No summary available.
ሐምል 28 ቀን 2002 ዓ.ም ዳኞች፡- ሒጏስ ወልደ ኂሩት መለሰ ታፈሰ ይርጋ አልማው ወላ ዓሉ መሐመድ አመልካች፡- ወ/ሮ ገነት በላይ ጠበቃ - ኮልኔል መላኩ ካሣዬ ቀረቡ ተጠሪ፡- አቶ ፋኔት ተክለ - ሞግዚት ነጋ ቦንገር በላለበት ይታያል መዝገቡን መርምረን የሚከተለውን ፍርድ ሰጥተናል።
ጉዲዩ የቀረበው አመልካች የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት መጋቢት 10 ቀን 2001 ዓ.ም በተፃፈ የሰበር አቤቱታ ስለጠየቁ ነው። ክርክሩ በመጀመሪያ የታየው በፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ነው።
የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት የአቶ ተክለ ነጋ ውርስ እንዱጣራ ለውርስ አጣሪ መርቷል። የውርስ አጣሪው የሟች አቶ ተክለ ነጋ ወራሾች ህፃን ኬሩዝ ተክለና ህፃን ፋኔት ተክለ መሆናቸውንና የውርሱ ንብረት ክፍል የሚሆነውን ጥሬ ገንዘብና ያክሲዮን ድርሻ በመዘርዘር የውሣኔ ሐሳብ አቅርቧል። ለዚህ ክርክር መነሻ የሆነው ጉዲይ ለአሁን አመልካች ለሥር ተጠሪ ከፔፕሲ ኮላ ዓለም አቀፍ መስሪያ ቤት የተከፈላቸው መሆኑ በማስረጃ የተረጋገጠው 166,449.97 የአሜሪካን ድላር/አንድ መቶ ስልሣ ስድስት ሺ አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ከዘጠና ሰባት ሣንቲም/ የአሜሪካን ድላር ለአመልካች ጥቅም የተገባ የኢንሹራንስ ፖሉስ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ባለመኖሩ የውርስ ሃብት ነው በማለት የውርስ አጣሪው ያቀረበው ሃሳብ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ተቀብል አጽድቆታል። የውርስ አጣሪው ከላይ መጠኑ የተገለፀው የአሜሪካን ድላር አመልካች እንዱካፍለ ያቀረበውን የውሣኔ ሐሳብ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በማጽደቁ ተጠሪ ይህንን በመቃወም ይግባኝ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርበዋል።
ተጠሪዋ ለከፍተኛ ፍርድ ቤት ባቀረቡት የይግባኝ ማመልከቻ ሟች አቶ ተክለ ነጋ ከፔፕሲ ኮላ ዓለም አቀፍ ተጠሪ ጽ/ቤት ለአፍሪካ አህጉር ሥራ አስኪያጅ በሆኑበት ጊዜ የሕይወት ኢንሹራንስ የገባው እንደ አውሮፖውያን አቆጣጠር 07/01/98 (ከታህሣሥ 19 ቀን 1990 ዓ.ም) እስከ አውሮፖውያን አቆጣጠር 05/21/2001 (ከግንቦት 13 ቀን 1993 ዓ.ም) ነው በዚህ ጊዜ 166,449.97(አንድ መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ብር ከዘጠና ሰባት ሣንቲም) የአሜሪካን ድላር ለአሁን አመልካች (መልስ ሰጭ መክፈለ ተረጋግጧል)። ይህ ገንዘብ የውርስ ንብረት ክፍል ሆኖ በወራሾች መካከል ብቻ ሉከፊፈል ሲገባው የሥር መልስ ሰጭ የአሁን አመልካች የሕይወት ኢንሹራንስ ተጠቃሚ ሣይሆኑ የገንዘቡ ተጠቃሚ እንደሆኑ መደረጉ ተገቢ አይደለም የሚል ይግባኝ አቅርበዋል።
የአሁኑ አመልካች በበኩላቸው ለከፍተኛው ፍ/ቤት መስቀለኛ ይግባኝ አቅርበዋል። አመልካች ባቀረቡት መስቀለኛ ይግባኝ ሟች አሜሪካዊና የሕይወት ኢንሹራንስ የገባው በአሜሪካን አገር በሚገኝ ኩባንያ ኢንሹራንስ ከፊዩም የአሜሪካን ኩባንያ በሆነበት ሁኔታ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ጉዲዩን አይቶ የወሰነው የሥረ ነገር ሥልጣን ሳይኖረው ነው በማለት አመልክተዋል። የከፍተኛው ፍርድ ቤት የአሁን አመልካች ተጠሪዋ ላቀረቡት ይግባኝ የሰጡትን መልስና የአሁን ተጠሪዎች ለአመልካች የመስቀለኛ ይግባኝ የሰጡትን መልስ ከተቀበለና ግራ ቀኙን ካከራከረ በኋላ የዓለም አቀፍ የግለሰብ ሕግ ጥያቄ ስላልተነሣ የፋዳራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ጉዲዩን ለማየት ሥልጣን አለው። የአሁን አመልካች የኢንሹራንስ ክፍያው ለሟች አሰሪ መስሪያ ቤት የከፈላቸው መሆኑን እንጂ የሕይወት ኢንሹራንስ ለእሳቸው ጥቅም የተደረገ መሆኑን የሚያስረዲ ማስረጃ አላቀረቡም። ፍርድ ቤቱ ይህንን ለማጣራት የኢንሹራንስ ውለ እንዱቀርብ ትእዛዝ ሰጥቶ ውለ ተፈልጏ እንዲልተገኘ መሥሪያ ቤቱ ጥር 22 ቀን 2000 ዓ.ም በፃፈው ደብዲቤ አረጋግጧል። ስለሆነም አመልካች የሕይወት ኢንሹራንስ ውል የተለየ ተጠቃሚ መሆናቸውን የኢንሹራንስ ውለ በማቅረብ ያላስረደ ስለሆነ የሕይወት ኢንሹራንሱ የሟች የውርስ ንብረት ክፍል በመሆን ለሟች ልጆችና ወራሾች ብቻ የሚተላለፍ ነው በማለት የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827/1/ መሰረት በማድረግ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አመልካች ከኢንሹራንስ ገንዘቡ ግማሹን ትውሰድ በማለት የሰጠውን ውሣኔ ሽሮታል።
አመልካች በዚህ ውሳኔ ቅር በመሰኘት ይግባኝ ለፋዳራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት አቅርበዋል። ይግባኝ ሰሚ ችልቱ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የሰጠው ውሣኔ ጉድለት የላለበት መሆኑን በመግለጽ ይግባኙን በፍትሐብሕር ሥነ-ሥርአት ሕግ ቁጥር 337 መሰረት ሰርዞታል። አመልካች መጋቢት 10 ቀን 2001 ዓ.ም ባቀረቡት የሰበር አቤቱታ ጉዲዩን ማየትና መወሰን የሚችለው በአሜሪካን ግዛት ውስጥ ያለ የስረ ነገር ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት መሆን ሲገባው የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የዲኝነት ሥልጣን አለኝ በማለት የሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 በመተርጏም ረገድ የከፍተኛው ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሕግ ስህተት ሰርቷል። ይህ ድንጋጌ በሕይወት ኢንሹራንስ ተጠቃሚ የሚሆኑ ባል ወይም ሚስት መብት ሙለ በሙለ በሚያሣጣና የህይወት ኢንሹራንስ ገንዘቡን ወደ ሟች ወራሾች ሙለ በሙለ ለማስተላለፍ በሚችል መንገድ መተርጏም የለበትም። አመልካች የኢንሹራንስ ገንዘብ ተከፍሎቸዋል። የህይወት ኢንሹራንስ ተጠቃሚ ባይሆኑ ኖሮ አይከፈላቸውም ነበር ስለዚህ በህይወት ኢንሹራንስ ልዩ ተጠቃሚ ስለመሆናቸው አላስረደም ተብል የተሰጠው ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ነው። የበታች ፍርድ ቤቶች የንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 2/ሀ/ ድንጋጌዎች ከግምት ውስጥ ሣያስገቡ የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት ስለሆነ በሰበር ታይቶ እንዱታረምልኝ በማለት አመልክተዋል።
ተጠሪ ሞግዚታቸው የተሻረ መሆኑ ተገልጿል። ስለሆነም ተጠሪዋ ፋኔት ተክለ በሚል ስም በጋዜጣ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቶ በጋዜጣ ጥሪ የተደገላቸው ቢሆንም ጉዲዩ በላለበት እንዱታይ ፍርድ ቤቱ ትእዛዝ ሰጥቷል። ከሥር የክርክር አመጣጥና በሰበር የቀረበው ክርክር ከላይ የተገለፀው ሲሆን የከፍተኛው ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት አመልካች ሟች ከገባው የሕይወት ኢንሹራንስ የምታገኘው ድርሻ የላትም የሕይወት ኢንሹራንስ ክፍያው የሟች ውርስ ንብረት ክፍል ስለሆነ የሕይወት ኢንሹራንስ ገንዘቡን የሟች ልጆችና ወራሾች ብቻ ይካፈለ በማለት የሰጠው ውሣኔ አግባብነት ያላቸውን የሕግ ድንጋጌዎች ትርጉምና የተፈፃሚነት ወሰን መሰረት በማድረግ የተሰጠ ነው ወይስ አይደለም? የሚለውን ጭብጥና ላልች ተዛማጅነት ያላቸው ነጥቦች በዝርዝር መመርመር የሚያስፈልገው ሆኖ አግኝተነዋል።
ከላይ የተያዘው ጭብጥ እልባት ለመስጠት በመጀመሪያ አመልካች የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የህይወት ኢንሹራንስ ገንዘቡን በተመለከተ የዲኝነት ሥልጣን የላቸውም? የሟች አሰሪ መሥሪያ ቤት የኢንሹራንስ ገንዘቡን ለእኔ መክፈለ የሕይወት ኢንሹራንስ ውለ ልዩ ተጠቃሚ መሆኔን ያስረዲል በማለት ያቀረቧቸውን ክርክሮች ተገቢነት ማየት ያስፈልጋል።
የውርስ ማጣራት አንደኛው ተግባር የሟች ወራሾች እነማን እንደሆኑ መለየት የሟች ውርስ ሐብት ክፍል የሚሆነውንና የሟችን እዲ አጣርቶ መለየትና መወሰን የሚያጠቃልል ነው። በውርስ ማጣራት ሑደት አመልካች የተቀበለት 166,447.97(አንድ መቶ ስልሳ ስድስት ሺህ አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ከዘጠና ሰባት ሣንቲም) የአሜሪካን ድላር የውርስ ንብረት ክፍል ነው ወይስ አይደለም? የሚለው ጥያቄ አከራካሪ ጭብጥ ሲሆን ጥያቄው በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት ለመወሰን የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች የዲኝነት ሥልጣን ያላቸው በመሆኑ አመልካች ጉዲዩን ለማየትና ለመወሰን የዲኝነት ሥልጣን የፋዳራል ፍርድ ቤቶች የላቸውም በማለት ያቀረቡት ክርክር በመዝገቡ የተያዘው ክርክሩ በአመልካችና የሟች ወራሾች በሆኑ ሁለት ኢትዮጵያውያን መካከል መሆኑን፣የክርክሩም መሰረታዊ ጉዲይ በሟች አሰሪ መስሪያ ቤት በኩል የተከፈለው ወደ አገር ውስጥ የተላከው የህይወት ኢንሹራንስ ገንዘብ የሟች ውርስ ንብረት ክፍል ነው ወይስ አይደለም? የሚልና በውጭ አገር የሚገኙ የሕግ ወይም የተፈጥሮ ሰዎች በክርክሩ ተካፊይ የማይሆኑበት መሆኑን ያላገናዘበ በመሆኑ አልተቀበልነው።
ይህም የህይወት ኢንሹራንስ ውለ ልዩ ተጠቃሚ መሆኔን የሚያስረዲ ነው በማለት ያቀረቡት ክርክር ተገቢነው ወይስ አይደለም የሚለው ነው። አመልካች የህይወት ኢንሹራንስ ውለ የተለዩ ተጠቃሚ መሆናቸውን የሚያስረዲ ማስረጃ በተለይም አመልካችን የህይወት ኢንሹራንስ ውለ ተጠቃሚ በማድረግ ሟች የመድን ዋስትና ከሰጠው የመድን ድርጅት ጋር የገባውን ውል እንዱያቀርቡ ተጠይቀው ውለን ሉያቀርቡ አለመቻላቸው በሥር ፍርድ ቤትና በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረጋግጧል። ለአንድ ለተለየ ተጠቃሚ የሚደረግ የህይወት ኢንሹራንስ ውል በዝርዝር የሚይዛቸው ጉዲዮችን የንግድ ሕግ አንቀጽ 195 በዝርዝር ይደነግጋል። አመልካች የኢንሹራንስ ፖሉሲው ልዩ ተጠቃሚ ነኝ ካለ በንግድ ሕጉ አንቀጽ 195 እና 701/1/ የተደነገጉትን ዝርዝር ጉዲዮች የሚያሥረዲ የኢንሹራንስ ውልና ፖሉሲ በማቅረብ የማስረዲት ግዳታ አለባቸው። አመልካች ይህንን የማስረዲት ግዳታና ኃላፉነታቸውን ያልተወጡ መሆኑን የሥር ፍርድ ቤት በመደበውና ተቀብል ሪፖርቱን ባፀደቀው የውርስ አጣሪና በከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረጋግጧል።
አመልካች የሟች ልጆች ሞግዚትና የሟች ሚስት በመሆናቸው ምክንያት ይሁን ወይም በልላ ምክንያት በሟች መኖሪያ ቤት በኩል የኢንሹራንስ ገንዘቡ ተከፍሎቸዋል። የህይወት ኢንሹራንስ ገንዘቡ አመልካች መክፈለ ብቻውን አመልካች በንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት የህይወት ኢንሹራንስ ውለ ተጠቃሚ መሆናቸውን አያስረዲም ከሚል መደምደሚያ ላይ የከፍተኛው ፍርድ ቤት የደረሰው ሟች የህይወት መድን ሽፊን ከሰጠው የኢንሹራንስ ኩባንያ ጋር ያደረገው የኢንሹራንስ ውል እንዱላከለት ትእዛዝ ሰጥቶ የህይወት ኢንሹራንስ የውል ሰነደ ተፈልጏ ሉገኝ አለመቻለ የሟች አሰሪ መሥሪያ ቤት ከገለጹለት በኋላ ነው። ስለሆነም አመልካች በንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 1 መሰረት የህይወት ኢንሹራንስ ውለ ተጠቃሚ መሆናቸው የተገለፀ መሆኑን አግባብነት ያለው ማስረጃ በማቅረብ አላስረደም በማለት የከፍተኛው ፍርድ ቤት እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችልት ውሣኔ የሰጡት የህይወት ኢንሹራንስ ውለን ለማስቀረብና ፍሬ ጉዲዩን ለማጣራት ተገቢውን ጥረት ካደረጉ በኋላ በግራ ቀኙ በኩል የቀረበውን ማስረጃ በመመዘን በመሆኑ አመልካች የህይወት ኢንሹራንስ ውለ ተጠቃሚ መሆኔን አስረድቻለሁ በማለት ያቀረቡት የሰበር አቤቱታ ተገቢነት የላለውና የሰበር ችልት በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 80 ንኡስ አንቀጽ 3/ሀ/ እና በአዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀጽ 10 የተሰጠውን ሥልጣንና ኃላፉነት ያላገናዘበ በመሆኑ አልተቀበልነውም።
ሟች የንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 1 እና በንግድ ሕግ ቁጥር 695 በተደነገገው መሰረት የህይወት ኢንሹራንስ ውለን ያደረገው ለአመልካች ወይም ለልጆቹ ህፃን ኬራዝ ተክለና ህፃን ፋኔት ተክለ ልዩ ጥቅም ያደረገ ስለመሆኑ የሚያስረዲ ማስረጃ አልቀረበም። የህይወት መድን ውል በመድን ውል በተጠቃሚነት ለተገለፀው ሰው ወይም ሰዎች ወይም ኢንሹራንስ ከገባው ሰው መብት ላላቸውና ስማቸው በተጠቃሚነት ላልተገለፁ ሰዎች ላደረግ እንደሚችል ከንግድ ሕግ ቁጥር 692 ንኡስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ለመገንዘብ ይቻላል።
ሟች በገባው የሕይወት ኢንሹራንስ ውል ተጠቃሚ የሚሆነውን ሰው በንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 1 የገለፀ በሆነ ጊዜ የኢንሹራንስ ውለ መሰረት ገንዘብ ለማን ይከፈላል የሚለው ጥያቄ በዚህ መዝገብ አከራካሪ ጭብጥ ሆኖ አልቀረበም። በያዝነው ጉዲይ ሟች ያደረገው የኢንሹራንስ ውል ለአመልካች ወይም ለልጆቹ ልዩ ጥቅም የተደረገ መሆኑን የማይገልጽና ለተለየ ተጠቃሚ ያልተደረገ ነው በማለት የበታች ፍርድ ቤቶች የደረሱበት መደምደሚያ ተገቢነት ያለው ቢሆንም ሟች ባደረገው የህይወት ኢንሹራንስ ውል በንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ መሰረት የኢንሹራንስ ውለ ተጠቃሚ ወይም ተጠቃሚዎች ያልገለፀ በሆነ ጊዜ በህይወት ኢንሹራንስ ውል መሰረት በሚከፈለው ገንዘብ ላይ መብት የሚኖራቸው እነማን ናቸው? ጉዲዩስ የትኛውን የሕግ ድንጋጌ መሰረት በማድረግ ይወስናል የሚለውን ሰፉ የሕግ ክርክር ያስነሳ ጭብጥ አስመልክቶ የከፍተኛው ፍርድ ቤትና ይግባኝ ሰሚው ፍ/ቤት የሰጡት ውሣኔና የደረሱበት መደምደሚያ በዝርዝር መታየት ያለበት ሆኖ አግኝተነዋል።
ሀ. የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ ይዘትና መሰረታዊ ባህሪ ለመረዲት በኢትዮጵያ የውርስ ሥርአት ከሟች ወደ ወራሾች የሚተላለፈው መብትና ግዳታ በተመለከተ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 826 ንኡስ አንቀጽ 2 የተደነገገውን ጠቅላላ መርህ ማገናዘብ ያስፈልጋል። በርካታ አገሮች ለምሣላ ሩሲያ ከሟች ወደ ወራሾቹ በውርስ ሉተላለፈ የሚችለ ንብረቶችና መብቶች በዝርዝር ያስቀምጣለ። የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 826/2/ የሟች ውርስ ክፍል ሆነው ለወራሾቹ ሉተላለፈ የሚችለ ንብረቶችና መብቶች ምንምን እንደሆኑ ከመዘርዘር ይልቅ በሟች መሞት የሚያቋርጡ የሟች መብቶችና ግዳታዎች ለሟች ወራሾችና የኑዛዜ ባለስጦታዎች የሚተላለፈ መሆኑን በመርህነት የሚደነግግ መሆኑን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 826 ንኡስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። ይህም ማለት በሟች መሞት ምክንያት ቀሪ የሚሆኑና ሟች በግለ ብቻ ሉሰራባቸው የሚችለ መብቶችና ሟች በግለ ብቻ እንዱፈጽማቸው የሚገደድባቸው ግዳታዎች ውጭ ያለ በሟች መሞት ምክንያት የማይቋረጡ መብትና ግዳታዎች ለሟች ወራሾች የሚተላለፈ መሆኑ በአጠቃላይ መርህነት ተደንግጓል።
የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 እና የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 828 በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 826 ንኡስ አንቀጽ 2 የተደነገገው ጠቅላላ መርህ ለየት ባለ ሁኔታ ሕግ አውጭው የደነገጋቸው ልዩ የሕግ ድንጋጌዎች ናቸው። የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 “በውርስ ውስጥ የሚገኘው ስለሕይወት ኢንሹራንስ ውል” በሚል እርስ ንኡስ አንቀጽ 1 “ሟች ተጠቃሚውን ያልወሰነ እንደሆነ ወይም ኢንሹራንሱ ለሟች ወራሾች ጥቅም የተደረገ እንደሆነ ሟች በፈረመው ስለ ህይወት ኢንሹራንስ ውል አፈፃፀም የሚከፈለ ገንዘቦች የውርስ ንብረት ክፍል ይሆናለ” በማለት የሚደነግግ ሲሆን ንኡስ አንቀጽ 2 “ተቃራኒ ሁኔታ ሲኖር የውርስ ክፍል አይሆንም” በማለት ይደነግጋል።
የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ድንጋጌ በሞት ጊዜ እንዱከፈል የተደረገ የህይወት ኢንሹራንስ ውል መሰረት የሚከፈል የኢንሹራንስ ገንዘብ በሟች መሞት ምክንያት የማይቋረጥ ይልቁንም ገንዘቡ የሚጠየቀው ኢንሹራንስ ገቢው ከዚህ ዓለም በሞት ሲለይ መሆኑን በመገንዘብ ሕግ አውጭው በሞት ጊዜ የሚከፈል የህይወት ኢንሹራንስ ውል በንግድ ሕግ ቁጥር 695 እና በንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 1 በተደነገገው መሰረት የህይወት ኢንሹራንስ ውለ ተጠቃሚ ወይም ተጠቃሚዎች የተደረገ በሆነ ጊዜ የኢንሹራንስ ገንዘቡ የውርስ ንብረት ክፍል እንደማይሆንና ወራሾቹ ድርሻ አለን ብለው የመብት ጥያቄ ሉያነሱ የማይችለ መሆናቸውን በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 2 በግልጽ የሚደነግግ ሲሆን፣የሕይወት ኢንሹራንስ ውል ተከፊይ የሆነ ገንዘብ የሟች የውርስ ሐብት ክፍል የሚሆነው በመጀመሪያው ሟች “ለወራሾቹ” በሚል መንገድ ኢንሹራንስ ውለ በተጠቃሚነት የገለፀ ከሆነ መሆኑን ሁለተኛው ሟች የኢንሹራንስ ተጠቃሚ ማን እንደሆነ ሣይገልጽ በቀረ ጊዜ እንደሆነ በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 ይደነግጋል። ድንጋጌው በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 826 ንኡስ አንቀጽ 1 ከተደነገገው ጠቅላላ መርህ በተለየ ሁኔታ በህይወት ኢንሹራንስ ውል መሰረት የሚከፈል ገንዘብ በምን ሁኔታ የሟች የውርስ ሐብት ክፍል እንደማይሆንና የሟች ወራሾች የመብት ጥያቄ እንደማያነሱ የሚደነግግ ነው።
ለ/ የንግድ ሕግ ቁጥር 705 የንግድ ሕግ ቁጥር 705 የህይወት ኢንሹራንስ ክፍያ የሟች የውርስ ክፍል ስለሚሆንባቸውን ሁኔታዎች በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 የተደነገጉትን ሁኔታዎች የሚያሰፊ ነው። ድንጋጌው የሕይወት ኢንሹራንስ ውለ ለተለየ ተጠቃሚ የተደረገ መሆኑን በማይገልጽበት ጊዜ ብቻ ሣይሆን ሟች የኢንሹራስን ውለ ተጠቃሚ ነው ብል የገለፀውን ሰው በንግድ ሕግ ቁጥር 703 መሰረት በመሻር ላላ ተጠቃሚ ያልገለፀ ሆኖ በሚገኝበት ጊዜ ወይም ተጠቃሚው ፈቃደን ሣይገልጽ በመሞቱ ምክንያት ውድቅ በሆነ ጊዜ የኢንሹራንስ ገንዘቡ የሟች የውርስ ንብረት ክፍል እንደሚሆንና ለሟች ወራሾች እንደሚተላለፍ የሚገልጽ ነው። የንግድ ሕግ ቁጥር 705 “ተጠቃሚው ሣይለይ የተደረገ ኢንሹራንስ” በሚል ርእስ “ተጠቃሚው ተለይቶ ያልታወቀ እንደሆነ ወይም ተሽሮ እንደሆነ ወይም በሕይወት የላለ በመሆኑ ውድቅ የሆነ እንደሆነ ስለሞት የተደረገው የኢንሹራንስ ዋናው ገንዘብ የሚከፈለው ኢንሹራንሱን ለተዋዋለው ሰው ውርስ ነው” በማለት በግልጽ ይደነግጋል።
ከዚህ በላይ የተደነገጉት የሕግ ድንጋጌዎች የተጠሪ ሞግዚት ሟች ባደረገው የሕይወት ኢንሹራንስ ውል መሰረት አመልካች የተቀበለት ገንዘብ የሟች ውርስ ክፍል በመሆኑ ለሟች ወራሾች ብቻ ሉከፊፈል ይገባል በማለት የሚያቀርቡትን ክርክር የሚደግፍና የሟች ወራሾች የኢንሹራንስ ተጠቃሚው በኢንሹራንስ ውለ ተለይቶ ባልተገለፀበት ጊዜ የሚኖራቸውን ሰፉ መብት የሚደነግጉና የሟችን ባል ወይም ሚስት በኢንሹራንስ ገንዘቡ መብት የላለው መሆኑን የሚያሣዩ ናቸው።
ሐ. የንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 2 የንግድ ሕግ ቁጥር 701 “ለሞት በሆነ ኢንሹራንስ ተጠቃሚ የሆነ ሰው” በሚል ርእስ ሥር በንኡስ አንቀጽ 2 “ስማቸው በውለ ላይ ተለይቶ ባይጠቀስም /ሀ/ ጋብቻው የተደረገው የኢንሹራንስ ውለ ከተፈረመ በኋላ ቢሆን እንኳን የኢንሹራንስ ውል የፈረመው ባል ወይም ሚስት /ለ/ የኢንሹራንስ ውል ሲፈርም የተወለደት የኢንሹራንስ ውል ፈራሚ ልጆች ተለይተው የታወቁ ተጠቃሚዎች ተብለው ይቆጠራለ” በማለት ይደነግጋል። ይህ ድንጋጌ ሟች የኢንሹራንስ ውለን ተጠቃሚ ሣይገልጽ የኢንሹራንስ ውል ባደረገ ጊዜ ከኢንሹራንስ ውለ ከመፈረሙ በፉት ወይም በኋላ ኢንሹራንስ ውል የተዋዋለው ሰው ጋር በጋብቻ የተሣሰሩ ሚስት ወይም ባልና የኢንሹራንስ ውለ ሲፈረም ተወልደው የነበሩ ልጆቹ የኢንሹራንስ ውል ተጠቃሚ የሚሆኑ መሆናቸውን የሚደነግግ ነው። በዚህ ድንጋጌ መሰረት የኢንሹራንስ ውል ፈራሚው ባል ወይም ሚስት የሟች ወራሽ ባይሆኑም ተጠቃሚው ተለይቶ ያልተገለፀበት የህይወት ኢንሹራንስ ውል የሕግ ተጠቃሚና ባለመብት እንደሚሆኑና የሟች አንደኛ ደረጃ ወራሾች ከሚሆኑት ከሟች ልጆች መካከል የኢንሹራንስ ውለ ሲፈረም የተወለደት የኢንሹራንስ ውለ የሕግ ተጠቃሚ እንደሚሆኑና የኢንሹራንስ ውለ ከተፈረመ በኋላ የተወለደት በዚህ ድንጋጌ መሰረት የተጠቃሚነት መብት የላላቸው መሆኑን የሚደነግግ ነው።
የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 እና የንግድ ሕግ ቁጥር 705 ድንጋጌዎችና የንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 2 ድንጋጌዎች እንዱሁ እንዲለ በአንድ ላይ ተፈፃሚ ለማድረግ በምክር የተለያየ ውጤት የሚያስከትለ መሆኑን በአመልካችና በተጠሪ መካከል በዚህ መዝገብ የተደረገው ክርክርና ፍርድ ቤቶቹ በየደረጃው የሰጡት ውሣኔ በማየት ለመገንዘብ ይቻላል። ሟች የሕይወት ኢንሹራንስ ውል ተጠቃሚ ሣይገልጽ የገባው የህይወት መድን ገንዘብ የይገባኛል ጥያቄን የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 እና የንግድ ሕግ ቁጥር 705 ድንጋጌ ብቻ መሰረት በማድረግ የወሰነው ከፍተኛ ፍ/ቤት የኢንሹራንስ ገንዘቡ ለሟች ወራሾች (ልጆች ብቻ) ይከፊፈል በማለት የወሰነውን ሲሆን በተቃራኒው ጭብጡን የንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 2 ድንጋጌ ብቻ የሚወስን አመልካችና የኢንሹራንስ ውለ ሲፈረም የተወለደችውን የሟች ልጅ ብቻ የኢንሹራንስ ተጠቃሚ እንደሆኑ የሚወሰንበት ሁኔታ እንደሚኖር ከላይ ይዞታቸውንና ዓላማቸውን በዝርዝር ያየናቸውን ድንጋጌዎች ያላቸውን ልዩነትና የሚያስከተለት ህጋዊ ውጤት በመመርመር ለመገንዘብ ይቻላል።
የሚለውን ጥያቄ በቅድሚያ መመለስ ያስፈልጋል።
በሁለት የሕግ ድንጋጌዎች መሰረታዊ ይዘትና በአንድ ላይ ሲፈፀሙ የሚያስከትለትን ተቃራኒ ውጤት ለማስቀረት ፍርድ ቤቶች የተለያዩ የሕግ አተረጓጏም መርሆችን በመጠቀም የሕግ ትርጉም በመስጠት ችግሩን የሚያቃልለ መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም ከላይ በተገለፁት ድንጋጌዎች በመካከል ያለውን መሰረታዊ ቅራኔ ለመፍታት ላልች ድንጋጌዎችን ለማስታረቅ ዘወትር የምንከተላቸው የሕግ አተረጓጏም ዘዳዎች (ጥበቦች) አገልግልት የላላቸው መሆኑን መገንዘብ ይቻላል። ፍርድ ቤቶች የዚህ አይነት ችግር ሲያጋጥም የሚከተለት የሕግ አተረጓጏም ጥበብ አንደኛው ከሁለቱ ሕጏች ማንኛው ቀድሞ እንደታወጀ ማንኛው በኋላ እንደታወጀ በመመርመር በኋላ የወጣው ሕግ ቀድሞ በወጣው ሕግ የተደነገገውን ድንጋጌ እንዲሻሻለው ወይም እንደሻረው ይቆጠራል የሚለውን የሕግ አተረጓጏም ዘዳ በመከተል በኋላ የታወጀውን ሕግ ተፈፃሚ በማድረግ ችግሩን ያቃልላለ። በያዝነው ጉዲይ የፍትሐብሕር ሕጉም ሆነ የንግድ ሕጉ በአንድ ቀን ማለትም ሚያዝያ 27 ቀን 1952 ዓ.ም የታወጀ መሆኑን በመግቢያቸው የተገለፀ በመሆኑ ይኸ የአተረጓጏም ዘዳ ከላይ በገለጽናቸው የሕግ ድንጌዎች መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት የሚያስችለን ሆኖ አልተገኘም።
በሁለት የሕግ ድንጋጌዎች ይዘትና በውጤት በአንድ ጉዲይ ልዩነት የሚያስከትል ሲሆን ፍርድ ቤቶች የሚከተለት ላላው የሕግ አተረጓጏም ዘዳ ስለ ልዩ ሁኔታ የተደነገገው ድንጋጌ በጠቅላላ የሕግ ድንጋጌዎች ላይ የበላይነትና ተፈፃሚነት ይኖረዋል የሚለው ነው። በያዝነው ጉዲይ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 ድንጋጌ በፍታብሓር ሕግ ቁጥር 826 ንኡስ አንቀጽ 2 ለተደነገገው መሰረታዊ ጠቅላላ መርህ በልዩ ሁኔታ የተደነገገ ልዩ ድንጋጌ ሲሆን የሕይወት ኢንሹራንስ ገንዘብ የሟች የውርስ ክፍል የሚሆንባቸውንና የማይሆንባቸውን ልዩ ሁኔታዎች የሚደነግግ ነው። በተመሣሣይ ሁኔታ የንግድ ሕግ ቁጥር 705 ተጠቃሚው ሣይለይ የተደረገ ኢንሹራንስ የሚመለከት ደንቦችን የያዘ ልዩ ድንጋጌ ሲሆን የንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 2 ድንጋጌዎችም በሞት ጊዜ የሚከፈልና ተጠቃሚው ያልተገለፀበት የህይወት ኢንሹራንስ ውለ በልዩ ሁኔታ ባል ወይም ሚስት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የሚደነግግ ልዩ ድንጋጌ መሆኑን ለመገንዘብ ይቻላል።
ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ድንጋጌዎች አንደኛውን ጠቅላላ የሕግ ድንጋጌ ላላውን ልዩ የሕግ ድንጋጌ ነው ብል ለመፈረጅ የማይቻልና ልዩ የሕግ ድንጋጌ በጠቅላላ የሕግ ድንጋጌ ላይ የበላይነትና ተፈፃሚነት ይኖረዋል።
የሚለውን የሕግ አተረጓጏም መርህ ለመከተል የሚያስቸግር ሆኖ አግኝተነዋል።
በእኛ በኩል በድንጋጌዎቹ መካከል ያለውን ልዩነት ለመፍታት ሕግ አውጭ እያንዲንደን የሕግ ድንጋጌ የደነገገው በነባራዊ ህይወት ውስጥ ተፈፃሚ እንደሆነና አንድ ማህበራዊ ችግር እንዱፈታ አስቦ ነው። ስለዚህ ለአንደኛው የሕግ ድንጋጌ የሚሰጠው የሕግ ትርጉም ላላውን ድንጋጌ ሙለ በሙለ ውጤት አልባ በማያደርግ መንገድና ሁለም ድንጋጌዎች ውጤታማ የሚሆኑበትን የሕግ አተረጓጏም መከተል አለበት የሚለውን የሕግ አተረጓጏም መርህ ጠቃሚና አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል። በዚህ አተረጓጏም መሰረት ተጠቃሚው በኢንሹራንስ ውለ ባልተገለፀበት ጊዜ የሟች ባል ወይም ሚስት የኢንሹራንሱን ገንዘብ ከሟች ወራሾች ጋር የሚካፈለበትን ልዩ ሁኔታ በመከተል የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 የንግድ ሕግ ቁጥር 705 እና የንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 2/ሀ/ ድንጋጌዎች በማጣጣም የሟች ወራሾችም ሆኑ የሟች ባል ወይም ሚስት በሕግ የተሰጣቸውን መብት ሙለ በሙለ ሣያጡ የኢንሹራንሱ ገንዘብ እንዱካፈለ በማድረግ ሁለም የሕግ ድንጋጌዎች ውጤታማ ተፈፃሚነት እንዱኖራቸው ማድረግ የተሻለው የሕግ አተረጓጏም መንገድ መሆኑን ተገንዝበናል።
ስለሆነም በፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 እና በንግድ ሕግ ቁጥር 705 ተጠቃሚው ተለይቶ ባልተገለፁበት የህይወት ኢንሹራንስ ውል መሰረት በሚከፈል የኢንሹራንስ ገንዘብ የመካፈል መብት ያላቸው የሟች ወራሾችና የንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 2/ሀ/ መሰረት የኢንሹራንስ ውለ ተጠቃሚ የመሆን መብት ያላቸው የሟች ሚስት ወይም ባል የኢንሹራንስ ገንዘቡን የመጠየቅ በሕግ እንደ ልዩ ተጠቃሚ የሚቆጠር መብት ያላቸው በመሆኑ አንድ ላይ የኢንሹራንስ ገንዘቡ ተጠቃሚና ተካፊይ ሉሆኑ ይገባል ብለናል።
ስለሆነም የአመልካችና የተጠሪ ክርክርም ከላይ በዝርዝር ያስቀመጥነውን የሕግ አተረጓጏም በመከተል መፍታት ሲገባቸው የከፍተኛ ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ችልት ለአመልካች በንግድ ሕግ ቁጥር 701 ንኡስ አንቀጽ 2/ሀ/ የተረጋገጠላትን መብት ሙለ በሙለ ዋጋ በሚያሣጣ ሁኔታ የፍትሐብሕር ሕግ ቁጥር 827 ንኡስ አንቀጽ 1 በመተርጏም የኢንሹራንስ ገንዘቡ የሟች የውርስ ክፍል ስለሆነ አመልካች መብት የላትም።
የኢንሹራንስ ገንዘቡን የሟች ልጆችና ወራሾች ብቻ እኩል ይካፈለ በማለት የሰጡት ውሣኔ መሰረታዊ የሕግ ስህተት ያለበት በመሆኑ በፍትሐብሕር ሥነ- ሥርአት ሕግ ቁጥር 348/1/መሰረት በማሻሻል አመልካች ከሟች ልጆችና ወራሾች ጋር የኢንሹራንስ ገንዘቡ ተጠቃሚ የመሆን መብት አላት በማለት ወስነናል።
የፋዳራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የጠቅላይ ፍ/ቤት ይግባኝ ችልት የሰጡት ውሣኔ ተሻሽሎል።
የህይወት ኢንሹራንስ ገንዘብ በሆነው 166,449.97(አንድ መቶ ስልሣ ስድስት ሺ አራት መቶ አርባ ዘጠኝ ) የአሜሪካን ድላር ከጠዘና ሰባት ሳንቲም በተመለከተ የሟች ሚስት የሆኑት አመልካችና የሟች ልጆች ወራሽ የሆኑት ሕፃን ኬሩዝ ተክለና ህፃን ፋኔት ተክለ በሕግ ጥበቃ የተሰጠው መብትና ጥቅም አላቸው ብለናል።
አመልካች የኢንሹራንስ ገንዘቡን ግማሹን ብር 83,224(ሰሚኒያ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ሃያ አራት) የአሜሪካን ድላር ይውሰደ ብለናል።
የሟች ልጆች ወራሾች የሆኑት ህፃን ኬሩዝ ተክለና ህፃን ፋኔት ተክለ(ተጠሪ) ቀሪውን 83,224(ሰማኒያ ሶስት ሺ ሁለት መቶ ሃያ አራት) የአሜሪካን ድላር እኩል ይካፈለ ብለናል።
ይህ ፍርድ በፋዳራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችልት በሙለ ድምጽ ተሰጠ።
No topics extracted.