No summary available.
ታህሳስ 20 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ተገጌ ጌታነህ መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጠሪ፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው ጉዲይ በብድር የተሰጠን ገንዘብ የመክፈያ ጊዜ ጋር በተያያዘ ዕዲው እንደተከፈለ ሉቆጠር የሚችልበትን የሕግ አግባብና ትርጉም የሚመለከት ነው።
ክርክሩ የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጀ ፍርድ ቤት ሲሆን ከሣሽ የነበረው የአሁኑ አመልካች ባቀረበው አቤቱታ የአሁኑ አንደኛ ተጠሪ ለንግድ ስራቸው ማስፊፉያ የሚውል ታህሳስ 11 ቀን 1987 ዓ.ም በተፃፈ የብድር ውል ብር 10,000.00(አስር ሺህ ብር) የተበደሩ መሆኑን፣ ዋናውን ብድርና ልዩ ልዩ ወጪዎችን ጨምረው በዓመት 14% /አስራ አራት በመቶ/ ወለድ እየታሰበ ከታህሳስ 11 ቀን 1987 ዓ.ም ጀምሮ በየወሩ ብር 900.00(ዘጠኝ መቶ) እየከፈለ ሳያቋርጡ እስከ ታህሳስ 10 ቀን 1988 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ከፍለው ለማጠናቀቅ መስማማታቸውን፣ ሁለተኛ ተጠሪ ደግሞ አንደኛ ተጠሪ ለተበደረው ለዚሁ የገንዘብ መጠን የአንድነትና የነጠላ ዋስ በመሆን መፈረማቸውን በመግለፅ ዋናውን ብድር ብር 10,000.00(አስር ሺህ) እስከ ሐምል 24 ቀን 1992 ዓ.ም ድረስ የታሰበ ወለድ ብር 13,783.64(አስራ ሦስት ሺህ ሰባት መቶ ሰማንያ ሦስት ብር ከስድሳ አራት ሣንቲም) እና ለኢንሹራንስ የተከፈለ ብር 1,813.80(አንድ ሺህ ስምንት መቶ አስራ ሦስት ብር ከሰማኒያ ሣንቲም) ስለመሆኑ በመዘርዘር በድምሩ ብር 25,097.54(ሃያ አምስት ሺህ ዘጠና ሰባት ብር ከሃምሳ አራት ሣንቲም) ያልተከፈለ ዕዲ የመቀጫ ወለድ 3% ጨምሮ በድምሩ 17% ወለድ እየታሰበ ተጠሪዎች ባልተነጣጠለ ኃላፉነት እንዱከፍለ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት ጠይቋል።
አንደኛ ተጠሪ ቀርበው የቀረበባቸውን ክስ በመቃወም ክሱ በይርጋ ቀሪ ነው፣ መክፈል ያልቻልኩት በደረሰብኝ ኪሳራ ስለሆነ ለመክፈል የማልችል ስለሆነ ባንኩ ተገንዝቦ ከአስር ዓመት በላይ ስለቆየ ክሱ ውድቅ ነው የሚለትን ክርክሮች አንስተው ተከራክረዋል። ሁለተኛ ተጠሪ በበኩላቸው ባንኩ በተበዲሪው ላይ ክስ መስርቶ ሀብቱን ሣያጣራ በዋሱ ላይ ክስ መመስረቱ ያላግባብ መሆኑን፣ ባንኩ በአዋጅ በተሰጠው ሥልጣን መጠቀም ሲገባው ክስ መመስረቱም ከአዋጁ ዓላማ ውጪ መሆኑን ዘርዝረው ክሱ ውድቅ ሁኖ በነፃ ልሰናበት ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ጉዲዩን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለከተው የፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤትም ጉዲዩን ከመረመረ በኋላ አመልካች ለአንደኛ ተጠሪ የሰጠው ብድር ክፍያ መጠናቀቅ የነበረበት በውላቸው መሰረት እስከ ታህሳስ 10 ቀን 1988 ዓ.ም ነው፣ አመልካች በዚህ ጊዜ ውስጥ አልጠየቀም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) መሰረት አበዲሪው የተወሰነ ጊዜ ተበጅቶለት በዓመት ወይም ከዓመት በፉት የሚከፈለውን የገንዘብ ዕዲ ሣይጠይቅ እስከ ሁለት ዓመት ጊዜ ከቆየና ከሁለት ዓመት ጊዜ በኋላ ከጠየቀ ገንዘቡ በተበዲሪው እንደተከፈለ ወይም ዕዲው ምህረት እንደተደረገለት ሕግ ግምት ይወስዲል፣ ፋዳራለ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም በሰ/መ/ በሰጠው ውሣኔ ላይ በሕግ ግምት የሚሸፈን የፍሬ ነገር ክርክር ተከሳሽ ፍሬ ነገሩን ካደ አልካደ ፍርድ ቤቶች የሕግ ግምቱን ተፈፃሚ ማድረግ አለባቸው የሚል አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል የሚል ምክንያት በመያዝ አመልካች በተጠሪዎች ላይ ያቀረበው ክስ ተቀባይነት የለውም፣ ገንዘቡ በጊዜ ማለፍ እንደተከፈለ የሚቆጠር ነው የተጠሪዎች ግዳታ ቀሪ ሆኗል በማለት ወስኗል። አመልካች በዚሁ ውሣኔ ባለመስማማት ይግባኙን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቦ ይግባኙ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁጥር 337 መሰረት ተሰርዞበታል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም በዚሁ የበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የህግ ስህተት ተፈፅሟል በማለት ለማስቀየር ነው።
የአመልካች ነገረ ፈጅ የካቲት 22 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈት 3(ሦስት) ገፅ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሣኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈፅሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቅርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ የሥር ፍርድ ቤት ለጉዲዩ መሰረት ያደረገው ድንጋጌ አግባብነት የላለው መሆኑን፣ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2025 ስር የተመለከተውን ያላገናዘበ የሰበር ችልት ለፍ/ህ/ቁጥር 2024 የሰጠው ትርጉምም አምኖ ለሚከራከር ተከራካሪ ተፈፃሚነት የላለው መሆኑን በመጥቀስ ውሣኔው መሰታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ነው ተብል ተሽሮ ተጠሪዎች በሥር ፍርድ ቤት በቀረበባቸው ክስ መሰረት በብድር ዕዲ የሚፈለግባቸውን .54(ሃያ አምስት ሺህ ዘጠና ሰባት ብር ከሃምሳ አራት ሣንቲም) ተከፍል እስከሚያልቅ ድረስ 17% (አስራ ሰባት በመቶ) ወለድ እየታሰበ ከክርክሩ ወጪና ኪሣራ ጋር በአንድነትና በነጠላ እንዱከፍለ ይወሰንለት ዘንድ ዲኝነት መጠየቁን የሚያሳይ ነው። ይህ የሰበር ሰሚ ችልትም አመልካች በስር ፍርድ ቤት ያቀረበው ክስ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) መሰረት እንደተከፈለ ይቆጠራል በሚል ውድቅ እንዱሆን የመወሰኑን አግባብነት ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ቀርቦ እንዱታይ አድርጓል።
No topics extracted.
ለተጠሪዎች ጥሪ ተደርጎላቸው ሁለተኛ ተጠሪ መጥሪያ ደርሷቸው ያልቀረቡ ሲሆን አንደኛ ተጠሪ ቀርበው ሰኔ 28 ቀን 1999 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ መልሣቸውን ሰጥተዋል። ይዘቱም ባጭሩ የፍ/ብ/ህ/ቀጥር 2024(ረ) ለጉዲዩ አግባብነት ያለው መሆኑን፣ የሰበር ችልት በመ/ የሰጠው የሕግ ትርጉም ለጉዲዩ አግባብነት ያለው መሆኑን ዕዲው አለመከፈለን አምነው የተከራከሩት ሁኔታ አለመኖሩን ገልፀው የሥር ፍርድ ቤት ውሣኔ ሉፀና ይገባል በማለት የተከራከሩ ስለመሆኑ የሚያሣይ ነው። የአመልካች ነገረ ፈጅም ሐምል 25 ቀን 1999 ዓ.ም በተፃፈ የመልስ መልስ ማመልከቻ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ መሰረት ውሳኔ እንዱሰጥ ተከራክረዋል።
የጉዲዩ አመጣጥ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የቀረበውን ክርክር ጉዲዩ ለሰበር ችልት ቀርቦ ላታይ ይገባዋል ሲባል ከተያዘው ጭብጥ አኳያ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል።
ጉዲዩን እንደመረመርነው የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች ለተጠሪዎች ያበደረውን ብድርና ወለድ እንደተከፈለው ይቆጠራል በማለት ፍርድ ለመስጠት መሰረት ያደረጉት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024(ረ) ስር የተመለከተውን የሕግ ግምት በመሆኑ በዚህ አንቀፅ የተጠቀሰው የሕግ ግምት ለባንኮች የሚሰራ መሆን አለመሆኑ ይሰራል የሚባል ቢሆን አመልካች በምስክር፣ በሰነድና በላልች አግባብነት ባላቸው ማስረጃዎች ግምቱን ለማስተባበል ይችላል ወይስ አይችልም? የሚለት ነጥቦች መፈታት ያለባቸው ጭብጦች ሆነው አግኝተናቸዋል።
ለጉዲዩ እልባት ለመስጠት በቅድሚያ የሕግ ግምት ምንነት ባሕርያት በጠቅላላውና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2024(ረ) ድንጋጌን ይዘትና ባህሪን በትኩረት ማየትና መመርመር ያስፈልጋል።
የሕግ ግምት የሚለውን ጽንሰ ሀሳብ ስንመለከተው ሕግ አውጪውን ለግምት መነሻ ከሚሆኑ የተወሰኑ ፍሬ ጉዲዮች በመነሳት አንድ ድርጊት ተፈፅሟል ወይም አልተፈፀመም ብል የሚደርስበትን መደምደሚያ በሕግ የሚደነግጋቸውን ሁኔታዎች የሚያመላክት ነው። የሕግ ግምቶች ዳኞች አንድን ፍሬ ጉዲይ የተፈፀመ ወይም ያልተፈፀመ መሆኑን በማስረጃ በማረጋገጥ ረገድ የሚገጥማቸውን ክፍተት በመሙላትና የማስረዲት ሸክም ያለበትን ወገን ጫናውን በማቃለል በኩል የላቀ ጠቀሜታ ያላቸው መሆኑ ይታመናል። ጠቅለል ባለመልኩ ሲታይም የሕግ (የህሉና) ግምት ዓይነተኛ ዓላማ የማስረዲት ሸክም ያለበትን ወገን ጫና የማቃለል፣ ውሳኔ ሰጪ አካልንም ተገቢና ግልፅ ሆኖ የሚታይ የጠራ ማስረጃ ካላገኘ ወደ ውሳኔ በአፊጣኝ እና በቀላለ እንዱደርስ ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚሰጥ መሆኑ ይታመናል።
በተያዘው ጉዲይ አከራካሪ ወደሆነው የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 ስንመጣ ይህ ድንጋጌ በጠቅላላው ሲታይ በሕግ የሕሉና ግምት የሚሸፈን የፍሬ ነገር ነጥብን (Legal Presumptions) የሚመለከት ሲሆን ዓይነቱም ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2025 እና 2026 ድንጋጌዎቹ ጋር ተዛምድ ሲታይ ውስን የሆነ የማስተባበያ ማስረጃ የሚቀርብበት የሕግ የህሉና ግምት ነው። የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 የተለያዩ የክፍያ አይነቶች የሚዘረዝር ሆኖ ድንጋጌው በጠቅላላው ሲታይ ግን በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሉከፈለ የሚገቡ ክፍያዎች (እዲዎች) በዚሁ የሁለት አመት ጊዜ ውስጥ ሳይጠየቁ የቀሩ እንደሆነ ክፍያውን(እዲውን) የመክፈል ኃላፉነት ያለበት ወገን የተባለውን ክፍያ (እዲ) እንደተከፈለ የሕግ ግምት እንደሚወሰድበት ያስገነዝባል።
ለተያዘው ጉዲይ ቀጥተኛ፣ አግባብነትና ተፈጻሚነት ያለው ድንጋጌ በተጠቀሰው ቁጥር በፉደል(ረ) ስር የተመለከተው ድንጋጌ ሲሆን ሙለ ይዘቱም በሚከተለው መልኩ የተቀመጠው ነው።
ቁ 2024 በሁለት አመት የተወሰነ ጊዜ እዲው እንዱከፈል መጠየቅ ከሚገባበት ቀን ጀምሮ እስከ ሁለት ዓመት ሳይከፈል የቀረ ገንዘብ እንደተከፈለ የሚቆጠረው (ረ) በብድር ለተሰጠ የገንዘብ ወለድና በጠቅላላውም የዓመት ጊዜ ተወስኖለት በየዓመቱ ወይም ከዚህ ባነሰ የጊዜ ውሳኔ ውስጥ ሉከፈል የሚገባው ዕዲ የሆነ እንደሆነ ነው።
የዚሁ ድንጋጌ የእግሉዘኛው ቅጂም፡- Art.2024 presumption of payment after two years The following debts shall be deemed to have been paid where two years have elapsed since they fell due: (f) interest on loans and generally any sum payable annually or at shorter periodical intervals. በሚል ተቀምጧል። ከላይ ከተጠቀሰው ድንጋጌ ይዘት አቀራረፅ እና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው የድንጋጌው መጀመሪያ ፓራግራፍ የመክፈያ ጊዜያቸው ከደረሰ ጊዜ አንስቶ ሁለት አመት ያለፊቸው እዲዎች(ክፍያዎች) እንደተከፈለ ይቆጠራለ የሚል ሲሆን በተከታይ የተዘረዘሩት ንዐስ ድንጋጌዎች ደግሞ የሕግ ግምት የሚወሰድባቸውን የክፍያ (እዲ) ዓይነቶችን የሚዘረዝር ነው። በድንጋጌው ፉደል(ረ) ስር የተመለከተው ሲታይ በብድር የተሰጠ ወይም ለማናቸውም የአከፊፈል ሁኔታ በየአመቱ ወይም ከአመት ባነሰ ጊዜ እየተከፈለ እንዱያልቅ ጊዜ ተቆርጦለት የተሰጠ ገንዘብ ላይ የሚታሰብ ወለድ እዲው ከበሰለበት ወይም በየተወሰነ ጊዜ የሚከፈል ገንዘብ ከሆነ ደግሞ ገንዘቡ ተከፍል ማለቅ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ሁለት ዓመት ያለፈ እንደሆነ በእነዚህ ክፍያዎች (እዲዎች) ላይ ሉጠየቅ የሚችለው የወለድ ክፍያ እንደተከፈለ የሕግ ግምት የሚወሰድ መሆኑን ያሳያል።
ከላይ እንደተመለከትነው ይህ ድንጋጌ አስገዲጅ የሆነ የሕግ ግምት መሆኑ የመጀመሪያው ባህሪው ሲሆን ማናቸውም የተፈጥሮም ሆነ የሕግ ሰው(ባንክና ላልች አበዲሪ ተቋማት) የገንዘብ ብድር ካበደረ በኋላ ብድሩ ተከፍል የሚያልቅበትን የጊዜ ገደብ ካበቃ ከሁለት ዓመት በኋላ የብድሩ የወለድ ይከፈለኝ ጥያቄ በሕግ እንደተከፈለ የሚገመት መሆኑን የሚደነግግ ድንጋጌ ነው። በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር የተመለከተው የሕግ ግምት ለዳኞች የሕሉና ሚዛን እድል የማይሰጥ ዳኞች የነገሩን ሁኔታ በማየት ሲፈልጉ የሚጠቀሙበት፣ ከነገሩ ሁኔታ አንፃር አስፈላጊ ሆኖ ካላገኙት የሚተውት ፈቃጅ የሆነ የሕግ ግምት አይደለም። በአንጻሩ ይኸው ድንጋጌ የሚሸፍነው ጉዲይ ባጋጠማቸው ጊዜ ዳኞች ያለምርጫ ሉከተለትና ሉፈፅሙት የሚገባ አስገዲጅ የሕግ ግምት ነው።
በዚህ ድንጋጌ ስር የሰፈረው የሕግ ግምት ሁለንም አይነት ዕዲዎች በአጠቃላይ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ባንኮች በሚሰጧቸው ብድሮችም ጋር ተያይዘው የሚነሱ ጉዲዮችን ጭምር የሚመለከት ነው። በመሆኑም አመልካች ይኸው አንቀፅ ባንኮች ለሚያቀርቡት ክስ አግባብነት የለውም በማለት ያቀረበው ክርክር ተቀባይነት ያለው አይደለም።
ከዚህ ጋር ተያይዞ መታየት ያለበት ላላው ነጥብ ይኸው የሕግ ግምት የሚመለከተው ወለደን ብቻ ነው ወይስ ዋናውን ዕዲ ያጠቃልላል የሚለው ጥያቄ ነው። ጉዲዩን የተመለከተው የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ድንጋጌውን በመጠቀስ ወለደ ብቻ ሳይሆን ዋናውን ዕዲ ጭምር ሁለት ዓመት ካለፈው እንደተከፈለ ይቆጠራል በማለት ወስኗል። አመልካች ባንክ ይህ ትክክለኛ ትርጉም አይደለም በማለት ይከራከራል።
በዚህ ረገድ የቀረበውን ቅሬታ ለመፍታት የድንጋጌውን አቀራረፅ እና መንፈስ በጥንቃቄ መመርመር ይስፈልጋል። አከራካሪ የሆነው የሕግ አንቀፅ በብድር ለተሰጠ የገንዘብ ወለድና በጠቅላላውም የዓመት ጊዜ ተወስኖለት በየዓመቱ ወይም ከዚህ ባነሰ የጊዜ ውሳኔ ውስጥ ሉከፈል የሚገባው ዕዲ የሆነ እንደሆነ …(ሰረዝ የተጨመረ) በማለት የሚደነግግ ነው። ከዚሁ የሕግ ድንጋጌ መገንዘብ እንደሚቻለው የድንጋጌው የመጀመሪያው ክፍል በብድር የተሰጠ የገንዘብ ወለድን በልዩ ሁኔታ ጠቅሶ በሁለት ዓመቱ የሕግ ግምት ውስጥ እንደሚካተት ያስቀምጣል። ሕግ አውጪው በዚሁ አንቀፅ የሰፈረው የሕግ ግምት ዋናውንም ዕዲ እንደያጠቃልል ቢፈልግ ኖሮ ወለደን ለይቶ ያስቀምጣል ተብል አይገመትም። ስለዚህ በድንጋጌው የመጨረሻ ክፍል የሚገኘውና “ሉከፈል የሚገባው ዕዲ” የሚለው ሐረግ ብድርን ለመመልከት የገባ ነው ለማለት የሚቻል ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም ድንጋጌው ወለደንና ዋናውን ዕዲ ለይቶ በሕግ ግምት የሚሸፍነው ወለደ ብቻ እንደሚሆን አድርጊ እያለ በመጀመሪያው ደረጃ ፍርድ ቤት ዋናው ዕዲ ጭምር ሁለት ዓመት ካለፈው በሕግ ግምት እንደተከፈለ ይቆጠራል ተብል የተሰጠው ውሳኔ ትክክል ሆኖ አላገኘነውም።
በሁለተኛ ደረጃ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር የተደነገገው የሕግ ግምት በማስረጃ ቀሪ ላሆን የሚችለው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2025 ድንጋጌ ስር በተመለከቱት መንገድች ነው። ሆኖም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 ስር የተቀመጠውን የሕግ ግምት ለማፍረስ የሚያስፈልጉት ማስረጃዎች በጣም ውስንና በሕግ በግልጽ የተደነገጉ መሆናቸውን ማየትና በጥብቅ ሥርዓት እና በውስን የማስረጃ ዓይነቶች ብቻ ሉስተባበል የሚችል የሕግ ግምት መሆኑን መገንዘብ የግድ ይላል። በዚህም መሰረት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር የተደነገገው የሕግ ግምት ቀሪ ላሆን የሚችለው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2025 ስር እንደተመለከተው ባለዕዲው በፁሐፍ ዕዲውን ያመነ እንደሆነ በሕግ የተደነገገው የጊዜ ውሳኔ ሳይደርስ ባለገንዘቡ ገንዘቡን እንዱከፍለው ባለዕዲውን ከፍርድ ቤት አስጠርቶ የሆነ እንደሆነ ነው። ከዚህም በላይ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2026 ድንጋጌ ሲታይ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር የተመለከተው በሕግ የተሸፈነ የፍሬ ነገር የህሉና ግምት ከመሒላ ቃል በስተቀር በልላ ማስረጃ ሉፈርስ እንደማይችል ደንግጓል።
በመሆኑም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር የተመለከተው የሕግ ግምት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2025 ስር በተመለከቱት ሁለት ዓይነት ማስረጃዎች ቀሪ የሚሆን ሲሆን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2026 ንዐስ ቁጥር ሁለትና ሦስት ድንጋጌዎች መሰረት ደግሞ በመሒላ ቃል ካልሆነ በቀር በልላ አይነት ማስረጃ ሉስተባበል የማይችል ማስረጃ መሆኑን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2026(1) ድንጋጌ በግልፅ ያስቀመጠው ጉዲይ ነው። ይህም በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር የተመለከተውን የሕግ ግምት ለማስተባበል ያለው ዕድል ውስንና ጠባብ መሆኑን የሚያስገነዝብ ነው። እንግዱህ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 አስገዲጅ የሆነ እና በውስን መንገድች ብቻ ሉስተባበል የሚችል የሕግ ግምት መሆኑ ሁለት ግልፅና የተለዩ ባሕርያት ያለት ድንጋጌ መሆኑን ከላይ ከገለፅናቸው ህጋዊ ምክንያቶች መገንዘብ የምንችለው ነጥብ ነው።
በልላ በኩል የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ድንጋጌ ስር የተደነገገውን የሕግ ግምት ባንኮች ለማስተባበል የሚችለት በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 2025 እና 2026 ድንጋጌ ስር በተመለከቱት ማስረጃዎች ብቻ ነው ወይስ የሰው ምስክር የሰነድና ላልች ማስረጃዎችን በማቅረብ የሕግ ግምቱን ማፍረስና ማስተባበል ይችላለ? በልላ አገላለፅ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2026 ንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ መሰረት ባንኮች ያበደሩትን ብድርና ወለድ ያልተከፈላቸው መሆኑን ለማስረዲት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ ላይ ተፈፃሚነት አለው ወይስ የለውም? የሚለው ነጥብ ላታይ የሚገባው ነጥብ ሆኖ ተገኝቷል።
ለጥያቄው ተገቢውን ምላሽ ለማግኘት ይቻል ዘንድም ባንኮችና ላልች ገንዘብ አበዲሪ ተቋማት ገንዘብ ያበደሩ መሆኑን ያበደሩት ገንዘብ ያልተከፈላቸው መሆኑን ለማስረዲት ሉያቀርቡ ስለሚገባው የማስረጃ አይነት እንደዚሁም በተመሳሳይ ሁኔታ የባንክና የላልች ገንዘብ አበዲሪ ተቋማት ደንበኞች ገንዘብ ያለመበደራቸውን ወይም ብድር መክፈላቸውን ለማስረዲት ሉያቀርቡ ስለሚገባው የማስረጃ አይነት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2473 ንዐስ አንቀፅ ሁለት የተደነገገውን ማየትና ማገናዘብን ያስፈልጋል።
በመሰረቱ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2472(1) በብድር የተሰጠ ገንዘብ ከአምስት መቶ የኢትዮጵያ ብር በላይ ሲሆን የብድሩን ውል በፁሐፍ ወይም በፍርድ ቤት በተደረገ የእምነት ቃል ወይም መሒላ ካልሆነ በቀር ለማስረዲት የማይቻል መሆኑን በአስገዲጅ ኃይለ ቃል የደነገገ ሲሆን የተጠቀሰው ድንጋጌ ንዐሰ ቁጥር ሁለት ደግሞ በንዐስ ቁጥር አንድ ከተመለከተው ልዩ የሰነድ ማስረጃ በስተቀር ለብድር ውል ማናቸውም ላላ ማስረጃ ለማቅረብ የማይቻል መሆኑን ደንግጓል።
ሆኖም በባንክ፣ በአበዲሪ ተቋማት እና በደንበኞቻቸው መካከል ያለውንና የሚኖረውን የጠበቀ እምነትና ግንኙት፣ ባንኮችና አበዲሪ ተቋማት የዕለት ተዕለት የሥራ ተግባራቸው ብድር በመስጠትና ተከፊይ የብድር ገንዘብ በመሰብሰብ ቀልጣፊ የፊይናንስና የንግድ ግንኙነት እንዱኖር በማድረግ በኩል ከፍተኛ ድርሻ ያላቸው መሆኑን በማገናዘብ ሕግ አውጪው ባንኮችና ላልች አበዲሪ ተቋማት ደንበኞቻቸው ገንዘብ የተበደሩና የተበደሩትን ገንዘብ ያልከፈለ መሆኑን ለማስረዲት በተመሳሳይ ሁኔታ የባንክ ተበዲሪ ብድር ያልወሰደ ወይም የወሰደውን ብድር የከፈለ መሆኑን ለማስረዲት በሰው ምስክር እና በሕሉና ግምት ለማስረዲት የሚችለ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2473(2) ስር ተደንግጓል። ይህ ድንጋጌ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2472 ድንጋጌ ጋር ተጣምሮ ሲነበብ በባለባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ስላለ ግንኙነት ላቀርብ የሚችለውን ማስረጃ አይነት በተመለከተ አመላካች የሕግ ድንጋጌ በመሆኑ ባንኮችም ሆነ ተበዲሪዎች የሰነድ የሰው ማስረጃ እና ላልች አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎችን በማቅረብ ለማስረዲት የሚችለ መሆኑን ያስገነዝባል። የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2473 ንዐስ ቁጥር ሦስት ድንጋጌ በተለየ ሲታይም በባለባንኮችና በደንበኞቻቸው መካከል ስላለ ግንኙነቶች የብድርን ውል ወይም የተበደረውን ገንዘብ መልሶ መክፈልን በምስክሮች ወይም በአእምሮ ግምት ለማስረዲት የሚቻል ስለመሆኑ መደንገጉ ከላይ የተመለከተውን ምክንያት የሚያጠናክር ነው።
የባንክ ደንበኞች የተበደሩትን የብድር ወለድ የከፈለ መሆኑን በሕሉና ግምት ለማስረዲት ከሚችልባቸው ሁኔታዎች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ድንጋጌ ስር የተመለከተው የሕግ ግምት አንደኛው ሲሆን ይህ ከሆነ አበዲሪው ባንክ ደንበኛው በህሉና ግምት ከፍዬዋለሁ በማለት ያቀረበበትን ክርክር ለማስተባበልና የብድሩ ወለደ ያልተከፈለው መሆኑን ለማስረዲት በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2473(2) ስር በተደነገገው መሰረት የሰው ምስክር፣ የህሉና ግምት፣ የሰነድና ላልች ማስረጀዎችን በማቅረብ ግምቱን ማስተባበል የሚችል በመሆኑ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2026 ንዐስ ቁጥር አንድ ድንጋጌ ለባንኮችና ለደንበኞቻቸው መብት ልዩ ጥበቃ የሚያደርገውን የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2473 ንዐስ ቁጥር ሁለት ድንጋጌን ዋጋ በሚያሳጣ መልኩ ሉተረጎምና ተፈፃሚ ላሆን አይገባም። በመሰረቱ የብድር አገልግልት መስጠት፤ ከተሰጠውም ብድር በማትረፍ የተሻለ አገልግልት መስጠት የባንክ እና አበዲሪ የፊይናንስ ተቋማት ዋና ተግባር ብቻ ሳይሆን ለእነዚህ ተቋማት ሕልውና መሰረት ሲሆን ተበዲሪዎች ብድሩን ለማንኛውም የኢኮኖሚ መስክ ለማዋል የሚችለት ይኸው የአበዲሪ ገንዘብ ተቋማት ህልውና ሲጠበቅ ነው። ይህ ሉሳካ የሚችለው ደግሞ ህግ አውጭው ለእነዚህ ተቋማት ያደረገውን ልዩ ጥበቃ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት በሕጉ ሉፈፀም የሚችል ውጤት የሚሰጥ ትርጉም በመሰጠት መሆኑን አምነንበታል። ስለሆነም በእነዚህ ሕጋዊ ምክንያቶች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2026(1) ስር የተመለከተው ድንጋጌ በባንኮች፣ በላልች አበዲሪ ተቋማት እና በደንበኞቻቸው መካከል ያለውን ግንኙነት በተመለከተ ተፈፃሚነት የላለው የሕግ ድንጋጌ ሆኖ አግኝተነዋል።
ስለሆነም ባንኮች በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024(ረ) ስር በተመለከተው የሕግ ግምት የሚገዙ ቢሆንም ለደንበኞቻቸው ያበደሩት የብድር ወለድ ያልተከፈለ መሆኑን የሰው ምስክር፣ የሰነድና ላላ ማስረጃ በማቅረብ ይህን የሕግ ግምት ለማስተባበል የሚችለበት የፍርድ ሂደት መኖር ይገባዋል። በዚህ መሰረት በመሆኑ የበታች ፍርድ ቤቶች አመልካች የብድሩ ወለደ ያልተከፈለው መሆኑን ለማስረዲት እድለን ሳይሰጡ፣ ያቀረባቸውንም ማስረጃዎችን ሳይመረምሩና ሳይመዝኑ ውሳኔ መስጠታቸው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2473(2) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ መንፈስና ዓላማውን ባላገናዘበ መልኩ ሆኖ ስለአገኘነው ውሳኔው መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ አግኝተናል።
በስር ፍርድ ቤት በዋና ተበዲሪነት የተከሰሱት የአሁኑ አንደኛ ተጠሪ ከስር ጀምሮ ያቀረቡትን ክርክር በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 2024 ስር የሰፈረው የሕግ ግምት እና አመልካች ካቀረባቸው ማስረጃዎች አንፃር ነገር ስንመለከተው በአመልካች የተጠየቀው እዲ ያልተከፈለ መሆኑን ተገንዝበናል። ስለሆነም አንደኛ ተጠሪ የሕግ ግምት ተጠቃሚ ቢሆኑም አመልካች ይህንን የሕግ ግምት ሉያፈርስ የሚችል በቂ ማስረጃ ያቀረበ በመሆኑ በክርክሩ ሂደት በተረጋገጠው መሰረት አንደኛ ተጠሪ ዕዲውን የማይከፈለበትን ህጋዊ ምክንያት አላገኘንም።
የሁለተኛ ተጠሪ ክርክር ሲታይም አመልካች በአንደኛ ተጠሪ ክስ መስርቶ ሃብት ሳያጣራና በህጉ በተሰጠው ስልጣን መሰረት መብቱን ሳያስከብር ዋሱ ላይ ክስ መመስረት አይችልም በማለት የሚከራከሩ የነበረ መሆኑንና በዚህ ችልትም ካለመቅረባቸውም በላይ የአንደኛ ተጠሪ ክርክር የሚጠቅማቸው አለመሆኑን ተገንዝበናል። ሁለተኛ ተጠሪ የገቡት የዋስትና ዓይነት የአንድነትና የነጠላ እንደመሆኑ መጠን አመልካች ተጠሪን ከዋናው ተበዲሪ ጋር በአንድ ላይ መክሰሱ ከፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 1933(1) ድንጋጌ አንፃር ህጋዊ ሲሆን በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረትም የተሰጠውን ሥልጣን ባንክ የሚጠቀመው መያዣ በአስያዡ ተበዲሪዎች ላይ ሆኖ በእነዚህ ተበዲሪዎችም ቢሆን ባንክ በአዋጁ የተሰጠውን ሥልጣን በመተው ፍርድ ቤት ክስ ከመመስረት የሚከለክልበት ህጋዊ ምክንያት አለመኖሩን ሕጎቹ ያሳያለ። በመሆኑም ሁለተኛ ተጠሪም በገቡት ግዳታ አይነትና በክርክሩ ሂደት በተረጋገጠው መሰረት ለክርክሩ መነሻ የሆነውን ገንዘብ ለአመልካች የማይከፍለበትን ህጋዊ ምክንያት አላገኘንም። በዚህም ምክንያት ተከታዩን ወስነናል።
ው ሣ ኔ