No summary available.
የሰ/መ/ ሐምል 29 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ሂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- እነ ወ/ሮ አተረፈች ዘውዳ - ወኪል ዶ/ር ደረጀ አሻጋሪ - ቀረቡ ስለ ሁለተኛ አመልካች ጠበቃ ወኪል እስራኤል ተክላ - ቀረቡ።
ተጠሪ፡- አቶ ዘውደ ወሰኔ ቀረበ **
መዝገቡ ተመርምሮ ተከታዩ ፍርድ ተሰጥቷል።
**
ጉዲዩ ሳይናዘዝ የሞተ ሰው ውርስ ተጠቃሚዎችን በሚመለከት በሕጉ ያለውን ቅደም ተከተልና አፈፃፀሙን የሚመለከቱትን የውርስ ሕግ ድንጋጌዎችን ትርጉም የሚመለከት ነው። ክርክሩ የተጀመረው የአሁኑ ተጠሪ የሟች ወ/ሮ አያልነሽ ዘውዳ ወራሽ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ መያዛቸውንና የሟቿ ንብረቶች በተጠሪዎች መያዛቸውን ገልጸው ውርስ እንዱያጣራላቸው የውርስ አጣሪ በፍርድ ቤት እንዱሾምላቸው ህዲር 24 ቀን 2001 ዓ.ም በፋዳራለ መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ባቀረቡት አቤቱታ መነሻ ነው። የአሁኑ አመልካቾችም በስር ፍርድ ቤት ቀርበው ተጠሪ የወራሽነት ማስረጃውን ያገኙት የሟች እህትና ወንድም መኖራቸውን በመደበቅ በመሆኑ የወራሽነት ማስረጃው ተቀባይነት የለውም በማለት የተጠሪ የውርስ አጣሪ ይሾምልኝ ጥያቄ ወድቅ ላሆን ይገባል ሲለ ተከራክረዋል። ጉዲዮን በመጀመሪያ ደረጃ የተመለተው ፍርድ ቤትም ግራ ቀኙ ከሟች ጋር ያላቸውን የዝምድና ደረጃ በማጣራት ተጠሪ የሟች እናት እህት ልጅ ስለሆኑ ሟችን በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 842 እና ተከታዮቹ መሰረት ሉወርሱ ይችላለ ወደ ሚለው ድምዲሜ በመድረስ የሟች ወ/ሮ አያልነሽ ዘውዳ የውርስ ሐብት እንዱጣራ በማለት አዟል። በዚህ ፍርድ አመልካቾች ባለመስማማት ይግባኛቸውን ለፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቢያቀርቡም ፍርድ ቤቱ አመልካቾች ተጠሪ ያገኙትን የወራሽነት ማስረጃ ሳያሰርዙ የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄን መቃወም እንደማይችለ ገልፆ ውርስ አጣሪው በፍርድ ቤት እንዱሾም ተብል መወሰኑ ተገቢ ነው በማለት የይግባኝ ባዩችን ቅሬታ ሳይቀበለው ቀርቷል። የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበውም ይህንኑ ውሳኔ በመቃወም ለማስለወጥ ነው።
አመልካች ሚያዝያ 29 ቀን 2001 ዓ.ም በጻፈት አራት ገጽ የሰበር አቤቱታ በበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ተፈጽሟል የሚለበትን ምክንያት ዘርዝረው አቀርበዋል። ይዘቱም ባጭሩ፡የበታች ፍርድ ቤቶች ውሳኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 843 እና 844(3) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ ያላገናዘበ በመሆኑ ሉታረም የሚገባው ነው በማለት መከራከራቸውን የሚያሳይ ነው። አቤቱታው ተመርምሮም አመልካቾች የሟች ወንድምና እህት ተጠሪ ደግሞ የሟች እናት እህት ልጅ ስለሆኑ ውርሱ ሉጣራ ይገባል ተብል መወሰኑ ባግባቡ መሆን ያለመሆኑን ለመመርመር ሲባል ጉዲዩ ለሰበር ችልት እንዱቀርብ ተደርጎ ተጠሪ የጽሁፍ መልሳቸው እንዱያቀርቡ በችልት ተነግሯቸው ከሄደ በኋላ በተሰጣቸው ቀነ ቀጠሮ ሳያቀርቡ በመቅረታቸው በጽሐፍ መልስ የመስጠት መብታቸው ታልፎል።
የጉዲዩ አመጣጥ አጠር አጠር ባለመልኩ ከላይ የተገለፀው ሲሆን ይህ ችልትም የግራ ቀኙን ክርክር፣ ለሰበር አቤቱታው መነሻ ከሆነው ውሳኔ እና አግባብነት ካላቸው ድንጋጌዎች ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ መርምሮታል። እንደመረመረውም ተጠሪ የሟች እናት እህት ልጅ በመሆን የሟች ወንድም እና ልጅ እያለ ሟችን ሉወርሱ ? ይችላለ? ወይስ አይችለም? የሚለው ጭብጥ ምላሽ የሚያስፈልገው ሆኖ ተገኝቷል።
ከክርክሩ ሂደት መገንዘብ የተቻለው ተጠሪ የሟች ወራሽነታቸውን የሚያሳይ ማስረጃ ከተገቢው ፍርድ ቤት ካገኙ በኋላ የሟች ውርስ ንብረት እንዱጣራላቸው ለስር ፍርድ ቤት አቤቱታ ሲያቀርቡ አመልካቾች የሟች እህትና ወንድም እያለ ተጠሪ ሉወርሱ አይችለም በማለት የውርስ ማጣራት ሂደት እንዲይጀመር ተቃውሞ ማንሳታቸውን ነው። የስር ፍርድ ቤት የአመልካቾችን ተቃውሞ ሳይቀበለው የቀረው ተጠሪ የሟች እናት እህት ልጅ ስለሆነ በተተኪነት ወራሽ ሉሆኑ ይችላለ በሚል ምክንያት ነው። እኛም ጉዲዩን አግባብነት ካለው ሕግ ጋር በማገናዘብ በሚከተለው መልኩ ተመልክቷል።
በመሰረቱ በውርስ ህጋችን ውስጥ ያለት ደንቦች ሳይናዘዝ የሞተ ሰው ወራሾች በቀጥታ ከሟች ውርስ ተካፊይ ሉሆኑ የሚችለ የሟች የስጋ ዘመድች እና እነዚህ ወገኖች ከላለ እነዚህን ወገኖች በመተካት የሚወርሱ ወገኖች በሚል በሁለት መንገድች ከፍለው ያስቀምጣለ። በልላ አገላለጽ የሟች የስጋ ዘመድች በሟች ውርስ ሉካፈለ የሚችለት በቀጥታ ወራሽነት ወይም በተተኪነት ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 842 ተከታዩቹ ድንጋጌዎች ያስገነዝባለ። ሕጉ የሟችን ወራሾች ቅደም ተከተል አስቀምጧል። የሟቹ የመጀመሪያ ወራሽ የሟች ልጆች እንደሆኑ ሕጉ በአንቀጽ 842 ስር በግልጽ ያስቀመጠ ሲሆን የሟች የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ከላለ የሟች ንብረት ለሁለተኛ ደረጃ ዘመድች እንደሚተላለፍ እነዚህ ሁለተኛ ደረጃ ዘመድች የሚባለበትም የሟች እናትና አባት መሆናቸውን የሟች አባትና እናት ሟችን ቀድሞ ከሞቱ የእነርሱ ተወላጆች ማለትም የሟች ወንድምና እህት ወይም የወንድሞቹና የእህቶቹ ተወላጆች እናትና አባቱን በመተካት በሟች ውርስ እንደሚካፈለ የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 843 እና 844 ድንጋጌዎች ይዘት የሚያሳየን ጉዲይ ነው። የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 844(3) ድንጋጌ ከሟች እናት እና አባት በአንደ መስመር ወራሽ ቢታጣ የሟች ውርስ ወደ ላላው መስመር በሙለ ሉተላለፍ እንደሚችል ደንግጓል።
No topics extracted.
ከእነዚህ የሕጉ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ተተኪ ወራሽነት የተፈጻሚነት ወሰን ወደታች በሚቆጠሩ ተወላጆች እንጂ ወደ ጎን በሚቆጠር ዝምድና ትስስር አለመሆኑን ነው። ይህ ችልትም የድንጋጌዎቹ አፈፃፀም በዚህ መልኩ ስለመሆኑ በሰ/መ/ በቀረበው ተመሣሣይ የህግ ክርክር ከአዋጅ ቁጥር 454/97 በየትኛውም እርከን የሚገኘውን ፍርድ ቤት የሚያስገድድ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል።
ወደ ተያዘው ጉዲይ ስንመለስም አመልካቾች የሟች ወ/ሮ አያልነሽ ዘውዳ እህቶች ናቸው ሟች ላልች እህትና ወንድሞች ያላቸው መሆኑንም ተረጋግጧል። ተጠሪ የሟች እናት እህት ልጅ መሆናቸውን በሚገባ ተረጋግጧል። በመሆኑም ተጠሪ ወደታች የሚቆጠሩ ተወላጅ ሳይሆኑ የሟች እናት እህት የሆኑት (የሟች አክስት) ልጅ ሲሆኑ የተጠሪ እናት ወደ ጏን የሚቆጠሩ የሟች የስጋ ዘመድ ናቸው። በዚህ አግባብ የሚቀርብ የወራሽነት ጥያቄ ምላሽ የሚያገኘው በፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 843 እና 844 ድንጋጌዎች መሰረት ነው። ሟች ወ/ሮ አያልነሽ ዘውዳ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ (ልጅ) የላላቸው ሲሆን እነዚህ ወገኖች አለመኖራቸው ከተረጋገጠ የሟችን ውርስ ሉወስደ የሚገባቸው የሟች እናት እና አባት ሲሆኑ በውርሱ የሚካፈለት በሁለተኛ ደረጃ ወራሽነት ነው። የሟች እናት እና አባት በሕይወት አለመኖራቸው የተረጋገጠ ሲሆን እነዚህ ወገኖች ሳይኖሩ ሲቀሩ በሟች ውርስ ሉካፈለ የሚገባቸው የሟች እህትና ወንድሞች ናቸው። የሟች እህትና ወንድሞች ሟችን የሚወርሱት ደግሞ ወላጆቻቸውን ተክተው ነው። የሟች እናት ወደታች የሚቆጠር ላላ ልጅ አልተዉም። ለሟች እህትና ወንድም ያለት በአባት መስመር ብቻ ስለመሆኑ ተጠቅሷል። እንዱህ ሲሆን የሟች ውርስ ተጠቃልል የሚሄደው በአባታቸው ልጆች በኩል እንጂ ሟችን ወደ ጎን በሚቆጠሩ የአሁኑ ተጠሪ እናት ላሆን አይችልም። ስለሆነም የስር ፍርድ ቤት የፍ/ብ/ሕ/ቁጥር 843 እና 844 ድንጋጌዎችን አፈጻጸም በሚገባ ሳይለይ በደፈናው ተጠሪ ተተክተው ሟች ወ/ሮ አያልነሽን መውርስ ይችላለ በማለት የደረሰበት ድምዲሜ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆኖ አግኝተናል። ወራሽ ላሆን የማይችል ሰው ደግሞ የሟች ውርስ ንብረት ይጣራልኝ የሚልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ስለሆነም ተጠሪ ከመነሻውም የሟች ውርስ እንዱጣራላቸው ይዘው የቀረቡት ማስረጃ ሕጋዊ ባለመሆኑ የውርስ ይጣራልኝ አቤቱታውን ለማቅረብ መብት ወይም ጥቅም አልነበራቸውም ለማለት የሚያስችል ነው። የፋዳራለ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተጠሪ የያዙት የወራሽነት ማስረጃ በማስረጃነቱ በማንኛውም የክርክር ደረጃ ተቃውሞ የሚቀርብበት ሆኖ እያለ ማስረጃው ባልተሰረዘበት ሁኔታ አመልካቾች የውርስ ይጣራልኝ ጥያቄ ተቀባይነት የለውም በማለት ሉከራከሩ አይችለም ሲል የአመልካቾችን ይግባኝ ሳይቀበል ማለፈና የስር ፍርድ ቤትን ውሳኔ ማፅናቱ መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ሆ5ኖ አግኝተናል። በዚህም መሰረት ተከታዩን ወስነናል።