No summary available.
ግንቦት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሂሩት መለሰ ተሻገር ገ/ስላሴ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- እነ ሙና እንድሪስ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ልማት ባንክ - አልቀረቡም መዝገቡን መርምረን ተከታዩን ፍርድ ሰጥተናል።
ይህ ጉዲይ የተጀመረው በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ሲሆን አመልካቾች በተጠሪና በሥር አንደኛ ተከሳሽ ላይ ባቀረቡት ክስ በአዱስ አበባ ከተማ በወረዲ 6 ቀበላ 13 ክልል ቁጥር 563 የሆነው ቤት ለከሳሾችና ለአንደኛ ተከሳሽ ከወላጆቻችን በውርስ የተላለፈልን ንብረት ሲሆን አቶ ጅላል አብደልመናን የተባለ ግለሰብ ከሁለተኛ ተከሳሽ ላይ ገንዘብ ሲበደሩ አንደኛ ተከሳሽ አካለመጠን ባላደረሱት ወራሾች ላይ የተሰጠውን የሞግዚትነት ሥልጣን መሰረት አድርጎ የጋራ የውርስ ንብረት የሆነውን ቤት በመያዣነት ሰጥቷል። በአንደኛ ተከሳሽ የተፈጸመው ተግባር ከፍ/ብ/ሕ/ቁ/300 እና 1266 አኳያ ሕገ-ወጥ ስለሆነ ሐምል 7 ቀን 1987 ዓ.ም እና ጥቅምት 16 ቀን 1987 ዓ.ም የፈረመው የመያዣ ውል ፈራሽ ነው ተብል እንዱወሰንና የቤቱንም ካርታ ሁለተኛ ተከሳሽ እንዱመልስ ይወሰንልን በማለት ጠይቀዋል።
የከሳሾች ክስና ማስረጃ ለተከሳሾች ደርሶ መልስ እንዱሰጡ ታዞ አንደኛ ተከሳሽ ተጠርቶ ባለመቅረቡ ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ትዕዛዝ ተሰጥቷል።
ሁለተኛ ተከሳሽ/የአሁን ተጠሪ/ ቀርቦ ለክሱ ምክንያት የሆነውን ቤት በመያዣነት መያዙን አምኖ ይህንን ለማድረግ የቻለው አንደኛ ተከሳሽ በቤተዘመድ ጉባኤ ዓማካይነት በ24/1/87 ዓ.ም የሞግዚትነት ሥልጣን ተሰጥቶት ፍ/ቤትም ቀርቦ በመፅደቁ ምክንያት እንደሆነና የተሰጠውም የሞግዚትነት ሥልጣን ሞግዚት በሆነላቸው ሰዎች ስም የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት በዋስትና ለመስጠት እንደሚችል በሰነደ ላይ ስለተመለከተ በመሆኑ ለአንደኛ ተከሳሽ በተሰጠው የሞግዚትነት ሥልጣን ላይ ተመስርቶ የመያዣ ውለ መፈረሙ በአግባቡ ስለሆነ የመያዣ ውለ የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት ተከላክሎል።
የፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤትም የመያዣ ውለ ሉፈርስ ይገባል ወይንስ አይገባም የሚለውን ጭብጥ መስርቶ ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ የቤተዘመድ ጉባኤ አንደኛ ተከሳሽን ሞግዚት አድርጎ የሾመው በ18/1ዐ/81 ዓ.ም ሲሆን ጥቅምት 11 ቀን 1987 ዓ.ም የሞግዚትነት ሥልጣኑ ፍ/ቤት ቀርቦ ፀድቋል። በሞግዚትነት ማፅደቅ ውሳኔውም ላይ ከከሳሾች መካከል አንደኛ እና ሁለተኛ ከሳሾች ከሞግዚት አስተዲደር ነጻ የወጡ መሆኑ ተመልክቷል። አንደኛ ተከሳሽ ሞግዚት በሆነላቸው ስም የተመዘገበ የሚንቀሳቀስም ሆነ የማይንቀሳቀስ ንብረት በመያዣ ወይም ዋስትና ለመስጠት የተፈቀደለት ቢሆንም የመያዣ ውለን በተፈራረሙ ጊዜ አንደኛ እና ሁለተኛ ከሳሾች ከሞግዚት አስተዲደር ነጻ ወጥተው የነበረ ስለሆነ ያለ እነሱ ስምምነት የመያዣ ውለን መፈራረሙ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1266”ን” የሚጻረር ነው።
በመሆኑም በወረዲ 6 ቀበላ 13 ክልል የቤ.ቁ 563 ተመዝግቦ የሚገኘው የከሳሾችና የአንደኛ ተከሳሽ የጋራ የውርስ ሀብት ሆኖ እያለ አንደኛ እና ሁለተኛ ከሳሾች ስምምነታቸውን ሳይሰጡ በአንደኛ ተከሳሽ በኩል ከሁለተኛ ተከሳሽ ጋር የመያዣ ውል የተፈጸመው የሕጉን ድንጋጌ ባልተከተለ ሁኔታ ስለሆነ ጥቅምት 1987 ዓ.ም እና ሐምል 1987 ዓ.ም የተደረገ የመያዣ ውል ፈራሽ ነው በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
የሥር ሁለተኛ ተከሳሽ የአሁን አመልካች በውሳኔው ቅሬታ አድሮበት የይግባኝ ቅሬታውን ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርቦ ፍ/ቤቱም በበኩለ ግራ ቀኙን አከራክሮ አንድ ውል እንዱፈርስ ተዋዋይ ወገን ያልሆኑ ሦስተኛ ወገኖች አቤቱታ ማቅረብ የሚችለት በፍ/ብ/ሕ/ቁ/ 1808(2) እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች መሰረት ነው።
ውለ የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ጊዜ አንስቶ ከ2 ዓመት በኋላ የውል ይሰረዝልኝ ክስ ላቀርብ እንደማይችል ጉዲቱ የደረሰበት ሰው አካለመጠን የደረሰ ሰው ከሆነ ክሱን ማቅረብ የሚገባው ውለ በተደረገ በ2 ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1810(1) ላይ ተደንግጓል። በተያዘው ጉዲይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱት መ/ሰጭዎች ውለ ሲደረግ ለአቅመ አዲም የደረሱ መሆናቸው ከ4ኛ-7ኛ የተጠቀሱትም መ/ሰጭዎች ከ1995 ዓ.ም ጀምሮ ለአካለመጠን የደረሱ መሆናቸው በመ/ሰጭዎች ያልተካደ በመሆኑ የውል ይሰረዝልኝ ክሱ 2 ዓመት ያለፈው መሆኑን ፍ/ቤቱ ተገንዝቧል። ስለሆነም በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1810(1) መሰረት የውለ ይሰረዝልኝ ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት ውሳኔ ሰጥቷል።
የሥር ከሳሾች/የአሁን አመልካቾች/ በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ቅሬታ አድሮባቸው የይግባኝ ቅሬታቸውን ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ያቀረቡ ቢሆንም በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 337 መሰረት ፍ/ቤቱ ይግባኙን ሳይቀበለው ቀርቷል።
No topics extracted.
የሰበር አቤቱታው የቀረበው ይህንኑ በመቃወም ሲሆን አቤቱታው ተመርምሮ የአመልካቾች የውል ይፍረስልኝ ክስ በ2 ዓመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል ተብል በፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት መወሰኑ ለሰበር ቀርቦ መጣራት የሚገባው ሆኖ በመገኘቱ ይህ ችልት አቤቱታው ለሰበር እንዱቀርብ አድርጏ ተጠሪን በመጥራት ግራ ቀኙን አከራክሯል።
በአጠቃላይ የክርክሩ ይዘት ከላይ የተመለከተው ሲሆን በበኩላችንም አቤቱታው ለሰበር ያስቀርባል ከተባለበት ነጥብ አኳያ ጉዲዩን እንደሚከተለው መርምረናል።
አንድ ውል በሚመሰረትበት ጊዜ የችልታ ወይንም የፈቃድ ጉድለት ያለበት ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ችልታ አልነበረኝም ወይንም ፈቃዳን በአግባቡ አልሰጠሁም በሚለው ተዋዋይ ወገን ብቻ ጠያቂነት ውለ ሉፈርስ እንደሚችል እንደዚሁም ውለ የተደረገበት ጉዲይ ለሕግ ወይንም ለሞራል ተቃራኒ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜና የውለ አጻጻፍ ሥርዓትም ባልተጠበቀ ወቅት ከተዋዋይ ወገኖች መካከል ወይንም በውለ ጥቅም አለኝ በሚል 3ኛ ወገን ዓማካይነት የውል ይፍረስልኝ ጥያቄ ሲቀርብ ውለ ሉፈርስ እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1808(1) እና (2) ላይ ተመልክቷል።
የውል ይፍረስልኝ ክስ ማቅረቢያ ጊዜውን በተመለከተም ውለ የማይረጋበት ምክንያት ከቀረበት ጊዜ አንስቶ በ2 ዓመት ውስጥ ካልቀረበ በይርጋ ሉታገድ እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1810 ላይ ተመልክቷል።
በተያዘው ጉዲይ በፋዳራል መ/ደ/ፍ/ቤት ውለ ሉፈርስ ይገባል ተብል ውሳኔ የተሰጠው የጋራ ባለንብረቶች የሆኑት አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች ፈቃዲቸውን አልሰጡም በሚል ምክንያት ነው።
በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1810 ላይ የተመለከተው የ2 ዓመት ይርጋ ጊዜ ተፈጻሚነቱ ውለ የማይረጋበት ምክንያት ቀሪ በሚሆንበት ጊዜ ሲሆን ይህም የሚመለከተው ከአንደኛው ተዋዋይ ወገን ችልታ ወይንም ፈቃድ ጉድለት ጋር የተያያዘ በሚሆንበት ጊዜ ነው። ውለ ከችልታ ወይንም ከፈቃድ ጋር በተያያዘ ጉድለት አለበት በሚባልበት ጊዜ ይህንኑ መሰረት አድርጎ ክስ የሚያቀርበው ወገን በ2 ዓመት ክሱን ካላቀረበ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1810 መሰረት በይርጋ ቀሪ እንደሚሆን መገንዘብ ይቻላል።
ነገር ግን በተያዘው ጉዲይ ውለ እንዱፈርስላቸው የጠየቁት አንደኛ እና ሁለተኛ አመልካቾች ለውለ መፍረስ በምክንያትነት የጠቀሱት የጋራ የሆነውን የውርስ ሀብት ለመሸጥም ሆነ በመያዣ ለመስጠት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1266 መሰረት የጋራ ባለሀብቶች ስምምነት አስፈላጊ ሆኖ ሳለ የሥር አንደኛ ተከሳሽ ያለ እኛ ስምምነት የጋራ የውርስ ሀብት የሆነውን ቤት ለሁለተኛ ተከሳሽ/ለአሁን ተጠሪ/ በመያዣነት የሰጠ ስለሆነ ውለ ሉፈርስ ይገባል በማለት ነው። አንደኛ እና ሁለተኛ አመልካቾች ተዋዋይ ወገን ካልሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1808(1) መሰረት ውለ የችልታ ወይንም የፈቃድ ጉድለት ያለበት ስለሆነ ሉፈርስ ይገባል በማለት ሉጠይቁ የማይችለ በመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1810 ላይ የተመለከተው የ2 ዓመት ይርጋ ጊዜ ለዚህ ጉዲይ አግባብነት አይኖረውም።
በልላ በኩልም በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ በአንቀጽ 318 ላይ የተቀመጠውን የይርጋ ጊዜ በተመለከተም አካለመጠን ያላደረሰ ልጅ በሞግዚቱ ላይ የሚያቀርበውን ክስ አስመልክቶ ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን በዚህ ጉዲይ ግን ውለ ፈራሽ ነው የተባለው ከፍ ብል እንደተጠቀሰው ከሞግዚት አስተዲደር ነጻ ወጥተዋል በተባለት አንደኛ እና ሁለተኛ አመልካቾችን አስመልክቶ ስለሆነ ድንጋጌው ለዚህ ጉዲይ አግባብነት ያለው አይደለም።
እንግዱህ ተጠሪ ያነሳው የይርጋ ክርክር በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1810 እና በቤተሰብ ሕጉ የሚሸፈን ባይሆንም የጋራ የሆነን ንብረት ለማስተላለፍ ወይንም በዋስትና ለመስጠት የሁለንም የጋራ ባለንብረቶች ስምምነት ማግኘት እንዲለበት በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1266 ላይ የተመለከተ ሲሆን ነገር ግን የጋራ ባለንብረት ከሆኑት መካከል አንደኛ እና ሁለተኛ ተጠሪዎች በመያዣ ውለ ስምምነታቸውን ያልሰጡ ስለሆነ ይህም ውለ ሕግን የሚጻረር መሆኑን የሚያመለክት ነው። አንድ ውል ሕግን የሚቃረን ነው በሚባልበት ጊዜ እንዱፈርስ ጥያቄ መቅረብ ያለበት በ10 ዓመት ጊዜ እንደሆነ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 1845 ድንጋጌ መረዲት ይቻላል። አመልካቾች ክሱን ቀረቡት ደግሞ በሕጉ ላይ የተቀመጠው የ10 ዓመት ጊዜ ከማለፈ በፉት ስለሆነ አቤቱታቸው በይርጋ የታገደ አይደለም።
ሲጠቃለልም የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የአመልካቾች ክስ በ2(ሁለት) ዓመት ይርጋ ቀሪ ሆኗል ያለው ለጉዲዩ አግባብነት በላለው ድንጋጌ ላይ ተመስርቶ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈጸመበት ሆኖ አግኝተነዋል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ. በ1/9/2000 ዓ.ም የአመልካቾች ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኗል በማለት የሰጠው ውሳኔ እንደዚሁም የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ. ሐምል 28 2001 ዓ.ም ይህንኑ ውሳኔ በማጽናት የሰጠውን ትዕዛዝ በፍ/ብ/ሕ/ሥ/ሥ/ቁ 348(1) መሰረት ሽረነዋል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪ በፍሬ ጉዲይ ረገድ ያቀረበውን የይግባኝ ቅሬታ መርምሮ የበኩለን ውሳኔ እንዱሰጥበት ጉዲዩ ተመልሶለታል።
ግራ ቀኙ ወጭና ኪሳራ ይቻቻለ።