No summary available.
ሚያዝያ 07 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ብርሃነ ገብረ ሐይለ - ጠበቃ ሐጏስ ደበሱ ቀረቡ ተጠሪ፡- አንሲዮን ኮንትር ላፊም - የቀረበ የለም **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ በቤት ኪራይ የሚከፈለውን የተርን ኦቮር ታክስ ክፍያን የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ አመልካች በመሰረቱት ክስ ተጠሪ በአዱስ አበባ ከተማ በቦላ ክፍለ ከተማ ቀበላ 06 በቁጥር 459 የተመዘገበና የአመልካች ንብረት የሆነውን ቤት ሰኔ 26 ቀን 1998 ዓ.ም በተደረገ የቤት ኪራይ ውል በኪራይ ይዞ ለሦስት አመታት በቢሮነት እና በማከማቻነት መገልገለን፣ በዚህም መሰረት የቤት ኪራይ በድምሩ ብር 612,000.00(ስድስት መቶ አስራ ሁለት ሺህ) መከፈለን፣ ለማከማቻነትና ለመሳሰለ አገልግልት በኪራይ ለተያዘ ቤት በሚከፈል የቤት ኪራይ ላይ በመቶ አስር(10) የሆነ የተርን ኦቨር ታክስ በአገልግልት ተጠቃሚ የሆነው ተከራይ እንዱከፍል፣ አከራዩም ታክሱን ከቤቱ ኪራይ ጋር ከተከራዩ ላይ እየሰበሰበ ሥልጣን ላለው ግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት ገቢ እንዱያደርግ የውክልና ስልጣን እንደሰጠውና ግዳታ የሚጥልበት መሆኑን፣ በኪራይ ውለም ተከራይ ከታክሱ ነፃ እንዲልሆኑ ታክሱ ከቤት ኪራይ ገቢ ጋር ስላልተከፈለ አመልካች በህጉ መሰረት ለታክሱ ክፍያ በቅድሚያ ተጠያቂ ሆነው ላንድ አመት በተከፈለ የቤት ኪራይ ገቢ ብር 204,000.00(ሁለት መቶ አራት ሺህ ብር) ላይ የታሰበ ተርን ኦቮር ታክስ ብር 20,400.00(ሃያ ሺህ አራት መቶ ብር) ለግብር ሰብሳቢ አካል መክፈላቸውን፣ ለተጨማሪ የሁለት ዓመት ጊዜ በተከፈለ የቤት ኪራይ ክፍያ .00(አራት መቶ ስምንት ሺህ ብር) ላይ የሚታሰብ የተርን ኦቨር ታክስ .00(አርባ ስምንት ሺህ ብር) እንዱከፈል፣ እንዱሁም የታክስ እዲው ብር 61,000.00(ስልሳ አንድ ሺህ ብር) በሕግ በተወሰነው የመክፈያ ጊዜ ውስጥ ባለመከፈለ ምክንያት መቀጫ ተጨምሮበት እንዱከፈል የአዋጁ ድንጋጌ እንደሚያስገድድ፣ ለጠበቃ ብር 11,000.00(አስራ አንድ ሺህ ብር) የተርን ኦቨር ታክስ ለመክፈል ግዳታ መግባታቸውን ገልጸው ተጠሪ በድምሩ ብር 61,200.00(ስልሳ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር) እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል። የአሁኑ ተጠሪም ለክሱ በሰጠው መልስ የቤት ኪራይ መኖሩን ሳይክድ ሕጉ ተከራይ ታክሱን እንዱከፍል የሚያስገድድ ነው ቢባል እንኳ በውለ አንቀጽ 6 ስር በመንግስት ባለስልጣናት የሚጣለው ማንኛውም ቀረጥ አከራይ እንዱከፍል በማያሻማ መልኩ የተቀመጠ በመሆኑ ተፈፃሚነት ያለው ውለ መሆኑን፣ ታክሱ በወቅቱ ባለመከፈለ ለሚጣለው መቀጮ ግዳታ ያለበት አከራይ መሆኑን በመግለፅ ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር አመልካች ብር 20,400.00(ሃያ ሺህ አራት መቶ ብር) ለግብር ሰብሳቢው መስሪያ ቤት መክፈላቸው ስለተረጋገጠና ተከራይም የተርን ኦቨር ታክስ የመክፈል ግዳታ ያለበት መሆኑን በመግለፅ ይህንኑ ገንዘብ ተጠሪ ለአመልካች ከዲኝነት ገንዘቡ እና ከጠበቃ አበል ከሆነው ብር 2040.00(ሁለት ሺህ አርባ) እንዱሁም ከቴምብር ቀረጥ ጋር እንዱከፍላቸው፣ ብር 61,200.00(ስልሳ አንድ ሺህ ሁለት መቶ) ግን አመልካች ለታክስ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት መክፈላቸውን ሳያረጋግጡ ተከራዩን(ተጠሪን) ሉጠይቁ አይችለም በማለት ውድቅ አድርጎባቸዋል።
ተጠሪ ብር 61,200.00 ሉከፍለ አይገባም በተባለው የውሳኔ ክፍል አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ የውሳኔ ከፍል ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ነሐሴ 15 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታቸው ተመርምሮም ተርን ኦቨር ታክሱን አመልካች ከፍለው ካጠናቀቁ በኋላ ነው መጠየቅ የሚችለት በሚል የተሰጠውን ውሳኔ ክፍል አግባብነቱን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ግራ ቀኙ መልስና የመልስ መልሳቸውን በፁሐፍ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪው የአመልካችን ቤት በኪራይ ይዞ በቢሮነትና በማከማቻነት እንደተገለገለበት እንዱሁም ቤቱ ለተጠቀሰው አገልግልት በመዋለ ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 308/1995 መሰረት ለአመልካች ለተከፈላቸው የቤት ኪራይ ገቢ ላይ ከመቶ አስር (10%) የሚከፈል ተርን ኦቨር ታክስ የሚከፈልበት ስለመሆኑ በተጠሪ ማስተባበያ ማስረጃ ያልቀረበበት ከመሆኑም በላይ በስር ፍርድ ቤትም የተረጋገጠ ጉዲይ መሆኑን ነው። የስር ፍርድ ቤት ተጠሪ ለታክሱ ኃላፉነት ያለበት መሆኑን አምኖ የአመልካችን የዲኝነት ጥያቄ ያልተቀበለው አመልካች ብር 40,800.00 (አርባ ሺህ ስምንት መቶ ብር) ለታክስ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት መክፈላቸው አልተረጋገጠም በሚል ነው። ይሁን እንጂ አመልካች በአዋጅ ቁጥር 308/1995 አንቀፅ 2(3፣ 5፣ 7፣ 8፣ 9 እና 12) እና 6 ድንጋጌዎች መሰረት ታክሱን ለአስከፊይ ባለሥልጣን ገቢ የማድረግ ግዳታ አለባቸው።
ይህንን በሕጉ የተጣለባቸውን ግዳታ ለመወጣት ደግሞ ታክሱን ለታክስ ሰብሳቢው መስሪያ ቤት ገቢ ከማድረጋቸው በፉት ከአገልግልት ገዥው ላይ ሉከፈል ከሚገባው ታክስ ክፍያ መጠየቅ የሚከለክላቸው ምክንያት የለም። የስር ፍርድ ቤት አመልካች ታክሱን ለታክሱ ባለስልጣን ገቢ ሲያደርጉ ነው መጠየቅ የሚችለት በማለት ያስቀመጠው ምክንያት በሕጉ ያልተመለከተ ቅድመ ሁኔታ ነው። በመሆኑም አመልካች በሕጉ የተጣለባቸውን ግዳታ ለመወጣት ተጠሪን ክፍያ እንዱፈፅሙ መጠየቃቸው ተቀባይነት የማያገኝበት አጥጋቢና ሕጋዊ ምክንያት ስለላለ በዚህ ረገድ የስር ፍርድ ቤት የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ጥር 08 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ ግንቦት 18 ቀን 2001 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሻሽሎል።
ተጠሪ ለአመልካች ብር 40,800.00(አርባ ሺህ ስምንት መቶ ብር) እንዱከፍል ብለናል።
በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር የወጡትን ላልች ወጪዎችን በተመለከተ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻቻለ ብለናል።
No topics extracted.