No summary available.
ሀምላ 28 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሐጎስ ወልደ ሂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- አቶ ተስፊልደት ኪዲኔ - ቀረቡ ተጠሪዎች፡-
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት ስላመለከቱ ነው።
የአመልካችና የተጠሪዎች የክርክር መነሻ አቶ ኪዲኔ ንዎቱ በህይወት በነበሩበት ጊዜ አድርገውታል የተባለውን ኑዛዜ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ነው። ተጠሪዎች ሟች ኪዲኔ ንዎቱ ጥር 30 ቀን 1984 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ አለ በማለት ለቀድሞው ልደታ አውራጃ ፍርድ ቤት በማቅረብ ሚያዝያ 24 ቀን 1984 ዓ.ም አስወስነዋል።
የአሁን አመልካች ለፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ሟች አድርገውታል የተባለው ኑዛዜ ስለ ግልፅ ኑዛዜ አደራረግ የተደነገገውን መሥፈርት የማያሟላ ሟች ካሎቸው ወራሾች ልጁና ወራሹ የሆንኩትን እኔን አመልካችን የረሣና የእኔን መብትና ጥቅም የሚጎዲና በዝምታ የሚነቅል ትክክለኛ የሟች ኑዛዜ ሣይሆን የሀሰት ሰነድ በመሆኑ ከዚህ በፉት የልደታ አውራጃ ፍርድ ቤት በመዝገብ ቁጥር 631/84 ሚያዝያ 24 ቀን 1984 ዓ.ም ኑዛዜው ህጋዊ መሆኑን በማረጋገጥ የሰጠው ውሣኔ ይሰርዝልኝ በማለት አመልክቷል። የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ሟች ጥር 30 ቀን 1984 ዓ.ም አደረጉት የተባለው ኑዛዜ ራሳቸው የፃፈት ወይም እርሳቸው እየተናገሩ ላላ ሰው የፃፈው መሆኑን አይገልፅም። ኑዛዜው የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 881 ንዐስ አንቀፅ 2 ፍርማሉቲ የማያሟላ ስለሆነ ፈራሽ ነው በማለት የአውራጃው ፍርድ ቤት የሰጠውን ውሳኔ ሰርዟል። ተጠሪዎች በዚህ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት አቅርበዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የግራ ቀኙን ክርክር ከሰማ በኋላ ኑዛዜው “እኛም ከላይ በስም የተገለፅነው አቶ ኪዳኔ ንዎቱ ክፍላ ሀብትና ንብረታቸውን ለ…. በኑዛዜ ሲሰጡ አይተንና ሰምተን ፈርመናል” የሚል ሀረግ ያለው መሆኑን በመግለፅ ኑዛዜ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 881 የተደነገገውን መሥፈርት ያሟላል በማለት የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ውሣኔ ሽሮታል። አመልካች ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት አቅርበው ይግባኝ ሰሚው ችልት የከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሣኔ የህግ ወይም የፍሬ ጉዲይ ስህተት የላለበት መሆኑን በመግለፅ ይግባኙን በፍትሐብሕር ሥነ- ሥርዓት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል።
አመልካች ጥር 5 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ተጠሪዎች የኑዛዜ ተጠቃሚና ወራሽ መሆናቸውን ለማስረዲት ያቀረቡት ኑዛዜ ትክክለኛ ሰነድ አይደለም። ተጠሪዎች በኑዛዜው ላይ በምስክርነት የተገለፁትን ሰዎች በፍርድ ቤት በማስረጃነት ያላቀረቡት ኑዛዜው በሀሰት የተዘጋጀ መሆኑን ያሣያል። ኑዛዜው ህጋዊ ነው ቢባል እንኳን ሟች ያለምንም ምክንያት እኔን ከውርሱ የሚነቅል ኑዛዜ በማድረግና በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 938 መሰረት ከውርስ የነቀለበትን ምክንያት ስላልገለፀና ኑዛዜው የሟች ወራሽ የሆንኩት የረሣና ጉዲት ያደረሰብኝ በመሆኑ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1123 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት ፈራሽ ላሆን ይገባል በማለት ያቀረብነው ክርክር አላግባብ የታለፈብኝ በመሆኑ የከፍተኛ ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት ያለበት ነው በማለት አመልክቷል። ተጠሪዎች በበኩላቸው 1984 ዓ.ም በፍርድ ቤት ታይቶ ህጋዊነቱ የተረጋገጠውን ኑዛዜ አመልካች ኗሪነታቸው በውጭ አገር ነው በማለት ኑዛዜውን በላለንበት ለማስፈረስ ያደረጉትን ጥረት ዘርዝረን ያቀረብነውን ይግባኝ የከፍተኛው ፍረድ ቤት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የህግ ስህተት የለበትም። ኑዛዜው የህጉን ፍርም ያሟላ ነው አመልካች የሚያቀርቡት ክርክር የህግ መሰረት የለውም የሚል መልስ አቅርበዋል። አመልካች የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 1123 በመጥቀስ የሰበር አቤቱታቸውን በማጠናከር የፅሐፍ የመልስ መልስ ሰጥተዋል። ከሥር የክርክሩ አመጣጥና በሰበር የተደረገው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን እኛም ጉዲዩን መርምረናል። ጉዲዩን እንደመረመርነው ሟች አቶ ኪዲኔ ንዎቱ ጥር 30 ቀን 1984 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በተጠሪዎች የሚያስገኘውን መብትና በአመልካች የወራሽነት መብት ላይ የሚኖረው ውጤት ምንድን ነው? የሚለውን ጭብጥ አግባብነት ካላቸው የህግ ድንጋጌዎች ጋር ማገናዘብ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
አመልካች ሟች አቶ ኪዲኔ ንዎቱ ያደረጉት ግልፅ ኑዛዜ በሀሰት የተዘጋጀ ነው። የፍታብሓር ህግ ቁጥር 881 ፍርማሉቲ አያሟላም በማለት ያቀረቡት ክርክር ማስረጃ የመመዘንና ፍሬ ጉዲይ የማጣራት ስልጣን ያላቸው ፍርድ ቤቶች የአመልካችንና የተጠሪን ማስረጃዎችና የኑዛዜ ሰነደን በመመርመር ኑዛዜው ህጋዊ ፍርማሉቲዎችን የሚለና የሟች ያደረጉት ትክክለኛ ኑዛዜ መሆኑን በማረጋገጥ ውሣኔ ሰጥተውበታል። ጉዲዩ ለሰበር የቀረበውም የኑዛዜውን ትክክለኛነትና ህጋዊ መስፈርት ያሟላ መሆኑን በሰበር አጣርቶ ለመወሰን ሣይሆን ኑዛዜው የሚያስከትለውን ውጤት አግባብነት ካላቸው የፍትሐብሕር ህግ ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ ውሣኔ ለመስጠት ነው። ስለሆነም በማለት በሰበር የሚያቀርበው ክርክር ህጋዊ መሰረት የላለው በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ሟች ጥር 30 ቀን 1984 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ ትክክለኛና የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 881 ድንጋጌዎች መስፈርት የሚያሟላ ሰነድ ነው። ሆኖም ሟች ያደረጉት ኑዛዜ በባህሪው የተለያዩ የህግ ጥያቄዎችን የሚያስነሣ ይዘት ያለውና የሟች ኑዛዜ በህግ ረገድ የሚያስከትለው ውጤት ምንድን ነው? የሟች ኑዛዜ ተፈፃሚነትስ በምን መንገድ መሆን አለበት የሚለትን ጥያቄዎች የሚያስነሣ ነው።
ሟች ጥር 30 ቀን 1984 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ መሰረታዊ ይዘት ሲታይ “እኔ አቶ ኪዲኔ ንዋቱ ክፍል በአዱስ አበባ ከፍተኛ 24 ቀበላ 13 የቤት ቁጥር 1370 ነዋሪ የሆንኩ በሰው ልጅ ላይ በመኖር መሞትም ስላለ ሐብትና ንብረቴን በሙለ ለግል ቤቴ ወ/ሮ ዘሀቡ ይመር ቸኮልና ልጆች 1/ አቶ ፀጋይ ኪዲኔ ንዎቱ 2/ አቶ ገብረህይወት ኪዲኔ ንዎቱ በእኔ ስም ያለውን ሀብትና ንብረቴን በሙለ ለልጆችና ለባለቤቴ የሰጠኋቸው በመሆኔ በትክክል አእምሮዬ አስቤ የተናዘዝኩ ስለሆነ ከእነዚህ ላላ በእኔ ንብረት ተጠቃሚ እንደሆኑ ያልፈቀድኩና ሐብትና ንብረቴም ወራሾች መሆናቸውን አረጋግጨ ተናዝዣለሁ የሚል ነው።
ይኸ የሟች ኑዛዜ መሰረታዊ ዓላማው የሟች ንብረት ወራሾች በኑዛዜው ውስጥ ስማቸው የተጠቀሰው ተጠሪዎች ብቻ መሆናቸውን ማረጋገጥ መሆኑን በኑዛዜው ውስጥ “ከእነዚህ ላላ በእኔ ንብረት ተጠቃሚ እንደሆኑ ያልፈቀድኩና የሐብትና ንብረቴ ወራሾች መሆናቸውን አረጋግጬ ተናዝዣለሁ። በማለት ካደረጉት የኑዛዜው ማደማደሚያ ሀረግ ለመገንዘብ ይቻላል። ሟች በኑዛዜው የንብረታቸው ጠቅላላ ወራሾች ተጠሪዎች ብቻ እንደሆኑ ሀሳብና ፍላጎት የነበራቸው መሆኑንና በኑዛዜው ውስጥ ስማቸው ያልተገለፁ ላልች የሟች የህግ ወራሾች በውርሣቸው ተካፊይ እንዲይሆኑ እንደሚፈልጉ ከእነዚህ ላላ በእኔ ንብረት ተጠቃሚ እንደሆኑ ያልፈቀደ መሆኑን በመግለፅ ኑዛዜ ትተው አልፈዋል።
አመልካች የሟች አቶ ኪዲኔ ንዎቱ ልጅና ወራሽ መሆናቸውን የፋዳራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መጋቢት 26 ቀን 1996 ዓ.ም የሰጠውን ውሣኔ በማስረጃነት አቅርበዋል። ተጠሪዎች ይኸንን የአመልካች በፍርድ የተረጋገጠ ወራሽነት የሚያስቀርና ፍርደ የተሰረዘ ወይም የተሻረ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ ያላቀረቡ መሆኑን የበታች ፍርድ ቤቶች ከሰጡት ውሣኔ ለመገንዘብ ይቻላል። ይኸም ሟች ጥር 30 ቀን 1984 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 842 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት የሟች ልጅና አንደኛ ደረጃ ወራሽ መሆናቸው በፍርድ በተረጋገጠው በአመልካች የወራሽነት መብትና ከሟች ውርስ ንብረት ድርሻቸው እንዱሰጣቸው በሚያቀርቡት ጥያቄ ላይ ምን ህጋዊ ውጤት ያስከትላል? የሚለውን ጥያቄ የሚያስነሳ ነው። ከላይ እንደተገለፀው ሟች በኑዛዜው ስማቸው ከተጠቀሱት ውጭ ያለ ወራሾች በውርሳቸው እንዱካፈለ ያልፈቀደ መሆኑን ገልፀዋል። ይኸም ሟች በስም ሣይጠቅሱ ከተጠሪዎች ውጭ ያለ ያለ ኑዛዜ ወራሾች በሙለ በውርሳቸው እንዲይካተት ግልፅ በሆነ ቃል በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 937 ንዐስ አንቀፅ 1 ድንጋጌ መሰረት ለመንቀል ኑዛዜ ያደረጉ መሆናቸውን ያስረዲል።
ሟች ከተጠሪዎቹ ውጭ ያለ ኑዛዜ ወራሽ ነኝ ብል በውርሱ ተካፊይ ለመሆን የሚመጣ ማንኛውም ወራሽ ከውርሣቸው እንዱሣተፍ ፈቃድ የላላቸው መሆኑን በመግለፅ አመልካችን በቀጥታ ስማቸውን በመጥቀስ ሣይሆን በተዘዋዋሪ መንገድ ከውርስ ለመንቀል ኑዛዜ አድርገዋል። ሆኖም ሟች አመልካችና ላላ ያለ ኑዛዜ ወራሽ ነኝ ብል የሚመጣ ሰው በውርሣቸው ተካፊይ እንዲይሆን በመግለፅ ያደረጉት ኑዛዜ አመልካች በሟች ውርስ በወራሽነት እንዲይሣተፈ የማድረግ ህጋዊ ውጤት የለውም። ምክንያቱም አመልካች የሟች ልጅና የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ናቸው። ማንኛውም ሰው ከውርስ ለመንቀል የደረሰበትን ምክንያት በኑዛዜው ውስጥ ካልገለፀ በቀር ልጁን ወይም ወደታች የሚቆጠር ተወላጁን ከውርስ ለመንቀል ያደረገው ኑዛዜ የማይፀናና ህጋዊ ውጤት እንደማይኖር የፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 938 ንዐስ አንቀፅ 1 በግልፅ የሚደነግግ በመሆኑ ነው።
ሟች ጥር 30 ቀን 1984 ዓ.ም ባደረጉት ግልፅ ኑዛዜ ውስጥ ስሙ ያልተገለፀ ወራሻቸው በውርሳቸው እንዱሳተፈ ፈቃድ የላላቸው መሆኑን የገለፁ ቢሆንም በኑዛዜው ስማቸው ከተገለፁት ሁለት ልጆቻቸው ሁለተኛና ሶስተኛ ተጠሪ ውጭ ያለ ወራሾቻቸውን ለምን በውርሳቸው ተካፊይ እንደሆኑ እንዲልፈለጉና ከውርስ በኑዛዜ እንዱነቀለ በኑዛዜው ውስጥ የሰጡት ምክንያት የለም። አመልካች የሟች ልጅና በፍታብሓር ህግ ቁጥር 842 ንዐስ አንቀፅ 1 መሰረት የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ በመሆኑ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ሟች ምክንያቱን ሣይገልፅ ከውርስ ለመንቀል ያደረጉት ኑዛዜ የማይፀና መሆኑ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 938 ንዐስ አንቀፅ 1 በግልፅ የተደነገገ በመሆኑ ሟች ያደረጉት ኑዛዜ አመልካች በሟች ውርስ በመሣተፍ ድርሻውን ከመጠየቅ የሚገድበው አይደለም። ስለሆነም አመልካች ያደረጉት ኑዛዜ አመልካች በሟች ውርስ በወራሽነት እንዲይሣተፍ የማድረግና ከውርሱ የመነቀል ውጤት የሚያስከትል ሆኖ አግኝተነዋል።
የሟች ጠቅላላ የኑዛዜ ወራሽ የሆነ ሰው በኑዛዜው ውስጥ ሟች ተቃራኒ ውጤት ያለው መሆኑን ካልገለፀ በስተቀር የሟች ያለኑዛዜ ወራሽ እንደሆነ እንደሚቆጠር በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 915 ንዐስ አንቀፅ 1 ተደንግጓል። በያዝነው ጉዲይ ሟች አንደኛ ተጠሪ በሁለተኛ እና ሶስተኛ ተጠሪዎች ጋር የጠቅላላ የንብረታቸው ወራሽ መሆናቸውን ከመግለፅ ውጭ ላላ የገለፁት ሁኔታ የላለ በመሆኑ አንደኛ ተጠሪ እንደ ሟች ያለኑዛዜ ወራሽ (አንድ ልጅ) ተቆጥረው በውርሱ የመካፈል መብት ይኖራቸዋል። ስለሆነም ሟች ጥር 30 ቀን 1984 ዓ.ም ያደረጉት ኑዛዜ ሚስታቸው የሆኑት አንደኛ ተጠሪ እንደሟች አንድ ወራሽ ተቆጥረው በውርሱ የመሣተፍ ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ አግኝተነዋል።
በልላ በኩል ኑዛዜው ሁለተኛ ተጠሪና ሶስተኛ ተጠሪ ከአንደኛ ተጠሪ ጋር በመሆን የሟች ጠቅላላ የኑዛዜ ወራሽ መሆናቸውን ከሚገልፅ በስተቀር እያንዲንዲቸው ከውርሱ ንብረት ስለሚደርሳቸው ድርሻ የማይዘረዝር በመሆኑ በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 2017 መሰረት የተደረገ የሀብት ክፍፍል ነው ብል ለመደምደም አይቻልም።
ከዚህ በተጨማሪ በኑዛዜው ሟች ልጃቸውና አንደኛ ደረጃ ወራሻቸው የሆነውን አመልካች በውርሱ እንዲይካፈል ለመንቀል አስበው ያደረጉትና አመልካችን ለመንቀል የተናገሩት ቃል በፍትሐብሕር ህግ ቁጥር 938 ንዐስ አንቀጽ 1 የተገለፀውን መስፈርት የማያሟላ በመሆኑ ህጋዊ ውጤት የላለው በመሆኑ ሟች ለሁለተኛ እና ሶስተኛ ተጠሪዎች ያደረጉት ኑዛዜ ሁለተኛና ሶስተኛ ተጠሪዎች ልጆቻቸውና ወራሾቻቸው መሆናቸውን ከማረጋገጥ ውጭ የተለየ ህጋዊ ውጤት የሚያስከትል ሆኖ አላገኘነውም።
በአጠቃላይ ሟች ጥር 30 ቀን 1984 ያደረጉት ኑዛዜ ህጋዊ ውጤት ስንመረምረው ኑዛዜው አመልካች ከውርስ የሚነቀል የሚያስከትል አይደለም። አንደኛ ተጠሪ እንደ ሟች አንድ ወራሽ ተቆጥረው በሟች ውርስ እንዱሳተፈ የሚያስችልና ሁለተኛና ሶስተኛ ተጠሪዎች የሟች ልጆችና ወራሾች መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ነው።
የበታች ፍርድ ቤቶች ሟች ያደረጉት ኑዛዜ ህጋዊና ፍርሙን ያሟላ መሆኑን ብቻ ሳይሆን ኑዛዜው አመልካችና በተጠሪዎች መብት ላይ የሚያስከትለው ህጋዊ ውጤት ምን እንደሆነ ሣይዘረዝሩ ማለፊቸው ተገቢ ሆኖ ባለማግኘታችን ውሣኔአቸውን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርዓት ሕግ ቁጥር 348(1) መሰረት አሻሽለናል። በዚህ መሰረት አንደኛ ተጠሪና የሟች ሚስት እንደ አንድ የሟች ልጅና ወራሽ ተቆጥረው የሟችን ውርስ ከልጆቻቸው ጋር የመካፈል መብት ይኖራቸዋል። በመሆኑም የሟችን የውርስ ሀብት አመልካች ሁለተኛ ተጠሪ ሶስተኛ ተጠሪና አንደኛ ተጠሪ እኩል ድርሻ የማግኘት መብት አላቸው በማለት ወስነናል።
ው ሣ ኔ
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
የሟች ኑዛዜ በከፉል ህጋዊ ውጤት የላለው በመሆኑ የሟች የውርስ ንብረት አመልካች ሁለተኛ ተጠሪ ሶስተኛ ተጠሪና አንደኛ ተጠሪ በወራሽነት ተሣትፈው በእኩል ድርሻ ያገኛለ በማለት ወስነናል።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምፅ ተሰጠ።
No topics extracted.