No summary available.
ህዲር 15 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሃይ ታደሰ ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ አመልካች፡- አቶ መዝገቡ መድህኔ - ጠ/ሐጎስ ደበሱ ቀረቡ ተጠሪ፡- የአ.አ ከተማ አስተዲደር - ነ/ፈጅ አትርሣው ወልዳ ቀረቡ
በዚህ መዝገብ የሰበር አቤቱታ የቀረበው አመልካች ተጠሪ ላወጣው ጨረታ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ብር 20,000(ሃያ ሺህ) ሉመለስ አይገባም ተብል የተሰጠውን ውሳኔ ለማስለወጥ ነው። አመልካች በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ ተጠሪ ባወጣው የጨረታ ብር 2,000,000(ሁለት ሚሉዮን) የሚያወጡ 32 አይነት እቃዎች ለማቅረብ የተወዲደሩ ቢሆንም ያሸነፈት በሁለት አይነት እቃዎች ብቻ በመሆኑ ውል እንዱሞለ የቀረበላቸውን ጥያቄ ባለመቀበላቸው ተጠሪ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ አልመልስም በማለቱ ገንዘቡን እንዱመልስላቸው ጠይቀዋል። ተጠሪም ለክሱ በሰጠው መልስ አመልካች ባሸነፈባቸው ሁለት አይነት እቃዎች ውል እስካልፈረሙ ድረስ ገንዘቡ ሉመለስላቸው እንደማይገባ ተከራክሯል። ፍ/ቤቱም አመልካች በዋስትና ሰነደ ላይ የተመለከተውን ግዳታ እስካልተወጡ ድረስ ገንዘቡ ሉመለስላቸው አይገባም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጎታል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ይግባኝ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት አቅርበው የነበረ ቢሆንም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቶባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። የሰበር አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በመባለም ግራ ቀኙ ቀርበው የቃል ክርክራቸው ተሰምቷል። መዝገቡም እንደሚከተለው ተመርምሯል።
ተጠሪ ባወጣው የጨረታ ማስታወቂያ አመልካች 32 አይነት እቃዎች ለማቅረብ ተወዲድረው ለጨረታ ማስከበሪያም የእነዚህ እቃዎች ዋጋ አንድ በመቶ ማስያዛቸውን ከክርክሩ ሂደት ተገንዝበናል። አመልካች የተወዲደሩበት የጠቅላላ ንብረቶቹ ዋጋ ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሉዮን) ስለሆነ የተያዘው ገንዘብ ብር 20,000(ሃያ ሺህ) ስለመሆኑና አመልካች ከተወዲደሩበት 32 አይነት እቃዎች ውስጥ ያሸነፈት በሁለት እቃዎች ብቻ ለመሆኑ ግራ ቀኙ አልተካካደም። አከራካሪው ጉዲይ አመልካች ላሸነፈበት ሁለት እቃዎች ውል አለመፈረማቸው ያስያዙት ብር 20,000(ሃያ ሺህ) እንዲይመለስላቸው ይከለክላል ወይስ አይከለክልም? የሚለው ነው።
የጨረታ ማስከበሪያ ማለት አንድ ተጫራች ጨረታውን ቢያሸንፍ ውል የሚፈፅም ለመሆኑ ዋስትና እንዱሆን የሚያዝ ገንዘብ ነው። ለውል መፈፀም ዋስትና ሲባል የሚያዝ ገንዘብ እንደመሆኑም መጠን የጨረታው አሸናፉ ባሸነፈው መሰረት ውል ካልፈረመ የጨረታው ማስከበሪያ ይያዝበታል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ብር 2,000,000 (ሁለት ሚሉዮን) ለሚያወጡ 32 ዓይነት እቃዎች ተጫርተዋል። ለጨረታ ማስከበሪያም የተጫረቱባቸውን ጠቅላላ እቃዎች ዋጋ አንድ በመቶ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) አስይዘዋል። ከክርክሩ ሂደትም አመልካች ከተወዲደሩባቸው እቃዎች ውስጥ ያሸነፈት በሁለቱ እቃዎች ብቻ መሆኑን ተረድተናል። ተጠይቀውም ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ያልሆኑት እነዚህን ሁለት እቃዎች በተመለከተ ነው። አመልካች 20,000(ሃያ ሺህ) ብር የጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ጠቅላላ ለተጫረቱበት እቃዎች በመሆኑ ጠቅላላው የጨረታ ገንዘብ ሉያዝ የሚገባው አመልካች በተወዲደሩባቸው እቃዎች በሙለ አሸናፉ ቢሆኑና በዚሁ መሰረት ውል አልፈርምም ቢለ ነበር።
አመልካች ያሸነፈት ግን በሁለት እቃዎች በመሆኑ ለነዚህ እቃዎች ውል ለመፈረም ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የጨረታው ማስከበሪያ ሉያዝ የሚገባው አሸናፉ በሆኑባቸው እቃዎች ዋጋ መጠን የተያዘው ገንዘብ እንጂ አመልካች ለ32 አይነት እቃዎች ላስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ በጠቅላላ ላሆን አይገባም ባላሸነፈባቸው ዕቃዎች ቀድሞውንም ውል ለመዋዋል ስለማይችለ ለነዚህ እቃዎች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ውል አልፈፀሙም ተብል ሉያዝባቸው የሚገባበት ምክንያት የለም። በመሆኑም አመልካች ላሸነፈት ሁለት አይነት እቃዎች ውል አልፈረሙም በሚል ለ32 አይነት እቃዎች ያስያዙት ብር 20,000(ሃያ ሺህ) በሙለ ሉያዝ ይገባል በሚል የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ሆኖ ተገኝቷል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ጥቅምት 25 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ሐምል 15 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሻሽሎል።
No topics extracted.
አመልካች ለ32 ዓይነት እቃዎች ካስያዙት ብር 20,000(ሃያ ሺህ) ሉያዝባቸው የሚገባው ጨረታ ያሸነፈባቸው ሁለት እቃዎች ዋጋ አንድ በመቶ ብቻ ስለሆነ ይኸው ገንዘብ ተቀንሶ ቀሪው ገንዘብ እንዱመለስላቸው ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።