No summary available.
መጋቢት 6 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሃይ ታደሰ ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡-
አመልካቾች በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ተጠሪዎች ሆቴላቸውን ተከራይተው የኪራዩ ዘመን ሲያበቃ ለመመለስ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ተከሰው በፍርድ ሆቴለን ስለመለሱ ከውል ውጪ ሆቴለን ይዘው ለተገለገለበት ጊዜ የኪራይ ገንዘብና ያላግባብ ለበለፀጉበት በበለፀጉበት መጠን እንዱከፍለ ክስ አቅርበው ፍ/ቤቱ ከ2-4 ያለትን አመልካቾች ከክሱ ነፃ በማድረግ አንደኛ አመልካች ከውል ውጪ በሆቴለ ለ86 ወራት በመገልገል ያለአግባብ የበለፀጉበትን ብር 602,000.00(ስድስት መቶ ሁለት ሺህ) ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍለ በመወሰኑና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይህንኑ ውሳኔ በማጽናቱ የቀረበ የሰበር አቤቱታ ነው።
ተጠሪዎች በክሳቸው ዝርዝር አመልካቾች ሆቴለን የውለ ዘመን ካበቃ በኋላ ሆቴለን ያለአግባብ ይዘው በመገልገላቸው ኪሳራ ከፍለው ሆቴለን እንዱለቁ ስለተወሰነባቸው ከኀዲር 2 ቀን 1989 ዓ.ም ጀምሮ ሆቴለን ለተጠሪዎች እስካስረከቡበት ታህሳስ 26 ቀን 1996 ዓ.ም ድረስ የድርጅቱን ኪራይና ወለድ፣መብት ሳይኖራቸው ይዘው ባይጠቀሙ ኖሮ ተጠሪዎች ሉያገኙ ይችለ የነበረውን ጥቅምና ወለድ እንዱሁም ከ1995-1996 ዓ.ም ያገኙትን ትርፍ በአጠቃላይ ብር 2,102,261.35(ሁለት ሚሉዮን አንድ መቶ ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ አንድ ብር ከሰላሣ አምስት ሣንቲም) እንዱከፍሎቸው ጠይቀዋል።
አመልካቾች ለስር ፍ/ቤት በሰጡት መልስ ከ2-4 ያለት አመልካቾች ላይ የቀረበው ክስ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
5 መሰረት ውድቅ ነው፣ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2143 መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው፣ድርጅቱን የያዝነው በመንግስት መመሪያ መሰረት ከኪ.ቤ.አ.ድ ተከራይተን ስለሆነ አላግባብ በልጽጋችኋል ልንባል አይገባም፣ከ2-4 ያለት ጠ/ካሣሁን አሰፊ ቀረቡ አመልካቾች በድርጅቱ ስለመስራታችን የቀረበ ማስረጃ የለም፣ተጠሪዎች አጥተዋል ልባል የሚችለው ኪራይ ብቻ በመሆኑ የታጣ ገቢ ሉጠይቁ አይችለም፣ከውል ውጪ ደረሰ በሚለት ጉዲት ወለድ መጠየቅ አይችለም በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም በአመልካቾች የቀረበውን መቃወሚያ ውድቅ ካደረገ በኋላ ከ2-4 ያለት አመልካቾች ድርጅቱን ይዘው ተገልግለዋል ማለት አይቻልም ተብል በመ/ቁ. 11597 ስለተወሰነና ስለመገልገላቸው ማስረጃ ያልቀረበ በመሆኑ ከክሱ ነፃ ናቸው፣አንደኛ አመልካች ግን በፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤትም ሆነ በፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት የሆቴል ድርጅቱን ያለአግባብ ይዘው በመቆየታቸው ተጠሪዎች ላይ ለሚደረሰው ጉዲት ሃላፉ ስለሆኑ ኪሳራ ሉከፍለ ይገደዲለ ስለተባለ ሃላፉ ናቸው በማለት ከኀዲር 1989 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 27 ቀን 1996 ዓ.ም ድረስ የ86 ወር ብር 602,000.00(ስድስት መቶ ሁለት ሺህ ብር) ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር እንዱከፍለ በማለት ውሳኔ ሰጥቷል። አመልካቾች በዚህ ውሳኔ ላይ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካቾች ክሱ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.2143 በይርጋ ሉታገድ ይገባል፣አንደኛ ተጠሪ ድርጅቱን የተገለገልኩት በመንግስት መመሪያ ከኪ.ቤ.አ.ድ ጋር ባደረኩት የኪራይ ውል በመሆኑ ያለበቂ ምክንያት እንደተገለገልኩ ተደርጏ ያለአግባብ በልጽገሃል ልባል አይገባም፣ተጠሪዎች ቀደም ሲል ሲከሱ ድርጅቱ እስኪለቀቅላቸው ድረስ ኪራይ መጠየቅ ሲችለ ነጥለው ባቀረቡት ክስ ላይ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216 መሰረት ድጋሚ ክስ ሉያቀርብ አይችለም፣ የሰራሁት ከ2-4 ካለት አመልካቾች ጋር ኃ/የተ/የግ/ማህበር ማቋቋም በመሆኑ ብቻዬን ሃላፉ ልባል አይገባም፣ለኪ.ቤ.አ.ድ በወር ብር 4,767.00(አራት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ሰባት) ስከፍል ስለነበር ይኸው ገንዘብ ሉቀነስ ይገባል፣ወለድ ልከፍል አይገባም፣ሉከፈል ይገባል ከተባለም ያለአግባብ መበልጸጌ በፍ/ቤት ከተረጋገጠበት ጊዜ ጅምሮ ላሆን ይገባል፣ከ2-4 የተጠቀሱት አመልካቾች ወጪና ኪሳራ ሉታሰብላቸው ይገባል በማለት ስር ፍ/ቤት ውሳኔ እንዱሻርላቸው ጠይቀዋል። ይህ ችልት አመልካቾች ያቀረቧቸው ቅሬታዎች ለሰበር ችልት ቀርበው እንዱታዩ በማዘዙ ተጠሪዎች ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
No topics extracted.
አመልካቾች ለዚህ ሰበር ችልት ካቀረቡት ቅሬታ አኳያ ይህ ችልት ምላሽ ሉሰጣቸው ይገባል ብል ያመነባቸው፣
ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን ይገባል? አይገባም?
ክሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216/4/ መሰረት በድጋሚ ላቀርብ አይችልም? ይችላል?
አንደኛ አመልካች ብቻቸውን ለክሱ ሃላፉ ናቸው? አይደለም?
ሃላፉ ናቸው ከተባለ መጠኑን አስመልክቶ የተሰጠው ውሳኔ የሕግ ስህተት አለበት? የለበትም?
አንደኛ ተጠሪ ወለድ ሉከፍለ ይገባል? አይገባም?
ከ2-4 ያለት አመልካቾች ወጪና ኪሳራ እንዱከፈላቸው አለመወሰኑ መሰረታዊ ሕግ ስህተት ነው?
አይደለም? የሚለት ናቸው። ችልቱም እያንዲንደን ጭብጥ በየተራ ተመልክቷል።
ይርጋ በተመለከተ ከፍ ሲል እንደተመለከትነው ተጠሪዎች ክስ የመሰረቱት አንደኛ ተጠሪ ከውልና ከሕግ ውጪ የተጠሪዎችን የሆቴል ድርጅት ይዘው በመገልገል ያለአግባብ በመበልፀጋቸው ኪሳራ ከፍለው ድርጅቱን ለቀው እንዱያስረክቡ ስለተወሰነባቸው የፍ/ቤቱ ውሳኔ ካረፈበት ዘመን ጀምሮ ድርጅቱን እስካስረከቡበት ጊዜ ድረስ ያለአግባብ በድርጅቱ በለፀጉበት መጠን እንዱከፍለ ነው። አንደኛ አመልካች ክሱ የቀረበው ነሐሴ 16 ቀን 1996 ዓ.ም ስለሆነ ከነሐሴ 16 ቀን 1994 ዓ.ም በፉት ያለው በፍ/ሕ/ቁ. 2143 መሰረት በይርጋ ቀሪ ነው ሲለ ተከራክረዋል። የስር ፍ/ቤትም ለተያዘው ጉዲይ አግባብነት ያለው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2143 ሳይሆን የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1677/1/ እና 1845 ነው በማለት መቃወሚያውን ውድቅ አድርጓል። ችልቱም ጉዲዩን እንደመረመረው አግባብነት ያለው የትኛው የሕግ ድንጋጌ ነው የሚለው እንዲለ ሆኖ አንደኛ አመልካች እንደሚለት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2143 ነው ቢባል እንኳን ክሱ በይርጋ ቀሪ ላሆን የሚችል አይደለም። ተጠሪዎች ቀደም ሲል በነበረው ክርክር አንደኛ አመልካች ድርጅቱን የውለ ዘመን ካበቃ በኋላ ድርጅቱን ያለአግባብ በመያዛቸው ድርጅቱን እንዱለቁና ኪሳራ እንዱከፍለ ጥቅምት 22 ቀን 1989 ዓ.ም ያቀረቡት ክስ በፍ/ቤት ክርክር ሲደረግበት ቆይቶ በመጨረሻ በጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ያገኘው ሚያዝያ 21 ቀን 1995 ዓ.ም ነው። ከዚህ በኋላ በዚህ መዝገብ የቀረበውን ጉዲይ አስመልክቶ ተጠሪዎች ክስ ያቀረቡት ነሐሴ 16 ቀን 1996 ዓ.ም ነው። ይርጋ ከሚቋረጥባቸው ምክንያቶች አንደኛው ባለገንዘቡ መብቱ እንዱታወቅለት በፍ/ቤት ክስ አቅርቦ ለባለእዲው አስታውቆ የተገኘ እንደሆነ መሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1851/ለ/ ስር የተመለከተ በመሆኑ ተጠሪዎች መብታቸውን ለማረጋገጥ ያቀረቡት ክስ ይርጋውን ስለሚያቋርጠውና በዚህ መዝገብ በቀረበው ጉዲይ ላይ ክስ የቀረበው የቀድሞው ክስ የመጨረሻ ውሳኔ ካገኘ በኋላ ሁለት አመት ሳይሞላው በመሆኑ አንደኛ አመልካች ይርጋውን በተመለከተ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
ክሱ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216/4/ መሰረት ድጋሚ ላቀርብ አይገባም የተባለው በተመለከተ ተጠሪዎች ቀደም ሲል ባቀረቡት ክስ አንደኛ አመልካች የኪራይ ዘመኑ ካበቃ በኋላ የሆቴል ድርጅቱን ይዘው ስለተገለገለ ክስ እስከቀረበበት ግዜ ድረስ ያለውን ኪራዩን ከፍለው እንዱወጡና ክስ ከተመሰረተ በኋላ ላለው ጊዜ የመክሰስ መብታቸው እንዱጠበቅላቸው ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም አንደኛ አመልካች ያለአግባብ የሆቴል ድርጅቱን ስለያዙ ክስ እስከተመሰረተበት ጊዜ ድረስ ያለውን ኪሳራ ሲወስን ከክሱ በኋላ ላለው ጊዜ በሕጉ መሰረት የመክሰስ መብታቸውን ጠብቆላቸዋል። በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 216/2/3/ መሰረት ከሳሽ ክሱን ለማቅረብ ምክንያት የሆኑትን ሁለ አጠቃል ማቅረብ እንዲለበትና ክስ ለማቅረብ ሲችል ሆነ ብል ቀንሶ ባስቀረው ንብረት ላይ ድጋሚ ክስ ለማቅረብ የማይቻል መሆኑን አጠቃላይ መርህ ያስቀምጣል። ይሁን እንጂ ፍ/ቤትን በማስፈቀድ ሉጠየቅ ይገባው ከነበረው ውስጥ ቀንሶ ማስቀረት እንደሚቻልና በከፉል በቀረው መብት ላይም ድጋሚ ክስ ማቅረብ የሚችል ስለመሆኑ ንኡስ ቁጥር 4 ልዩ ሁኔታን አስቀምጧል። በተያዘውም ጉዲይ ተጠሪዎች ከክሱ በኋላ ላለው ጊዜ የመክሰስ መብታቸውን ፍ/ቤቱ የጠበቀላቸው በመሆኑ ቀደም ሲል ሉከሱ ሲገባ ቀንሰው ስላስቀሩ በድጋሚ ሉከሱ አይገባም የሚለው የአንደኛው አመልካች ክርክር ተቀባይነት የለውም።
አንደኛ አመልካች ለደረሰው ጉዲት ሃላፉ ናቸው አይደለም? የሚለውን በተመለከተ ቀደም ሲል ተጠሪዎች ባቀረቡት ክስ አንደኛ አመልካች የተጠሪዎች ሃብት መሆኑን እያወቁ በውል ወይም በሕግ ሆቴለ ላይ ያገኙት መብት ሳይኖር ከተጠሪዎች ፈቃድ ውጪ በእምቢተኝነት ይዘው በመቆየታቸው ተጠሪዎች ራሳቸው ሰርተው እንዱጠቀሙበት ወይም ለአንደኛ አመልካች ባከራዩት መንገድ ለላላ ሰው አከራይተው የኪራይ ገቢ እንዲያገኙበት በማድረግ ጉዲት በማድረሳቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2027/2/ እና 2028 መሰረት በሃላፉነት ሉጠየቁ የሚገባ ከመሆኑም በላይ በፍ/ሕ/ቁ. 2162 መሰረት ኪሳራ ሉከፍለ ይገደዲለ በማለት አንደኛ አመልካች ብቻቸውን ሃላፉነት ያለባቸው መሆኑን የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ውሳኔ ሰጥቷል። በመሆኑም የአንደኛ አመልካች ሃላፉነት ቀደም ሲል ውሳኔ የተሰጠበት ጉዲይ በመሆኑ ብቻቸውን ኪሳራ የመክፈል ሃላፉነት አለባቸው።
የኪሳራውን መጠን በተመለከተ ይህን ነጥብ አስመልክቶ አንደኛ አመልካች ያቀረቡት ክርክር ቤቱን መንግስት ባወጣው መመሪያ መሰረት ከኪ.ቤ.አ.ድ ከታህሣሥ 1 ቀን 1988 ዓ.ም ጀምሮ ተከራይተው ለድርጅቱ በወር ብር 4,767.00(አራት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ሰባት) ሲከፍለ ስለነበር የስር ፍ/ቤት ይህንኑ ገንዘብ ሉቀነስ ይገባ ነበር የሚል ነው። አንደኛ አመልካች የሆቴል ድርጅቱን ያለበቂ ምክንያት ይዘው በመገልገላቸው አላግባብ በበለፀጉበት መጠን ሃላፉ መሆናቸው ተወስኗል። የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ሲሰጥ የኪሳራው መጠን ከደረሰው ጉዲት ጋር ተመጣጣኝ መሆን እንዲለበትና ተጠሪዎች ያጡት ጥቅም በኪራይ መጠን ልክ ታስቦ መሆን እንዲለበት የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት አስቀድሞ መወሰኑን ከግምት በማስገባት ተጠሪዎች የሚገባቸው ድርጅታቸው ከውል ወይም ከህግ ውጪ በአንደኛ አመልካች በመያዙ ምክንያት እነሱ ባጡት ልክና አመልካቹ ራሳቸውን ባበለፀጉበት መጠን ሲሆን ይህም የድርጅቱ የኪራይ መጠን ነው በማለት በወር ብር 7,000.00(ሰባት ሺህ) ታስቦ የ86 ወር ብር 602,000(ስድስት መቶ ሁለት ሺህ) ወስኗል። በልላ ሰው የስራ ድካም ወይም የላላ ሰው ሃብት በሆነ ነገር በመገልግል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው አላግባብ ጥቅም ባገኘበት መጠንና ለባለሃብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው አድራጏቱ ባደረሰው ጉዲት መጠን ለባለሃብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ኪሳራ መክፈል እንደሚገደድ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2162 ስር ተመልክቷል። ተጠሪዎች ላይ የደረሰው የጉዲት መጠን በድርጅቱ ኪራይ መጠን እንደሆነ ቀደም ሲል የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሆነ በዚህ ጉዲይ ፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ወስነዋል። ነገር ግን አንደኛ አመልካች ለታህሣሥ 1 ቀን 1988 ዓ.ም ጀምረው ከኪ.ቤ.አ.ድ ጋር ባደረጉ የኪራይ ውል ለድርጅቱ ብር 4,767.00 ኪራይ ይከፍለ እንደነበር የገለፁትን ተጠሪዎች ክደው አልተከራከሩም። በመሆኑም አንደኛ አመልካች አላግባብ በለፀጉ ልባል የሚችለው ከድርጅቱ የኪራይ መጠን ላይ ለኪ.ቤ.አ.ድ ሲከፍለ የነበሩ ኪራይ ተቀንሶ በልዩነት በሚገኘው የገንዘብ መጠን ነው። 1ኛ አመልካች በአንድ በኩል ለኪ.ቤ.አ.ድ ኪራይ ሲከፍለ ቆይተው በድጋሚ ለተጠሪዎች ገንዘቡን ይክፈለ ማለት አለአግባብ ከበለጸጉበት ገንዘብ በላይ እንዱከፍለ ማድረግ በመሆኑ ከላይ በተጠቀሱት ድንጋጌዎች የተመለከቱት የኪሳራ አከፊፈል ደንብን የሚጥስ ይሆናል። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች አንደኛ አመልካች ያለአግባብ ከበለጸጉበት በላይ እንዱከፍለ መወሰናቸው መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተነዋል።
ወለድን በተመለከተ አንደኛ አመልካች ያለአግባብ በልጽገዋል ተብል ለቀረበ ክስ ወለድ ሉከፈል እንደማይገባና ይገባል የሚባል ቢሆን እንኳን ሉከፈል የሚገባ ያለአግባብ መበልፀጋቸው በፍርድ ከተረጋገጠበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ተከራከረዋል። አንደኛ አመልካች የተጠሪዎች የሆቴል ድርጅት ከሕግና ከውል ውጪ ይዘው በመገልገል ያለአግባብ መበልፀጋቸው በመረጋገጡ ኪሳራ እንዱከፍለ ተወስኖባቸዋል። በመሆኑም ገንዘቡን ከፍለው እስኪያጠናቅቁ ድረስ ወለድ የማይከፍለበት የሕግ ምክንያት የለም። በልላ በኩል እኚሁ ተጠሪ አላግባብ መበልፀጋቸው የተረጋገጠው በዚህ መዝገብ የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ቀደም ሲል የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ሚያዝያ 21 ቀን 1995 ዓ.ም ውሳኔ ሲሰጥ ነው። በመሆኑም የስር ፍ/ቤቶች አንደኛ አመልካች በዚህ ጉዲይ ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ገንዘቡን እንዱከፍለ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የለውም።
ወጪና ኪሣራን በተመለከተ በስር ፍ/ቤት ከሁለት እስከ አራት ያለት አመልካቾች ከክሱ በነፃ በመሰናበታቸው በጉዲዩ ረቺ መሆናቸውን ተገንዝበናል። ነገር ግን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.462 ስር እንደተመለከተው ፍ/ቤቱ በክስ ምክንያት የሚከፈለውን ወጪና ኪሳራ በተመለከተ ሉከፈል የሚገባው መሆን አለመሆኑን፣ማን እንደሚከፍልና ምን ያሕል እንደሚከፈል ፣ከምን ሃብት ላይ እንደሚከፈል በአጠቃላይ ትክክል መስል በሚገመተው ሁኔታ ትእዛዝ መስጠት የሚያስችለው ሰፉ ስልጣን አለው። በመሆኑም የክርክሩን ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማካተት ግራ ቀኙ ወጪና ኪሳራ እንዱቻቻለ መወሰኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ነው ለማለት አላስቻለንም።
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 33915 ሰኔ 28 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 31943 ጥር 15 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሎል።
አንደኛ አመልካች የተጠሪዎችን የሆቴል ድርጅት ያለአግባብ ይዘው የበለፀጉበትን መጠን በወር ብር 7000(ሰባት ሺህ) በመሆኑና ከዚህ ገንዘብ ውስጥ አንደኛ አመልካች ለኪ.ቤ.አ.ድ ሲከፍለ የነበረው ብር 4,767.00 (አራት ሺህ ሰባት መቶ ስልሳ ሰባት) ሉቀነስ ስለሚገባ አንደኛ ተጠሪ የ86 ወራት በወር ብር 2,233.00(ሁለት ሺህ ሁለት መቶ ሰላሳ ሶስት) ታስቦ በጠቅላላው ብር 192,038(አንድ መቶ ዘጠና ሁለት ሺ ሰላሳ ስምንት) ክስ ከቀረበበት ጊዜ ጀምሮ ተከፍል እስከሚያልቅ ከሚታሰብ ህጋዊ ወለድ ጋር ለተጠሪዎች ይክፈለ።
ቀሪው የስር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
በተሻሻለው ውሳኔ መሰረት መፈፀም ይቻል ዘንድ ይህ ችልት ሚያዝያ 13 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው የእግድ ትእዛዝ ተነስቷል።