No summary available.
ታህሣሥ 2ዐ ቀን 2ዐዐ2 ዳኞች፡- ተገኔ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ በብድር የተሰጠን ገንዘብ የመክፈያ ጊዜ ጋር በተያያዘ ዕዲው እንደተከፈለ ሉቆጠር የሚችልበትን የሕግ አግባብና ትርጉም የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበሩት የአሁኑ ተጠሪ መጋቢት 16 ቀን 1997 ዓ.ም. በፃፈት አቤቱታ የአሁኑ አመልካቾች ጥር 24 ቀን 199ዐ በተፃፈ የብድር ውል ብር 32,ዐዐዐ.00 /ሰላሣ ሁለት ሺህ ብር/ የተበደሩ መሆኑን፣ ብድሩን በየሣምንቱ ብር 25ዐ.00 እየከፈለ እስከ ነሐሴ 3ዐ ቀን 1992 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍለው ለማጠናቀቅ መስማማታቸውን፣ ተበዲሪዎች በጋራ በጠቅላላው ብር 9ዐ9ዐ /ዘጠኝ ሺህ ዘጠና ብር/ የመለሱላቸው ሰለመሆኑ በመዘርዘር ቀሪውን ብር 22,91ዐ.00 /ሃያ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ አስር ብር/ ከነወለደ አመልካቾች እንዱከፍለ ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት ጠይቀዋል።
ተጠሪዎችም ቀርበው የቀረበባቸውን ክስ በመቃወም ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው፣ ፈርመን የወሰድነው ገንዘብ የለም፣ አበዲሪው ፊርማችንን የሚያውቁ በመሆናቸው እራሳቸው ውለን አዘጋጅተውና ገንዘቡን በመሰላቸው ሞልተው ያቀረቡት ሰነድ ነው፣ የቀረበው የብድር ውለ ሰነድ ትክክል ነው ቢባል እንኳ ውለ በተፈፀመበት ጊዜ ለዕለት የምንመገበው ያጣን ችግረኞች ስለነበርን ይህንኑ አጋጣሚ ተጠቅመው ጥቂት ገንዘብ አበድረው በ7ዐ% /ሰባ በመቶ/ አስበው ካበደሩን ገንዘብ ጋር ደምረው ያስፈረሙን ሕገ-ወጥ የአራጣ ብድር ውል በመሆኑ ፈራሽ ነው የሚለትን ክርክሮች አንስተው ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም በብድር ውለ ላይ አለ የተባለውን ፊርማ በፋዳራል ፖሉስ የፍረንሲክ ምርመራ እንዱከናወን ከአደረገ በኋላ ጉዲዩን በመመርመር ውለ ላይ ያለው ፊርማ የተበዲሪዎች መሆኑ ተረጋግጧል፣ ውለ ሕገ-ወጥ ልባል የሚችልበት ምክንያት የለም በማለት የተጠሪዎችን መከራከሪያ ውድቅ ከአደረገ በኋላ ለክሱ ኃላፉ በማድረግ በክሱ የተጠቀሰውን ብር 22,91ዐ.00 /ሃያ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ አስር ብር/ ክሱ ከቀረበበት ቀን አንስቶ ከሚታሰብ ወለድ ጋር ለተጠሪ እንዱከፍለ በማለት ወስኗል። አመልካቾች በዚሁ ውሣኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ቀረቡ።
ይግባኛቸው በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል በማለት ለማስቀየር ነው።
አመልካቾች የካቲት 17 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈት 3 /ሦስት/ ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡የሥር ፍርድ ቤት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24/ረ/”ን” ድንጋጌ መሰረት ተደርጎ የቀረበውን ክርክር ውድቅ ማድረጉ ያላግባብ መሆኑን፣ ውሣኔውም ለዚሁ ድንጋጌ ሰበር ችልቱ በመ/ቁጥር 17ዐ68፣ 14ዐ47 የሰጠውን ትርጉም ያላገናዘበ መሆኑን በመጥቀስ ውሣኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብል የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ተሽሮ አመልካቾች በተጠሪ በብድር ዕዲ የሚፈለግባቸው ገንዘብ የለም ተብል ከክርክሩ ወጪና ኪሣራ ጋር ይወሰንላቸው ዘንድ ዲኝነት መጠየቃቸውን የሚያሣይ ነው። ይህ የሰበር ሰሚ ችልትም አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት በፍ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24/ረ/ መሰረት ያቀረቡት ክርክር የመታፈን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ አድርጓል።
ለተጠሪ ጥሪ ተደርጎላቸው ቀርበው ሐምል 24 ቀን 2ዐዐዐ ዓ.ም. በፃፈት ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል። ይዘቱም ባጭሩ- የፍ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24/ረ/ ለጉዲዩ አግባብነት የላለው መሆኑን፣ በሥር ፍርድ ቤትም ያልተነሳ መሆኑን፣ አመልካቾች ዕዲው ያልተከፈለ መሆኑን ስለአመኑ ክርክራቸው ተቀባይነት የላለው መሆኑን ገልፀው የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሉፀና ይገባል በማለት የተከራከሩ ስለመሆኑ የሚያሳይ ነው። አመልካቾች ጥቅምት ዐ4 ቀን 2ዐዐ1 ዓ.ም. በተፃፈ የመልስ መልስ ማመልከቻ የፍ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24/ረ/”ን” መሰረት ያደረገ ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ያነሱ መሆኑን በመጥቀስ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መሰረት ውሣኔ ይሰጥልን ሲለ ተከራክረዋል።
No topics extracted.
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም በግራ ቀኙ የቀረበውን ክርክር ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሣኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ጉዲዩ ለሰበር ችልት ያስቀርባል ተብል ከተያዘው ጭብጥ አኳያ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው በተጠሪ እና በአመልካቾች መካከል የብድር ውለ የተፃፈው ጥር 24 ቀን 199ዐ ዓ.ም. ሆኖ የብድሩ አመላለስም በየሣምንቱ ብር 25ዐ.00 /ሁለት መቶ ሃምሣ ብር/ አየተከፈለ እስከ ነሐሴ 3ዐ ቀን 1992 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ሉጠናቀቅ መስማማታቸውን፣ የአሁኑ ተጠሪ የብድር ገንዘቡን አመልካቾች አልመለሱም፤ ሉከፍለኝ ይገባል በማለት በፍርድ ቤት ክስ የመሰረቱት መጋቢት 16 ቀን 1997 ዓ.ም. መሆኑ እና አመልካቾች ስለ ውለ ህጋዊ አለመሆን በውለ ላይ ያለው ፊርማ የእነሱ አለመሆኑና ውለም አራጣ ልባል የሚችል መሆኑን በመጥቀስ ኃላፉነት የለብንም በማለት መከራከራቸውን ነው። በዚህ ችልት አመልካች አጥብቀው የሚከራከሩት የስር ፍርድ ቤት የብድር እዲው ክፍያ ጥያቄ በሁለት ዓመት የጊዜ ማለፍ እንደተከፈለ ሉቆጠር ይገባል በማለት ያቀረብነውን ክርክር ያለፈው ያላግባብ ነው በሚል ነው። ተጠሪ ደግሞ ይህ የአመልካቾች ክርክር በሥር ፍርድ ቤት ያልተነሳ አዱስ ክርክር በመሆኑ በዚህ ችልት መከራከሪያ ላሆን አይችልም በማለት ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ በሕግ የሚሸፈን የፍሬ ነገር ክርክርን በተከራካሪ ወገኖች ባይነሳም ፍርድ ቤቱ በራሱ ሉያነሳው የሚችለው ጉዲይ በመሆኑና ይህም ስለመሆኑ ይህ ችልት ከዚህ በፉት በሰ/መ/ቁጥር 17ዐ68 እና በላልች በርካታ መዛግብት አስገዲጅ የሆነ የሕግ ትርጉም የሰጡበት በመሆኑ አመልካቾች በሥር ፍርድ ቤት ማንሣት አለማንሳታቸው ሉያስከትል የሚችለው የሰነ-ሥርዓት ግድፈት ስለላለው ተጠሪ በዚህ ረገድ ያቀረቡትን ክርክር የምንቀበለው ሆኖ አልተገኘም።
በዚህ ጉዲይ ዋናውና የሕግ ትርጉም የሚያስፈልገው ነጥብ፤ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24/ረ/ ድንጋጌ አግባብነቱ ለዋናው የብድር ገንዘብ ነው? ወይስ ለብድሩ ገንዘብ ወለድ ብቻ? የሚለው ጥያቄ ነው። ለዚህ ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ይቻል ዘንድ ስለ የሕሉና ግምት ምንነትና ዓይነቶች እንዱሁም የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24/ረ/ ድንጋጌን ይዘት፣ አቀራረጹንና መንፈሱን በሚገባ መረዲት ያስፈልጋል።
በመሰረቱ የሕሉና ግምት /Presumption/ ሲባል ቀደም ብል በነገሮች መካከል የነበራቸውን የግንኙት ልምድ መሰረት በማድረግ /Experience of previous connections/ ከታመኑ ወይም በማስረጃ ከተረጋገጡ ፍሬ ነገሮች በመነሳት በአንፃሩ ላላ አዱስ ፍሬ ነገር መከሰትን ወይም እውነትን በአእምሮ መቀበል /inference/ ማለት ስለመሆኑ በዚህ ረገድ የተፃፈት የሕግ ምሁራን ጽሁፍች ያሳያለ። የዚህ ጽንሰ ሀሳብ ውጤትም አንድን አከራካሪ የሆነ ፍሬ ነገር መኖር አለመኖር በማስረጃ ማረጋገጥ ሳያስፈልግ እንዲለ መቀበል ስለመሆኑም ያሰምሩበታል።
ይሁን እንጂ የሕሉና ግምት ዓይነቶች የተለያዩ ስለሆኑ ውጤታቸውን ፍርድ ቤት የሚቀበልበት መንገድም የተለያየ ነው። ጠቅለል ባለ መልኩ ሲታይም የሕግ የሕሉና ግምት ዓይነተኛ ዓላማ የማስረዲት ሸክም ያለበትን ወገን ጫና የሚያቃልል ውሣኔ ሰጪ አካልንም ተገቢና ግልጽ ሆኖ የሚታይ የጠራ ማስረጃ ካላገኙ ወደ ውሣኔ በአፊጣኝ እና በቀላለ እንዱደርስ ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑ ይታመናል።
በተያዘው ጉዲይ አከራካሪ ወደሆነው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24 ስንመጣ ይህ ድንጋጌ በጠቅላላው ሲታይ በሕግ የሕሉና ግምት የሚሸፈን የፍሬ ነገር ነጥብን /Legal presumptions/ የሚመለከት ሲሆን ዓይነቱም ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ25 እና 2ዐ26 ድንጋጌዎች ጋር ተዛምድ ሲታይ ውስን የሆነ የማስተባበያ ማስረጃ የሚቀርብበት /not freely rebuttable/ የሕግ የሕሉና ግምት ነው። የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24 የተለያዩ የክፍያ ዓይነቶች የሚዘረዝር ሆኖ ድንጋጌው በጠቅላላው ሲታይ ግን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሉከፈለ የሚገቡ ክፍያዎች /እዲዎች/ በዚሁ የሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሳይጠይቁ የቀሩ እንደሆነ ክፍያውን /እዲውን/ የመክፈል ኃላፉነት ያለበት ወገን የተባለውን ክፍያ /እዲ/ እንዱከፈለ የሕግ ግምት እንዱወሰድበት ያስገነዝባል።
ለተያዘው ጉዲይ ቀጥተኛ አግባብነትና ተፈፃማነት ያለው ድንጋጌ በተጠቀሰው ቁጥር በፉደል /ረ/ ስር የተመለከተው ድንጋጌ ሲሆን ሙለ ይዘቱም በሚከተለው መልኩ የተቀመጠው ነው።
ቁ 2ዐ24 በሁለት ዓመት የተወሰነ ጊዜ እዲው እንዱከፈል መጠየቅ ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈል የቀረ ገንዘብ እንደተከፈለ የሚቆጠረው።
/ረ/ በብድር ለተሰጠ፣ የገንዘብ ወለድና በጠቅላላውም የዓመት ጊዜ ተወስኖለት በየዓመቱ ወይም ከዚህ ባነሰ የጊዜ ውሣኔ ውስጥ ሉከፈል የሚገባው ዕዲ የሆነ እንደሆነ ነው።
የዚሁ ድንጋጌ የእንግሉዝኛው ቅጂም፡- Art. 2024 presumption of payment after two years The following debts shall be deemed to have been paid where two years have elapsed since they fell due: /f/ Interest on loans and generally any sum payable annually or at shorter periodical intervals.
በሚል ተቀምጧል።
ከላይ ከተጠቀሰው ድንጋጌ ይዘት አቀራረጽ እና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው የድንጋጌው መጀመሪያ ፓራግራፍ የመክፈያ ጊዜያቸው ከደረሰ ጊዜ አንስቶ ሁለት ዓመት ያለፊቸው እዲዎች /ክፍያዎች/ እንደተከፈለ ይቆጠራለ የሚል ሲሆን በተከታታይ የተዘረዘሩት ንዐስ ድንጋጌዎች ደግሞ የሕግ ግምት የሚወሰድባቸውን የክፍያ /እዲ/ ዓይነቶችን የሚዘረዝር ነው። በድንጋጌው ፉደል /ረ/ ስር የተመለከተው ሲታይ በብድር የተሰጠ ወይም ለማናቸውም የአከፊፈል ሁኔታ በየአመቱ ወይም ከዓመት ባነሰ ጊዜ እየተከፈለ እንዱያልቅ ጊዜ ተቆርጦለት የተሰጠ ገንዘብ ላይ የሚታሰብ ወለድ እዲው ከበሰለበት ወይም በየተወሰነ ጊዜ የሚከፈል ገንዘብ ከሆነ ደግሞ ገንዘቡ ተከፍል ማለቅ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት ያለፈ እንደሆነ በእነዚህ ክፍያዎች /እዲዎች/ ላይ ሉጠየቅ የሚችለው የወለድ ክፍያ እንደተከፈለ የሕግ ግምት የሚወሰድ መሆኑን ያሳያል። ይህም የሚያስገነዝበው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24/ረ/ ስር የተመለከተው ድንጋጌው ተፈፃሚነት የሚኖረው በብድር ለተሰጠ ገንዘብ ወለድ ላይ መሆኑንና ዋናውን የብድር ገንዘብ የማይጨምር መሆኑ ነው። ምክንያቱም ድንጋጌው ዋናውን የብድር ገንዘብ የሚጨምር ቢሆን ኖሮ ሕግ አውጪው የብድርን ገንዘብንና ወለድ በማለት ያስቀምጠው ነበር እንጂ ለብቻው ነጥል የብድር ገንዘብ ወለድን በማለት አይጽፈውም ነበር። ብድር ዋናው ዓላማ ሰዎች ዘርፈ ብዙ የሆኑ የግልና ማኀበራዊ ችግሮቻቸውን ማቋቋሚያ መንገድ ሆኖ ለኑሮ ድኀነትንና መድኀን መሆን ነው ተብል ይታመናል።
ሕጉም የዚህ ዓይነት ዓላማ ያለውን የሰዎች ሕጋዊ ግንኙነት መጠበቅ አለበት። ሕግ ሲተጎምም ሉፈፀም የሚችል ውጤት እንዱኖረው በማድረግ ስለመሆኑም ጠቅላላ የሕግ አተረጓጎም ደንቦች የግድ የሚለት ነው። በመሆኑም ከብድር አስፈላጊነትም ሆነ ከሕግ አተረጓጎም ደንብ አንፃር ሲታይ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24/ረ/ ሥር የተመለከተው ድንጋጌ ተፈፃሚነቱ በብድር ለተሰጠ የገንዘብ ወለድ እንጂ ለዋናው የብድር ገንዘብ አለመሆኑን ከድንጋጌው ይዘት፣ አቀራረጽና መንፈስ የምንገነዘበው ነጥብ ሆኖ አግኝተናል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም ተጠሪ በሥር ፍርድ ቤት ክስ ሲመሰርቱ ዲኝነት የጠየቁት ዋናውን የብድር ገንዘብ ሲሆን አመልካቾች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24/ረ/ መሰረት እንደተከፈለ ይቆጠራል በማለት የሚከራከሩት ይህንኑ ዋናውን የብድሩ ገንዘብ ነው። በግራ ቀኙ መካከል የተደረገው የብድር ውል ስምምነት የብድር ገንዘቡ በብድሩ ወቅት ወለድ የሚታሰብበት ስለመሆኑ አይገለጽም። ተጠሪ ዲኝነት ሲጠይቁ ወለድ እንዱታሰብላቸው የገለጹትም ከክሱ በኋላ ያለውን ሕጋዊ ወለድ ነው። በመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2ዐ24/ረ/ መሰረት በሁለት ዓመት ጊዜ ማለፍ እንደተከፈለ ሉቆጠር እና በፍ/ቤቱ የሕግ ግምት የሚወሰድበት የብድር ወለድ በተያዘው ጉዲይ የለም። አመልካቾች በዚህ ረገድ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት ያለው ሆኖ አልተገኘም። ስለሆነም አመልካቾች ብር 22,91ዐ /ሃያ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ አስር ብር/ ለተጠሪ በስር ፍርድ ቤት ክስ ከቀረበበት ቀን አንስቶ ከሚታሰብ ዘጠኝ በመቶ /9%/ ወለድ ጋር እንዱከፍለ መወሰኑ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ለማለት አልተቻለም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ