No summary available.
ጥር 13 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ አመልካቾች፡-
አቶ ፈታሂ ባየህ
ወ/ሮ ጽጌ ባየህ
ወ/ሮ ተዘራ ባየህ
ፍሬሕይወት ባየህ በራሣቸውና በላልች ወኪልቻቸው
አቶ ዘውገ ባየህ አቶ ፈታሂ ባየህ ቀረቡ።
ሰብለሥላሴ ባየህ
ወ/ሮ ማስረጃ ባየህ ተጠሪዎች፡-
ወ/ሮ አስራት ባየህ - ከክርክሩ ውጪ ሁነዋል።
ዱያቆን ገ/ሕይወት ንጋቱ ቀረቡ።
ቀኝ ጌታ ልሳነወርቅ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ የውርስ ቤት ይለቀቅልን ጥያቄ የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የአሁኑ አመልካቾች ግንቦት ዐ2 ቀን 1998 ዓ.ም. አሻሽለው በፃፈት እና በአሁኑ ተጠሪዎች ላይ በመሰረቱት የክስ ማመልከቻ ነው። የክሱ ይዘትም፡- አመልካቾች እና አንደኛዋ ተጠሪ ከሟች ወላጆቻቸው ከአዛዥ ባየሕ ገ/ኢየሱስና ከእናታቸው ከወ/ሮ ደብሪቱ ኃ/ጊዮርጊት በውርስ የተላለፈላቸው በአዱስ አበባ ከተማ፣ በልደታ ክፍለ ከተማ ቀበላ 15/16/17 ወስጥ የሚገኙ በአባታቸው ስም ተመዝግበው የሚታወቁትን፣ ቁጥራቸው 922፣ 738፣ 739 እና 74ዐ የሆኑ ቤቶች እንዲላቸው፣ የቤቶቹን ስመ ሃብት አንደኛ ተጠሪ በራሳቸው ስም በማድረግ ቁጥራቸው 739 እና 74ዐ የሆኑትን ቤቶች ከሁለተኛ እና ለሦስተኛ ተጠሪዎች በወለድ አግድ በማስያዝ ብድር ተበድረው ለግላቸው እንደሚጠቀሙበትና በስምምነት ክፍፍል እንዱደረግ ሲጠየቁ ፈቃደኛ ሆነው ባለመገኘታቸው የውርስ አጣሪ ተሹሞ ውርሱ እንዱጣራ ለፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካቾች በማመላከት ፍርድ ቤቱ የውርስ አጣሪ በመሾም ውርሱ ከተጣራ በኋላ ሪፖርቱ ለፍርድ ቤቱ ጥር 14 ቀን 1998 ዓ.ም. ተልኮ የካቲት ዐ9 ቀን 1998 ዓ.ም. ፍርድ ቤቱ የመዘገበው መሆኑን፣ በዚህ የውርስ አጣሪው ሪፖርት አጠቃላይ የውርስ ሃብት ግምት እና የወራሾች ድርሻ እንዱሁም የተጠቀሙበት ሀብት መጠን ተለይቶ መቀመጡን፣ አንደኛ ተጠሪ ያላግባብ ቤቱቹን ሕጋዊ ባልሆነ የወለድ አግድ ውል ለሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ያሰያዙ መሆኑንና በወለድ አግድ ውል ቤቶቹን የያዙት ተጠሪዎችም አስያዧ መብት ሳይኖራት እያወቁ የያዙት መሆኑን ዘርዝረው ቁጥራቸው 739 እና 74ዐ የሆኑ ቤቶችን ተጠሪዎች እንዱያስረክቡ፣ አጠቃላይ የውርስ ሃብት የሆኑ ንብረቶች ከእነ ይዞታቸው በአውራሽ አባታቸው ስም የነበረው የባለቤትነት ማረጋገጫ ስም በአመልካቾች ስም እንዱዛወር ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቀቸውን የሚያሳይ ነው።
የአሁኑ ሁለተኛ ተጠሪም ለክሱ በሰጡት መልስ፣ ለክርክሩ ምክንያት የሆነው ቤት በአዋጅ ተወርሷል ተብል የቀበላው መስተዲደር አከራይቶ ቆይቶ እያለ አንደኛ ተጠሪ ከአዋጅ ውጪ ያላግባብ፣ የተወረሰ /የተወሰደ/ ነው በማለት በፍርድ ቤት ከሰው በፍርድ ኃይል አስለቅቀው በመረከብ በፍ/ቤት ውሣኔ ባለመብት ሆነው፣ የቤት ባለቤትነት ደብተርና ካርታም በስማቸው አረጋግጠው፣ ይዞታቸው በመሆኑ፣ መጋቢት ዐ1 ቀን 1994 ዓ.ም.
በተፃፈ የውል ሰነድ ብር 1ዐ,ዐዐዐ.00 /አስር ሺህ/ ተቀብለው ቁጥሩ 739 የሆነውን ቤት እስከ መጋቢት 1999 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ ወለድ አግድ ውል፤ ለአምስት ዓመት በማስያዝ የተዋዋለ መሆኑን፣ ቤቱም ተረክበው ይዘው እንደሚገኙና አንደኛ ተጠሪ የተበደሩትን ገንዘብ ሲመልሱ ቤቱን እንደነበረ ሉያስረክቧቸው መዋዋላቸውን፣ አመልካቾች በስምምነት ድርሻቸውን ይዘው እየተጠቀሙ የሚገኙ በመሆኑና በቤቱ ላይ አንደኛ ተጠሪ በሕጉ አግባብ ባለመብት ከሆኑ በኋላ ያቋቋሙት የወለድ አግድ ውል ሕጋዊ መሆኑን እንዱሁም አንደኛ ተጠሪ ቤቱን በብዙ ድካምና ወጪ አስመልሰው መያዛቸውን እያወቁና እየተረደ መብት ሳይኖራቸው ቤቱን አስይዘዋል ማለታቸው በሕግ ተቀባይነት የላለው ነው በሚል ተከራክረዋል። አንደኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች መጥሪያ ደርሷቸው የጽሁፍ መልስ መስጠት መብት የታፈባቸው ሲሆን ሦስተኛ ተጠሪ በቃል ክርክር ወቅት ቀርበው ቁጥሩ 74ዐ የሆነ ቤት በወለድ አግድ ውል ለሰባት ዓመታት እንደያዙ፣ የውለ ዘመንም እስከ ጥር 2ዐዐ7 ዓ.ም.
No topics extracted.
መሆኑን ገልፀው ጊዜው ሳያልቅ ቤቱን የሚያስረክቡበት ምክንያት እንደላለ ጠቅሰው ተከራክረዋል።
ጉዲዩ በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው ፍርድ ቤትም የግራ ቀኙን ክርክር ከመረመረ በኋላ በቤት ቁጥር 739 የተቋቋመው የወለድ አግድ ውለ የውል ዘመኑ ማብቃቱን በመግለጽ አንደኛ ተጠሪ የተቀበለትን ብር 1ዐ,ዐዐዐ.00(አስር ሺህ) ለሁለተኛ ተጠሪ መልሰው ሁለተኛ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካቾች እና ለአንደኛ ተጠሪ ሉያስረክቡ ይገባል ቤቱንም አመልካቾችና አንደኛ ተጠሪ እኩል ሉካፈለት ይገባል ሲል የወሰነ ሲሆን የቤት ቁጥር 74ዐ የሆነውን በተመለከተ ደግሞ የወለድ አገድ ውለ እስከ ጥር 2ዐዐ7 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ በመሆኑ ሦስተኛ ተጠሪ ቤቱን ሉያስረክቡ እንደማይገባ፣ የውለ ዘመን ሲያልቅ በውለ የተገለፀውን ገንዘብ አንደኛ ተጠሪ ለሦስተኛ ተጠሪ መልሰው ሦስተኛ ተጠሪ ቤቱን ለአመልካቾችና ለአንደኛ ተጠሪ እንዱያስረክቡና ቤቱንም ሉከፊፈለት እንደሚገባ፣ እንዱሁም በቤት ቁጥር 739 እና 74ዐ እስኪከፊፈለ ድረስ በአመልካቾችና በአንደኛ ተጠሪ ስም የባለቤትነት ማረጋገጫ ደብተርና ካርታ በጋራ ሉያወጡበት ይገባል ሲል ወስኗል። በዚህ ውሣኔ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበው ግራ ቀኙ ከተከራከሩ በኋላ የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ፀንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሣኔ በመቃወምና ለማስቀየር ነው።
አመልካቾች ሚያዝያ 21 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በፃፈት አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ ላይ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡- አንደኛ ተጠሪ በአከራካሪው ቤቱ ላይ ሙለ መብት የላላቸው ሆኖ እያለ እና የወለድ አግድ ውለም በሕጉ አግባብ ያልተመዘገበ መሆኑ ተረጋግጦ እያለ የውርስ ንብረቱ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች እንደያዙት እንዱቆዩ የተደረገው እና ውለ ሕጋዊ ነው መባለ ያላግባብ ስለሆነ ሉታረም ይገባል በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም የወለድ አግድ ውለ ሕጋዊ ነው መባለ ባግባቡ መሆን አለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ለሰበር ችልቱ እንዱቀርብ ተደርጎ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ኀዲር 1ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
በፃፈት ሦስት ገጽ የመልስ ማመልከቻ የአመልካቾች የሰበር አቤቱታ ነጥብ በሥር ፍርድ ቤት ያልተነሳ ስለመሆኑ እና ውለ ሕጋዊ ነው የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሉፀና ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። አንደኛ ተጠሪ ከክርክሩ ውጪ እንዱሆኑ ተደርጎአል። አመልካቾች ታህሣሥ ዐ8 ቀን 2ዐዐ2 ዓ.ም.
በፃፈት ሁለት ገጽ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልቱ ሲቀርብ ከተያዘው ጭብጥ አንፃር በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤቶች ያቀረቡት ክስ ይዘት ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ቤቶች በውርስ ያገኗቸው መሆኑን፣ በእነዚህ ቤቶች ላይ አመልካቾችና አንደኛ ተጠሪ ያላቸው ድርሻ በውርስ አጣሪ ተለይቶ መታወቁንና ቤቶቹን ለማካፈል አንደኛ ተጠሪ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን እንዱሁም ሕጋዊ ባልሆነ የወለድ አግድ ውል ለሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ቤቶቹን አንደኛ ተጠሪ አስተላልፈው እንደሚገኙ ገልፀው ቤቶቹን እንዱያስረክቧቸውና የቤቶቹ ስመ ሃብት ወደ ወራሾች እንዱዞር ይወሰን ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሳይ መሆኑን ነው። የአሁኑ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ደግሞ የወለድ አግድ ውለ በሕጉ አግባብ የተደረገ ስለሆነ ቤቶቹን ልናስረክብ አይገባም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ከመዝገቡ ተመልክተናል። ከዚህ የግራ ቀኙ ክርክር መገንዘብ የሚቻለው አመልካቾች በግልጽ እየተቃወሙ ያለት የወለድ አግድ ውለ በሁለት ምክንያቶች ሕጋዊ አይደለም በማለት የሚከራከሩ መሆኑን ነው። ይኸውም አንደ ውለ የተደረገው በንብረቱ ላይ ሙለ መብት በልላቸው አንደኛ ተጠሪ በመሆኑ ሕጋዊ አይደለም የሚል ሲሆን ላላው ተደረገ የተባለው የወለድ አግድ ውልም ቢሆን ስልጣን ባለው አካል ፉት የልተደረገና ያልተመዘገበ ስለሆነ ሉፀና የሚገባው አይደለም የሚል ነው። እንግዱህ የአመልካቾች ክርክር ቤቱ ያላግባብ ተይዞብናል የሚል ስለመሆኑ በቀላለ የምንገነዘበው ጉዲይ ነው። ስለዚህ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች የአመልካቾች ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ያልተነሳና የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 181ዐ ያላገናዘበ ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር የአመልካቾችን የስር ክርክር ይዘቱን ባግባቡ መሰረት ያላደረገ ስለሆነ ተቀባይነት ያለው አይደለም። ይልቁንም የወለድ አግድ ውለ ስልጣን ባለው አካል ፉት ያልተደረገና ንብረቱ በሚገኝበት መዝገብ ያልተመዘገበ ስለመሆኑ ተጠሪዎች በማመን የሚከራከሩ መሆኑን የሚያሳይ ነው። የወለድ አግድ ውለ ስልጣን ባለው አካል ፉት ያልተደረገና ያልተመዘገበ ከሆነ ውጤቱ ምንድነው? የሚለውን በዚህ ረገድ የተደነገጉትን የፍትሐብሕር ሕግ ድንጋጌዎች በማየት ምላሽ ማግኘት የሚችለው ነጥብ ነው።
በመሰረቱ የወለድ አግድ ውል የሚቋቋመው የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣን መቋቋም የሚመለከቱት ድንጋጌዎችን በመከተል ስለመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 3118 ድንጋጌ ያጣቅሳል። በዚህ አግባብ ቀጥተኛ ተፈፃሚነት ያላቸው ድንጋጌዎች የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 3ዐ45 እና 3ዐ52 ሲሆኑ በእነዚህ ድንጋጌዎች መሰረት በማይንቀሳቀስ ንብረት ላይ የሚደረግ የመያዣ ውል በጽሁፍ መሆን እንዲለበትና የማይንቀሳቀስ ንብረት በሚገኝበት መዝገብ መመዝገብ እንዲለበት የስገነዝባለ። ይህን ያላሟላ የማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ ውል የሕግ ውጤት አይኖረውም።
በመሆኑም የወለድ አግድ ውል በሕጉ ጥበቃ የሚደረግው በሕጉ አግባብ ተቋቁሞ ሲገኝ ብቻ ነው። በተያዘው ጉዲይ ግን በዚሁ መንገድ የተደረገ የወለድ አግድ ውለ የለም። ስለሆነም ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች አበድረናል የሚለትን ገንዘብ ከሚመለከተው ሰው በሕጉ አግባብ ከሚጠይቁ በስተቀር ለክርክሩ ምክንያት የሆኑትን ቤቶች የሚይዙበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። የበታች ፍርድ ቤቶችም የወለድ አግድ ውል የተባለው በሕጉ አግባብ የተቋቋመ መሆን አለመሆኑን ከሕጉ ጋር ሳያገናዝቡት ቤቶቹን ተጠሪዎች ሉለቁ አይገባም በማለት የሰጡት ውሣኔ አመልካቾችን በውርስ የተላለፈላቸውን የባለቤትነት መብትን ያጣበበ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል። በዚህ ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ
በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁጥር 1ዐ218 ጥቅምት ዐ1 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. ተሰጥቶ በፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በመ/ የካቲት 27 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. የፀናው ውሣኔ ተሻሽሎል።
ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተጠሪዎች ከአንደኛ ተጠሪ ጋር አድርገናል። የሚለት የወለድ አግድ ውል ፈራሽ ነው ብለናል።
ሁለተኛ ተጠሪ የቤት ቁጥር 739፣ ሦስተኛ ተጠሪ ደግሞ የቤት ቁጥር 74ዐ ለአመልካቾች ሉያሰረክቡ ይገባል።
አመልካቾች እና አንደኛ ተጠሪ በቤቶቹ ላይ በጋራ ያላቸውን መብትና ጥቅም በሥር ፍርድ ቤት የተሰጠው ውሣኔ እንደተጠበቀ ነው ብለናል።
በዚህ ችልት ለተደረገው ክርክር የወጣውን ወጪና ኪሣራ የየራሳቸውን ይቻለ ብለናል።