No summary available.
መጋቢት 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ፍዚያ ሁሴን ተጠሪ፡- አቶ ውብሸት ተ/ወልድ
ተጠሪ በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በአመልካችና በልላ ግለሰብ ላይ በመሰረቱት ክስ በወረዲ 17 ቀበላ 24 ክልል ውስጥ ቁጥር 050 የሆነው ቤት በወር 500.00(አመስት መቶ ብር) ለአመልካች አከራይተው የነበረ ቢሆንም አመልካች ያልከፈለት የቤት ኪራይ መኖሩን፣ የኪራይ ውለ ዘመን ካበቃ በኋላም አመልካች ቤቱን ያለአግባብ ይዘው ስለተጠቀሙ እንዱሁም ቤቱን ለስር ሁለተኛ ተከሳሽ በማስተላለፍ ሁለቱም ያለአግባብ ስለበለፀጉ አመልካች ያልከፈለት የኪራይ ገንዘብ ብር 26,000(ሃያ ስድስት ሺህ) እንዱከፍለ እንዱሁም ሁለቱም ተከሳሶች በቤቱ ያለአግባብ በመበልፀጋቸው ኪሳራ እንዱከፍለ እና ቤቱን እንዱያስረክቧቸው ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ ቤቱ በመንገድ ስራ ምክንያት በመፍረሱ የቤቱን መመለስ አስመልክቶ በቀረበው ጥያቄ ላይ የሚሰጥ ውሳኔ የለም በማለትና አመልካችን በተመለከተ የቀረቡትን ላልች የዲኝነት ጥያቄ ውድቅ በማድረግ አመልካች ከተጠሪ ላይ ቤት ተከራይተው የውለ ዘመን ሲያበቃ ቤቱን መመለስ ሲገባቸው ይዘው ያለአግባብ በመበልፀጋቸው ብር 26,000(ሃያ ስድስት ሺህ) ኪሳራ ይክፈለ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ሁለቱን ወገኖች ሰምቶ የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ አፅንቷል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ሆኖ ቅሬታው በአጭሩ የቤቱ ባለንብረት ነን በማለት ከአመልካች ኪራይ ሲቀበል የነበረው ቀበላ ጣልቃ እንዱገባ ጠይቄ መከልከለ አግባብ ስላልሆነ፣ ውለ ፀንቶ ከሚቆይበት ጊዜ ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት ድረስ 10 አመት ስለሚያልፍ ክሱ በይርጋ ቀሪ በመሆኑ፣ አላግባብ መበልፀግን መሰረት በማድረግ ክስ ለማቅረብ የንብረቱ ባለቤት መሆን ስለሚያስፈልግ የስር ፍ/ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉሻር ይገባዋል የሚል ነው።
ይህ ችልት አመልካች ከቤቱ ባለንብረት ጋር የኪራይ ውል በማድረግ ኪራይ ሲከፍለ የነበረ በመሆኑ በዛው ጉዲይ አላግባብ መበልፀግ በሚል ገንዘብ እንዱከፍለ የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪም ክርክራቸውን በፁሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም ጉዲዩን ለሰበር ችልት ያስቀርባል ከተባለበት ጭብጥና አግባብነት ካለው የህግ ድንጋጌ አኳያ መርምሯል።
ከክርክሩ ሂደት ለክርክር ምክንያት የሆነውን ቤት ባለንብረት ቀበላው መሆኑ፣ ቤቱን በቅድሚያ ከቀበላው የተከራዩት ተጠሪ መሆናቸው፣ አመልካች ቤቱን መጀመሪያ የተከራዩት ከተጠሪ ላይ መሆኑ የተረጋገጠ ፍሬ ነገር ስለመሆኑ ተረድተናል። ከዚህ በኋላ ግን ቀበላው ከተጠሪ ጋር የነበረውን የኪራይ ውል ሰርዞ ቤቱን ለአመልካች ማከራየቱን ተጠሪ ክደው ያቀረቡት ክርክር የለም። በልላ ሰው ድካም ወይም የላላ ሰው ሃብት በሆነ ነገር በመገልገል በቂ ባልሆነ ምክንያት ጥቅም ያገኘ ሰው አላግባብ ጥቅም ባገኘበት መጠንና ባደረሰው ጉዲት መጠን ለባለሃብቱ ወይም ጉልበቱ ለደከመው ሰው ኪሳራ ሉከፍል እንደሚገደድ የፍ/ብ/ህ/ቁ 2162 ይናገራል። በመሆኑም በዚህ ድንጋጌ መሰረት ኪሳራ የሚጠይቀው ሰው የንብረቱ ባለሃብት መሆኑን ማረጋገጥና ተከሳሹ በንብረቱ ያለበቂ ምክንያት መገልገለን ማስረዲት አለበት።
በተያዘው ጉዲይ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት የቀበላው መሆኑ አልተካደም። ተጠሪም በአንድ ወቅት ቤቱን የተከራየ ግለሰብ እንጂ ባለሃብት አይደለም። በልላ በኩል ደግሞ የቤቱ ባለሃብት የሆነው ቀበላው ከተጠሪ ጋር ያደረገውን የቤት ኪራይ ውል አቋርጦ ከአመልካች ጋር ከነሐሴ 1988 ዓ.ም ጀምሮ የኪራይ ውል አድርጓል።
በመሆኑም ተጠሪ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ የቤቱ ላይ የነበራቸው የተከራይነት መብትም ቢሆን አክትሟል። ከዚህ ጊዜ በኋላም ተጠሪ በቤቱ ላይ ያገኙት የተከራይነት መብት ስለመኖሩ ያቀረቡት ክርክር የለም። በተጨማሪም አመልካች በቤቱ ሲገለገለ የቆዩት ከቤቱ ባለቤት ከሆነው ቀበላ ተከራይተው በመሆኑ በቤቱ ያለበቂ ምክንያት ተገልግለዋል ለማለት አይቻልም። በአጠቃላይ አመልካች በቤቱ ያለበቂ ምክንያት ያለአግባብ መገልገል በልጽገዋል በማለት ተጠሪ ያቀረቡት ክስ ከፍ ሲል በተገለጹት ምክንያቶች ተቀባይነት የለውም። የስር ፍ/ቤትም ተጠሪው በአንድ ወቅት ቤቱን ከቀበላ ተከራይተው ለአመልካች ማከራየታቸውን ብቻ በመመልከት አመልካች ያለአግባብ በልፅገዋል ሲል ብር 26,000(ሃያ ስድስት ሺህ) እንዱከፍለ የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል። በመሆኑም ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
No topics extracted.
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 6 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ህዲር 5 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
አመልካች አለአግባብ በልፅገዋል ልባል ስለማይችል ብር 26,000(ሃያ ስድስት ሺህ) ለተጠሪ ሉከፍለ አይገባም ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
መዝገቡ ተዘግቷል። ለመዝገብ ቤት ይመለስ።