No summary available.
ሰኔ 28 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ እታፈራሁ ኃ/ማርያም - የቀረበ የለም ተጠሪ፡-
ገዲዩ ተጠሪዎች የሸጡላቸው ቤት በሚገኝበት ቦታ ላይ ተጨማሪ ግንባታ ያከናወኑ ቢሆንም ተጠሪዎቹ ስም ስላላዛወሩላቸው ለቤቱ መግዣ የከፈለት ገንዘብ እንዱመለስላቸውና በተጨማሪ ለሰሩት ቤት ግምቱ እንዱከፈላቸው ጠይቀው ፍ/ቤቱ ተጠሪዎች የሽያጩን ገንዘብ እንዱከፍለ ሲወስን አመልካች ተጨማሪ ሰራሁ ያለትን ቤት ግምት ክፍያ ውድቅ በማድረግ በሰጠው ውሳኔ ላይ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
አመልካች ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ተጠሪዎች በድሬደዋ ከተማ ቀበላ 02 ክልል ውስጥ ካላቸው ይዞታ ላይ ቀንሰው ከሸጡላቸው እና ብር 29,000(ሃያ ዘጠኝ ሺህ) ከከፈሎቸው በኋላም ስመ-ርስቱን ለማዛወር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የወሰደትን ገንዘብ እንዱመልሱ በይዞታው ላይ ብር 80,000(ሰማኒያ ሺህ) የሚያወጣ ቪላ ቤት ስለሰሩ ይህንኑ ገንዘብ እንዱመልሱላቸውና በአደራ ያስቀመጡት እቃ ዋጋ እንዱከፍሎቸው ጠይቀዋል። ተጠሪዎች በበኩላቸው የሽያጭ ውል ማድረጋቸውን ሳይክደ ስመ-ርስቱን ለማዛወር ፈቀደኛ ስለሆኑ የሽያጩን ገንዘብ የሚመለሱበት ምክንያት የላለ መሆኑንና አመልካች በረቂቅ የሽያጭ ውለ ካልተስማሙ የሰሩትን ቤት አፍርሰው ከሚሄደ በቀር የቤቱን ግምት የሚከፍለበት ምክንያት የላለ መሆኑን በተጨማሪም በአደራ የተረከቡት ንብረት አለመኖሩን በመግለፅ ተከራክረዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የቤት ሽያጭ ውለ ህጉ በሚጠይቀው መሰረት በውል አዋዋይ ፉት ወይም በዲኛ ፉት ስላልተደረገ ረቂቅ ቢሆንም ይህንን መነሻ በማድረግ አመልካች ብር 29,000(ሃያ ዘጠኝ ሺህ) ለተጠሪዎች ስለከፈለ ተጠሪዎች ይህንኑ ገንዘብ እንዱከፍለ በቦታው ላይ አመልካች ሰራሁ የሚለትን ቤት ስለከፈለ ተጠሪዎች ይህንኑ ገንዘብ እንዱከፍለ በቦታው ላይ አመልካች ሰራሁ የሚለትን ቤት በተመለከተ ምንም እንኳን በቦታው ላይ አመልካች ቤት መስራታቸውን ተጠሪዎች ያልካደ ቢሆንም አመልካች የገለፁትን ያህል ገንዘብ ለማውጣታቸው ያቀረቡት ማስረጃ ስለላለ ጥያቄው ተቀባይነት የለውም አመልካች ለተጠሪዎች በአደራ የሰጡት ንብረት ስለመኖሩ በማስረጃ ስላላስረደ በዚህ ረገድ የቀረበው ክስም ተቀባይነት የለውም በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ቢያቀርቡም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቶባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው።
አመልካች በቅሬታቸው አመልካች በይዞታው ላይ ቤት ስለመስራታቸው ተጠሪዎች ስላመኑ ግንባታው በባለሙያ ተገምቶ እንዱቀርብ ማድረግ ወይም ቢያንስ ተጠሪዎች ያወጣል ያለትን ግምት እንኳን እንዱከፈል ማድረግ ሲችል መታለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው የሚል ነው። ችልቱም ተጠሪዎች አመልካች ለቤት መስሪያ ያወጣችውን የተወሰነውን እንከፍላለን እያለ የስር ፍ/ቤት ጥያቄውን ውድቅ የማድረጉን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ቀርበው የቃል ክርክራቸው ተሰምቷል። ተጠሪዎች አመልካች ቤት መስራታቸውን ሳይክደ በመጠኑ ላይ ተከራክረዋል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
የቀረበ የለም አመልካች በስር ፍ/ቤት ክስ የመሰረቱት ከተጠሪዎች ጋር ያደረጉት የቤት ሽያጭ ውል ሉፈፀም ባለመቻለ በሽያጩ ውል ምክንያት የከፈለት ገንዘብ እንዱሁም ቤቱን ገዝቸዋለሁ በሚል ሃሳብ በይዞታው ላይ የሰሩት ተጨማሪ ቤት ግምት እንዱከፈላቸው ነው። ተጠሪዎች ለክሱ በሰጡት መልስ በሽያጩ ውል መሰረት ለመፈፀም ፈቃደኛ በመሆናቸው ገንዘቡን ሉመልሱ እንደማይገባ ገልፀዋል። ምንም እንኳን አመልካች ክስ ሲመሰርቱ ውለ ይፍረስልን በሚል በግልፅ ያስቀመጡት ነገር ባይኖርም የክሱ ይዘት ሲታይ ውለ ፈርሶ ወደነበርንበት እንድመለስ የሚል ጥያቄ ያዘለ ነው። ተጠሪዎችም የሚከራከሩት በውለ መሰረት ለመፈፀም ፈቃደኛ በመሆናቸው ውለ ሉፈርስ አይገባም በማለት መሆኑን መረዲት ይቻላል። ለክርክር ምክንያት የሆነው የሽያጭ ውል ህጉ የሚጠይቀውን የአፃፃፍ ፍርምን የተከተለ አለመሆኑን ከመዝገቡ ተረድተናል። በህጉ የተመለከተውን የአፃፃፍ ፍርም አለመከተልም ውለን ለማፍረስ በቂ ምክንያት እንደሚሆን በፍ/ብ/ህ/ቁ 1808(2) መገንዘብ ይቻላል። ውለ መፍረሱ የሚያስከትለው ውጤትም ተዋዋዮቹን በተቻለ መጠን ውለታው ከመደረጉ በፉት ወደነበሩበት ሁኔታ መመለስ ነው። የስር ፍ/ቤት በውሳኔ ላይ አመልካች የውል ይፍረስልኝ ክስ አላቀረቡም በማለት ቢተችም ከፍ ሲል እንደተመለከተው የአመልካች ክስ ይዘት ይኸው ሲሆን ፍ/ቤቱም ቢሆን ውለ የህጉን መስፈርት ያላሟላ በመሆኑ ግራ ቀኙ ወደነበሩበት ሉመለሱ እንደሚገባ ተቀብሎል። በዚህም መሰረት ተጠሪዎች በሽያጩ ውል ምክንያት የወሰደትን ገንዘብ እንዱመልሱ ወስኗል። ነገር ግን በተያዘው ጉዲይ ግራ ቀኙ ወደነበሩበት የሚመለሱት ተጠሪዎች የሽያጩን ገንዘብ እንዱከፍለና አመልካች ቤቱን እንዱያስረክቡ በማድረግ ብቻ አይደለም። አመልካች ተጨማሪ ቤት ሰርቻለሁ በማለት የሚከራከሩ ሲሆን ተጠሪዎችም አመልካች ቤት መስራታቸውን አልካደም።
No topics extracted.
ክርክራቸው ሉከፍለ በሚገባቸው የቤት ግምት መጠን ላይ ነው። ተጠሪዎች ፍ/ብ/ህ/ቁ 1179 እና 1180 መሰረት አመልካች በይዞታው ላይ ለገነቡት ቤት ሉከፍለ የሚገባው የቤቱን ግምት ¼ ነው በማለት ተከራክረዋል። እነዚህ የህጉ ድንጋጌዎች ባለይዞታ ሳይቃወም በይዞታው ላይ የተሰራውን ግንባታ ለማስለቀቅ ስለሚችልበት ሁኔታ የሚናገሩ ናቸው። አመልካች ግን ግንባታውን የሰሩት በዚህ አይነት ሁኔታ ሳይሆን በግራ ቀኙ በተደረገው የሽያጭ ውል መሰረት ቤቱን ገዝቻለሁ፣ የቤቱ ባለቤት ሆኛለሁ በሚል እምነት ነው። ምንም እንኳን ውለ በህግ የተደነገገውን የአፃፃፍ ስርዓት ባለመከተለ ፈራሽ ቢሆንም ውለ በመፍረሱ ወይም በመሰረዙ ምክንያት ንብረት የመመለስ ግዳታ ያለበት ሰው ንብረቱን ለውጦ ወይም በዚሁ ላይ ወጪ አውጥቶ ከሆነ ባወጣው ወጪ መጠን ሉጠይቅ እንደሚገባ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1818 ያመለክታል። ስለሆነም አመልካች ቤቱን እንዱለቁ ሲደረግ ተጠሪዎች ሉከፍለ የሚገባው አመልካች በይዞታው ላይ የሰሩት ቤት የሚያወጣውን ዋጋ በሙለ እንጂ በፍ/ብ/ህ/ቁ 1179 እና 1180 መሰረት አይደለም። ተጠሪዎች በዚህ የሰበር ችልት አመልካች ቤቱን ያለ ግንባታ ፈቃድ የሰሩት በመሆኑ የቤቱን ግምት ልንከፍል አይገባም በማለት የተከራከሩ ቢሆንም ይህ ክርክር በስር ፍ/ቤት ያልተነሳ አዱስ ክርክር በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። በልላ በኩል የስር ፍ/ቤት አመልካች ቤት ለመስራታቸው በተጠሪዎችም መታመኑን ተቀብሎል። የአመልካችን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው ቤቱን ለመስራት ብር 80,000(ሰማኒያ ሺህ) ለመውጣቱ አመልካች ማስረጃ አላቀረቡም። ነገር ግን ቤት መስራቱ እስካልተካደ ድረስ የቤቱን ዋጋ ግምት ለማወቅ ምትክ ዲኛ ሉሾም የሚችል መሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 132 ስር ተመልክቷል። በመሆኑም ፍ/ቤት ግምቱ በባለሙያ ተገምቶ እንዱቀርብ ማድረግ ሲችል አመልካች አላስረደም በሚል ብቻ ማለፈ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።