No summary available.
ሀምላ 12 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የባህርና ትራንዚት አገልግልት ድርጅት
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጠው ውሣኔ የህግ ትርጉም ስህተት ያለበት ስለሆነ ይታረምልኝ በማለት ጥር 12 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ስላመለከቱ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው። በከፍተኛው ፍርድ ቤት አመልካች በአጭር ሥርዓት እንዱታይለት ባቀረበው ማመልከቻ ከተጠሪ ጋር እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1978 ዓ.ም የትራንዚት አገልግልት የሰጠና የደንበኝነት ውል ያለው መሆኑን ገልፆ አመልካችና ተጠሪ ሂሳብ ተሣሥበው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 1978 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2004 በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1970 ዓ.ም እስከ ሰኔ 23 ቀን 1996 ዓ.ም አመልካች ለተጠሪ ለሰጠው አገልግልት ያልተከፈለ ብር 7,955,271.42(ሰባት ሚሉዮን ዘጠኝ መቶ ሃምሣ አምስት ሺ ሁለት መቶ ሰባ አንድ ብር ከአርባ ሁለት ሣንቲም) ያለ መሆኑን በማረጋገጥ ተጠሪ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 23-09-99 እና ግንቦት 28 ቀን 1999 ዓ.ም የተፃፈ ሰነድችን ፈርሟል። ስለዚህ ገንዘቡን እንዱከፍል በማለት ክስ አቅርቧል ተጠሪ በይርጋ ጊዜ ያለውን ዕዲ አመልካች በአጭር ሥርዓት ታይቶ እንዱወሰንለት የጠየቀ በመሆኑ መከላከያ እንዱያቀርብ ይፈቀድልኝ በማለት ጠይቋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት ተጠሪ ያቀረበው ብቁ መከላከያ አይደለም በማለት ውድቅ አድርጎ ተጠሪ አመልካች በክሱ የጠየቀውን ገንዘብ እንዱከፍለ በማለት ወስኗል።
ተጠሪ በከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት አቅርቧል። ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት አመልካች አስራስድስት ዓመት ካለፈ በኋላ የአገልግልት ክፍያ እንዱከፈለው የጠየቁ በመሆኑ ክሱ በይርጋ ይታገዲል በማለት ወስኗል። ተጠሪ አመልካች ለሰበር ባቀረበው አቤቱታ ይግባኝ ሰሚው ችልት ውሣኔ የሰጠው የህግ ትርጉም በተከራካሪ ያልቀረበና በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1846 ድንጋጌ ያላገናዘበ ነው። አመልካችና ተጠሪ የረዥም ጊዜ ደንበኞች ቢሆንም በየወቅቱ ሂሳባቸው እያጣሩ የሚዘጉ አልነበረም። ተጠሪ ለአመልካች የከፈለው የአገልግልት ዋጋና ያልከፈለው ሂሳብ ተጣርቶ የታወቀው እንደ ኤ.አ 23-9-99 በጋራ ሑሳቡን በማስታረቅ በተሰራው ሥራ ነው። አመልካች ክፍያውን ለመጠየቅ የሚችለው ሑሳቡ ተጣርቶ የሁለቱ ወገኖች ሂሳብ ለማስታረቅ ሥራ ከተሰራና ሑሳቡ ከተለየ በኋላ በመሆኑ ይግባኝ ሰሚው ችልት አገልግልት የተሰጠበትን ዓመት መነሻ በማድረግ ይርጋው አልፎል በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ከዚህ በተጨማሪ በይግባኝ ችልት አተረጓጎም የአስር ዓመት ይርጋ ያላለፈበትን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 23-9-89 እስከ 23-9-99 ያለውን ሑሳብ አላግባብ በይርጋ ይቋረጣል በማለት መወሰኑ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር እንዱታረምልን በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ በበኩለ የይርጋ ጊዜው መታሰብ ያለበት አመልካች አገልግልቱን ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ መሆን አለበት። አመልካች የትራንዚት ሥራውን ጨርሶ ንብረቱን ለተጠሪ ካስረከበበት ወይም በውለ በእሱ በኩል ያለውን ግዳታ ከተወጣበት ቀን ጀምሮ ሑሳቡን ከመጠየቅ የሚከለክለው ነገር የለም። የይርጋ መከራከሪያ ክሱን ለመከላከል ጠቃሚ ነጥብ መሆን አንስተን የከፍተኛ ፍርድ ቤትን ጠይቀናል ስለዚህ በተከራካሪዎች ያልተነሣ ነጥብ ይግባኝ ሰሚው በጭብጥነት በመያዝ የሰጠው ውሣኔ የለም። ስለዚህ የአመልካች ማስረጃዎች አመልካች ክፍያ የጠየቀው ክስ ካለፈ በኋላ መሆኑን የሚያስረደ በመሆኑ የሰበር አቤቱታው የህግ መሰረት የለውም በማለት መልስ ሰጥቷል። አመልካች በፅሐፍ የመልስ መልስ አቅርቧል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የአመልካች ክስ የይርጋ የጊዜ ገደብ ያለፈበት በመሆኑ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥ አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ መርምረናል።
ከላይ የተገለፀውን ጭብጥ ለመወሰን በመጀመሪያ የይርጋ የጊዜ ገደቡ መቆጠር ያለበት ከመቼ ጀምሮ ነው? የሚለውን ጥያቄ መመለስና በሁለተኛ ደረጃ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረበውን ክስ ሙለ በሙለ በይርጋ ቀሪ ነው ብል መወሰኑ ተገቢ መሆኑን መመርመር ያስፈልጋል።
No topics extracted.
አመልካችና ተጠሪ የሚከራከሩት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1846 ድንጋጌ የየራሳቸውን ትርጉም በመስጠት ነው። የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1846 “የይርጋው መነሻ ጊዜ” በሚል ርዕስ “የይርጋው ቀን መቆጠር የሚጀምረው ግዳታን ለመጠየቅ ተገቢ ከሆነው ወይም ውለ የሚሰጠው መብት ከሚሰራበት ቀን ጀምሮ ነው” በማለት ይደነግጋል። የዚህን ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ አመልካችና ተጠሪ ካላቸው ግንኙነት አንፃር ስንመለከተው አመልካች ተጠሪ ከውጭ አገር የሚያስገባቸውን ዕቃዎች አስፈላጊ የሆኑ የወደብና የጉምሩክ ፍርማሉቲዎች በማሟላት ዕቃውን ለተጠሪ እንዱረከብ የማድረግ ግዳታ ያለበት ስለመሆኑና ተጠሪ አመልካች ለሰጠው የትራንዚት ግልጋልት ዋጋ የመክፈል ግዳታ ያለበት ስለመሆኑ ግራቀኙ አልተካካደም። አመልካች አስፈላጊ የሆኑ የወደብ አስተዲደራዊ ፍርማሉቲዎችና የጉምሩክ ፍርማሉቲዎች በማሟላት አንድ ዕቃ ወደ አገር ውስጥ እንዱገባ በማድረግ ለሰጠው አገልግልት ወዱያውኑ ተጠሪ ክፍያ እንዱፈፅምለት የመጠየቅና ተጠሪ እንቢተኛ ቢሆን በፍርድ ከስሶ የአገልግልት ዋጋውን ከመቀበል የሚያግደው ነገር የለም። ተጠሪ ለአመልካች የትራንዚት የአገልግልት ዋጋ የሚከፍለው በየወቅቱ የነበራቸው ሑሳብ በጋራ ተሰርቶ የአመልካችና የተጠሪ ሑሳብ መስማሚያ ሰነድ ሲቀርብ ስለመሆኑ አመልካችና ተጠሪ የተስማሙበት ልዩ የውል ስምምነት ያላቸው ስለመሆኑ አመልካች ያቀረበው ማስረጃ የለም። በአመልካችና በተጠሪ መካከል የዚህ አይነት ግልፅ የውል ስምምነት ከላለ አመልካች የተጠሪን ዕቃ ለማስገባት አስፈላጊ የሆኑ የትራንዚት አገልግልት ሰጥቶ ዕቃው ወደ አገር ውስጥ ካስገባና ተጠሪ እንዱረከብ ካደረገበት ቀን ጀምሮ ክፍያ የመጠየቅ መብት አለው። ተጠሪ ለሰጠው አገልግልት ክፍያ የመጠየቅ መብቱን አገልግልቱን ከሰጠ በኋላ በሚቀጥለው ቀን እንዲይሰራበት የሚከለክለው ግልፅ የሆነ የውል ቃል ወይም የህግ ድንጋጌ የለም። ስለሆነም አመልካች ለተጠሪ ለሰጠው እያንዲንደ የትራንዚት አገልግልት አገልግልቱን ከሰጠበት ቀን ጀምሮ የአገልግልት ክፍያ ተጠሪ እንዱከፍል መጠየቅ የሚቻልና በመብቱ ሉሰራበት የሚቻል በመሆኑ አመልካች የአገልግልት ክፍያ ለመጠየቅ የሚችለው ሂሳቡ በጋራ ተሰርቶ ከታረቀበት ቀን ጀምሮ ነው ተብል የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1846 ይተርጎምልኝ በማለት ያቀረበው ክርክር የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1846 ድንጋጌ ይዘት፣ መንፈስና ዓላማ ያላገናዘበና የህግ ድጋፍ የላለው ነው። ስለሆነም የአስር ዓመቱ የይርጋ የጊዜ ገደብ መቆጠር ያለበት አመልካች ለተጠሪ የትራንዚት አገልግልቱን ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ መሆን ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጠው ውሣኔ በከፉል ትክክል ሲሆን በከፉል መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ስላገኘነው በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት በማሻሻል ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሻሽሎል።
አመልካች በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር ከ1970 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ህዲር 11 ቀን 1990 ዓ.ም ለሰጠው የትራንዚት አገልግልት ተጠሪ ክፍያ እንዱፈፅም በፍርድ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበው ክስ በአስር ዓመት የይርጋ ጊዜ ገደብ ይታገዲል ብለናል።
አመልካች በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከህዲር 12 ቀን 1990 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 23 ቀን 1996 ዓ.ም ለሰጠው የትራንዚት አገልግልት ተጠሪ ክፍያ እንዱፈፅም በፍርድ ይወሰንልኝ በማለት ያቀረበው ክስ በይርጋ ቀሪ አይሆንም ብለናል።
የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር አመልካች ከህዲር 12 ቀን 1990 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 23 ቀን 1996 ዓ.ም ለሰጠው የትራንዚት አገልግልት ተጠሪ ሉከፍለኝ ይገባል የሚለውን የአገልግልት ክፍያ ለይቶ እንዱያቀርብ በማድረግና የግራ ቀኙን ክርክር በመስማት ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341(1) መሰረት መልሰንለታል ይፃፍ።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።