No summary available.
ግንቦት 19 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲቲዩት - የቀረበ የለም ተጠሪ፡- አቶ ተፈሪ ማሞ - በላለበት
ተጠሪ የአመልካች ድርጅት ሰራተኛ የነበሩ ሲሆን የኤም.ኤስ.ሲ ትምህርት እንዱከታተለ ከአመልካች ጋር ባደረጉት ውል አመልካች በትምህርት በሚቆዩበት ጊዜ ደመወዝ፣ የት/ቤት ክፍያ፣ ለምርምር ማካሄጃ የሚፈልጉትን ሉከፍልና ተጠሪ ደግሞ በትምህርት ለቆዩባቸው እያንዲንደ ወር የሁለት ወራት አገልግልት ለመስጠት ግዳታ ገብተው ትምህርቱን ከተማሩ በኋላ በግዳታቸው መሰረት ግልጋልት ስላልሰጡ በውለ መሰረት እንዱፈፅሙ ወይም አመልካች ያወጣውን ወጪ ብር 326,092.57 ከነወለደ እንዱከፍለ በማለት አመልካች ክስ አቅርቧል። ተጠሪ ለክሱ መልስ እንዱሰጡ ተጠርተው ስላልቀረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል። ጉዲዩ የቀረበለት የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤትም አመልካችና ተጠሪ መጋቢት 19 ቀን 1994 ዓ.ም ባደረጉት ውል አመልካች ለ24 ወራት ደሞዝ እየከፈለ ተጠሪን ለማስተማርና ተጠሪ ትምህርታቸውን አጠናቀው ሲመለሱ በአመልካች መ/ቤት ለመስራት ግዳታ መግባታቸውን ካረጋገጠ በኋላ ተጠሪ በውለ መሰረት እንዱፈፅሙ ማድረጉ የግል ነፃነታቸውን የሚጋፊ በመሆኑ፣ ግራ ቀኙ ባደረጉት ውል ላይ ተጠሪ ግዳታቸውን ባይፈፅሙ አመልካች ያወጣውን ገንዘብ ለመመለስ ግዳታ ስላልገቡና አመልካችም ውል እንዱፈርስ ስላልጠየቁ ገንዘቡን እንዱከፍለ የቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጓል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው የነበረ ቢሆንም ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሰርዞታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታው፤ ተጠሪ ወደውና ፈቅደው የፈረሙት ውል የግል ነፃነታቸውን ይነካል የሚል እምነት የለንም፣ በውለ መሰረት ቢፈፅሙ የግል ነፃነታቸውን ይነካል የሚባል ቢሆን እንኳን ውለ በአመልካች በኩል ተፈፅሞ ያበቃ በመሆኑና ተጠሪ ግዳታቸውን ስላልተወጡ ውለ የሚፈርስበት ሁኔታ አይኖርም፣ ውለን መፈፀም ግዳታቸውን የሚነካ ከሆነ ግዳታቸውን በአይነት ወይም በገንዘብ የመመለስ የውልም ሆነ የህግ ግዳታ አለባቸው በማለት የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ እንዱሻር ጠይቋል። ይህ ችልትም አመልካች ለተጠሪ ትምህርት ያወጣቸው ወጪዎች ሳይከፈል የመታለፈን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪ እንዱቀርቡ ተጠርተው ስላልቀረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ተደርጓል። ችልቱም መዝገቡን ከተያዘው ጭብጥ አኳያ መርምሯል።
አመልካች ክስ የመሰረተው ከተጠሪ ጋር ባደረጉት ውል መሰረት አመልካች ግዳታውን ከፈፀመ በኋላ ተጠሪ ግዳታቸውን ባለመወጣታቸው በውለ መሰረት እንዱፈፅሙ ካልሆነ የከፈላቸውን ደሞዝና የትምህርት ቤት ወጪዎች እንዱተኩለት ነው። ተጠሪ አልፈፀሙም የተባለው ትምህርታቸውን ሲጨርሱ ተመልሰው በአመልካች መ/ቤት ግልጋልት የመስጠት ግዳታቸውን ነው። ከፍ ሲል እንደተመለከተው አመልካች አንደኛው የዲኝነት ጥያቄ ተጠሪ በውለ በገቡት ግዳታ መሰረት በመ/ቤቱ ውስጥ አገልግልት እንዱሰጡ ነው። ነገር ግን የስር ፍ/ቤት እንዲለው ተጠሪ በግድ አገልግልት እንዱሰጡ ማድረጉ የግል ነፃነታቸውን የሚነካ በመሆኑና እንዱህ ባለ ጊዜ ደግሞ ውለ በግድ እንዱፈፀም ማድረግ የተከለከለ በመሆኑ (የፍ/ብ/ህ/ቁ 1776 ይመለከቷል) ውለ በግድ እንዱፈፀም የቀረበው የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ ተቀባይነት የለውም።
በአማራጭ የቀረበው የዲኝነት ጥያቄ ስንመለከት ተጠሪ በውለ መሰረት ለመፈፀም ካልፈቀደ ተጠሪ በትምህርት ላይ በቆዩበት ወቅት አመልካች ለተጠሪ የከፈለው ደሞዝና የትምህርት ቤት ወጪዎች እንዱተካለት የሚጠይቅ ነው። የስር ፍ/ቤት ይህን ጥያቄ ውድቅ ያደረገው በግራ ቀኙ በተደረገው ውል ተጠሪ ግልጋልት ባይሰጡ አመልካች ያወጣውን ወጪ ለመተካት ግልፅ ግዳታ አልገቡም በማለት ነው። ግራ ቀኙ ካደረጉት ውል አመልካች ተጠሪ በትምህርት በሚቆዩበት ጊዜ ደሞዛቸውንና ላልች ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች ለመሸፈን ተጠሪ ደግሞ ትምህርታቸውን ጨርሰው ሲመለሱ አመልካች ድርጅት ውስጥ ለማገልገል ግዳታ መግባታቸውን የስር ፍ/ቤት አረጋግጧል። ተጠሪ ትምህርታቸውን ተምረው የጨረሱ በመሆኑ አመልካች ግዳታውን ፈፅሟል። ተጠሪ ግን በእርሳቸው በኩል የሚፈለገውን ግዳታ አልፈፀሙም። ተዋዋይ ወገን የውለን ግዳታ ያልፈፀመ ከሆነ ላላው ወገን ውለ ባለመፈፀሙ ምክንያት የደረሰበት ጉዲት ካለ የጉዲት ኪሳራ እንዱከፈለው ለመጠየቅ እንደሚችል ከፍ/ብ/ህ/ቁ 1771(2) እና 1790(1) መረዲት ይቻላል። ይህን ነጥብ በተመለከተ ይህ የሰበር ችልት በመ/ እና በላልችም መዝገቦች ላይ የህግ ትርጉም ሰጥቶበታል። በመሆኑም አመልካች ተጠሪ በውለ መሰረት ባለመፈፀማቸው ኪሳራ እንዱከፈለው መጠየቁ ተገቢ ሆኖ አግኝተነዋል።
No topics extracted.
ኪሳራ ሉከፈለው ይገባል የሚባል ከሆነ የኪሳራው መጠን ምን ያህል ላሆን ይገባል የሚለው በቀጣይነት ላታይ ይገባዋል። ተዋዋይ ወገን ግዳታውን ሳይፈፅም ቀርቶ በልላው ወገን ላይ ጉዲት ደርሶ ከሆነ የኪሳራው ልክ ከውል ውጪ ስለሚደርስ ኃላፉነት በሚመለከተው ድንጋጌዎች መሰረት ሉወሰን እንደሚገባ የፍ/ብ/ህ/ቁ 1790(2) ያመለክታል። በዚህም መሰረት አመልካች ሉካስ የሚገባው ከደረሰበት ጉዲት ጋር ተመዛዛኝ የሆነ ኪሳራ እንደሆነ ከፍ/ብ/ህ/ቁ 2090(1) እና 2091 መገንዘብ ይቻላል። በመሆኑም አመልካች ተጠሪ በትምህርት ላይ እያለ ምን ያህል ደመወዝ እንደከፈላቸው እንዱሁም ከትምህርቱ ጋር ተያያዥነት ላላቸው ጉዲዮች ምን ያህል ወጪ እንዲወጣ በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠ ነገር ስለመኖሩ መዝገቡ አያሳይም። የኪሳራውን ልክ ለመወሰን ደግሞ እነዚህ ነገሮች ሉረጋገጡ ይገባል።
በአጠቃላይ አመልካች ከተጠሪ ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት ተጠሪ ትምህርቱን ከተከታተለ በኋላ በራሳቸው በኩል ያለውን የውል ግዳታ ባለመፈፀማቸው አመልካች ላይ ለደረሰው ጉዲት ኪሳራ ሉከፍለ ሲገባ ወጪውን ለመተካት በውለ ላይ በግልፅ አልተስማሙም በሚል ጥያቄው ውድቅ ማድረጉ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 08 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሐምል 20 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትዕዛዝ ተሽሯል።
ተጠሪ በትምህርት ላይ በቆዩበት ጊዜ አመልካች ያወጣውን ወጪ ተጠሪ የመክፈል ግዳታ አለባቸው ብለናል።
አመልካች ተጠሪ በትምህርት ላይ በቆዩበት ጊዜ ያወጣውን ወጪ ለማስረዲት ያቀረበውን ማስረጃ መሰረት አድርጎ በማጣራት የኪሳራውን መጠን እንዱወስን ጉዲዩን ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 343(1) መሰረት መልሰናል።
በዚህ ፍ/ቤት ያወጣውን ወጪ አመልካች ራሱ ይቻል።