኘው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024 ድንጋጌ በፉደል/ረ/ ስር የተመለከተው ሲሆን ሙለ ይዘቱም በሚከተለው መልኩ የተቀመጠው ነው።
ቁ. 2024 በሁለት አመት የተወሰነ ጊዜ እዲው እንዱከፈል መጠየቅ ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈል የቀረ ገንዘብ እንደተከፈለ የሚቆጠረው፡- /ረ/ በብድር ለተሰጠ፤ የገንዘብ ወለድና በጠቅላላውም የዓመት ጊዜ ተወስኖለት በየዓመቱ ወይም ከዚህ ባነሰ የጊዜ ውሳኔ ውስጥ ሉከፈል የሚገባው እዲ የሆነ እንደሆነ ነው። የዚሁ ድንጋጌ የእንግሉዝኛው ቅጂም፡- Art.2024 presumption of payment after two years The following debts shall be deemed to have been paid where two years have elapsed since they fell due: (f) interest on loans and generally any sum payable annually or at shorter periodical interval.
በሚል ተቀምጧል። ከላይ ከተጠቀሰው ድንጋጌ ይዘትና እና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው የድንጋጌው መጀመሪያ ፓራግራፍ የመክፈያ ጊዜያቸው ከደረሰ ጊዜ አንስቶ ሁለት አመት ያለፊቸው እዲዎች(ክፍያዎች) እንደተከፈለ ይቆጠራለ የሚል ሲሆን በተከታይ የተዘረዘሩት ንኡስ ድንጋጌዎች ደግሞ የሚወሰንባቸውን የክፍያ (እዲ) ዓይነቶችን የሚዘረዘር ነው። በድንጋጌው ፉደል/ረ/ ስር የተመለከተው ሲታይ በብድር የተሰጠ ወይም ለማናቸውም የአከፊፈል ሁኔታ በየአመቱ ወይም ከአመት ባነሰ ጊዜ እየተከፈለ እንዱያልቅ ጊዜ ተቆርጦለት የተሰጠ ገንዘብ ላይ የሚታሰብ ወለድ እዲው ከበሰለበት ወይም በየተወሰነ ጊዜ የሚከፈል ገንዘብ ከሆነ ደግሞ ገንዘቡ ተከፍል ማለቅ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት ያለፈ እንደሆነ በእነዚህ ክፍያዎች (እዲዎች) ላይ ሉጠየቅ የሚችለው የወለድ ክፍያ እንደተከፈለ የሕግ ግምት የሚወሰድ መሆኑን ያሳያል። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024/ረ/ ስር የተመለከተው ድንጋጌው ተፈፃሚነት የሚኖረው በብድር ለተሰጠ ገንዘብ ወለድ ላይ ሲሆን ዋናውን የብድር ገንዘብ የማይጨምር መሆኑን የድንጋጌው ይዘትና አቀራረጽ ያስገነዝባል። ምክንያቱም ድንጋጌው ዋናውን የብድር ገንዘብ የሚጨምር ቢሆን ኖሮ የብድር ገንዘብንና ወለድ በማለት ያስቀምጠው ነበር እንጂ ለብቻው ነጥል የብድር ገንዘብ ወለድን በማለት አይጽፈውም ነበር። ይህ ስለመሆኑም ይህ ችልት በ
እና
በአዋጅ ቁጥር 454/97 አንቀጽ 2/1/ መሰረት በየትኛውም እርከን የሚገኝ ፍርድ ቤት የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል።
ወደተያዘው ጉዲይ ስንመለስም እቁብ ከመሰረቱ ብድር አይደለም፤የብድር ባህርይም የለውም። እቁብ ሰዎች ባላቸው አቅም መሰረት ገንዘብ ለማጠራቀም የሚጠቀሙበት ማህበራዊ እሴት ነው። እቁብ ዋናው ዓላማ አባላቱ የቁጠባ ባህል እዱኖራቸው የሚያደርግ ነው። በመሆኑም የእቁብ አባል ለላላው አባል እንደ ተበዲሪ ወይም አንደ ለላላው ከወዱሁ ባለገንዘብ ነው ልባል የሚችልበት የስምምነት አይነት አይደለም። ምናልባት አባለ እጣው ደርሶት ከተጠቀመ በኋላ ቀሪውን እጣ ካልከፈለ እንደማንኛውም ደንበኛ እቁቡን ካልከፈለው አባል ላይ ግዳታ የሚጥል ነው የሚል ክርክር ተቀባይነት ይኖረዋል። ይህም ጉዲይ ተቀባይነት የሚኖረው በጠቅላላው ሕጉ የተመለከቱትን ይርጋ ደንቦችን መሰረት አድርጏ ሲቀርብ ላሆን ይገባል። የአመልካቾች ጠበቃ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024/ረ/ ለጉዲዩ አግባብነት ይኖረዋል በማለት የሚራከሩት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1677/1/ ድንጋጌን በማጣቀስ ነው።
ይሁን እንጂ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የጠቅላላ ውል ድንጋጌዎች በአንድ ጉዲይ ተፈፃሚ እንዱሆኑ የሚደረገው ከጉዲዩ ተፈፃሚነት ያላቸው መሆኑ በቅድሚያ ሲረጋገጥ ነው። ስለሆነም ይህ ድንጋጌ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 ስር የተመለከቱት ጉዲዮች ተለይተው በተቀመጡበት ሁኔታ ለእቁብ ተፈፃሚ የሚሆንበት የሕግ አተረጓጏም ደንብ የለም። ሕጉም እቁብ የሚቋቋምበትን ዓላማ የመጠበቅ ሐሳብ ያለው ነው ተብል ይታሰባል። ሕግ ሲተረጏምም ሉፈፀም የሚችል ውጤት እንዱኖረው በማድረግ ስለመሆኑም ጠቅላላ የሕግ አተረጓጏም ደንቦች የግድ የሚለት ነው። በመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024/ረ/ ስር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈፃሚነቱ በብድር ለተሰጠ የገንዘብ ወለድ እንጂ ለዋናው የብድር ገንዘብ አለመሆኑን ከድንጋጌው ይዘትና አቀራረጽ የምንገነዘበው ነጥብ በመሆኑ ለእቁብ ገንዘብ ተፈፃሚ የሚሆንበትን አግባብ አላገኘንም። በዚህም ምክንያት የፋዳራለ ከፍተኛ ፍ/ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚው ችልት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024/ረ/ ለጉዲዩ አግባብነት የለውም በማለት መወሰናቸው ሕጋዊ እንጂ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የላለበት ሆኖ አግኝተናል፡ በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.