No summary available.
ሐምል 30 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ትእግስት ነጋሽ - ቀረቡ ተጠሪ፡-
በዚህ መዝገብ የቀረበው የውርስ ሃብት ለመካፈል የቀረበን ጥያቄን የሚመለከት ነው። አመልካች በፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት ባቀረቡት ክስ የሟች አባታቸው አቶ ነጋሽ ደሳለኝ ወራሽ መሆናቸው ገልጸው የሟችና የአንደኛ ተጠሪ የጋራ ሃብት የሆነ ቤት ከነሰርቪሱና ላልች ንብረቶችን አንደኛ ተጠሪ ስለያዙ ውርስ እንዱጣራ አመልክተው ተጠሪዋ የአመልካችን ልጅነት ሳይክደ ሟች በሰጡት ኑዛዜ አመልካች እንዱያገኙ ከተናዘዙት ብር 5,000(አምስት ሺህ) ውጪ ሉጠይቁ አይችለም ብለው የተቃወሙ ሲሆን ሟች በቤቱና በሰርቪሱ እንዱሁም በቤት ቁሳቁስ ላይ ያላቸውን ድርሻ አንደኛ ተጠሪ በስማቸው አዛውረው እንዱጠቀሙና እሳቸው ስለሞቱ ንብረቱ በሙለ ለቀሪዎቹ ተጠሪዎች እንዱተላለፍ ተናዘዋል። ሟች ለአመልካች ብር 5,000(አምስት ሺህ) ከመስጠት በቀር እንደላልቹ ልጆች አላካፈለኝም። ከኑዛዜው ነቅለውኛል። በመሆኑም ኑዛዜው ሉፈረስ ይገባል በማለት አመልክተዋል። አንደኛ ተጠሪ ለክሱ በሰጡት መልስ ጥያቄው ከ3 ወር በኋላ የቀረበ በመሆኑ ይርጋ ያግደዋል፣ ኑዛዜው ተፈፃሚ ላሆን የሚችል ነው፣አመልካች ብር 5,000(አምስት ሺህ) ስለተሰጣቸው ከውርስ አልተነቀለም በማለት ክሱ ውድቅ እንዱሆንላቸው ጠይቀዋል። ቀሪዎቹም ተጠሪዎች ወደክርክሩ ጣልቃ ገብተው ባቀረቡት ክርክር ጥያቄው በይርጋ ቀሪ ነው፣ድርሻ አንሶኛል ለምትለው ድርሻዋን ለማወቅ የውርስ አጣሪ ስለተሾመ የአጣሪውን ሪፖርት መጠበቅ ግድ ይላል፣ውርስ የመጣራቱ ሂደት እስኪጠናቀቅ መዝገቡ ተዘገቶ ይቆይ በማለት ጠይቀዋል። ፍ/ቤቱም ጉዲዩን ተመልክቶ የይርጋ መቃወሚያው ውድቅ ካደረገ በኋላ ኑዛዜው ለአመልካች በግልጽ 5,000(አምስት ሺህ) ይከፈላት ስለሚል ለመፈፀም የሚቻል ነው፣በኑዛዜው ስጦታ ስለተደረገላቸው ተነቅያለሁ ማለት አይችለም፣ሟች ለወራሾቻቸው በፈለጉት መጠን ሃብታቸውን በኑዛዜ ማከፊፈል ይችላለ፣ስለሆነም ኑዛዜው የሚፈርስበት ምክንያት የለም በማለት ክሱን ውድቅ አድርጏ አመልካች ለአንደኛ ተጠሪ ብር 5,000(አምስት ሺህ) የጠበቃ አበል እንዱከፍለ ወስኗል። አመልካች በዚህ ውሳኔ ላይ ለፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት ይግባኝ አቅርበው ፍ/ቤቱ ጠበቃ አበል እንዱከፍለ የተሰጠውን የውሳኔ ክፍል ብቻ ለመመርመር ሲያስቀርብ ኑዛዜውን በተመለከተ በተሰጠው ውሳኔ ላይ የቀረበውን ይግባኝ ግን ውድቅ አድርጏታል።
የአሁኑ የሰበር አቤቱታ የቀረበው በዚህ ውሳኔ ላይ ነው። አመልካች በቅሬታቸው፣በኑዛዜው የተመለከተው ድርሻ ማነሱን፣ገንዘቡ ከየትኛው ሃብት ላይ እንደሚከፈልና ማን እንደሚከፍል ስለማያመለክት ለመፈፀም የሚቻል እንዲልሆነ፣ ያለምንም ህጋዊ ምክንያት ከኑዛዜ የተነቀለ መሆኑን ገልጸው ኑዛዜ እንዱፈረስ ያቀረቡት ክስ ውድቅ መደረጉ ተገቢ አይደለም፣በማለት ውሳኔ እንዱሻርላቸው ጠይቀዋል። ችልቱም ይህን የአመልካች አቤቱታ ለመመርመር አቤቱታው ለሰበር ሰሚ ችልት ያስቀርባል ብሎል። ተጠሪዎችም በሰጡት የፁሁፍ መልስ፤ሟች በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 920 በሚፈቅደው መሰረት የጋራ ሃብት ድርሻቸውን አንደኛ ተጠሪ በሕይወት እያለ ወራሾች እንዲይካፈለ አግደዋል፣ከ2-5 ያለት ተጠሪዎች ከአንደኛ ተጠሪ የተወለደ በመሆኑ ተጠሪዋ በህይወት እያለ እንደማይጠይቁ በመገመት ለአመልካች ብር 5,000(አምስት ሺህ) ሰጥተዋል፣በማለት የስር ፍ/ቤት ውሳኔ የሕግ ስህተት ስለላለው ውሳኔው እንዱፀናላቸው ጠይቀዋል። ችልቱም መዝገቡን መርምሯል።
አመልካች በስር ፍ/ቤት ያቀረቡት ክስ ሟች አባታቸው በተውት ኑዛዜ ለልጆቻቸው ያደረጉት ክፍፍል ከማነሱም በላይ ያለምንም ምክንያት ከውርስ የነቀሎቸው በመሆኑ ኑዛዜው እንዱሻርላቸው ነው። ከውርስ ተነቅያለሁ የሚለውን በተመለከተ በኑዛዜው አመልካች ብር 5,000(አምስት ሺህ) የተሰጣቸው መሆኑን አመልካችም አልካደም። ክርክራቸው አነስተኛ ድርሻ ማግኘታቸው ከውርስ ሃብት እንደተነቀለ የሚያስቆጥር መሆኑን ነው። ነገር ግን ከውርስ መነቀል ማለት ደግሞ ከውርስ ሃብቱ ምንም አይነት ድርሻ አለማግኘት እንጂ አነስተኛ ድርሻ ማግኘት ባለመሆኑ በዚህ ረገድ የቀረበው ቅሬታ ተቀባይነት የለውም።
በልላ በኩል አመልካች ሟች የውርስ ሃብት ክፍፍል ሲያደርጉ ለአመልካች ከሚገባቸው በላይ አሳንሰው ሰጥተዋቸዋል የሚል ክርክር ያቀርባለ። በፍ/ብ/ሕ/ቁ.913 የኑዛዜ ቃል የተናዡን ተቃራኒ ሃሳብ የሚገልጽ ካልሆነ በቀር በውርስ ሃብት አንድ ድርሻን ወይም አንድ ንብረትን ሟቹ ለወራሾቹ መስጠቱ ተራ የሆነ የክፍያ ደንብ እንጂ እንደ ኑዛዜ ስጦታ እንማይቆጠር ያመለክታል። ይህ ድንጋጌ በኑዛዜ የኑዛዜ ስጦታ (legacy) እንዱሁም የክፍያ ደንብ (rule of partition) ማድረግ እንደሚቻል የሚናገር ነው። በመርህ ደረጃ አንድ ሰው ከውርስ ሃብት መካከል አንድን ንብረት ለወራሾቹ መስጠቱ የኑዛዜ ስጦታ አያስኘውም። ይልቁንም ይህ አይነት ኑዛዜ ሕጉ የሚቀበለው እንደ አንድ የክፍያ ደንብ ነው። በመሆኑም አንድ ወራሽ ለወራሹ አንድን ሃብት ሲናዘዝ የኑዛዜው አፈፃፀም የስጦታ(legacy) አፈፃፀምን በመከተል ሳይሆን የክፍያ ደንብን (partition) በመከተል የሚከናወን ነው። የክፍያ ደንብ የሚከናወነውም ከአንቀጽ 1117 ጀምሮ ባለት ድንጋጌዎች ነው። ይህን በተመለከተ ይህ የሰበር ችልት በመ/ቁ. 18394 አስገዲጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቶበታል። አመልካች የሟች ልጅ በመሆናቸውም ለእርሳቸው የተሰጠው ብር 5,000(አምስት ሺህ) ከፍ ሲል በተጠቀሰው ድንጋጌ መሰረት የክፍያ ደንብ ነው።
No topics extracted.
ምንም እንኳን ሟች በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1017 መሰረት ውርስ ሃብታቸውን በሚፈልጉት መልክ መደልደል ቢችለም ድልድል ሲያደርጉ ግን አንድ ተወላጅ ከሚደርሰው ከሩብ የበለጠ ጉዲት ደርሶበት ከሆነ ክፍፍለ እንዱቀር ጥያቄ ማቅረብ እንደሚችል በፍ/ብ/ሕ/ቁ. 1123/1/ ስር ተመልክቷል። በተያዘውም ጉዲይ ቢሆን ሟች ሃብታቸውን በሙለ አንደኛ ተጠሪ በሕይወት እስካለ እንዱጠቀሙበትና ከእሳቸው ህይወተ-ህልፈት በኋላ ግን ሃብቱ በሙለ ለላልች ልጆች እንዱሰጥ ተናዘዋል። ለአመልካች እንዱሰጣቸው የተናዘዙት ብር 5,000(አምስት ሺህ) ብቻ ነው።
በመሆኑም የሟቹ ድርሻ ንብረታቸው ተጣርቶ አመልካች ሉደርሳቸው ከሚገባው ከሩብ የበለጠ ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑ አለመሆኑ ሉረጋገጥ ይገባ ነበር። ከ2 እስከ 5 ያለት ተጠሪዎችም ቢሆኑ በስር ፍ/ቤት የአመልካች ድርሻ እንዱታወቅ ውርሱ ሉጣራ እንደሚገባ ተከራክረዋል። የስር ፍ/ቤት ግን አመልካች የደረሰባቸው ጉዲት ምን ያህል መሆኑን ሳያጣራ አመልካች ብር 5,000(አምስት ሺህ) የተሰጣቸው በመሆኑ ከኑዛዜ አልተነቀለም በሚል ብቻ ጥያቄውን ውድቅ አድርጏታል። ምንም እንኳን አመልካች ከውርስ ተነቅያለሁ የሚል ክርክር ቢኖራቸውም በተጨማሪ ግን በክፍፍለ ድርሻቸው ያለአግባብ ማነሱንና ጉዲት የደረሰባቸው መሆኑን የሚያሳይ ይዘት ያለው ክርክር አቅርበዋል። የስር ፍ/ቤት አመልካች አልተነቀለም በማለት የደረሰበት ድምዲሜ ተገቢ ቢሆንም የአመልካችን የክፍያ ደንብ ጥያቄ ሳይመረምር አልፍታል። በመሆኑም የስር ፍ/ቤት አመልካች ክፍያውን በተመለከተ ያቀረቡት ጥያቄ ሳይመረምር ማለፈ መሰረታዊ የሕግ ስህተት በመሆኑ ተከታዩ ውስኔ ተሰጥቷል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 145134 ሰኔ 5 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ እና የፋ/ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 82145 ሐምል 7 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ትእዛዝ ተሻሽሎል።
የፋ/መ/ደረጃ ፍ/ቤት የሟች የአቶ ነጋሽ ደሳለኝ የውርስ ሃብት እንዱጣራ አድርጏ አመልካች የደረሰባቸውን ጉዲት ካረጋገጠ በኋላ የኑዛዜውን ውጤት አስመልክቶ ተገቢውን እንዱወስን ጉዲዩን በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 343/1/ መሰረት መልሰናል።
ግራ ቀኙ ወጪና ኪሳራ የየራሳቸውን ይቻለ።