No summary available.
የሰ/መ/ ጥር 19 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሃይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ አልማው ወላ አመልካች፡- ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ - ጠበቃ ውብሸት ሥ/ጊዮርጊስ ቀረቡ ተጠሪ፡- የቦንጋ ማዘጋጃ ቤት ከፊ ዞን ዐ/ህግ - ነ/ፈጅ ደበበ ወንድሙ ቀረቡ
ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው በከፊ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ነው። የአሁኑ ተጠሪ ለፍ/ቤቱ ባቀረበው ክስ አመልካች ዘመናዊ ሆስፒታል ለመገንባት ቦታ ጠይቀው 1,931 ካ.ሜ ቦታው ተሰጥቷቸው ግንባታውን ስላቋረጡ ውለ ተሰርዞ ግንባታው በራሳቸው ወጪ አፍርሰው ቦታውን ለተጠሪ እንዱያስረክቡ እንዱሁም ከ1996 ዓ.ም - 1999 ዓ.ም የቦታና የቤት ግብር ብር 52,782.35(ሃምሳ ሁለት ሺህ ሰባት መቶ ሰማንያ ሁለት ሺህ ብር ከሰላሳ አምስት ሳንቲም) እንዱከፍለ በማለት ጠይቋል። አመልካች ለክሱ በሰጡት መልስ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ካቀረቡ በኋላ ለዋናው ጉዲይ በሰጡት መልስ ግንባታው የተቋረጠው በፕሮጀክቱ ሳይት ላይ ተጠሪ የኮንቴነር ሱቆች በማቆሙና ይህም የግንባታ እቃዎች በመኪና ተጭነው እንዲይገቡና እንዲይራገፍ እንቅፊት በመሆናቸው በተጨማሪም የግንባታ እቃ ዋጋ በመናሩ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑን፣ ለሆስፒታል አገልግልት ለሚውል ጅምር ቤት ፕሮጀክቱ ሳይጠናቀቅ የቦታና የቤት ግብር ሉከፈል የማይገባ መሆኑንና በግራ ቀኙ መሃከል ውል ባለመኖሩ ክሱ ውድቅ እንዱደረግላቸው ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም ክርክሩን መርምሮ አመልካች ሳይት ፕላኑ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ ግብር የመክፈል ሃላፉነት አለባቸው፣ የግንባታ ዕቃዎች ወደ ግቢው በመኪና ተጭኖ እንዲይገባ ያገደው ነገር የለም፣ ግራ ቀኙን የሚገዛ ህጋዊ ውጤት ያለው ውል አለ፣ ከዱዛይኑ አኳያ ከግማሽ በላይ የተከናወነ በመሆኑ ውለ ተሰርዞ ለጅምር ግንባታው ግምቱን ተጠሪ ለአመልካች ከፍል ግንባታውን ከነይዞታው ይረከብ በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ ግራ ቀኙ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የሁለቱን ወገኖች ክርክር ተመልክቶ አመልካች የቦታና የቤት ግብር ሉከፍለ አይገባም፣ ግንባታው የተቋረጠው በአመልካች ድክመት ወይም ጥፊት ሳይሆን ተጠሪ ባቆማቸው የኮንቴነር ሱቆች ችግር ምክንያት ለመሆኑ የፍ/ቤት ዲኛው ቦታው ድረስ በመሄድ አረጋግጠዋል፣ የግንባታ ዕቃዎች እጥረት ለግንባታው መቋረጥ አስተዋፅኦ አድርጓል፣ ተጠሪ ያቀረበው የይዞታ ማረጋገጫ ም/ወረቀት አመልካች የሆስፒታል ግንባታ በሚመለከት የፀና ውል መኖሩን አያስረዲም፣ ውል አለ ቢባል እንኳን በውለ መሰረት እንዲይፈፀም አስተዋፅኦ ያደረገው ተጠሪ ስለሆነ ውለ ሉሰረዝ የሚችልበት ሁኔታ የለም አለ ቢባል እንኳን ግንባታው ከ55% በላይ ስለተገነባ ወደነበሩበት መመለስ አስቸጋሪ ይሆናል በማለት ለግንባታው እንቅፊት የሆኑት ኮንቴነሮች ተጠሪ እንዱያነሳና ግንባታው ይቀጥል፣ አመልካች የቦታና ቤት ግብር አይከፍለም በማለት የስር ፍ/ቤትን ውሳኔ ሽሯል።
በዚህ ውሳኔ ላይ ተጠሪ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረበ ሲሆን ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የከፍተኛ ፍ/ቤትን ውሳኔ በማሻሻል አመልካች የቤትና ቦታ ግብር ሉከፍለ ይገባል፣ አመልካች ቀሪ ግንባታውን ሉያጠናቅቁ የሚገባበት ጊዜ ተጠሪ ወስኖ እንዱያሳውቃቸው፣ ተጠሪ በሚሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታውን ማጠናቀቅ ካልቻለ ውለ ተሰርዞ ተጠሪ ቦታውንና ግንባታውን ባለበት ሁኔታ የመረከብ መብቱ ተጠብቋል፣ ለግንባታ ስራው እንቅፊት የሆኑት ኮንቴነር ሱቆች ተጠሪ በየደረጃው በመለየት እንዱያፈርስ በማለት ወስኗል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው ግንባታውን ያላጠናቀቁት በእርሳቸው ጥፊት ሳይሆን በፕሮጀክቱ ሳይት ዙሪያ ህገ-ወጥ የኮንቴነር ሱቆች እንዱለጠፈና የግንባታው ግብዓቶች ለመጫንና ለማራገፍ ባለመቻለ መሆኑን፣ ተጠሪ እነዚህን ኮንቴነሮች በማንሳት ግንባታው እንዱቀጥል የማድረግ ኃላፉነቱን አለመወጣቱን፣ ግንባታው መጠናቀቅ የሚገባበትን የጊዜ ገደብ ተጠሪ ወስኖ እንዱያስታውቅ መደረጉ የህግ መሰረት እንደላለው የቦታና የቤት ግብር ሉከፈል የሚገባው ግንባታው ሙለ በሙለ ተጠናቆ ስራ ላይ በዋለ ቤት በመሆኑ ግብር ሉከፍለ እንደማይገባ ለፕሮጀክቱ ግንባታ ከፍተኛ መጠን ያለው መዋለ ንዋይና የሰው ሃይል ስለፈሰሰበት የተፈጠረው መሰናክል ተወግድ ግንባታውን ተጠሪ እንዱረከብ መወሰኑ የህግ ስህተት ነው የሚል ነው። ይህ ችልት ግንባታው የሚጠናቀቅበትን የጊዜ ገደብ ተጠሪ ወስኖ ለአመልካች እንዱያሳውቅ እና አመልካች ለቦታና ቤት ግብር እንዱከፍል የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ቀርበው የቃል ክርክራቸው ተሰምቷል። ችልቱም አቤቱታ የቀረበበት ውሳኔ ከተገቢው ህግ አኳያ መርምሯል።
ከፍ ሲል እንዲየነው አመልካች ሆስፒታል ለመገንባት ቦታ የተረከቡ ቢሆንም ግንባታውን አለማጠናቀቃቸው ያልተካደ ፍሬ ነገር ነው። ተጠሪም ይህንን መሰረት አድርጎ ነው ውለ እንዱፈርስ የጠየቀው።
No topics extracted.
አመልካች በበኩላቸው ግንባታውን ያላጠናቀቁት በግዳለሽነት ሳይሆን በፕሮጀክት ሳይቱ ላይ ተጠሪ የኮንቴነር ሱቆች በማቆሙና ይህም የግንባታ እቃ ለማስገባትና ለማራገፍ እንቅፊት በመሆኑና በሃገሪቱ የግንባታ እቃም ዋጋ በከፍተኛ መጠን በመናሩ በመሆኑ ውለ ሉፈርስ እንደማይገባ ተከራክረዋል። ከመዝገቡ ላይ አመልካች ቦታውን ሚያዚያ 1993 ዓ.ም ተረክበው እስከ 1996 አጋማሽ ድረስ ግንባታውን ያከናውኑ እንደነበር ተገንዝበናል። ከዚህም በተጨማሪ በፕሮጀክት ሳይቱ ላይ የኮንቴነር ሱቆች የቆሙት በ1997 መጨረሻ ወይም በ1998 መጀመሪያ ላይ ለመሆኑ የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ማረጋገጡን ከውሳኔ ግልባጩ ተመልክተናል። ለሰበር ችልቱ ከተሰጠው የዲኝነት ስልጣን አንፃር ይህ ችልት በስር ፍ/ቤት የተረጋገጠውን ፍሬ ነገር ትክክል ነው አይደለም የሚለውን ሳይመረምር እንዲለ የሚቀበለው ይሆናል። በዚህ መሰረት አመልካች ለግንባታው ስራ እንቅፊት ሆኑብኝ በማለት የሚጠቅሷቸው የኮንቴነር ሱቆች በሳይቱ አካባቢ የቆሙት አመልካች የግንባታ ስራውን ካቋረጡ እጅግ ዘግይቶ ነው። በመሆኑም ግንባታው በተጠሪ አስተዋፅኦ መቋረጡን በማንሳት ያቀረቡት ክርክር ፍ/ቤቱ ውድቅ በማድረጉ የሰራው የህግ ስህተት አለ ለማለት አይቻልም። በልላ በኩል የክልለ ደንብ ቁጥር 41/97 አንቀፅ 8(3) የግንባታ ቦታ የተረከበ አስገንቢ በ6 ወር ጊዜ ውስጥ ሥራውን መጀመር እንዲለበት እና እስከ ሁለት አመት ማጠናቀቅ እንዲለበት ያስጠነቅቃል። ትልልቅ ግንባታዎችን በተመለከተ ግን ውል ሰጪውን አካል በማስፈቀድ ጊዜውን ማራዘም እንደሚቻል ይፈቅዲል። ከፍ ሲል እንዲየነው አመልካች ቦታውን የተረከቡት ሚያዚያ 1993 ዓ.ም ነው።
ነገር ግን ግንባታውን እስካሁን አላጠናቀቁም። እንደውም ከ1996 ዓ.ም አጋማሽ ጀምሮ ግንባታው ተቋርጧል።
ቀደም ብል እንደተመለከትነው ግንባታው የተቋረጠው በኮንቴነር ሱቆቹ ምክንያት ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም። ለግንባታው መቋረጥ ላላው የሰጡት ምክንያት የግንባታ ዕቃዎች ዋጋ መናርን ነው። በእርግጥ በአገሪቷ ውስጥ የግንባታ ዕቃ ዋጋ መናር ተከስቶ እንደነበር የስር ፍ/ቤቶች ተቀብለውታል። ነገር ግን በዚህ ችግር ምክንያት ግንባታው የሚዘገይ ከሆነ ከፍ ሲል በተጠቀሰው ደንብ መሰረት ውል ሰጪው አካል ጊዜውን እንዱያራዝም መጠየቅና ማራዘም በተገባቸው ነበር። ይህንን ስለማድረጋቸው ግን ማስረጃ አለመቅረቡን ከመዝገቡ ተረድተናል። በመሆኑም በህጉ የተቀመጠው የጊዜ ገደብ እንዱራዘም ሳይጠይቁና በዚሁ ጊዜ ውስጥ ግንባታውን ሳያጠናቅቁ ውለ ሉፈርስ አይገባም በማለት ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
ከዚህ ላላ አመልካች ተጠሪ ግንባታው ሉጠናቀቅ የሚገባበት ጊዜ ወስኖ እንዱያሳውቅ መወሰኑ የህግ መሰረት የለውም በማለት ይከራከሩ እንጂ በክልለ ደንብ መሰረት በደንቡ ግንባታ ለማጠናቀቅ የተቀመጠው ጊዜ እንዱረዝም ፈቃድ የሚሰጠው ውል ሰጪው አካል እንደመሆኑ መጠን የጊዜውንም እርዝመት እራሱ እንደሚወስን መገንዘብ ይቻላል። በዚሁ መሰረት ተጠሪ አመልካች ግንባታውን ማጠናቀቅ የሚገባቸውን ጊዜ ወስኖ እንዱያሳውቃቸው መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ነው ማለት አልተቻለም።
በመጨረሻም አመልካች ለጅምርና ጥቅም ላይ ላልዋለ ቤት የቦታና የቤት ግብር እንድከፍል የተሰጠው ውሳኔ የህግ ድጋፍ የለውም ይበለ እንጂ በክልለ አዋጅ ቁጥር 51/1994 እና በደንብ ቁጥር 41/1997 የከተማ ባለይዞታ የሆነ ማንኛውም ሰው ግንባታ ቢጨርስም ባይጨርስም የአገልግልት ተጠቃሚ በመሆኑ ብቻ የተጠቀሱት ግብሮች እንደሚከፍል ይደነግጋል። አመልካች በተቃራኒው ለጅምር ቤት የቤትና የቦታ ግብር እንዲይከፈል የሚከለክል ህግ ስለመኖሩ የጠቀሱት ነገር የለም። በመሆኑም በዚህም በኩል የተሰጠው ውሳኔ የህግ ስህተት ተፈፅሞበታል ለማለት አልተቻለም። በአጠቃላይ በፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት ለማለት ስላልተቻለ ተከታዩ ውሳኔ ተሰጥቷል።
የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ የካቲት 25 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።
ይህ ችልት ጥቅምት 25 ቀን 2002 ዓ.ም የሰጠው የእግድ ትዕዛዝ ተነስቷል። ለሚመለከተው ክፍል ይተላለፍ።