No summary available.
መጋቢት 22 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ወ/ሮ አልማዝ ተሰማ - ጠ/ደሣለኝ ደምሴ ተጠሪ፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው ውል ይፈፀምልኝ ጥያቄን የሚመለከት ነው። አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመሰረቱት ክስ ተጠሪዎች ቤት ሸጠውላቸው አብዛኛውን ገንዘብ የተቀበለ መሆኑን ገልፀው ቀሪውን ክፍያ ተቀብለው ቤቱን ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ቤቱን እንዱያስረክቧቸው ጠይቀዋል። ተጠሪዎችም ለቀረበባቸው ክስ በሰጡት መልስ አመልካች እንዱፈፀምላቸው የሚጠይቁት ውል ከተደረገ 10 አመት ያለፈው በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት የመ/ደረጃ መቃወሚያና ላልች ክርክሮች አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም ውለ የተደረገው የካቲት 18 ቀን 1985 ዓ.ም ሲሆን ክስ የቀረበው ደግሞ ከ14 ዓመት በኋላ ሐምል 6 ቀን 1999 ዓ.ም በመሆኑ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው በማለት ክሱን ውድቅ አድርጓል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት አቤቱታ አቅርበው የስር ፍ/ቤት የሰጠውን ውሳኔ አፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው ተጠሪዎች ቀሪ ገንዘብ አልተከፈለንም በማለት በአመልካች ላይ ክስ አቅርበው ውለ አይፈርስም ተብል ህዲር 15 ቀን 1993 ዓ.ም ውሳኔ ስለተሰጠ ይርጋው ይቋረጣል፣ ውለ ሉፈርስ ይገባል?
አይገባም? የሚለው ክርክር ውጤት ሳያገኝ ውል ሉፈፀም ይገባል? አይገባም? የሚል ክርክር ላቀርብ ስለማይገባ የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት የሚል ነው። ይህ ችልትም ግራ ቀኙ ለክርክር ምክንያት የሆነው የሽያጭ ውል ይፈርሳል አይፈርስም? በሚለው ነጥብ ላይ በፍ/ቤት ሲከራከሩ የቆዩ መሆኑ ከተረጋገጠ የአመልካች የንብረት ልረከብ ጥያቄ በይርጋ ሉታገድ ይገባል የሚለውን ዲኝነት አግባብነት ለማየት ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ አድርጓል። ተጠሪዎችም ቀርበው የቃል ክርክራቸው ተሰምቷል። ችልቱም መዝገቡን ከተያዘ ጭብጥ አኳያ መርምሯል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ክስ የመሰረቱት ከተጠሪዎች ጋር ባደረጉት የሽያጭ ውል መሰረት ተጠሪዎች ቤቱን እንዱያስረክቧቸው ነው። በልላ አነጋገር አመልካች እየጠየቁ ያለት ውል እንዱፈፀምላቸው ነው። በልላ አኳኋን ካልተወሰነ በቀር ውለ እንዱፈፀም ወይም ካለመፈፀሙ የተነሳ ስለሚደርስ ጉዲት ወይም ውለ እንዱፈርስ የመጠየቅ መብት በአስር አመት ይርጋ እንደሚቀር ፍ/ብ/ህ/ቁ 1845 ይናገራል። ተጠሪዎች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት መቃወሚያ አመልካች የውል ይፈፀምልኝ ጥያቄ ያቀረቡት ውለ ከተደረገ ከ10 አመታት በኋላ በመሆኑ ጥያቄው በይርጋ ሉታገድ ይገባል በሚል ነው። ከስር ፍ/ቤት መዝገብ እንደተረዲነውም በግራ ቀኙ መሃከል የሽያጭ ውል የተደረገው የካቲት 18 ቀን 1985 ዓ.ም ሲሆን ክሱ የቀረበው ግን ሐምል 6 ቀን 1999 ዓ.ም ከ14 አመት በኋላ ነው። በመሆኑም ከፍ ሲል በተጠቀሰው ድንጋጌ መሰረት ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል የሚለው መከራከሪያ አግባብነት አለው። በልላ በኩል ግን አመልካች ምንም እንኳን ውለ ከተደረገ 10 አመት ያለፈው ቢሆን ተጠሪዎች የቀረበ የለም ውለ እንዱፈርስላቸው ክስ መስርተው ክርክር ሲደረግ ቆይቶ ውለ አይፈርስም በሚል የመጨረሻ ውሳኔ የተሰጠው ህዲር 15 ቀን 1993 ዓ.ም በመሆኑ ይርጋውን ያቋርጠዋል እንዱሁም ውል ይፈርሳል አይፈርስም የሚለው ጭብጥ ክርክር ላይ እያለ ይኸው ውል ሉፈፀም ይገባል የሚል ክርክር እንዲይቀርብ ፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ 8 ይከለክላል በማለት ተከራክረዋል።
በፍ/ብ/ህ/ቁ. 1845 የተመለከተው የይርጋ ጊዜ ቢኖርም ይህ የይርጋ ጊዜ ግን በተለያዩ ምክንያቶች ሉቋረጥ እንደሚችል የፍ/ብ/ህ/ቁ. 1851 ያስቀምጣል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት ይርጋ ከሚቋረጥበት ምክንያት አንደ ባለገንዘቡ መብቱ እንዱታወቅለት በፍርድ ቤት ክስ አቅርቦ ለባለእዲው አሳውቆ የተገኘ እንደሆነ ነው። በተያዘው ጉዲይ ተጠሪዎች የሚከራከሩት ውል እንዱፈርስ ክስ አቅርበው የነበሩት ተጠሪዎች እንጂ አመልካች ባለመሆናቸው ይርጋው ሉቋረጥላቸው አይችልም በማለት ነው። ከመዝገቡም እንደተረዲነው በእርግጥም ቀደም ሲል ውለ እንዱፈርስ ክስ አቅርበው የነበሩ ተጠሪዎች ናቸው። በቀረበውም ክስ ፍ/ቤቱ የያዘው የሽያጩ ውል ሉፈርስ ይገባል አይገባም የሚለውን ጭብጥ ግን ውለ ሉፈፀም ይገባል አይገባም ከሚለው ጭብጥ ጋር ተያያዥነት ያለው ነው።
ምክንያቱም ውለ ሉፈርስ ይገባል ከተባለ ውጤቱ ግራ ቀኙ ውለን ለመፈፀም የሰሯቸው ስራዎች ሁለ ቀሪ ሆነው ወደነበሩበት መመለስ ሲሆን ውለ የማይፈርስ ከሆነ ደግሞ ውለ እንዱፈፀም ለሚጠይቀው ወገን የውለን መፈፀም እንዱጠይቅ መብት የሚሰጠው በመሆኑ ነው። በመሆኑም የውለን አፈፃፀም በተመለከተ በግራ ቀኙ መካከል የነበረው ክርክር ይርጋውን የሚያቋርጠው ነው። በአጠቃላይ ግራ ቀኙ በውለ መፍረስ አለመፍረስ ክርክር ላይ በነበሩበት ወቅት አመልካች ውል እንዱፈፀምላቸው ክስ ስላላቀረቡ ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው መባለ መሰረታዊ የህግ ስህተት የተፈፀመበት ነው። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
No topics extracted.
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ 6841 መጋቢት 9 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 29 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የአመልካች ክስ በይርጋ ቀሪ ላሆን አይገባም ብለናል። በመሆኑም በፍሬ ጉዲዩ ላይ የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ ሰምቶ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 341(1) መሰረት መልሰናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።