No summary available.
መጋቢት 07 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ ዘበነ ኃ/ማሪያም - ቀረቡ ተጠሪ፡-
ጉዲዩ የኪራይ ገንዘብን የሚመለከት ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በቀበላ ማህበራዊ ፍርድ ቤት ነው።
ክርክሩ ሲጀመር ከሳሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪዎች ሲሆኑ የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- አመልካች ከተጠሪዎች አንድ ክፍል የፀጉር ቤት ሱቅ በወር ብር 155.00(አንድ መቶ ሃምሳ አምስት ብር) ለመክፈል ተስማምተው፣ተከራይተው ከሐምል 1999 ዓ.ም እስከ ሕዲር 2001 ዓ.ም ድረስ ያለውን ውዝፍ የቤት ኪራይ እዲ ያልከፈለ መሆኑን በመግለጽ በገቡት የኪራይ ውል ግዳታ መሰረት እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስም የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ እና የፍሬ ነገር ክርክር አቅርበዋል።
በፍሬ ነገር ደረጃ በማንሳት የተከራከሩት የኪራይ ውል ከተጠሪዎች ጋር ማድረጋቸውን ሳይክደ ውለ የተደረገው ተጠሪዎች በፀጉር ቤቱ ላይ መብት ሳይኖራቸው በማጭበርበር በመሆኑ አዱስ የኪራይ ውል ከሕጋዊ ባለቤት (ሬድባር ከተባለ የገብረሰናይ ድርጅት) ጋር አድረገው ኪራዩን ለዚሁ ህጋዊ ባለቤት ለሆነው ማህበር በደረሰኝ እየከፈለ ሱቁን የሚሰሩበት መሆኑን ገልፀው ክሱ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ማስረጃ በመስማት ክርክሩን ከመረመረ በኋላ አመልካች የኪራይ ውለን ከሱቁ ህጋዊ ባለቤት ጋር አድርጌአለሁ በማለት የሚያቀርቡት ክርክር ተቀባይነት የላለው፣ህጋዊ ነው የተባለ ድርጅትም ወደ ክርክሩ እንዱገባ ተደርጏ አለመከራከሩ አግባብነት የላለው መሆኑን በመጥቀስ የአመልካችን ክርክር ውድቅ አድርጏ ለኪራይ ገንዘቡ ኃላፉ በማድረግ ብር 2,870.00(ሁለት ሺህ ስምንት መቶ ሰባ ብር) ለተጠሪዎች እንዱከፈለ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለአዱስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል። ከዚያም አመልካች በውሳኔው ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት በሰበር አቤቱታ ለአዱስ አበባ ከተማ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት ቢያቀርቡም ተቀባይነት አላገኙም። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
አመልካች ሰኔ 22 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱት በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። የአቤቱታው ይዘትም ባጭሩ፡- ተጠሪዎች በሱቁ ላይ ሕጋዊ መብት ሳይኖራቸውና የኪራይ ገንዘቡን አመልካች በአዱስ ኪራይ ውል መሰረት ለሕጋዊ አከራይ የኪራይ ገንዘቡን ከፍለው ባለበት ሁኔታ ተጠሪዎች ቀደም ሲል የኪራይ ውል አድርገዋል ተብል የኪራይ ገንዘቡን አመልካች በድጋሚ እንዱከፍለ መወሰኑ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባዋል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው፣አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች ተጠሪዎች ያከራዩኝ የእነርሱ ያልሆነ ቤት ነው እኔ ከቤቱ ትክክለኛ ባለንብረት ጋር የቤት ኪራይ ውል ተዋውዬ ለቤቱ ባለቤት ኪራይ ከፍያለሁ በማለት ካቀረቡት ክርክርና ማስረጃ ታልፍ ለተጠሪዎች የቤት ኪራይ ይክፈለ መባለ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏ ተጠሪዎች ቀርበው ታሕሳስ 21 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሦስት ገጽ ማመልከቻ መልሳቸውን ሰጥተዋል። አመልካች በበኩላቸው ጥር 19 ቀን 2002 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ ማመልከቻ የመልስ መልሳቸውን ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታ መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አኳያ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪዎችንና አመልካች የኪራይ ውል ማድረጋቸውን፣አመልካች ለተወሰነ ጊዜ የኪራይ ገንዘቡን ለተጠሪዎች ከከፈለ በኋላ ማቋረጣቸውን፣አመልካች የኪራይ ገንዘቡን ለተጠሪዎች አልከፍልም በማለት የሚከራከሩት የሱቁ ሕጋዊ ባለቤት አይደለም፣ምንም መብት የላቸውም በማለት ስለመሆኑ ነው። በልላ በኩል ተጠሪዎች ቤቱን ሬድባር ከተባለ የግብረሰናይ ድርጅት ያገኙት መሆኑን ጠቅሰው መከራከራቸውን ተገንዝበናል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤት የአመልካችን ክርክር ውድቅ ያደረገው በአመልካች በኩል የቀረቡት ማስረጃዎች ተቀባይነት የማያገኙበትን ምክንያት በመግለጽ ነው። እንዱሁም አመልካች የኪራይ ገንዘቡን ከፍዬአለሁ የሚለት ድርጅት ወደ ክርክሩ እንዱገባ አለመጠየቁም ተገቢነት የለውም በሚል ምክንያት ነው። ከዚህ በስር ፍርድ ቤት ከተደረገው ክርክርና ማስረጃ እንዱሁም ከስር ፍርድ ቤት የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት በግልጽ መገንዘብ የተቻለው ውሳኔው የተሰጠው በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን የኪራይ ውል መሰረት አድርጏ መሆኑን ሲሆን የኪራይ ውለ በሕጉ አግባብ ውድቅ ባልተደረገበት ሁኔታ አመልካች የተጠሪዎችን የባለቤትነት መብት መሰረት በማድረግ በኪራይ ውለ አልገደድም የሚለበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። በሕጉ አግባብ የተቋቋመ ውል በሕጉ አግባብ እስካልፈረሰ ድረስ በተዋዋይ ወገኖች መካከል አስገዲጅነት አለውና። በመሆኑም የተጠሪዎች የዲኝነት ጥያቄ የኪራይ ውለን መሰረት ያደረገ መሆኑ ተረጋግጦ አመልካች በገቡት ግዳታ ውዝፍ ኪራዩን እንዱከፍሎቸው መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
በበታች ፍርድ ቤቶች በጉዲዩ ላይ የተሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ፀንቷል።
በዚህ ችልት በተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።
ት እ ዛ ዝ
ለሚመለከታቸው አካላት ይፃፍ።