No summary available.
መጋቢት 22 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሂሩት መለሰ ብርሀኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ሸዋዬ ኑርዬ - ጠበቃ አቶ አበራ ማሬ ቀረቡ ተጠሪ፡- ምንአዩ ኃላፉነቱ የተወሰነ የግል ማህበር - ጠበቃ አቶ አበራ ታደሰ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትና የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት የሰበር አቤቱታ አመልካች ስላቀረቡ ነው።
ጉዲዩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው። በሥር ፍርድ ቤት አመልካች ከሳሽ ተጠሪ ተከሳሽ በመሆን ተከራክረዋል። አመልካች በሥር ፍርድ ቤት በከሳሽነት ቀርበው ሰኔ 24 ቀን 1998 ዓ.ም በተደረገ የእጅ በእጅ ሽያጭ ውል ብር 120,540.00(አንድ መቶ ሀያ ሺ አምስት መቶ አርባ ብር) ዋጋ ያለው የቢሮ ዕቃ ከተጠሪ(ተከሳሽ) ለመግዛት በመስማማት ብሩን ወዱያውኑ የከፈለ መሆኑንና ተጠሪ ግን የገዛሁትን የቢሮ ዕቃ ወዱያውኑ አላስረከበኝም። ተጠሪ ዕቃውን ስላላስረከበኝ ከሃምላ 1998 ጀምሮ ውለን ማፍረሴን ለተከሳሽ አሳውቄአለሁ። ተጠሪ ገንዘቡን ሉመልስልኝ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ገንዘቡን ከነወለደ እንዱከፍል ይወሰንልኝ በማለት ክስ አቅርበዋል። ተጠሪ በተከሳሽነት ቀርቦ ከከሳሽ (አመልካች) ጋር ያደረግሁት ውል የለም። ከሳሽ ያቀረቡት የእጅ በእጅ ሽያጭ የክፍያ ደረሰኝ ሰነድ ዕቃውን ሰነደን የያዘው ሰው የተረከበበትን ቀን የሚገልፅ ስለሆነ ሰነደ ዕቃውን ስለመረከባቸው በቂ አስረጅ ነው በማለት መልስ ሰጥቷል። የሥር ፍርድ ቤት ሁለት ጭብጦችን መስርቷል። የመጀመሪያው በተጠሪና አመልካች መካከል የእጅ በእጅ ሽያጭ ተፈፅሟል ወይስ አልተፈፀመም?
የሚል ሲሆን ሁለተኛው አመልካች ዕቃውን ተረክበዋል ወይስ አልተረከቡም? የሚለ ናቸው። የሥር ፍርድ ቤት በተጠሪና በአመልካች መካከል የእጅ በእጅ ሽያጭ የተፈፀመ መሆኑን በቂ ማስረጃ አልቀረበም፣ የሽየጭ ውል አለ ቢባል እንኳን በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2278(1) አመልካች ክፍያ ሲፈፅም ዕቃውን የሚረከብ መሆኑ ስለተደነገገና ይህንን በምስክር ማስተባበል ስለማይቻል ከሳሽ(አመልካች) ያቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሣኔ ቅር በመሰኘት ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርቧል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሣኔ አፅንቶታል።
አመልካች ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የሥር ፍርድ ቤት የሽያጭ ውል የለም በማለት የወሰነው እኔ ባቀረብኩት ሰነድ ስም አልተጠቀሰም በማለት ነው። ሆኖም እኔ ያቀረብኩት ክፍያ የፈፀምኩበት ደረሰኝ ነው።
የማይንቀሣቀስ ንብረት ሽያጭ ውል በፅሐፍ እንዱደረግ ህግ አያስገድድም። እኔ ደረሰኙን ይዤ መገኘቴ ከተጠሪ ጋር የዕቃ ግዥ የፈፀምኩ መሆኑን የሚያስረዲ ደጋፉ ማስረጃ ነው። ተጠሪ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2278 ዕቃውን አላስረከበኝም። ተጠሪ የሸጠውን ዕቃ የሚያስረክብበት የራሱ ሥርዓት ያለው ሲሆን በዚያ ሥርዓት መሰረት ዕቃውን ስለማስረከቡ አላስረዲም። በእኔ በኩል ተጠሪ የገዛሁትን ዕቃ ለማስረከብ የቆጠርኳቸውን ምስክሮች ለማስረዲት ያቀረብኩትን ጥያቄ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2278 እና ፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2006 የተሳሳተ ትርጉም በመስጠት ውለ እንዱፈርስና ወደ ነበርንበት እንድንመለስ አለመወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ስለሆነ በሰበር ታይቶ ይታረምልኝ በማለት አመልክቷል።
ተጠሪ በበኩለ አመልካች የያዙት ደረሰኝ ተጨማሪ እሴት ታክስ የተከፈለበት ደረሰኝ እንጅ የሽያጭ ውል መኖሩን የሚያስረዲ አይደለም። ፍርድ ቤቱ ለፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2278(1) የሰጠው ትርጉም ስህተት የለበትም። ድርጅታችን በመጋዘን የላለን ዕቃ እና ወዱያውኑ የማናስረክበውን ዕቃ ዋጋ የመቀበል ልምድ የለውም። አመልካች ውለ እንዱፈርስ ከሀያ ስምንት ቀናት በኋላ መሆኑ ውለን አጠራጣሪ ያደርገዋል የሚል ክርክር አቀርቧል። አመልካች የመልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር ግራ ቀኙ ያቀረቡት የፅሐፍ ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው የሥር ፍርድ ቤት የሰጠው ፍርድ በአግባቡ ነው ወይስ አይደለም?
የሚለው ጭብጥ መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ከመዝገቡ ለመረዲት እንደቻልነው አመልካች የቢሮ ዕቃ ከተጠሪ የገዙ መሆኑን የዕቃውን ዋጋ ገቢ ያደረጉ መሆኑንና ዕቃውን ከተጠሪ ተረክበው ያልወሰደ መሆኑን ለማስረዲት የፅሐፍ (የሰነድ) ማስረጃና የሰው ምስክሮች ዘርዝረው አቅርበዋል። የሥር ፍርድ ቤት የእጅ በእጅ ሽያጭ ውል በማለት ውሣኔ የሰጠው ተጠሪ ለአመልካች የቢሮ ዕቃ የሸጠ መሆኑን ለሽያጭ ውል በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2266 በተሰጠው ትርጉም መሰረት አመልካች ለማስረዲት ያቀረቧቸውን ሁለንም ማስረጃዎች በመመርመርና በመመዘን ሣይሆን አመልካች በሰነደ ማስረጃነት ያቀረቡትን የዕቃ ዋጋ የተከፈለበትና የተጠሪ ተጨማሪ እሴት ታክስ የሰበሰበ መሆኑን የሚያረጋግጠውን ከአመልካች እጅ የሚገኘውን ደረሰኝ ብቻ በመመርመር ነው። የሥር ፍርድ ቤት በአመልካችና በተጠሪ መካከል የቢሮ ዕቃ ሽያጭ ውል አለ ወይስ የለም? የሚለውን ጭብጥ የወሰነው ለጉዲዩ አግባብነት ያላቸውን በአመልካች በኩል የቀረቡ ማስረጃዎችን በመስማትና በመመርመር አለመሆኑ ከፍተኛ የሆነ የዲኝነት አካሄድ ሥርዓት ጉድለት የፈፀመ መሆኑን የሚያመለክት ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ያቀረቡት ደረሰኝ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2278(1) የተሸጠውን ዕቃ ማስረከብ ከዋጋው መከፈል ጋር አንድ ላይ መሆን እንዲለበት ስለሚደነግግ አመልካች ገንዘብ በተቀበለበት ጊዜ ዕቃዎቹን መረከቡን ደረሰኙ ያስረዲል ላላ ማስረጃ መሰማት አይቻልም በማለት የሰጠው የሕግ ትርጉም ተገቢ ሆኖ አላገኘነውም። የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2278 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ ቃል በቃል ሲነበብ “በውለ የተነገረ ተቃራኒ ነገር ከላለ በቀር የተሸጠውን ማስረከብ ከዋጋው መከፈል ጋር በአንድ ጊዜ መሆን አለበት” የሚል ነው ይህ ድንጋጌ በሻጭ ላይ ግዳታ የሚጥል ድንጋጌ ነው። የእጅ በእጅ ሽያጭ በሆነ ጊዜ የዕቃው ዋጋ ሲከፈል የተገዛውን ንብረት ወዱያውኑ ለገዥ የማስረከብ ግዳታ እንዲለበት ይደነግጋል። የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2278 ንዐስ አንቀፅ 2 ሻጭ ዕቃውን ለገዥ ሣያስረክብ ሉቆይ የሚችልበትን ልዩ ሁኔታ ይደነግጋል።
የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2278 ንዐስ አንቀፅ 1 በተደነገገው መሰረት ገዥ ገንዘቡን ከከፈለ ከግማሽ ሰዓት በኋላ ከሶስት ሰዓት በኋላ ወይም በማግስቱ ለመረከብ ተስማምቶ የነበረ መሆኑን በማናቸውም አይነት ማስረጃ ሉያስረዲ የሚችል ስለመሆኑ “በውለ የተነገረ ተቃራኒ ቃል ከላለ በቀር” ከሚለው የድንጋጌው ሐረግ ለመረዲት እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪ ገዥ የዕቃውን ዋጋ ሙለ በሙለ የከፈለ ቢሆንም ሻጭ ዕቃውን ወዱያውኑ በማስረከብ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2278 ንዐስ አንቀፅ 1 የተጣለበትን ግዳታና ኃላፉነት ያልተወጣ መሆኑን ለጉዲዩ አግባብነት ያለውን ማስረጃ በማቅረብ የማስረዲትን መብቱን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2278 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ የሚገደብ አይደለም። ከላይ የተገለፁትን ሁኔታዎች በማስረጃ በማረጋገጥ ገዥ የዕቃውን ዋጋ ለሻጭ ከፍል ዕቃውን ያልተረከበ መሆኑን በማስረዲት ሻጭ ዕቃውን እንዱያስረክበው ወይም የሽያጭ ውለ ፈርሶ ገንዘቡን እንዱመልስለት መጠየቅ የሚችል መሆኑን የፍታብሓር ህግ ቁጥር 2278 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ የማይገደብ ሆኖ እያለ የሥር ፍርድ ቤት አመልካች ለተጠሪ የዕቃውን ዋጋ ከፍዬ ዕቃውን አለመረከቤን በማስረጃ ላረጋግጥ በማለት ያቀረበውን ጥያቄ ለህጉ ድንጋጌ የተሣሣተ ትርጉም በመስጠት ዕቃውን አለመረከብህን በማስረጃ ለማረጋገጥ አትችልም በማለት የሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው። ይግባኝ ሰሚው ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከላይ የተገለፀው የዲኝነት አካሄድ ግድፈትና የህግ አተረጓጎም ስህተት ያለበትን ውሣኔ ሣያርም ማፅናቱ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሣኔና የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ ተሽሯል።
የፍደራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አመልካች ከተጠሪ ጋር የቢሮ ዕቃዎች ለማግዛት ውል የተዋዋለ መሆኑን፣ አመልካች ለዕቃዎቹ ክፍያ የፈፀመ መሆኑን ወይም አለመሆኑንና አመልካች ዕቃዎቹን ተረክቦ የወሰደ መሆኑን ወይም አለመሆኑን በአመልካችና በተጠሪ በኩል የሚቀርቡለትን አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎች በመስማትና በመመርመር ውሣኔ እንዱሰጥ በፍትሐብሕር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343(1) መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.