No summary available.
መጋቢት 22 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ ሐጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ ወንድወሰን ጥሩነህ ቀረቡ ተጠሪ፡- የወ/ሮ አሰገደች ካሣሁን ወራሽ ሄኖክ ሣሙኤል - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የኪራይ ቤትን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ አመልካች ባሁኑ ተጠሪ ላይ በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ጥቅምት 08 ቀን 2000 ዓ.ም በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም ባጭሩ፡- በቀድሞው አጠራር በወረዲ 21 ቀበላ 01 (ባሁኑ አጠራር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበላ 15) ቁጥር 288/45 የሆነውን ቤት ከሳሽ የሚያስተዲድረው ቤት አካል የሆነውን ቤት ተጠሪ ክሱ በስር ፍርድ ቤት እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ይዘው እየተጠቀሙ መሆኑን፣ቤቱን እንዱያስረክቡ ሲጠየቁም ለማስረከብ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸውን ገልጾ ቤቱን እንዱያስረክቡ፣ቤቱን እስኪያስረከቡ ያለውን ኪራይ እና በዚህ ክስ ምክንያት የወጣውን ወጪና ኪሳራ እንዱከፍለ እንዱወሰንለት ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። የአሁኑ ተጠሪም ለክሱ በሰጠው መልስ አውራሼ ቤቱን ተከራይታ ስትኖርበት የነበረ ሲሆን ኪራዩን ባግባቡ እየከፈልኩ የምኖርበት ነው፣አመልካች ቤቱን ልቀቅ ሲል ያቀረበው ምክንያትም የለም፣የሰጠኝ ተለዋጭ ቤትም የለም፣ስለሆነም ተወልጄ ያደግሁበት ቤት እንድለቅ የቀረበው ክስ አግባብ ስላለሆነ ውድቅ ላሆን ይገባል ሲል ተከራክሯል። ጉዲዩን በመጀመሪያ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር በመመርመር በአመልካችና በተጠሪ መካከል የአከራይ ተከራይ ግንኙነት መጀመሩን፣ አመልካች ይህ ሆኖ እያለ ተጠሪን ቤቱን ልቀቅ የሚልበትን ምክንያት ሳይገልጽ ቤቱን እንዱለቅለት ያቀረበው የዲኝነት ጥያቄ አግባብነት እንደላለው በምክንያትነት በመያዝ ተጠሪ ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ቤት የሚያስረክብበት ምክንያት የለም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ሙለ በሙለ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ ነሐሴ 28 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ ሁለት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የለም የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ የኪራይ ውለን ለማቋረጥ በመጠየቁ ውለ ሉቋረጥ የተፈለገበት ምክንያት አልተገለፀም በሚል አይቋረጥም ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጏ ተጠሪ ቀርበው የጽሐፍ መልሳቸውን ሰጥተዋል። የአመልካች ነገረፈጅም የመልስ መልስ ሰጥተዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ ሉመረመር ይገባል ተብል ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።፡ ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አከራካሪው ቤት ባለቤትነቱ የመንግስት ሆኖ የሚያስተዲድረው የአሁኑ አመልካች መሆኑን፣ቤቱን በተከራይነት የአሁኑ ተጠሪ ወላጅ እናት የሆኑት ሟች ወ/ሮ አሰገደች ካሳሁን ይዘው ሲጠቀሙት የቆዩ መሆኑን፣ተጠሪም በቤቱ በቤተሰብነት የኖሩበት ከመሆኑም በላይ አውራሻቸው ሲሞቱ ኪራዩን እየከፈለ መጠቀም መቀጠላቸውን፣አመልካች ለተጠሪ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ ቤቱን እንዱያስረክቡ ጥያቄ ቢያቀርብም ተጠሪ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ክስ ሉመሰርት የቻለ መሆኑን ነው። የስር ፍርድ ቤት እነዚህን ፍሬ ነገሮች አረጋግጦ የአመልካችን ክስ ውድቅ ሉያደርግ የቻለው አመልካች ቤቱን ተጠሪ እንዱለቅ ጥያቄ ሲያቀርብ ቤቱን ተጠሪ የሚለቁበትን ምክንያት አልገለፀም በሚል ምክንያት ነው። ተጠሪ አውራሽ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ በኋላ በአመልካችና በተጠሪ መካከል ጊዜው ያልተቆረጠለት የኪራይ ውል በመካከላቸው መመስረቱንም ከክርክር ሂደት መገንዘብ ተችሎል። በመሆኑም ምላሽ የሚያስፈልገው አቢይ ጥያቄ የዚህ አይነት የኪራይ ውል የሚቋረጠበት አግባብ እንዳት ነው? የሚለው ነው።
የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2966/1/ ሲታይ ላልተወሰነ ጊዜ የተደረገ የኪራይ ውልን አከራዩ ተከራዩን ወይም ተከራዩ አከራዩን በማስታወቅ ሉያልቅ እንደሚችል ደንግጓል። በዚህ ድንጋጌ መሰረት በአከራዩም ሆነ በተከራዩ ላይ በሕጉ በተጣለው ግዳታ ማስታወቂያ መስጠት ሲሆን የዚሁ ድንጋጌ ንኡስ ቁጥር ሁለት ደግሞ ውለ አለቀ የሚባለው በኪራዩ ውል ወይም በሕጉም መሰረት ተከታዩ የኪራይ ዘመን ዋጋ በሚከፈልበት ቀን ወይም የኪራዩ ውል ስለማለቅ ማስታወቁን ባይሰጥ ኑሮ ኪራዩ ሉከፈልበት ይገባው በነበረበት ቀን ስለመሆኑ ደንግጓል። ከእነዚህ ድንጋጌዎች ይዘት እና መንፈስ የምንገነዘበው ነጥብ ተከራይ እና አከራይ የኪራይ ውልን ማስታወቂያ በመስጠት ለማቋረጥ የሚችለ መሆኑን እንጂ ውለ የሚቋረጥበትን ምክንያት ጭምር የመግለጽ ግዳታ ያለባቸው አለመሆኑን ነው። በመሆኑም የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች የኪራይ ውለን ለማቋረጥ የሚፈልግበትን ምክንያት ጭምር መግለጽ ይኖርበታል በማለት ክሱን ወድቅ ያደረጉት በሕጉ አግባብ ያልተጣለበትን ግዳታ በመጨመር ሁኖ ስለተገኘ ውሳኔው ከላይ የተጠቀሰውን ድንጋጌ መንፈስ ያላገናዘበ፣የአመልካችን የመንግስት ቤቶችን የማስተዲደር ስልጣን ያጣበበ ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ስለተገኘ ተከታዩን ወስነናል።
No topics extracted.
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 69842 ጥቅምት 02 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 62626 ሰኔ 04 ቀን 2000 ዓ.ም የፀናው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽሯል።
ተጠሪ በቀድሞው አጠራር በወረዲ 21 ቀበላ 01 (ባሁኑ አጠራር በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ቀበላ 15) ቁጥር 288/45 የሆነውን ቤት ለአመልካች እንዱያስረክቡ፣ቤቱን እስኪያስረክቡ ያለውን ኪራይ እንዱከፍለ ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል፡