No summary available.
ሚያዝያ 05 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ጅቦኒ ቱና - ቀረቡ ተጠሪ፡- ወ/ሮ ብርቂ ኢርክታ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ዋስትናን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኗ ተጠሪ ባሁኗ አመልካች እና በላልች ሁለት ግለሰሶች በስር ቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤት በመሰረቱት ክስ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ አመልካች ሁለት ግለሰቦች (አቶ ፋደሳ ሽኑ እና አቶ ዘውደ ሽመልስ) የተጠሪን መኖሪያ ቤት ሰብረው ገብተው ስምንት ላደና ገብስ ሰርቀዋል ተብለው በተጠረጠሩበት ጉዲይ በአካባቢ ሽማገላዎች እና በአከባቢው ቡድን ፉት ቀርበው ፋደሳ ሸኑ ልጃቸው ስለሆነ፣ ዘውደ ሽመልስ ባለቤታቸው ስለሆነ በተጠረጠሩበት ጉዲይ ላባ እንዲልሆኑ ቦኩ ላይ ቀርበው ካልማለ የተጠቁትን የእህል ግምት ገንዘብ እከፍላለሁ በማለት የዋስትና ግዳታ በግዳታዋ መሰረት የተጠረጠሩትን ሰዎች በቦኩ አቅርባ ካለማስማሎ በተጨማሪ ሰዎቹን ሸሽገው የእህለን ግምት ሳያስከፍለ የቀሩ መሆኑን ገልፀው የእህለን ግምት እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸው የሚያሳይ ነው። የአሁኗ አመልካችም የገቡት ግዳታ አለመኖሩን ገልፀው ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር የአሁኗን አመልካች ለክሱ ኃላፉ በማድረግ የእህለን ግምት ብር 686.00(ስድስት መቶ ሰማንያ ስድስት ብር) እንዱከፍለ ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለወረዲው ፍርድ ቤት የሰበር አቤቱታቸውን ደግሞ ለኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካች ነሐሴ 01 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ ከጉዲዩ ለማስረጃነት በቀረበው ሰነድ ላይ የተገለፀው የአመልካች ግዳታ ተጠርጣሪዎቹን ለማቅረብ ሆኖ እያለ ለተጠረጠሩበት እህል ግምት ክፍያ ትፈፅሚያለሽ መባለ ከዋስትና ሕግ ድንጋጌዎች መንፈስ ውጪ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው።
አቤቱታቸውም ተመርምሮ በሰበር ችልቱ ላታይ ይገባዋል በመባለ ተጠሪ ቀርበው ጥር 19 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገፅ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምረናል። እንደመረመርነውም አመልካች የገቡት የዋስትና ግዳታ አለ ወይስ የለም? የሚለው ነጥብ በጭብጥነት ሉመረመር የሚገባው ሆኖ አግኝተናል።
በመሰረቱ ዋስትና በሕጉ ጥበቃ የሚያገኘው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1922 ድንጋጌ ስር የተመለከተውን መስፈርት አሟልቶ ሲገኝ ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ዋስትና ግልፅ መሆን ያለበት ከመሆኑም በላይ ከተደረገው ውል ወሰን ለማለፍ የማይችል እና ለግዳታው ዋስ የሆነበት የገንዘቡ ልክ በዋስትናው ውል መገለፅ አለበት። ዋስትና ይህን ፍርማሉቲ ከማሟላቱም በተጨማሪ ለዋስትናው መሰረት የሆነው ዋናው ጉዲይም ሕጋዊ መሆን አለበት።
በተያዘው ጉዲይ አመልካች ፈረሙ በተባለት ሰነድ የዋስትና ገንዘቡ በግልፅ ተገልጾ የተቀመጠ ካለመሆኑም በላይ ለግዳታው መሰረት ነው የተባለው ዋናው ጉዲይም ተጠርጣሪዎች በሕግ አስገዲጅነት በላለው ሁኔታ ቦኩ ሂደው እንዱምለ የሚጠይቅ ነው። ይህ ደግሞ በሕጉ አግባብ ጥበቃ የሚደረግለት የዋስትና ግዳታ አለ ለማለት የሚያስችል አይደለም። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለተገኘ ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በጀርማ ኮርጴሳ ቀ/ገ/ማ/ማህበራዊ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 050/2001 መጋቢት 02 ቀን 2001 ዓ.ም ተሰጥቶ በኤልፊታ ወረዲ ፍ/ቤት በመ/ ሰኔ 02 ቀን 2001 ዓ.ም፣ በኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችልት በመ/ ሐምል 15 ቀን 2001 ዓ.ም በትዕዛዝ የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
No topics extracted.
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።