No summary available.
የሰ/መ/ የካቲት 11 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካች፡- ወ/ሮ ስንቄ መስፍን - ጠበቃ ካሣሁን አሰፊ ቀረቡ ተጠሪ፡- የመንግስት ቤቶች ኤጀንሲ - ነ/ፈጅ ጅፊር አባገሮ ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የኪራይ ውልን መሰረት ያደረገ ሲሆን ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ ተጠሪ በአሁኑ አመልካች ላይ መጋቢት 11 ቀን 2000 ዓ.ም በመሰረተው ክስ መነሻ ነው። የክሱ ይዘትም በቀድሞ ወረዲ 02 ቀበላ 09 ውስጥ የሚገኘውን ቁጥሩ 026/3 የሆነ የተጠሪን ቤት ከአመልካች ጋር መጋቢት 01 ቀን 1998 ዓ.ም በተጻፈ የኪራይ ውል በወር ብር 629.00(ስድስት መቶ ሃያ ዘጠኝ ብር) ተጠሪ ሉከፍለና ከአከራይ ፈቃድ ውጪ ግንባታ ላያከናውኑ ግዳታ ገብተው (በመግባት) ውል ማድረጋቸውን ሆኖም አመልካች በውለ ላይ የገቡትን ግዳታ በመጣስ የተጠሪን የጽሐፍ ፈቃድን ሳያገኙ የቀድሞውን ማቴሪያል በመቀየር ሸክላ አልብሰው እንደተገኙና እንዱሁም የጭስ ቤቱን ጣሪያ ከፍታ ጨምረው መሰራታቸውን ዘርዝሮ ውለ ተቋርጦ ቤቱን እንዱያስረክቡ እስኪያስረክቡ፣ ድረስ የሚኖረውን ኪራይም እንዱከፍለ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ ነው። አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ በቤቱ የንግድ ድርጅት እንደመሆኑ መጠን ፅዲቱ እንዱጠበቅለት በማሰብ ተጠሪን በተደጋጋሚ እንዱያስጠግንና እንዱያድስ ጠይቀው በተገቢው ጊዜ ተገቢው ምላሽ ስላልተሰጣቸው በሆቴለ ስራ አስፈላጊ የሆነ ስራ መስራታቸውንና ይህንም ስራ በቀበላ አስተዲደሩ አግባብነት ያለው መሆኑ መረጋገጡን ገልፀው ግንባታው የኪራይ ውለን ለማቋረጥ በቂ ምክንያት አይደለም ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ በመመርመር የኪራይ ውለ ተቋርጦ አመልካች ቤቱን ሉያስረክቡ ይገባል እስኪያስረክቡ ድረስ ያለውን ኪራይም ሉከፍለ ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ አመልካች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የስር ፍርድ ቤት ውሳኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ጠበቃ ሰኔ 02 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈት ሦስት የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካች በቤቱ ላይ አድርገዋል የተባለው ተግባር/ሥራ/ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን የኪራይ ውል ለማቋረጥ የሚያበቃ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ነጥብ ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ ያስቀርባል ተብል የግራ ቀኙ የቃል ክርክር ሕዲር 09 ቀን 2002 ዓ.ም በዋለው ችልት ተሰምቷል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ከሰበር ችልት ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ ከአመልካች ጋር ያቋቋመው የኪራይ ውለ እንዱቋረጥ ዲኝነት የጠየቀው አመልካች በኪራይ ውለ የገቡትን ግዳታ በመጣስ ያለተጠሪ ፈቃድ ግንባታ አከናውነዋል በሚል መሆኑን አመልካች ግንባታውን ማከናወናቸውን ሳይክደ የተከናወነው ግንባታ ቤቱ ለሆቴል ስራ አገልግልት የሚውል በመሆኑ ለስራው አስፈላጊ መሆኑን ይህም በቀበላው ጽ/ቤትም ታይቶ ተገቢነቱ መረጋገጡን ማስረዲታቸውን ነው። እንግዱህ በኪራይ ውለ ላይ አመልካች በቤቱ ላይ የሚያከናውኑትን ግንባታ ለተጠሪ በቅድሚያ የማሳወቅ ግዳታ ያለባቸው መሆኑ አከራካሪ አለመሆኑን ተገንዝበናል። አከራካሪው ለኪራይ ውለ መቋረጥ ምክንያት የሚሆነው ምን አይነት ግንባታ ነው? የሚለው ነው። በተጠሪና በአመልካች መካከል የተደረገው የኪራይ ውል ማንኛውም ግንባታ የኪራይ ውለን ለማቋረጥ ምክንያት ስለመሆኑ እንደሚያሳይ ተጠሪ ገልፆ አለመከራከሩን የክርክሩ ሂደት ያሳያል። እንዱህ ከሆነ ጉዲዩ በጠቅላላ የውል ሕግ ድንጋጌዎች ስር የተመለከቱትን ስለውልች አተረጓጎም ደንቦችንና ኪራይን በተመለከተ የተደነገጉትን ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ እልባት ሉሰጠው የሚገባው ነው። በዚህም መሰረት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1732 ድንጋጌ ሲታይ በተዋዋዮች መካከል ሉኖር የሚገባውን የቅንነትንና የመተማመንን ግንኙነት መሰረት በማድረግና በጉዲዮቹ ውስጥ ያለውን ልማዲዊ ስርዓት በመከተል ውልች በቅን ልቦና ሉተረጎሙ እንደሚገባ ያሳያል። በልላ በኩል የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2953 ተከራዩ ሉያድሳቸው የሚገባውን የተከራያቸውን ቤቶች በራሱ ኪሳራ ለማደስ የሚገደድ ስለመሆኑ ሲደነግግ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2954 የማደስ ትርጉምን አስቀምጧል። ይኸውም ተከራዩ ቤቶችን ማደስ ይገባዋል የተባለትን(የሚባለውን) በኪራዩ ውል ተከራዩ ይፈጽማቸዋል ተብል የተወሰኑትን ስለመሆኑ ተቃራኒ የሚሆን ስምምነት ከላለ በቀር ቤቶችን የማደስ ስራዎች ተብለው የሚቆጠሩት ደግሞ መዝጊያዎችን ወይም መስኮቶችን፣ የቤት ወለልችን ወይም ንጣፍችን፣ የውሃ መቅጃ መዘውሮችንና የውሃ መስደጃዎችን ለማደስ አስፈላጊ የሆኑ ተግባሮችን እንደሆነ እንደዚሁም በተከራየው ቤት ለመጠቀም አስፈላጊ የሆኑትን ቤቶችን የማፅዲትና በደንብ የመያዝ ስራዎች ቤቱን እንደማደስ ያለ ተግባሮች ስለመሆናቸው ይደነግጋል።
No topics extracted.
በተያዘው ጉዲይ አመልካች ያከናወኗቸው የግንባታ ስራዎች በቤቱ ላይ መሰረታዊ ለውጥ ያመጡ ስለመሆኑ ያልተረጋገጠ ሲሆን በስር ፍርድ ቤት የተረጋገጠው ግንባታው ለሆቴለ ስራ አስፈላጊ ይልቁንም በሆቴለ ተነስቶ ለነበረው የእሳት አደጋ ተገቢውን ጥንቃቄ ለማድረግ የሚያስችል ስለመሆኑ ተረጋግጧል።
በመሆኑም አመልካች ያከናወኑት የግንባታ ስራ የኪራይ ውለን ለማቋረጥ ምክንያት ላሆን የማይችል በመሆኑ የስር ፍርድ ቤቶች ውለን በኪራይ ውለ ላይ የተመለከተውን “ግንባታ” የሚለውን ቃል ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1732፣ 2953 እና 2954 ድንጋጌዎች ይዘት እና መንፈስ ማገናዘብ ሲገባቸው ውለ ሉቋረጥ ይገባል ሲለ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ ሰኔ 20 ቀን 2000 ዓ.ም ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ መጋቢት 28 ቀን 2001 ዓ.ም የፀናው ውሣኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 348(1) መሰረት ተሽሯል።
አመልካች በቤቱ ላይ አድርገዋል የተባለው ተግባር/ሥራ/ በግራ ቀኙ መካከል የተደረገውን የኪራይ ውል ለማቋረጥ የሚያበቃ አይደለም ብለናል። የኪራይ ውለ በልላ ሕጋዊ ምክንያት እስካልተቋረጠ ድረስ አመልካች ቤቱን ሉያስረክቡ አይገባም ብለናል።
ለክርክሩ የወጣውን ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።