No summary available.
የካቲት 25 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- የኮንስትራክሽንና ቢዝነስ ባንክ አ/ማ - ነ/ፈጅ አስቴር በቀለ ቀረበች ተጠሪዎች፡-
የሰበር አቤቱታ የቀረበው የሥር ፍ/ቤት የወለድ ስላት እስከቀረበበት ቀን የተጠየቀውን ዲኝነት አልፍ ውሳኔ ከተሰጠበት በማለት የሰጠው ውሳኔ ግራ ቀኙ ያደረጉትን ውል ባለማገናዘብ የተሰጠ በመሆኑ እንዱታረም የሚል ነው።
ለክርክሩ መነሻ የሆነው ጉዲይ አመልካች ለተጠሪዎች የሰጠው የብድር ገንዘብ በከፉል ሳይከፈል የቀረ ስለመሆኑ ቀሪውን ገንዘብ ከልዩ ልዩ ወጪዎች ጋር እንዱከፍለ እንዱወሰን ዲኝነት በመጠየቁ ነው። የፋዳራል የመ/ደረጃ ፍ/ቤት ክስ የቀረበበትን ገንዘብ ብር 370,295.81 ውሳኔ ከተሰጠበት ነሐሴ 15/1999 ዓ.ም ጀምሮ ከሚታሰብ 10.5% ወለድ፣ለዲኝነት የተከፈለውን ብር 9,150.09 እና ወጪዎች በቁርጥ ብር 200.00 ብር ጋር በአንድነት እና በነጠላ እንዱከፍለ ውሳኔ ሰጥቷል።
አመልካች ወለደ መታሰብ ያለበት ክስ ከቀረበበት ግንቦት 22 ቀን 1999 ዓ.ም መሆን ይገባዋል ሲል የሥር ፍ/ቤት ሥህተት እንዱታረም ለከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ቢሆንም የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ባለመቀበል የሥር ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል።
አመልካች ለዚህ ሰበር ሰሚ ችልት ባቀረበው አቤቱታ በግራ ቀኙ መካከል በተደረገው የብድር ውል እዲው ተከፍል አለቀ ድረስ ያለማቋረጥ ከነወለደ ለመክፈል መስማማታቸው ጠቅሶ የሥር ፍ/ቤት ወለደን ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን እንዱታሰብ በማድረጉ አመልካች በልዩነት ብር 8,841.45(ስምንት ሺህ ስምንት መቶ አርባ አንድ ብር ከአርባ አምስት ሣንቲም) እንዲያገኝ አድርጓል በሚል ይኸው እንዱታረም አመልክቷል።
ሰበር ሰሚው ችልትም የአመልካች የዲኝነት ጥያቄ በሥር ፍ/ቤት የታለፈው በአግባቡ ስለመሆን አለመሆን ለመመረመር ተጠሪዎች እንዱቀርቡ አዟል። ተጠሪዎች በጋዜጣ ጥሪ ተደርጏላቸው ስላልቀረቡ ክርክሩ በላለበት ተሰምቷል።
የአመልካችን አቤቱታ ከሕጉ ጋር አገናዝበን መርምረናል። እንደመረመርነውም አመልካች የዋናው ገንዘብ ወለድ ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ እንዱታሰብ ዲኝነት ጠይቆ ሳለ የሥር ፍ/ቤት ያለፈው የተለየ ምክንያት ያለው ስለመሆኑ በውሳኔው ያልጠቀሰ መሆኑን ከመዝገቡ ተረድተናል።
በመሰረቱ የገንዘብ ብድር ውል በግራ ቀኙ መካከል ሲደረግ ወለደን ጨምሮ ለመክፈል ስምምነት የተደረገ ስለመሆኑ አላከራከረም። ተጠሪዎችም በሥር ፍ/ቤት የተጠየቀውን ገንዘብ ወለድ የማይከፍለበት ምክንያት ስለመኖሩ አላስረደም። ይህ ሁኔታ በላለበት የሥር ፍ/ቤት ወለደ መታሰብ ያለበት ውሳኔ ከተሰጠበት ቀን ነው ሲል የደረሰበት ድምዲሜ ከግራ ቀኙ ውል እና በተጠሪዎችም ባልቀረበ ክርክር መነሻ በመሆኑ አግባብነት ያለው አይደለም። ግራ ቀኙ ባደረጉት የገንዘብ ብድር ውል ተጠሪዎች ከነወለደ ሳያቋርጡ ለመክፈል ግዳታ የገቡ በመሆኑ ስለውልች በተደነገገው ፍ/ብ/ሕግ ቁ. 1731 እና 2478 መሰረት ወለድንም ጭምር የመክፈል ግዳታ አለባቸው። ወለደንም ጭምር ከጅምሩም መክፈል ያለባቸው ስለመሆኑ በውለታቸው የተመለከተ መሆኑ ከታወቀ አመልካች ቅጣት 3% ጭምር ክስ ከቀረበበት ቀን ጀምሮ እንዱታሰብ የጠየቀውን ዲኝነት የሥር ፍ/ቤት ማለፈ ያላግባብ በመሆኑ እና በዚህ ረገድ የግራ ቀኙን ስምምነት ያላገናዘበ በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስሕተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኘተናል። ስለዚህም ወለድን አስመልክቶ አመልካች እስካቀረበበት ከግንቦት 22 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ 10.5% ወለድ እንዱታሰብ መወሰን ሲገባው ውሳኔ ከተሰጠት ቀን ማለትም ነሐሴ 15 ቀን 2001 ዓ.ም ጀምሮ እንዱታሰብ በመወሰኑ በልዩነት አመልካችን ብር 8,841.45(ስምንት ሺህ ስምንት መቶ አርባ አንድ ብር ከአርባ አምስት ሣንቲም) ማሳጣቱ ስህተት በመሆኑ የሥር ፍ/ቤቶች ውሳኔ ረገድ ሉታረም ይገባል ብለናል።
ተከታዩን ውሳኔ ሰጥተናል።
የፋ/የመ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 02175 የሰጠው ፍርድ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 03481 የሰጠው ፍርድ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት በከፉል ተሻሽሎል።
No topics extracted.
ተጠሪዎች ያልከፈለትን ቀሪ የብድር ገንዘብ ወለድ ማለትም ሥር ፍ/ቤት ክስ ከቀረበበት ከግንቦት 22/1999 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 15 ቀን 2001 ዓ.ም ድረስ ያለውን ብር 8,841.45 (ስምንት ሺህ ስምንት መቶ አርባ አንድ ብር ከአርባ አምስት ሳንቲም) በሥር ፍ/ቤት ከተወሰነው ገንዘብ ጋር በአንድነት እና በነጠላ እንዱከፍለ ወስነናል።
በዚህ ችልት በተሻሻለው ውሳኔ መሰረት እንዱያስፈጽም ለሥር ፍ/ቤት ይፃፍ። መዝገቡ ተዘግቷል።
ይመለስ።