No summary available.
ኀዲር 10 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሐጏስ ወልደ ሑሩት መለሰ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አየለ ሐብተየስ - ጠ/ውብሸት ክብሩ ቀረቡ ተጠሪ፡-
ለዚህ ሰበር አቤቱታ መነሻ የሆነው ጉዲይ የጀመረው አመልካች ለፋ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ነው። አመልካች ለፍ/ቤቱ ባቀረቡት ክስ ከተጠሪዎች ለፍቶ ቤትነት ለ10 አመት የተከራዩትን ቤት መብራት ጠ/ሻምበል ተሾመ ደምሴ ቀረቡ ውሐ በመቁረጥ የፍቶ ቤት ስራው ሙለ በሙለ እንዱቋረጥ ስላደረጉ መብራቱን ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ክስ እስከቀረበበት ጊዜ ድረስ ላለት 76 ቀናት የተቋረጠ ጥቅም ብር 64,752(ስልሳ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ሁለት) ተጠሪዎች እንዱከፍለና መስመሩን እንዱቀጥለ ጠይቀዋል። ተጠሪዎችም ቀርበው አመልካች የተከራዩት ቤቱን እንጂ ውሐና መብራቱን አይደለም፣የኤላትሪክ ቆጣሪው የሚገኘው የሕብረት ባንክ የተከራየው ህንፃ ውስጥ ነው፣ለስራ እንዱያመቸው ባንኩ የኤላክትሪኩንና የውሐውን መስመር ለግለ እንድናደርግ ስለጠየቀ ተገቢ ማስጠንቀቂያ ለአመልካች በመስጠት መስመሩ መቋረጡ በሕግም ሆነ በሞራል የሚያስነቅፍ ስላይደለ የተቋረጠ ገቢ ልንከፍል አይገባም፣ክፈለ እንኳን ከአገር ውስጥ ገቢ በሚቀርብ ማስረጃ ሉወሰን ይገባል በማለት ተከራክረዋል።
ፍ/ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክርና ማስረጃ መርምሮ የመብራት መስመሩ በኪራይ ስምምነት ውስጥ ስላልተካተተ እና ህብረት ባንክ በሚጠቀምበት ህንፃ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ የመብራት መስመሩ ይቀጠልልኝ ሉለ አይችለም።
ነገር ግን ተጠሪዎች አመልካች ላላ የሃይል አቅርቦት አማራጭ ለመፈለግ የሚያስችል ቢያንስ የ1 ወር ጊዜ መስጠት ሲገባቸው ከቅን ልቦናና ከልማዲዊ አሰራር ውጪ የሆነ ተግባር በመፈፀማቸው የ1 ወር ትርፍ የመተካት ሐላፉነት ስላለባቸው በርትእ ብር 4000(አራት ሺህ) እንዱከፍለ ሲል ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅረበው ፍ/ቤቱ ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ተጠሪዎች ቤቱን ያከራዩት ለፍቶ ቤት ንግድ ስራ በመሆኑና ከፍቶ ማንሳት፣ማጠብና ተያያዠነት ያላቸው ሥራዎች በአላትሪክ ሃይል አማካኝነት የሚሰሩ እንደመሆኑ መስመሩን ማቋረጣቸው አይነተኛ የውል መጣስ ተግባር ስለሆነ ለተቋረጠ ገቢ ብር 64,572(ስልሳ አራት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ሁለት) ኪለፈለ ይገባ፣የተቋረጠውን መስመር መልሰው ይቀጥለ በማለት ወስኗል። ተጠሪዎች በዚህ ውሳኔ ላይ ለፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ የከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔን ሽሮ የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ውሳኔ አጽንቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታም የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው።
ችልቱም አቤቱታው ለሰበር ችልት ያስቀርባል በማለቱ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
በዚህ ጉዲይ ላታይ የሚገባቸው ጭብጦች ተጠሪዎች የኤላትሪክ መስመሩን መቁረጣቸው የውል መጣስ ተግባር መሆን አለመሆኑ ነው ከተባለ ተጠሪዎች በውለ መሰረት ሉፈጽሙና በክሱ የተጠቀሰውን ገንዘብ ሉከፍለ ግዳታ ያለባቸው መሆኑ አለመሆኑ ናቸው። ተጠሪዎች ለአመልካች ቤት ማከራየታቸውን ሳይክደ የሚከራከሩት ያከራዩት ቤቱን ብቻ እንጂ የኤላትሪክ መስመር አለመሆኑ ላይ ነው። በመሆኑም አመልካች ቤቱን ከመከራየት ጋር በኤላትሪክ መስመሩ የመጠቀም መብት አግኝተዋል አላገኙም የሚለውን ከግራ ቀኙ ስምምነት እና አግባብ ካለው ሕግ አኳያ መመርመር ያስፈልጋል። ከመዝገቡ መረዲት እንደሚቻለው የተጠሪዎችን ንብረት አመልካች በቅን ልቦና ከላልች ሰዎች ላይ ተከራይተው ፍጹም ፍቶ የሚል ድርጅት ከፍተው የሚጠቀሙበት በመሆኑና በቤቱ ላይ ላወጡት ወጪ ማካካሻ ይሆን ዘንድ ለ10 አመት ያለምንም ክፍያ እንዱጠቀሙበት ግራ ቀኙ ተስማምተዋል። በዚህ ስምምነት ላይ በግልጽ አመልካች የኤላትሪክ መስመር ስለመከራየታቸው የተመለከተ ነገር የለም የፋ/መ/ደረጃ እና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት አመልካች የተከራዩት ቤቱን ብቻ እንጂ የመብራት መስመር አይደለም ያለትም በስምምነቱ ላይ የኤላትሪክ መስመር ስለመከራየታቸው በግልጽ ባለመመልከቱ ነው። ነገር ግን ከስምምነቱ አመልካች ቤቱን የሚጠቀሙት ለፍቶግራፍ ማንሳት፣ማጠብና ማተም ስራ መሆኑን ተጠሪዎች ለአመልካች ቤቱን ሲያከራዩ ሚያውቁት መሆኑ ግልጽ ነው። አንድ ውል ደግሞ ሉተረጏም የሚገባው በተዋዋዮች መሃከል ሉኖር የሚገባውን የቅንነትና የመተማመን ግንኙት መሰረት በማድረግና ጉዲዮቹ ውስጥ ያለውን ልማዲዊ ሥርአት በመከተል በቅን ልቦና ላሆን እንሚገባው የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1732/1/ ያመለክታል። በተያዘው ጉዲይም ተጠሪዎች ቤቱን ለአመልካች ሲያከራዩ አመልካች ቤቱን ለምን አገልግልት እንደሚጠቀሙበት ያውቁ የነበረ በመሆኑና የአመልካችም ስራ ያለኤላትሪክ መስራት የማይቻል መሆኑን ሉገነዘቡ የሚችለ ሆኖ ሳለ ቤቱን ብቻ እንጂ ኤላትሪኩን እንዱጠቀሙ አልተስማማንም የሚለው የተጠሪዎች ክርክር የቅን ልቦና ተቃራኒ የሆነ ነው።
No topics extracted.
በተጨማሪ ውል ሲተረጏም ተዋዋዮች ውላቸውን ከማድረጋቸው በፉት ወይም በኋላ የነበሩበት ሁኔታ ሉመዘን እንደሚገባ የፍ/ሕ/ቁ. 1734/2/ ያመለክታል። በተያዘውም ጉዲይ ተጠሪዎች አመልካች ቤቱን ብቻ እንጂ ኤላትሪክ መስመሩን አብረው አልተከራዩም ይበለ እንጂ ስምምነት ካደረጉበት ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ መስመሩን እስካቋረጡበት ጊዜ ድረስ አመልካች በኤላክትሪኩ መስመር ሲጠቀሙ መቆየታቸው ግራ ቀኙ ስምምነት ባደረጉ ጊዜ ሃሳባቸው ምን እንደነበረ ያመለክታል። በልላ በኩል ለአንድ ቤት የሚዘረጋው አንድ የኤላትሪክ መስመር ከመሆኑ አኳያ ተጠሪዎች ቤቱን ሲያከራዩ ተከራይ በዚሁ የኤላትሪክ መስመር የመጠቀም መብት ሉኖረው ይገባል። በፍ/ብ/ሕ/ቁ.
1355 ስር እንደተመለከተውም በአንድ ቤት ከፉል ላይ ብቻ የመኖር መብት ያለው ሰው ለጋራ አገልግልት በተቋቋሙት ነገሮች ለመጠቀም መብት ያለው መሆኑን ያመለከታል። የኤላትሪክ መስመርም ለአጠቃላይ ቤቱ እንዱያገለግል የሚዘረጋ በመሆኑ አመልካች ለተከራዩት ቤት በኤላትሪክ መስመሩ የመጠቀም መብት ሉኖራቸው ይገባል። ከክርክሩ እንደተገነዘብነው ተጠሪዎች መስመሩን ያቋረጡት የመብራት ቆጣሪው ህብረት ባንክ በተከራየው የሕንፃው ክፍል ውስጥ የሚገኝ በመሆኑና ለስራ እንዱያመቸው መስመሩን ብቻውን እንዱጠቀምበት በመጠየቁ ነው። ነገር ግን አከራዩ ከፉል ህንፃውን ካከራየ በኋላ ላልች የህንፃውን ክፍልች ሲያከራይ የመጀመሪያውን ተከራይ ጥቅም መጠበቅ እንዲለበት የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 2947 ይገልፃል። በመሆኑም ተጠሪዎች ለህብረት ባንክ ከፉል ህንፃውን ሲያከራዩ አመልካችን በመብት እና ጥቅም በሚጏዲ መልኩ ላሆን አይገባም።
የአመልካች ጥያቄ ወድቅ የተደረገበት ላላኛው ነጥብ አመልካች ቤቱን እንዱገለገለበት የተሰጣቸው በነፃ በመሆኑ ውለ ለተጠሪዎች ግዳታን ብቻ የጣለ በመሆኑ ሉተረጏም የሚገባው ተጠሪዎችን በሚጠቅም መልኩ ነው በሚል ነው። ነገር ግን ምንም እንኳን አመልካች ቤቱን ያለምንም ክፍያ እንዱገለገለበት የተስማሙ ቢሆንም ለዚህ ስምምነት ምክንያት የሆነው ግን አመልካቾች በቤቱ ላይ ከፍተኛ ወጪ ያወጡበት በመሆኑ ላወጡት ወጪ ማካካሻ እንዱሆን ነው። ስለሆነው የተደረገው ውል አመልካች ቀደም ሲል ያወጡት ወጪ ከኪራዩ ገንዘብ ጋር እንዱጣጣ ታሳቢ ተደርጏ የተደረገ እንጂ ተጠሪዎች ምንም አይነት ጥቅም ያላስገኘ ነው ለማለት የሚቻል አይደለም። ውለም ፈጽሞ ጥቅም ለማሰገኘት እንዲልተደረገ ውል ተቆጥሮ በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1739 መሰረት ግዳታው በቀላል አኳኋን ሉተረጏም ይገባል መባለ አግባብ ያለው ሆኖ አላገኘነውም። በመሆኑም አመልካች ቤቱን ብቻ እንጂ የኤላትሪኩን መስመር አልተከራዩም የሚለው የተጠሪዎች ክርክር ከፍ ሲል በተዘረዘሩት ምክንያቶች ተቀባይነት ያለው አይደለም። በመሆኑም ተጠሪዎች የአምስት ቀን ማስጠንቀቂያ በመስጠት የኤላትሪክ መስመሩን መቁረጣቸው መሰረታዊ የውል መጣስ ተግባር መሆኑን ተረድተናል።
ተጠሪዎች የውል መጣስ ተግባር ፈጽመዋል ከተባለ ቀጥለን ይህ ድርጊት ስለሚያስከትለው ሃላፉነት እንመለከታለን። ውል ያልተፈፀመለት ሰው ውለ እንዱፈፀምለት ወይም ውለ እንዱፈርስለት ሉጠይቅ እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1771/1/ ስር ተመልክቷል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች እንደ ውለ እንዱፈፀምላቸው ጠይቀዋል።
ተጠሪዎችም የውል መጣስ ተግባር አለመፈፀማቸውን እንጂ እንደውለ መፈጸም የማይገደደበትን ላላ ምክንያት ያልገለፁ ስለሆነ የኤላትሪክ መስመሩን ሉቀጥለ ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ ተዋዋይ ወገን ግዳታውን ባልፈጸመ ጊዜ ውለን በግዳታ እንዱፈጽም ከመደረጉም በተጨማሪ ለደረሰው ጉዲት ካሳ እንዱከፈል እንደሚገደድ የፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1790/1/ ገልጿል። በተያዘው ጉዲይ አመልካች ኤላትሪክ መስመር በመቆረጡ ምክንያት ስራ ስላቆሙ የብር 64,572(ስልሳ አራት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ሁለት) ኪሳራ የደረሰባቸው መሆኑን ገልፀዋል ሲገልፁ ተጠሪዎች በበኩላቸው የአመልካች የንግድ ፈቃድ ተሰርዞ የነበረ በመሆኑ ኪሳራ ሉከፍለ እንደማይገባ ተከራክረዋል። ይሁን እንጂ ተጠሪዎች ሉያረጋግጡ የሚገባቸው አመልካች ያልሰሩና ገቢ ያላገኙ መሆኑን እንጂ የአመልካች ንግድ ፈቃድ መሰረዙን አይደለም። አመልካች ስራ ሰርተው ገቢ ያገኙ የነበረ መሆኑ እስከተረጋገጠ ድረስ ያለ ንግድ ፈቃድ መስራታቸው በሚመለከተው ክፍል ተገቢው እርምጃ ሉያስወስድባቸው የሚችል ከሚሆን በቀር ተጠሪዎችን ኪሳራ ከመክፈል ነፃ የሚያደርጋቸው አይሆንም። የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት የአገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት ከአመልካች ጋር ተመሳሳይ ስራ የሚሰራ ድርጅት የሚያገኘውን ገቢ አስመልክቶ የላከውን መረጃና በአመልካች ድርጅት ውስጥ የሚሰሩትን ሰራተኞች ስለ አመልካች ገቢ በምስክርነት ሰምቶ አመልካችን በክሱ ላይ የተመለከተውን ገቢ ያጡ መሆኑን አረጋግጧል። በመሆኑም የተረጋገጠውን ኪሳራ ተጠሪዎች የመክፈል ሃላፉነት አለባቸው። የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት ከተሰረዘ የንግድ ፈቃድ ኪሳራ እንዱከፈል ማድረግ ሕገ ወጥነትን ማበረታታት ነው ከማለት ውጪ አመልካች የተቋረጠባቸው ገቢ ሰላለመኖሩ ያጣራው ነገር እንደላለ ከመዝገቡ ተረድተናል።
በልላ በኩል ተጠሪዎች የ5 ቀናት ማስጠንቀቂያ ብቻ ሰጥተው መስመሩን በማቋረጣቸው በአመልካች ላይ ለደረሰው ኪሳራ የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት የሰጠውን የኪሳራ ገንዘብ ተገቢ ነው ማለቱ አመልካች የተቋረጠባቸው ገቢ የነበረ መሆኑን መቀበለን ያመለክታል።
በአጠቃላይ ተጠሪዎች አመልካች የተከራዩትን ቤት የኤላትሪክ መስመር መቁረጣቸው የውል መጣስ ተግባር አይደለም በማለት የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት የተፈፀመበት ሆኖ ተገኝቷል።
የፋ/መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 15812 መጋቢት 21 ቀን 1998 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔና የፋ/ጠቅላይ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 24407 ጥቅምት 27 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ተሽሯል።
የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 47038 ሰኔ 25 ቀን 1999 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ ፀንቷል።
ተጠሪዎች የቆረጡትን የኤላትሪክ መስመር ሉቀጥለ ይገባል። መስመሩን በመቁረጣቸው በአመልካች ላይ የደረሰውን ኪሳራ ብር 64,572 (ስልሳ አራት ሺህ አምስት መቶ ሰባ ሁለት) የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ ከሚታሰብ 9% ወለድ ጋር ይክፈለ ብለናል።
ወጪና ኪሳራ ግራ ቀኙ የየራሳቸውን ይቻለ።