No summary available.
ታህሣሥ 06 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- የህፃን ኮከቤ ተፈረ ሞግዚትና አስተዲዲሪ ፀሐይ በየነ ቀረበ ተጠሪ፡-
ለዚህ የሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው አመልካች በሞግዚታቻው አማካኝነት ለፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካች በክሳቸው የአመልካች እናት ንብረት ለማስተዲደር እንጂ ለመሸጥ ስልጣን ሳይኖራቸው ለአመልካች ከአባታቸው በውርስ የሚተላለፍላቸውን ቤት ለአንደኛ ተጠሪ የሸጡ በመሆኑና ሁለተኛ ተጠሪም ወኪል ነኝ በማለት ቤቱን ይዘው ስለሚገኙ የሽያጩ ውል ፈርሶ ወደነበርበት እንዱመልሱ እንዱወሰንላቸው ጠይቀዋል። ክሱ ለተጠሪዎች ደርሷቸው በሰጡት መልስ ከሳሽ ክሱን ለማቅረብ መብት የላቸውም ክሱም በይርጋ ቀሪ ይሆናል በማለት ክርክር አቅርበዋል። ፍ/ቤቱም አመልካች ክስ ለማቅረብ መብት የላቸውም የሚለውን መቃወሚያ ውድቅ ካደረገ በኋላ በአመልካች እናትና በአንደኛ ተጠሪ መሐከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል በፁሁፍና ውል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠው ሰው ወይም በፍርድ ቤት ፉት ያልተከናወነ በመሆኑ ረቂቅ እንጂ በህግ ፉት የሚፀና ውል ስላልሆነ ውል በላለበት ሁኔታ የውል ይፍረስልን ጥያቄ ላቀርብ አይችልም፣የይርጋ መቃወሚያም ላቀርብበት አይችልም በማለት መዝገቡን ዘግቶታል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የስር ውሳኔን አጽቶታል። የአሁን የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። ይህ ችልት የውል አፃፃፍ ፍርም አለመከተል በተዋዋይ ወገን ወይም በማናቸውም ያገባኛል ባይ ውል እንዱፈርስ ጥያቄ በቀረበ ጊዜ የሚታይ ነው ወይስ ፍ/ቤቱ በእራሱ አነሳሽነት ሉያየው ይችላል? የሚለውን የሕግ ነጥብ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በፁሁፍ አቅርበዋል።
ችልቱም መዝገቡ መርምሯል።
አመልካች በሞግዚታቸው አማካኝነት ያቀረቡት ክስ በአመልካች እናትና በአንደኛ ተጠሪ መሐከል የተደረገው የቤት ሽያጭ ውል እንዱፈርስና ግራ ቀኙ ወደነበሩበት እንዱመለሱ ነው። ተጠሪዎችም ቢሆኑ ይህ ውል ስለመደረጉ አምነው ላልች ክርክሮችን አቅርበዋል። ነገር ግን ፍ/ቤት የቤት ሸያጩ ውል በፁሁፍና ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ፉት ወይም ፍ/ቤቱ ያልተደረገ በመሆኑ ክርክር ላቀርብበት የሚችል ውል የለም በማለት ወስኗል። በእርግጥ የማይንቀሳቀስ ንብረት ባለቤትነትን ለማስተላለፍ የሚደረግ ውል በፁሁፍና ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ፉት ወይም በፍ/ቤት ካልተደረገ ውጤት የላለው መሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1723 ስር ተመልክቷል። ይህን በሕጉ የተመለከተው የአፃፃፍ ስርአትን አለመከተል የሚያስከተለው ውጤት ምን እንደሆነ ደግሞ በዚሁ ሕግ ቁጥር 1808/2/ ስር ተቀምጧል። በዚህም መሰረት የአፃፃፍ ስርአት ያላሟላ ውል የሚፈርሰው ከተዋዋዮቹ በአንደ ወይም ማናቸውም ጥቅም ያለው ሰው ሲጠየቅ እንደሆነ ተመልክቷል። ይህም አንድ የአፃፃፍ ስርአትን ያላሟላ ውል በሕጉ በተመለከቱት ሰዎች እንዱፈርስር ጥያቄ አስካልቀረበበት ድረስ ከጅምሩ ፈራሽ ነው ልባል እንደማይችል ያስገነዝበናል። ውለ የአፃፃፍ ስርአትን ባለመከተለ ምክንያት እንዱፈርስ ጥያቄ እስካልቀረበ ፍ/ቤቱ በራሱ አነሳሽነት የአፃፃፍ ስርዓቱን ምክንያት በማድረግ ውለን ከጅምሩ ውድቅ ሉያደርግ የሚችልበት የሕግ ምክንያት የለም። በዚህም ምክንያት የስር ፍ/ቤት በውለ የአፃፃፍ ስርአትን ባለመከተለ ምንም አይነት ክርክር ላቀርብበት አይችልም በሚል የደረሰበት መደምደሚያ የሕግ መሰረት ያለው ሆኖ አላገኘውም።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 14336 በሐምል 27 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 59734 ኀዲር 24 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት የመልካችን እና የተጠሪዎችን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ ተገቢውን ውሳኔ እንዱሰጥ ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ ይቻቻለ።
No topics extracted.