No summary available.
ሚያዝያ 8 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሽባባው ወላ - ጠበቃ ጌታቸው ውብሸት ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ሙለጌታ ዓባይ - ጠበቃ አቶ እንዲልካቸው ይላቅ ቀረቡ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው።
አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በከሳሽነት ቀርበው ተጠሪ ብር 7000(ሰባት ሺህ ብር) እስከ ግንቦት 30 ቀን 1991 ዓ.ም ሉመልስ ብድር ወስድ ያልከፈለኝ ስለሆነ ሉከፍለኝ ፈቃደኛ አልሆነም። ስለዚህ ከነ ወለደ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርቧል። ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርቦ የአመልካች ጥያቄ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 መሰረት ሁለት ዓመት ያለፈው በመሆኑ በይርጋ ይታገዲል። አክሲዮን ማህበር ለማቋቋም ውል ተዋውለን ብር 8000(ስምንት ሺህ ብር) ስለወሰደ እንዱቻቻልልኝ በማለት መልስ ሰጥቷል። የሥር ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ የብድር ገንዘቡ ሉከፈል ከሚገባው ከሁለት ዓመት በላይ የቆየ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 መሰረት እንደተከፈለ ይቆጠራል በማለት መልስ ሰጥቷል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርቧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤት ለፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 የሰጠው ትርጉም የተሣሣተ መሆኑን በመተንተን የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሽሯል። በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ተጠሪ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበው ይግባኝ ሰሚ ችልቱ የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የከፍተኛው ፍርድ ቤት ለፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024 የሰጠው ትርጉም ስህተት መሆኑን በመግለጽ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮ የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አጽንቶታል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024/ረ/ ጊዜ ተወስኖለት በየወቅቱ ለሚከፈል ገንዘብ እንጂ በአንድ ጊዜ ለሚከፈል ወለድ የሚያገለግል አይደለም። ከዚህ በተጨማሪ ተጠሪ እዲውን አልካደም የመቻቻል ጥያቄም ያቀረበ መሆኑ በመልሱ በግልጽ ተመልክቷል። የታመነ የብድር እዲ እንደከፈለ ይገመታል ተብል መወሰኑ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2025 ድንጋጌ የሚጥስ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል። ተጠሪ በበኩለ የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጠው ውሣኔ ተገቢ ነው።
በሁለት ዓመት ያልተከፈለ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024/ረ/ ቀሪ ይሆናል በማለት መልስ ሰጥቷል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው ተጠሪ ብድሩን አለመክፈለን በማመን የመቻቻል ጥያቄ እንዲቀረበ ከሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተገንዝበናል። አንድ ሰው ብድሩን አለመክፈለን አምኖ በሚከራከርበት ሁኔታ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024/ረ/ ተፈፃሚነት የሚኖረው አይደለም። ይኸም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2025/ሀ/ ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል። ከዚህ በተጨማሪ ከሳሽ በክሱ የገለፀውን ፍሬ ጉዲይ ተከሳሽ በከፉል ወይም በሙለ ካመነ በእምነቱም መሰረት ውሣኔ ላሰጥ እንደሚችል የፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 242/ረ/ በግልጽ የሚደነግግ በመሆኑ ተጠሪ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2024/ረ/ ድንጋጌ እንደ ይርጋ ድንጋጌ በመቁጠር ብድሩን አለመክፈለን ገልፆ መልስ ሰጥቶ ለሁለት ዓመት ስላልጠየቀ ልከፍል አይገባኝም በማለት ያቀረበው ክርክር የሕግ ድጋፍ የላለው ነው።
ከዚህ በተጨማሪ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024/ረ/ በዋናው ብድር ሣይሆን ለብድር የሚከፈለን ወለድን የሚመለከት ድንጋጌ መሆኑ የሰበር ችልት በሰበር መዝገብ ታህሣሥ 20 ቀን 2002 ዓ.ም አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። አመልካችና ተጠሪ ወለድ የሚከፈልበት የብድር ውል የላላቸው በመሆኑ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024/ረ/ በእነርሱ መካከል ያለውን የብድር ግንኙነት የሚመለከት አይደለም። ስለሆነም የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ባይ ችልት የሰጠው ውሣኔ ተሽሯል።
No topics extracted.
ተጠሪ ከአመልካች የተበደረውን ብር 7000(ሰባት ሺህ) በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ክስ ከቀረበበት ሰኔ 13 ቀን 1998 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ ዘጠኝ ፏርሰንት ወለድ ጋር ለአመልካች ይክፈል ብለናል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ ብለናል።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።