No summary available.
የካቲት 25 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሃይ ታደሰ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ወ/ሮ እመቤት ደርበው - የቀረበ የለም ከጠ/ሃይለ አግዘው ጋር ቀረቡ መ/ሰጪ፡- አቶ ታደለ ሰዲማ - የቀረበ የለም ከተባለ በኋላ ጠ/ሰመረ አሰፊ ቀረቡ በዚህ መዝገብ የቀረበልንን ጉዲይ ተመልክተን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ከክርክሩ ሂደት ለመገንዘብ እንደቻልነው አሁን በቀረበልን ጉዲይ መነሻ የሆነው የአሁን አመልካች ጣልቃ ገብ በመሆን በሆሳእና ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አቅርበውት የነበረው የውል ይፍረስልኝ ማመልከቻ ነው። አመልካችዋ ውል ይፍረስልኝ በማለት ጥያቄ ያቀረቡት ያለእርሳቸው ፈቃድ ባለቤታቸው የጋራ ንብረት የሆነውን ድርጅት ለአሁኑ መልስ ሰጭ ሸጦአል በማለት ነው። ጉዲዩን የተመለከተው ፍ/ቤት በውለ አፈፃፀም መሟላት የሚገባቸው የፍርም ቅድመ ሁኔታዎች እንደነበሩ ካረጋገጠ በኋላ ከውለ መፈፀም በኋላ የተፈጠሩ ላልች በርካታ ጉዲዮችን ግምት ውስጥ በማስገባት ተዋዋዮች ወደ ነበሩበት ይመለሱ ልባል አይገባም በማለት ውሳኔ ሰጠ። የአሁን አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ቢያቀርቡም ይግባኝ የቀረበለት የሐድያ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤትም ይግባኙን አጽንቷል። ይግባኝ ፍ/ቤቱ ውሳኔው ሲያፀና ከውለ መፈፀም በኋላ ድርጅቱን የገዛው የአሁን መልስ ሰጪ በርካታ ንብረት ሲያሰፍሩበት አመልካች በአጠገቡ ስለሚኖሩ ያውቁ እንደነበርም አትቷል። ከክርክሩ ሂደት አሁን አከራካሪ የሆነው ሽያጭ የተፈፀመው በ1992 ዓ.ም ሲሆን ጣልቃ ገብ ይፍረስልኝ ብለው የጣልቃ ገብነት ጥያቄ ያቀረቡት የአሁኑ መልስ ሰጪ ስም ይዛወርልኝ በማለት ሐምል 11 ቀን 1997 ባቀረቡት ማመልከቻ መሰረት በተመሰረተው ክስ ነው።
ለዚህ ፍርድ ቤት የቀረበው የሰበር ማመልከቻ እንዱፈርስ ጥያቄ የቀረበበት የወፍጮ የሽያጭ ውል ሕጉ የሚጠይቀውን የሁለቱም ተጋቢዎች ፈቃድና የምዝገባ ፍርማሉቱ አለማሟላቱ ከተረጋገጠ ላላ ምክንያት በማቅረብ ተዋዋዮቹ ወደነበሩበት ሉመለሱ አይገባም መባለ መሰረታዊ የሕግ ስህተት መፈፀሙን የሚያመለክት ነው የሚል ነው።
መልስ ሰጪ በጽሐፍ ባቀረቡት መልስ የፍርማሉቱ ጥያቄውንም ሆነ የፈቃድ ጉዲዮችን ከውለ በኋላ ከተደረገው ኢንበቨስትመንት ጋር በማነፃፀር ውለ አይፈርስም ተብል መወሰኑ አግባብ ነው ስለዚህ ውሣኔው ሉፀና ይገባል በማለት ተከራክሯል።
እኛም ውለ ከተፈፀመ በኋላ በተገዛው ንብረት ላይ የተደረገውን ለውጥ ግምት ውስጥ በማስገባት ውለ እንዱፀና መወሰኑ አግባብ መሆን አለመሆኑን አግባብነት ካላቸው የሕጉ ድንጋጌዎችና ይህ ፍርድ ቤት ቀደም ብል ከሰጣቸው የሕግ ትርጉም ውሣኔዎች ጋር በማያያዝ ተመልክተናል። በመሰረቱ የፈቃድ ወይም የፍርም ጉድለት ያለበት ውል ሕጉ መብት በሚሰጠው ሰው የይፍረስልኝ ጥያቄ ሲቀርብብት ፈራሽ እንደሚሆን በመርህ ደረጃ በሕጉ በግልጽ የሰፈረ ጉዲይ ነው። በመሆኑም ውለ በሚፈፀምበት ወቅት ጉድለት የነበረበት መሆኑ ከተረጋገጠ ውለ እንዱፈርስና ባለጉዲዮች ወደነበሩበት ሁኔታ እንዱመለሱ ማዘዝ ከፍርድ ቤት የሚጠበቅና ሕጉም የሚያዘው መርህ ነው። /የፍትሐብሕር ሕግ ቁ.1815 ይመለከታል/ ሆኖም ይህ ተዋዋዮችን ወደነበሩበት የመመለስ መርህ ተፈፃሚ ማድረግ የማይቻል ከሆነ ወይም ለአንደኛው ተዋዋይ ከፍተኛ ጉዲት የሚያስከትል ከሆነ ውለን ለመፈፀም የተከናወኑ ተግባራት ፀንተው እንደሚቆዩ የፍትሐብሕር ሕግ አንቀጽ 1817 በግልጽ ደንግጏታል። በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ውለ ሲመሰረት ጉድለት የነበረበት መሆኑን ቢያረጋግጥም ውለን ማፍረስ የማይቻል ወይም ለአንደኛው ወይም ለሁለም ወገን ከፍተኛ ጉዲት የሚያስከትል መሆኑን በሂደት ከተረዲ ተዋዋይ ወገኖች ወደነበሩበት ሉመለሱ አይገባም በማለት ትእዛዝ ላሰጥ ይችላል። ይህ ትርጉም ይህ የሰበር ችልት በላልች በርካታ ጉዲዮችም የተከተለው ነው።
አሁን በቀረበልን ጉዲይም ፍ/ቤቱ የተከተለው ይህን መርህ ነው። ውለ ሲመሰረት ጉድለት እንደነበረበት አረጋግጧል። በልላ በኩል ውለ በ1992 ዓ.ም ከተፈፀመ በኋላ በመልስ ሰጪ በኩል ተጨማሪ ንብረት የታከለበት መሆኑን ግንዛቤ ውስጥ አስገብቷል። አመልካችም በሰበር አቤቱታቸው ጭምር በተሸጠው ንብረት ላይ ተጨማሪ ግንባታ የተካሄደበት መሆኑን አይክደም። ሁኔታው ይህ ከሆነ ደግሞ ፍ/ቤቶች የውለ መፍረስ የሚያስከትለው ጉዲት በዝርዝር ገልጸው ውለን ከማፍረስ ይልቅ ፀንቶ እንዱቆይ ማዘዛቸው የሕጉን አንቀጽ 1817/1/ መንፈስና ግልጽ ቃል የተከተለ እንጂ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተሰራበት ውሳኔ ሰጡ ለማለት የሚያበቃ ሆኖ አላገኘነውም በመሆኑም በዚህ ጉዲይ የሥር ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሳኔ ሉፀና የሚገባው ሆኖ አግኝተነዋል።
No topics extracted.
በደ/ብ/ብ/ሕ/መ በሃዱያ ዞን የሆሳእና ከተማ አስተዲደር የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በመ/ቁ. 0024/98 እና የሐድያ ዞን በመ/ቁ. 04688 የሰጡት ውሳኔ ፀንቷል።
ግራ ቀኙ የራሳቸውን ወጪ ይቻለ።