No summary available.
ሐምል 22 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ብርሃኑ አመነው አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካቾች፡-
ተጠሪ፡- ወ/ሮ ፈልቃ ቤኛ - ጠበቃ ሙላት ፈለቀ ቀረበ መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
አቤቱታው የቀረበው የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 65587 ጥር 15 ቀን 2001 ዓ.ም በሰጠው ውሳኔ ላይ ነው። ክርክሩ በአሁኖቹ አመልካቾች ከሣሽነት የተጀመረው በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ነው። አመልካቾች ተጠሪን የከሰሱት ከአባታችን ልናገኝ የሚገባውን የውርስ ድርሻ ይዛ እየተጠቀመች ስለሆነ ውርስ አጣሪ ተሾሞ ድርሻችን እንዱለይ ይታዘዝልን በማለት ነው። ተጠሪ ለክሱ በሰጠችው ክሱ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል በማለት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ያቀረበች ሲሆን፣ፍ/ቤቱም መቃወሚያውን በመቀበል ክሱን ውድቅ አድርጏአል። በልላ በኩል ደግሞ አመልካቾች ውሳኔውን በመቃወም ለፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በማቅረባቸው ክርክሩ በድጋሚ ተሰምቶአል። በመጨረሻም ፍ/ቤቱ በፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የተሰጠውን ውሳኔ አጽንቶአል። የሰበር አቤቱታው የቀረበው በዚህ ላይ ነው።
አመልካቾች የካቲት 26 ቀን 2001 ዓ.ም በፃፈት ማመልከቻ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ተፈጽሞአል የሚለበትን ምክንያት በመግለጽ አቤቱታቸውን አቅርበዋል። በበኩላችንም አቤቱታውን መሰረት በማድረግ ተጠሪን አስቀርበን ክርክሩን ሰምተናል። አቤቱታው በሰበር ችልት እንዱታይ የተወሰነው በአመልካቾች የቀረበው የውርስ ይጣራልን ክስ /ጥያቄ/ በይርጋ ቀሪ ነው የመባለን አግባብነት ለመመርመር ነው።
በመሆኑም በዚህ ረገድ ግራ ቀኝ ወገኖች ያሰሙትን ክርክር አቤቱታ ከቀረበበት ውሳኔ እና ከሕጉ ጋር አገናዝበን ተመልክተናል።
ከሥር ጀምሮ ከተደረገው ክርክር መገንዘብ እንደቻልነው ተጠሪ የአመልካቾች አባት ሚስት ናት።
የአመልካቾች አባት እስከሞቱበት ጊዜ ድረስ አመልካቾች በዚሁ የአባታቸው እና የተጠሪ የጋራ ነው የተባለው ቤት ውስጥ በአባታቸው እና በተጠሪ ሲያድጉ ቆይተዋል። አባታቸው ከሞቱም በኋላም ተጠሪ እንደእናት በመሆን ስታሳድጋቸው እንደቆየች እና ንብረቱንም በጋራ ይዘው ሲያስተዲድሩት እንደነበር አመልካቾች በክርክራቸው ገልጸዋል። ከዚህም በተጨማሪ የባልና ሚስቱ የጋራ ንብረት እንዱለይ እና የአባታቸውን ድርሻ በወራሽነታቸው ማግኘት ይችለ ዘንድ ክስ የመሰረቱት ተጠሪ እነሱ ባላወቁት ምክንያት ከቤት ወጥታ በመሄድ ዘመድቼናቸው ከምትላቸው ሰዎች ጋር በመቀመጥዋ እንደሆነ በሰበር አቤቱታቸው ላይ በግልጽ በማመልከት ተከራክረዋል።
ተጠሪም ለሰበር አቤቱታው በጽሐፍ መልስ የሰጠች ሲሆን በአመልካቾች ክርክር በግልጽ በተነሱት ነጥቦች ላይ ምንም ማለት አልቻለችም። በዚህ ረገድ የመረጠችው በዝምታ ማለፍ ነው። በእርግጥ ከዚህ በፉት በሰበር ችልቱ የተሰጡትን ውሳኔዎች በመጥቀስ በሥር ፍ/ቤቶች የተሰጠው ውሳኔ ትክክል ነው እንዱባልላት ተከራክራለች።
ከዚህም በተጨማሪ ችልቱ ከጠበቃው ላቀረበው ጥያቄ ከተሰጠው ምላሽ ተጠሪዎች በፍሬ ነገር ረገድ ያነሱት ክርክር ትክክል እንደሆነ ለማረጋጥ ችለናል። የተጠሪ ጠበቃ ለቀረበለት ጥያቄ በሰጠው መልስ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ ንብረቱ/ቤቱ/ በአመልካቾች ይዞታ ሥር እንደሆነ አረጋግጦአል።
እንደምንመለከተው አመልካቾች የውርስ ድርሻ የጠየቁበት ንብረት ሁለቱም ወገኖች ይዘውት በጋራ ሲያስተዲድሩት የነበረ በመጨረሻም (ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ) በአመልካቾች ይዞታ ሥር ያለ ነው። አመልካቾች ወደ ክስ ያመሩትም ንብረቱ በዚህ ደረጃ ላይ እንዲለ ተጣርቶ የአባታቸው ድርሻ እንዱታወቅና ወራሽነታቸው ለእነሱ እንዱሆን እንዱወሰንላቸው እንደሆነ ግልጽ ነው። እውነታው ይህ ከሆነ ደግሞ ንብረቱ በተጠሪ እጅ (ተይዞ) እንደቆየ በማድረግ የተጠሪን የይርጋ መቃወሚያ ተቀባይነት ይኖረዋል የሚባልበት ሕጋዊ ምክንያት የለም። ተጠሪ የሰበር ችልቱ በሰበር መ/ቁ. 24675 የሰጣቸውን ውሳኔዎች በመጥቀስ ያቀረበችው ክርክርም እንዲየነው ውሳኔዎቹ የተሰጡት በዚህ መዝገብ ከተረጋገጠው ፍሬ ነገር የተለየ በሆነ ፍሬ ነገር ላይ በመመስረት በመሆኑ አግባብነት ያለው አይደለም። ሲጠቃለል የሥር ፍ/ቤቶች የአመልካቾች ክስ በይርጋ ቀሪ ሆኖአል።
No topics extracted.
በማለት የወሰኑት በፍትሐብሕር ሕጉ የተቀመጠውን የይርጋ ድንጋጌ እና የይርጋ መሰረተ ሃሳብ እንዱሁም የክርክሩን ፍሬ ነገር እግንዛቤ ውስጥ ባለማስገባት በመሆኑ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው ለማለት ችለናል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 108209 የካቲት 26 ቀን 2000 ዓ.ም የሰጠው ብይን እና የፋዳራል ከፍተኛ ፍ/ቤት በመ/ቁ. 65587 ጥር 15 ቀን 2001 ዓ.ም የሰጠው ውሳኔ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 348/1/ መሰረት ተሽረዋል።
የፋዳራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ክርክሩ በተከፈተው መዝገብ እንዱቀጥል በማድረግና ወደ ጉዲዩ ሥረ-ነገር በመግባት ግራ ቀኝ ወገኖችን በማከራከር ተገቢውን እንዱወስን ጉዲዩ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.
341/1/ መሰረት ይመለስለት ብለናል።