No summary available.
ጥቅምት 05 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- መንበረፀሐይ ታደሰ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ አብደራዛቅ ሐሚድ - ጠ/አስቻለው አሻግሬ - ቀረቡ ተጠሪ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - ነ/ፈጅ መንበረ አድማሱ - ቀረቡ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
በዚህ መዝገብ የቀረበው የመያዣ ውል ይፍረስልኝ ጥያቄ ነው። አመልካች ለፋ/መ/ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት ክስ ሐሚድና ቤተሰቡ የግብርና ውጤቶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከተጠሪ ላይ ለወሰደው ብድር አመልካች በአ/አበባ ከተማ ወረዲ 23 ቀበላ 12 ውስጥ የሚገኘውን ቤት በመያዣ ያስመዘገቡ ሲሆን አቶ ሐሚድ ይስሐቅ የተባለ ግለሰብም 2 ቤቶች በመያዣ ሰጥተዋል። ተበዲሪው ብድሩን አጠናቆ ባለመክፈለ ባንኩ በመያዣ የያዛቸውን ቤቶች በሃራጅ ለመሸጥ በመንቀሳቀሱ ባንኩ የአቶ ሐሚድ ይስሐቅ ቤቶችን በሐራጅ ሽጦ እዲውን በሙለ ከፍል አጠናቋል። እዲው ተከፍል ስለተጠናቀቀ በመያዣ የሰጠሁት ቤት ካርታ እንዱመልስልኝ ብጠይቀው ፈቃደኛ አልሆነም። የመያዣው ውለ ከተፈረመ 10 አመት ያለፈው በመሆኑ ቀሪ ሆኗል። ስለዚህ ባንኩ ቤቴን በሐራጅ ለመሸጥ የጀመረውን እንቅስቃሴ እንዱያቆም የያዘውን ካርታ እንዱመልስ፣ ያልተከፈለ እዲ ካለ የሂሳብ መግለጫ እንዱያቀርብና ቀሪውን ገንዘብ ከፍዬ ቤቴ ከመያዣነት እንዱለቀቅልኝ በማለት ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ ተበዲሪው የወሰደው ብድር ተከፍል ያልተጠናቀቀ በመሆኑና በፍ/ብ/ህ/ቁ 3058(1) የተመለከተው የ10 አመት ጊዜ ከማለፈ በፉት በመያዣ ንብረቱ ላይ እንቅስቃሴ የጀመረ ስለሆነ ክሱ ተቀባይነት የለውም በማለት ወስኗል። በዚህ ውሳኔ ላይ አመልካች ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ ያቀረቡ ቢሆንም የስር ፍ/ቤት ውሳኔ ፀንቶባቸዋል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። የአመልካች ዋነኛ አቤቱታ የመያዣው ውል ከተመዘገበ 10 አመት ስላለፈው በፍ/ብ/ህ/ቁ 3058(1) መሰረት መያዣው ቀሪ ነው የሚል ነው። ይህ ችልትም ይህንኑ የአመልካችን ቅሬታ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ችልት እንዱቀርብ በማድረግ ግራ ቀኙ ክርክራቸውን በጽሁፍ አቅርበዋል። ችልቱም መዝገቡን እንደሚከተለው መርምሯል።
አመልካች ሐሚድና ቤተሰቡ የግብርና ውጤቶች ኃ/የተ/የግ/ማህበር ለወሰደው ብድር ቤታቸውን በመያዣ ሰጥተዋል። የመያዣ ውለም የተመዘገበው በ1987 ዓ.ም መሆኑን እንዱሁም ተበዲሪው ድርጅት ብድሩን መክፈል ባለመቻለ ተጠሪ ለአመልካች ጥቅምት 24 ቀን 1992 ዓ.ም ማስጠንቀቂያ መስጠቱን አመልካች አልካደም።
አመልካች መያዣው ቀሪ ነው በማለት የሚከራከሩት የፍ/ብ/ሕ/ቁ 3058(1)”ን” በመጥቀስ ነው። በመሆኑም ይህን ድንጋጌ መመልከት ያስፈልጋል። አመልካች የጠቀሱት ይህ ድንጋጌም እንደሚከተለው ይነበባል።
የማይንቀሳቀስ ንብረት የመያዣ መብት ውጤት የሚኖረው ከተፃፈበት ቀን አንስቶ እስከ አስር ዓመት ድረስ ነው።
በዚህ ድንጋጌ መሰረት አንድ የመያዣ ውል ውጤት የሚኖረው መያዣው ከተመዘገበበት ቀን አንስቶ እስከ 10 አመት ድረስ ነው። በመሆኑም በመያዣ ውለ ምክንያት በሚገኙ ማናቸውም መብቶች መገልገል የሚቻለው ይኸው የተወሰነው ጊዜ ከማለፈ በፉት ይሆናል ማለት ነው። ይህ የጊዜ ዘመን ሉራዘም የሚችለው 10 ዓመቱ ከማለፈ በፉት ውለ እንዱታደስ አዱስ ምዝገባ ተከናውኖ ከሆነ ብቻ እንደሆነ ከፍ/ብ/ሕ/ቁ 3058(2) እንገነዘባለን። በመሰረቱ ይህ ህግ አመልካች እንደሚለት የይርጋ ድንጋጌ አይደለም። ይርጋ ማለት በህግ ተለይቶ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ በአንድ ጉዲይ ክስ ለማቅረብ የሚከለከልበት የህግ ፅንሰ-ሃሳብ ነው። በመሆኑም ይርጋ አንድ ሰው በጉዲዩ ላይ መብት ያለው ቢሆንም እንኳን ይህንን መብቱን ለመጠየቅ የማይችልበትን ገደብ የሚመለከት ነው። ይህ ክልከላም ተፈፃሚ የሚሆነው ክስ ከቀረበ በኋላ ተከሳሹ የይርጋ መቃወሚያ አንስቶ የተከራከረ ከሆነ ነው። ከሳሽ ክስ የማቅረብ መብቱ በይርጋ ቀሪ ከሆነ በኋላ ክስ አቅርቦ ተከሳሽ ክሱ በይርጋ ቀሪ መሆኑን በመግለፅ ካልተቃወመ ክሱ ተቀባይነት አግኝቶ መታየት ይቀጥላል። የጊዜ ገደቡ በማለፈ ብቻ ፍ/ቤት የይርጋውን በራሱ አነሳሽነት አንስቶ ክሱን ውድቅ ሉያደርግ አይችልም። የፍ/ብ/ሕ/ቁ 3058(1) የሚያስቀምጠው የይርጋን ጽንሰ-ሐሳብ አይደለም። የተጠቀሰው አንቀፅ የሚናገረው በህጉ የተመለከተው የጊዜ ገደብ ማለፍ የመያዣው ውለን ቀሪ (lapse) የሚያደርገውና ከዚሁ ጊዜ በኋላ መያዣ ውለ ተጠቃሚ የሆነው ሰው በመያዣው ላይ ያለው መብት የሚያበቃበትን ሁኔታ ነው። የመያዣ ውለ ከተመዘገበ በኋላ 10 ዓመት ሆኖት እንደሆነና እንዱታደስ ካልተጠየቀ ጠያቂ ባይኖርም አቃቤ መዝገቡ መያዣውን እራሱ ሉሰርዘው እንደሚገባ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 1632(2) ተመልክቷል። በመሆኑም መያዣ ሰጪው 10 አመት በማለፈ መያዣው እንዱሰረዝ ጥያቄ ባያቀርብም መዝጋቢው አካል ራሱ ምዝገባውን ሰርዞ መያዣውን ቀሪ ሉያደርገው ይገባል።
No topics extracted.
በልላ በኩል መያዣው ነሐሴ 17 ቀን 1987 ዓ.ም የተመዘገበ ቢሆን በመያዣ የተያዘው ቤት አመልካች ክስ እስከመሰረቱበት ህዲር 12 ቀን 1999 ዓ.ም ድረስ አለመሸጡን ከመዝገቡ መረዲት ይቻላል። አመልካችም ይህንኑ ጊዜ መሰረት አድርገው ነው መያዣው ቀሪ ነው ሲለ የሚከራከሩት። ተጠሪ በበኩለ መያዣው ከተመዘገበ በኋላ ተበዲሪው እዲውን ባለመክፈለ 10 አመቱ ሳያልፍ ጥቅምት 24 ቀን 1992 ዓ.ም ማስጠንቀቂያ ለአመልካች በመስጠቱ መያዣው ቀሪ አልሆነም ሲል ተከራክሯል። አመልካች የተባለው ማስጠንቀቂያ የደረሳቸው መሆኑን አልካደም። ክርክራቸው ማስጠንቀቂያ በመስጠት የይርጋ ጊዜን ማቋረጥ የሚቻለው ለዋና እዲ እንጂ ለማይንቀሳቀስ ንብረት መያዣ አይደለም የሚል ነው። ከፍ ሲል እንደተመለከትነው በፍ/ብ/ህ/ቁ 3058 ስር የተቀመጠው የጊዜ ገደብ የይርጋ ጊዜ ገደብ ባለመሆኑ ስለይርጋ ማቋረጫ ያቀረቡት ክርክር ተቀባይነት የለውም።
በልላ በኩል ግን ባለገንዘቡ የመያዣ ውለ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ 10 ዓመት ከማለፈ በፉት በመብቱ መገልገል ጀምሯል ልባል የሚችለው መቼ ነው? የሚለው ላታይ ይገባል። በአዋጅ ቁጥር 97/90 መሰረት ለሰጠው ብድር መያዣ የያዘ ባንክ ብድሩ ካልተከፈለው የ30 ቀናት ማስጠንቀቂያ በመስጠት ንብረቱን ለመሸጥና የባለቤትነት ስሙን ለገዢ ለማስተላለፍ እንደሚችል በቁጥር 3 ስር ተመልክቷል። በመሆኑም ባንኮች የመያዣ መብታቸውን መገልገል የሚጀምሩት ማስጠንቀቂያ በመስጠት ለመሆኑ ከዚህ ድንጋጌ መረዲት ይቻላል። በተያዘው ጉዲይም ቢሆን ተጠሪ ለአመልካች ጥቅምት 24 ቀን 1992 ዓ.ም ማስጠንቀቂያ በመስጠት በመብቱ መገልገል ጀምሯል።
መያዣው ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ሲቆጠር ደግሞ ማስጠንቀቂያ የተሰጠው 10 ዓመት ሳያልፍ ነው። ተጠሪ ማስጠንቀቂያ ከሰጠ በኋላ ቤቱን ሳይሸጥ የ10 ዓመቱ ጊዜ አልፍ ላሆን ይችላል። የቤቱ ሽያጭ ሳይጠናቀቅ 10 አመቱ ማለፈ ብቻውን ግን መያዣውን ቀሪ አያደርገውም። ላታይ የሚገባው ተጠሪ በመብቱ መገልገል የጀመረበት ጊዜ ነው። ከዚህ አኳያ ሲታይ ደግሞ መያዣው ቀሪ የሚሆንበት የህግ መሰረት የለም። በዚህም ምክንያት የስር ፍ/ቤቶች የአመልካችን ክስ ውድቅ በማድረግ የሰጡት ውሳኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት አለው ለማለት አልተቻለም።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ ታህሳስ 09 ቀን 2000 ዓ.ም እንዱሁም የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ ጥር 05 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጡት ውሳኔዎች በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 348(1) መሰረት ፀንተዋል።
ውሳኔው ስለፀና ይህ ችልት