No summary available.
ሰኔ 30 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሀኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ሳዱቅ ሐሰን - ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ቴላኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን - ነገረ ፈጅ አቶ ጌታነህ ቸሬ - ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት እና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው። የክርክሩ መነሻ ለውጭ አገር የተደወለ የስልክ አገልግልት ክፍያ ነው። አመልካች ተጠሪ ከታህሳስ ወር 2003 ዓ.ም እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር መስከረም 2004 ዓ.ም ድረስ የተጠቀመበትን ብር 19,793.52(አስራ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ዘጠና ሦስት ብር ከሃምሳ ሁለት ሣንቲም) እና የስልክ ቀፍ ዋጋ ብር 249.55(ሁለት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከሃምሳ አምስት ሣንቲም) በድምሩ ብር 20,043.07 (ሀያ ሺ አርባ ሶስት ብር ከሰባት ሣንቲም) የስልክ አገልግልት ክፍያና የቀፍ ዋጋ እንዱከፍለ ውሣኔ ይሰጥልኝ በማለት አመልክቷል። አመልካች በበኩለ የተጋነነ ሑሳብና ያልደወለበት የውጭ አገር የስልክ ሑሳብ የተጠየቁና ይኸም በኮንፒዩተር ስህተት የመጣ መሆኑን በመግለፅ ጉዲዩ እንዱመረመር ለአመልካች መሥሪያ ቤት ያመለከቱ መሆኑንና በዚህ መሰረት የታህሣሥ ወር ክፍያ ተመርምሮ ከብር 891.25(ስምንት መቶ ዘጠና አንድ ብር ከሃያ አምስት ሣንቲም) ወደ ብር 92.26 (ዘጠና ሁለት ብር ከሃያ ስድስት ሣንቲም) ዝቅ ያለ መሆኑን ገልፀው ሑሳቡ ሣይመረመር በዓለም ላይ ወደ ላላ አገር USSR ደውለሀል ተብዬ መከሰሴ ተገቢ አይደለም በማለት ተከራክረዋል። ተጠሪ የታህሣሥ ወር በአማካኝ ክፍያ እንዱፈፅሙ ስለተደረገ እንጅ ተመርምሮ ስህተት በመሆኑ ሑሳቡ አልተቀነሰም የተገለገለበትን ስልክ ዋጋ ሉከፍለ ይገባል በማለት ተከራክሯል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ አመልካች በክሱ የተገለፀውን ገንዘብ ለተጠሪ እንዱከፍል በማለት ውሣኔ ሰጥቷል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት አቅርበው ይግባኙ ተቀባይነት አላገኘም።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ባቀረበው የሰበር አቤቱታ የጠየቅሁት የስልክ ግልጋልት ክፍያ በኮንፒዩተር ስህተት ምክንያት ተጋንኖ የተጠየቀ ነው። ይኸ እንዱመረመርልኝ ያቀረብኩት አቤቱታ በመቀበል እንዱመረመር ሣይደረግ ተጠሪ የጠየቀውን ሂሳብ እንድከፍል መወሰኑ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክቷል። ተጠሪ በበኩለ ያቀረብነው ክስ በበቂ ማስረጃ የተረጋገጠ በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም በማለት መልስ አቅርቧል።
አመልካች የመልስ መልስ መልስ አቅርበዋል።
ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም መዝገቡን መርምረናል። መዝገቡን እንደመረመርነው ተጠሪ ከአመልካች ላይ የጠየቀው የስልክ ግልጋልት ዋጋ የተጋነነ በኮምፒዩተር ስህተት የመጣ ነው የሚለውን የአመልካች አቤቱታ መሰረት በማድረግ ጉዲዩ በባለሙያ ሣይመረመር ተጠሪ የጠየቀውን ሂሳብ በሙለ አመልካች እንዱከፍለ መወሰኑ ተገቢ ነው ወይስ አይደለም?
የሚለውን ጭብጥ በመያዝ መርምረናል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው አመልካች የስልክ መስመሩ ተገልጋይና የስልክ ቀፍው ባለይዞታ መሆኑ በእሱ ስልክ ቁጥር ወደ ውጭ አገርም ሆነ በአገር ውስጥ የተደረገው የስልክ ግንኙነት በእሱ የተፈፀመ ነው የሚል ግምት የሚያሣድር ነው። ሆኖም አመልካች የተጠየቀው የስልክ ግልጋልት ዋጋ ከወትሮው የተለየና የተጋነነ መሆኑን አመልካች እስከ አዱስ አበባ ዋናው መሥሪያ ቤት ድረስ ያመለከተ መሆኑንና እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር የታህሳስ ወር 2003 ብር 891.25(ስምንት መቶ ዘጠና አንድ ብር ከሃያ አምስት ሣንቲም) ተጠይቀው የነበረውን 92.26 /ዘጠና ሁለት ብር ከሀያ ስድስት ሣንቲም/ እንዱከፍል መደረጉን አመልካችና ተጠሪ አልተካካደም። አመልካችና ተጠሪ የተለያዩበት ዋናው ነጥብ አመልካች ኮንፒዩተሩ ተመርምሮ ስህተት ሆኖ በመገኘቱ በፉት የተጠየቅሁት ገንዘብ ተቀንሶ ከፍያለሁ ሲል ተጠሪ በበኩለ በአቨሬጅ ወጥቶና በዚያ መሰረት ተሰልቶ ነው እንዱከፍል የተደረገው በማለት ነው። አመልካችና ተጠሪ የሚካካደበት ምክንያት ቢሆንም እንደ አውሮፓሮውያን አቆጣጠር ከታህሳስ ወር 2003 ዓ.ም ጀምሮ ተጠሪ ከአመልካች የሚጠይቀው የስልክ ግልጋልት ክፍያ አመልካች በደንበኝነት በቆዩበት ጊዜ ይከፍለት ከነበረው አቬሬጅ ክፍያ በየወሩ ስምንት እጥፍ ብልጫ ያለውና የተጋነነ በመሆኑ ለመገንዘብ ይቻላል። ይኸንንም ሁኔታ በመቃወም አመልካች እንዱመረምርላቸው ጥያቄ ያቀረቡ መሆኑን ከበታች ፍርድ ቤት ውሣኔ ለመገንዘብ ችለናል።
No topics extracted.
አመልካች የተገለገለበትን የስልክ ግልጋልት ዋጋ የመክፈል ግዳታ ያለበት ሲሆን በተነፃፃሪው ተጠሪ የአመልካች የስልክ መስመር ከአመልካች ውጭ ላላ ሰው እንዲይገለገልበት ተገቢውን ጥበቃና ጥንቃቄ የማድረግና አመልካች ላገኘው ግልጋልት የአገልግልት ዋጋ የመጠየቅ መብት አለው። ተጠሪ ደንበኞቹ የተጠየቁት የአገልግልት ክፍያ ትክክለኛነት በሚጠይቁበት ወቅት የማስመርመሪያ ገንዘብ ከፍለው እንዱመረመር የሚያደርግ መሆኑ የሚታወቅ ነው። አመልካችና ተጠሪ ያላቸው የውል ግኑኝነትና በውል አፈፃፀም የሚነሡ ችግሮች በመጀመሪያ ተጠሪ በልምድ ባዲበረው አሰራር መሰረት መታየትና መጣራት ያለበት ነው። ይኸም በአመልካችና በተጠሪ መካከል ሉኖር የሚገባው ግኑኝነት ቅንነትንና መተማመንና በጉዲዩ ውስጥ ያለውን ልማዲዊ ሥርዓት በመከተል ሉፈታ የሚገባው በመሆኑ ከፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 1732 ድንጋጌ ለመገንዘብ ስለሚቻልና ተጠሪ ደንበኞቹ የተጠየቁት የአገልግልት ክፍያ የተጋነነ ነው ወይም ጥሪ ያላደረግሁበትን የውጭ አገር ስልክ አገልግልት ዋጋ እንድከፍል ተጠይቄአለሁ በሚለበት ወቅት ደንበኞቹ የተወሰኑ ሁኔታዎችን በማሟላት የሚመረመርበት በልምድ የዲበረ አሰራር ያለው በመሆኑ ተጠሪ እ.ኤ.አ በታህሳስ ወር 2003 የተጠየቀው ሂሳብ የተጋነነ መሆኑን አቤቱታ ሲያቀርብ ተገቢው ምርመራ ማድረግ ሲገባው ምርመራ አለማድረጉና እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከጥር ወር 2003 እስከ መስከረም 2004 ድረስ ያለው ሑሳብም ሣይመረመር አመልካች እንዱከፍለ መጠየቁና የበታች ፍርድ ቤቶችም በጉዲዩ ተገቢው ምርመራ ተደርጎ ዕውነታው ሣይረጋገጥ ተጠሪ የጠየቀውን ገንዘብ አመልካች ሙለ በሙለ እንድከፍል መወሰናቸው አመልካችን ግዳታና ኃላፉነትና በልምድ የዲበረውን የተጠሪን አሰራር ግንዛቤ ውስጥ ያላስገባና መሰረታዊ የህግ ስህተት አለበት በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የኦሮሚያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰጡት ውሣኔ ተሽሯል።
የዞኑ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አመልካች ለማስመርመር የሚገባውን ግዳታና ኃላፉነት እንዱወጣ በማድረግና የአመልካች መስመር እንዱመረመር በማድረግ በሚቀርብለት ውጤት መሰረት ተገቢውን ውሣኔ ይሰጥ ዘንድ ጉዲዩን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 343 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት መልሰን ልከንለታል።
በዚህ ፍርድ ቤት ያወጡትን ወጭና ኪሣራ ግራ ቀኙ ለየራሳቸው ይቻለ። ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ። መዝገቡ ተዘግቷል፤ ወደ መ/ቤት ይመለስ።